Tutorial for highschool students
174 subscribers
24 photos
25 videos
13 files
98 links
Educational channel
You can dm me at:
t.me/Abboud1088
Download Telegram
የጥያቄና መልስ ውድድሩ ፕሮግራም

ውድድሩ የሚካሄደው በ3 ዙሮች ነው።
የመጀመሪያ ሁለት ዙሮች የሚካሄዱት በክላስ ውስጥ ሲሆን አላማውም ለመጨረሻው ዙር ከአንድ ትምህርት ቤት 4 ተማሪዎችን ማስቀረት ነው።

ሶስተኛው እና የመጨረሻው ዙር ውድድር የሚካሄደው አዲስ በተሰራው ፓርክ ሲሆን ከሁለቱም ሀይስኩሎች በጠቅላላው 8 ተማሪዎች ተወክለው የሚወዳደሩ ይሆናል።

ፕሮግራሙ እንደሚከተለው ይሆናል፦
(የቀን አቆጣጠር በኢ/ያ አቆጣጠር ነው የተጻፈው)

ረቡዕ 6/12/2018
የ ወራቤ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የውስጥ ውድድር የሚካሄድበት ዕለት (በ1 ዙር የሚፈለገውን የተማሪ ቁጥር ካላደረስን ሁለተኛው ዙር ከሰዓት ይደረጋል።)

ሐሙስ
የዘሞ ባቴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የውስጥ ውድድር የሚካሄድበት ዕለት (በ1 ዙር የሚፈለገውን የተማሪ ቁጥር ካላደረስን ሁለተኛው ዙር ከሰዓት ይደረጋል።)

አርብ
-

ቅዳሜ
ለመጨረሻው ዙር ተወዳዳሪ ተማሪዎች ውድድሩን በተመለከተ ገለጻ ይደረጋል።

እሁድ
ሶስተኛው ዙር ውድድር የሚካሄድበት ዕለት


ስለዘህ በቀሩት ሁለት ቀናት ዝግጅታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ይሁን።

መመዝገብ ፈልጋችሁ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች አሁንም እየመዘገብኩ ስለሆነ በዚህ (@Abboud1088) መመዝገብ ትችላላችሁ።

መልዕክቱ ላልደረሳቸው ማድረሳችሁን አትርሱ። መልካም ጊዜ
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
🚫የገለጻ ቀን🚫
ሰላም

ከሁለቱም ሀይስኩሎች ለመጨረሻው ዙር ያለፋችሁ ስምንት (8) ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ከቀኑ 8:30 ሰዓት (በኢ/ያ አቆጣጠር) ወንዝ ዳር ፕሮጀክት ውስጥ በሚገኘው አዲሱ አዳራሽ እንድትገኙ ይሁን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🚫እሁድ 10/12/2018🚫
ሰላም ሰላም ሰላም

አመት ቀረ፣ ወር ቀረ፣ ሳምንት ቀረ እያልን ሰንብተን እነሆ ለታላቁ የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር 24 ሰዓታት ብቻ ቀሩን። አንድ ቀን ብቻ!
▪️እሁድ ከጠዋቱ 03:00 ሰዓት▪️📌

በከተማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስዋሰው ውድድር እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

በተለይ የዘሞ ባቴ ሀይስኩል ተማሪዎችና የወራቤ ሀይስኩል ተማሪዎች በዕለቱ ተገኝታችሁ ተወዳዳሪ ጓደኞቻችሁን እንድትደግፉ 🏁፣ እንድታበረታቱ 💪 እና የሞራል ድጋፍ እንድትሰጡ👏 ተጋብዛችኋል።

መልዕክቱ ላልደረሳቸው ማድረሳችሁን አትርሱ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
🚫ድህረ-ውድድር🚫
ሰላም

ከትናንት ወዲያ እሁድ ዕለት (10/12/2018 ዓ.ል.) ወራቤ ከተማ በሚገኘው ሜላያን ፓርክ አዳራሽ በተከማችን፣ በዞናችን እና በክልላችን ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለቱ ትምህርት ቤቶች መካከል በተካሄደው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስዋሰው ውድድር በሰላም አስደሳች በሆነ መልኩ ተጠናቋል።

በዚህ የውድድር ፕሮግራም ተሳታፊ የነበሩ የወራቤ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና የዘሞ ባቴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አስደሳች፣ እልህ አስጨራሽ እና ትጋት የታየበት ፉክክር ያደረጉ ሲሆን ለሽልማቱ ሲባል አቻ ውጤት የነበራቸውን ተማሪዎች በመለየት 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ የወጡ ተማሪዎችን ሸልመናል።

🥇 አንደኛ የወጣው በራሱ እስከ ጥግ የተማመነው 💅 የወራቤ አ/ሁ/ደ/ት/ቤት ተማሪ የሆነው ተማሪ አይመን ነስረዲን የ 10,000 ብር የገንዘብ ሽልማትና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።
🥈 ሁለተኛ የወጣው ትሁቱ 😇 የወራቤ አ/ሁ/ደ/ት/ቤት ተማሪ የሆነው ተማሪ ሙዓዝ ሙሐመድኑር የ 7,000 ብር የገንዘብ ሽልማትና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።
🥉 ሶስተኛ የወጣችው ሮኬቷ 🚀 የዘሞ ባቴ አ/ሁ/ደ/ት/ቤት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ሐናን ሙሰማ የ 5,000 ብር የገንዘብ ሽልማትና ሰርተፊኬት ተበርክቶላታል። (ስሟ "ሐናን ሮኬቷ" እንዲሆን ተወስኗል¡)

የውድድሩ አሸናፊዎችና ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ። ለኔ ከተወዳዳሪ ተማሪዎቼ በተጨማሪ፣ የማጣሪያ ውድድሩን የተሳተፉ ተማሪዎችና ትምህርቱን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ሁሉ አሸናፊዎች ናቸው።

በፕሮግራሙ ከሁለቱ ትምህርት ቤቶች ዳይሬክተሮች በተጨማሪ የሌሎች ት/ቤቶች ዳይሬክተሮች፣ መምህራን፣ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የዞናችን የመጅሊስ አመራር፣ የኦሮሚያ ባንክ ስራ አስኪያጅ፣ ወላጆች እና ተማሪዎች የተገኙ መሆናቸው የፕሮግራሙ ድምቀት አካል ሆኗል።

ምስጋና

ከ2016 ዓ.ል. መነሻ ጀምሮ በተለይ በዚህ አመት በሳምንት ለ6 ቀናት ያለመታከት ተማሪዎችን ሳስተምር ቆይቼ ለዚህ በመድረሴ በቅድሚያ አላህን ላመሰግን እወዳለሁ።

1. ለኔ በዚህ ምድር ላይ መገኘት ሰበብ ለሆኑ ወላጆቼ ምስጋና ይድረስ። ከወላጅነት ባሻገር "አብሽር" ብለውኛል፣ ደግፈውኛል፣ ጠግነውኛል።

2. በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የሚገጥሙኝን መሰናክሎች በብቃት እንድወጣ፣ በምን መልኩ ማስተማር እንዳለብኝ ምክረ-ሐሳቦችን ሲሰጠኝ ለነበረው፣ አስፈላጊ የሐሳብና የተግባር ድጋፍ ሲያደርግልኝ ለነበረው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሁማኒቲ ኮሌጅ ዲን ለሆነው አቶ አወል ሱንከሞ ምስጋናዬ ይድረስ።

3. እንደ እናት፣ ወዳጅ እና መካሪ የሐሳብ እና የምክር ድጋፍ ስታደርግልኝ ለነበረችው ሶፊያ ባርጊቾ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስ።

4. ከዚህ በመቀጠል የሀይስኩል መምህሮቼ የነበሩ እና ዛሬ ደግሞ የዚህ ፕሮጀክት አማካሪዎቼ ለሆኑት መምህር ዋበላ እና መምህር ኢብራሂም ምስጋናዬ ይድረስ። ተማሪ በነበርኩ ጊዜ እኔን ያስተማሩበት ውለታ እያለብኝ ዛሬ ለዚህ ስራ ከጎኔ በመቆም ውለታቸውን መክፈል የተራራ ያህል እንዲገዝፍብኝ አድርገዋል።

5. ባልጠበቅኩት ሁኔታ ቅዳሜ ማታ ስለፕሮጀክቱ እና የእሁዱን ፕሮግራም ሰምተው ሁሉን ትተው ይህን ፕሮግራም ከመታደም አልፈው በቀጣይ የማይቋረጥ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ለገቡልኝ ለከተማው መጅሊስ የወጣቶች ካውንስል ፕሬዝደንት አቶ አብዱልከሪም እና የዳሩል ሂጅረተይን አክሲዮን ማኅበር አባል ለሆነው አቶ ሳዲቅ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስ።

6. ኦሮሚያ ባንክ (ስራ አስኪያጁ አቶ መለሰን ጨምሮ) ለተማሪዎቼ ባደረገልኝ ነገር እና ወደፊትም በጋራ ተማሪዎችን የምናገለግልበትን እድል በማመቻቸቱ ምስጋና ይድረሰው።

7. በመቀጠል ተማሪዎቼን ማመስገን እፈልጋለሁ። ከኔ የሚጠቅም እውቀት እንደሚያገኙ በመተማመን በየፈረቃው ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የዚህ ፕሮጀክት ዋና አካል በመሆን የተሰጣቸውን የመማር ስራ በብቃት በመወጣት ለዚህ በመብቃታቸው ተማሪዎቼ ምስጋና ይድረሳቸው። እኔ ብቻ አልነበረም እነርሱን ያስተማርኩት፤ እነርሱም መምህሮቼ ነበሩ። ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። ነገ የተሻለ ቦታ እንደማያችሁ ምንም ጥርጥር የለኝም!

8. የወራቤ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ይህን ፕሮግራም እንዳከናውን የበኩሉን ድርሻ በመወጣቱ ምስጋና ይድረሰው።

9. ያልጻፍኳቸው ደጋፊዎቼ፣ መካሪዎቼና አጋዦቼ ምስጋና ይድረስ።

10. በመጨረሻም ማመስገን የምፈልገው #ራሴን ነው። በለጋ እድሜዬ ጊዜዬን በማይጠቅም ነገር ከማሳለፍ ይልቅ፣ ኅብረተሰቤ ላይ መ'ሸፈን ያለበትን ጉድለት አይቼ ያን ጉድለት ለመሙላት ባለኝ አቅም ተጨማሪ ነገር ሳልፈልግ ለሶስት አመታት ተማሪዎቼን ማገዝ በመቻሌ ራሴን ላመሰግን እወዳለሁ።

ከዚህ ፕሮግራም በኋላ ምን ታሰበ? ከዚህ በኋላ ይቀጥላል ወይስ ሙሉ በሙሉ ተቋጭቷል? እነማንን ለማካተት ታስቧል?
በቅርቡ መልሱን በተግባር የምናውቅ ይሆናል። በአላህ ፈቃድ በቅርቡ መልካም ዜና እንሰማለን። ⚪️

እናስታውስ
ዛሬ ለደረስንበት ቦታ ሰበብ የሆነውን ኅብረተሰባችንን ማገልገል ግዴታ እንጂ ነጻ ምርጫ አይደለም።

መልካም ጊዜ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🙏4❤1
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
🚫Natural Science or Social Science🚫
ሰላም

ይህ ሳምንት ለ2019 ዓ.ል. ምዝገባ የተጀመረበት ሳምንት በመሆኑ ከ10ኛ ክፍል ወደ 11ኛ ክፍል የተቀላቀላችሁ ተማሪዎች stream መረጣ ላይ ጥያቄዎችን እያነሳችሁ በመሆኑ ያለፈው አመት በተመሳሳይ ተማሪዎች ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠሁትን ምላሽ እንድታነቡት እጋብዛችኋለሁ።

ከታች የሚቀመጡላችሁን ማስፈንጠሪያዎች በመንካት ወደ ተጻፉት ጽሑፎች በመሄድ ጠቃሚ መረጃዎችን መውሰድ ትችላላችሁ።

ዘለግ ያለ ጽሑፍ ቢሆንም በህይወታችሁ ከምትወስኑት ትልቅ ውሳኔዎች አንዱ በመሆኑ ታግሳችሁ አንብቡ፤ አወያይታችሁ ምረጡ።

ክፍል 1
https://t.me/Werabesps/900

ክፍል 2
https://t.me/Werabesps/902

ክፍል 3
https://t.me/Werabesps/906
https://t.me/Werabesps/909
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1
Forwarded from Thoughts.. 🇪🇹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለአፍሪካ ጥሩ ዜና ነው። 11ኛ ክፍል ጂዮግራፊ ላይ ስማረው ጀምሮ ያብከነክነኝ የነበረ ነገር ነበር። በኔ ትውልድ ለማስተካከል እንቅስቃሴ መደረጉ ደስ ብሎኛል።

ተግባር ላይ ውሎ ቀጣዩ ትውልድ የአፍሪካን ትክክለኛ ማንነት የሚረዳበት እንዲሆን እመኛለሁ።

አሜሪካ = የአፍሪካ ቀንደኛ ጠላት!
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
እንኳን ለ2019 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ።

ከወደቁበት የመነሳት፣ ለፍቶ የማግኘት፣ አንብቦ የመረዳት፣ በጥሩ ውጤትና ስኬት የታጀበ አመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

መልካም የትምህርት ዘመን!
❤2👍1🙏1
ተማሪ ሆኖ እንዳሳለፈ ሰው እጅግ በጣም ደስ ከሚሉኝ ጊዜያት መሃል መስከረም ወር ገብቶ ትምህርት ስንጀምር ያለው ጊዜ ነው።

በአዲስ መንፈስ በቅዝቃዜ ዝናብ እየዘነበ መማሩ፣ እየተማርን ሳለ በዝናቡ ድምጽ ምክንያት መማር አለመቻሉ፣ እየሄድን ወይ እየተመለስን ሳለ በዝናብ መበስበሱ፣ ...

"ክላስ አሁን በመጀመሩ ተማሪ አይመጣም" እያላችሁ ከምትቀሩ ሂዱና ለወደፊቱ ህይወታችሁ የማይረሳ አስደሳች ማስታወሻ አስቀምጡ።

ባይሆን ትምህርት መጀመሩን ተከትሎ የሚመጣውን እንደ ጉንፋን ያሉ ተላላፊ የመተንፈሻ አካላት ህመም ጠንቀቅ እያላችሁ።
💯3🤝3🙏1
Forwarded from English For Ethiopia - በቀላሉ (Sam G)
​✅ Too vs. Enough — በቀላል መንገድ!

​1️⃣ Too = "ከመጠን በላይ" (Negative Meaning)

​አንድ ነገር ከሚገባው በላይ ሲሆን እንጠቀመዋለን። ሁልጊዜ ከቃሉ ፊት ይገባል!

​✅ Too + Descriptive Word (Adjective)

• ​Too expensive ➔ በጣም ውድ ነው (መግዛት አልችልም)
• ​Too late ➔ በጣም ዘግይቷል!

​2️⃣ Enough = "በቂ" (Sufficient)

​አንድ ነገር በቂ መሆኑን ለማሳየት እንጠቀምበታለን። ነገር ግን ቦታው እንደ ቃሉ ዓይነት ይለያያል፡

​▪️ ከማብራሪያ ቃል (Adjective) ጋር ከሆነ ➔ ከቃሉ በኋላ ይገባል!

​✅ Adjective + Enough

• ​Old enough ➔ በቂ እድሜ ያለው
• ​Tall enough ➔ በቂ ቁመት ያለው

• ​Example: "He is old enough to drive." (መኪና ለመንዳት እድሜው ደርሷል።)

​▪️ ከስም (Noun) ጋር ከሆነ ➔ ከስሙ በፊት ይገባል!

​✅ Enough + Object/Noun

• ​Enough money ➔ በቂ ገንዘብ
• ​Enough time ➔ በቂ ጊዜ

• ​Example: "I have enough time." (በቂ ጊዜ አለኝ።)


❌ hot too  ➔  ✅ too hot (ከፊት)
❌ enough old  ➔  ✅ old enough (ከኋላ)
❌ money enough  ➔  ✅ enough money (ከፊት)

❓ ለ Quiz
@Fetan_English

✅️ ለተማሪዎች መረጃ
@TemariNews

❤️ @English_Ethiopian ✅
🌐Follow Us
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
He was standing ___ to me.
Anonymous Quiz
24%
Closely
64%
Close
4%
Closeful
8%
Closefully
Thomas ___ that book yesterday.
ቶማስ ያን መፅሐፍ ትላንት ፈልጎት ነበር።
Anonymous Quiz
47%
Was needed
11%
Did needed
37%
Needed
5%
Need
Which one is correct?
Anonymous Quiz
59%
Ethiopia has...
41%
Ethiopia have...