Tutorial for highschool students
174 subscribers
24 photos
25 videos
13 files
98 links
Educational channel
You can dm me at:
t.me/Abboud1088
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጌታዬ..
ለካ ሀይስኩል ሳለን ከፊደላት እና ምልክቶች ጋር ነበር ጦርነታችን
ደግሞ'ኮ ምንም ይሁን መልሶችን ፈላልጠን ማምጣታችን!

ዛሬ ግን ሳየው ነው ቆሌዬ የተገፈፈው። 😑
ጌታ ከክፉ ድንጋጤ ይጠብቃችሁ
ጠላት እንዲህ አይደንግጥ 😳
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💯1
Doctors _____ help you unless you tell them what's worng.
Anonymous Quiz
56%
Can't
21%
Couldn't
8%
Shouldn't
15%
Mustn't
Common economics formula and their terms
❤3
ውድ ኢትዮጵያውያን ለ5 ሚሊዮን ኮደሮች ምዕራፍ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ!
‎
‎በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል። የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች 5,005,146 ሰልጣኞች ተመዝግበው ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀዋል። ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው።
‎
‎በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው። እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት፥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።
‎
‎ለወጣት ተማሪዎቻችን፤ መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው። ጊዜያችሁን በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥባችሁ፤ በመመዝገብና በመማር ወደ ትምህርት ገበታችሁ ስትመለሱ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ። ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን፥ የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ነው።
‎
‎የምትገነቡት ነገ የሚጀምረው ዛሬ ነው!
‎
‎ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:
‎ethiocoders.et/
❤1
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ)
ለሁላችሁም መልካም የማጠቃለያ ፈተና ይሁንላችሁ።
👍6
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ፈተና!

ከሁሉ በፊት መረጋጋትን አስቀድሙ። አላህ አብሯችሁ ይሁን።
❤3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#English

Though, Although, Even though

Their similarities and differences.
.
Main Channel
https://t.me/Werabesps 🚀
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial 🚀
.
DM
@Abboud1088 ☑
.
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
English for your day 😁✅

Rigged game vs Fair game
GOAT vs Rat
Man of the match vs player of the tournament
FIFA president vs Honest leader


Siuuuuuuu እያልን ;)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤3👌1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ኤአይ (AI)ን እንዴት እንጠቀም ?

ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለረጅም ጊዜ እና ያለገደብ መጠቀም የሰዎችን የፈጠራ ብቃት እና ነገሮችን በጥልቀት የመመርመና የማሰብ ክህሎትን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በቅርቡ የወጡ ተከታታይ ጥናቶች አመልክተዋል።

​በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች መረጃዎችን እና ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ በኤአይ (AI) ላይ ጥገኞች ሆነው ማከናወን ሲጀምሩ " ኮግኒቲቭ ሰረንደር " ወይም የአእምሮን የማሰብ ስራ ለቴክኖሎጂ አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌ ይታይባቸዋል።

ይህም አእምሮ በራሱ ጥረት መረጃዎችን የማቀናበር፣ የመተንተን እና አዳዲስ ሀሳቦችን የማመንጨት የተፈጥሮ ብቃቱ እንዲደክም ያደርገዋል።

በተለይ #ወጣቶች እና #ተማሪዎች ለተወሳሰቡ ጥያቄዎች እና ስራዎች ፈጣን ምላሽ ከኤአይ ማግኘት መልመዳቸው የራሳቸውን የአእምሮ አቅም የመጠቀም ተነሳሽነታቸውን እንደሚቀንሰው ተመራማሪዎች ያስጠነቅቃሉ።

ነገር ግን ቴክኖሎጂውን እየተጠቀሙ አእምሮን ሁል ጊዜ ንቁ፣ ብቁ እና ጤናማ አድርጎ ለማቆየት የሚረዱ በርካታ ሳይንሳዊ መንገዶች እንዳሉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።

የአእምሮን የአስተሳሰብ ብቃት ላለማጣት ምን አይነት ልምዶች ማዳበር ይቻላል ?

- ከኤአይ (AI) የተገኙ ምላሾችን ወይም መረጃዎችን በቀጥታ ወስዶ ከመገልበጥ ይልቅ " ይህ መረጃ ትክክል ነው ? ምን ጎደለው ? አመክንዮአዊ ነው ? " በማለት በራስ አእምሮ መርምሮ፣ መዝኖ መጠቀም።

- ማንኛውንም ስራ፣ ጽሑፍ ወይም ፕሮጀክት ከመጀመርዎ በፊት መነሻ ሀሳቦችን እና እቅዶችን በራስ አእምሮ ማመንጨት እና ማስታወሻ መያዝ። ኤአይ ስራውን ለማስጀመር ሳይሆን የተጀመረውን ስራ ለማደራጀት ወይም ለመፈተሽ ብቻ መጠቀም።

- የፈጠራ እና የጥልቅ አስተሳሰብን የሚያነቃቁ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስልታዊ ጨዋታዎችን መጫወት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ያለ ቴክኖሎጂ እገዛ ለመማር መሞከር።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መረጃዎች/ስራዎችን ለኤአይ ሰጥቶ ያለ ምንም ምርመራ፣ ማስተካከያና ደጋግሞ የማንበብ ጥረት በቀጥታ #በመገልበጥ አንዳንዴም እንደራስ ስራ ማስመሰል እየተለመደ መጥቷል። ይህ በጥልቀት ሳያስቡና ሳይመራመሩ በቴክኖሎጂ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ መሆን አእምሮን የማሰብ ስራውን እንዲተው በማድረግ፣ እውነታን የመተንተን እና የጥልቅ አስተሳሰብ ብቃትን በከፍተኛ ደረጃ እየገደለው ይገኛል ፤ ሰዎች ትንሽ ስራ እንኳን ለመስራት የማይፈልጉ ስልቹና ሰነፍ እያደረጋቸውም ነው።

ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ኤአይ (AI) የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሳይሆን እንደ ረዳት መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል የሚገባው ነው። ጥቅም የሚኖረውም የሰው ልጅ የራሱን የአስተሳሰብ ልዕልና ጠብቆ ሲቀጥል ብቻ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
🚫ልዩ መልዕክት🚫
ሰላም ወዳጆች

እንደሚታወቀው ባለፉት 3 አመታት በእንግሊዘኛ ትምህርት ለተማሪዎች ቲቶሪያል እየተሰጠ ቆይቷል። ዘንድሮ ካለፉት አመታት በተሻለ እና ሰፋ ባለ መልኩ ተማሪዎችን የማስተማር እና የማብቃት ስራ እየተሰራ ነው። አልሐምዱሊላህ

የዘንድሮው የእገዛ ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው ተማሪዎችን ካስተማርን በኋላ በአመቱ መጨረሻ በተማሪዎች መካከል የሚካሄድ የጥያቄና መልስ ውድድር መኖሩ ነው።

ውድድሮቹ በሁለት መልኩ እንዲደረጉ የታቀደ ሲሆን የመጀመሪያው በወራቤ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (ጁኒየር) ተማሪዎች መሃል የሚደረግ ነው። ይህ ፕሮግራም በሰኔ 29/2018 ዓ.ል. የተከናወነ ሲሆን አሸናፊ ተማሪዎቻችን በሰኔ 30 በወላጆች ቀን በወላጆች ፊት የሰርተፊኬትና የገንዘብ ማበረታቻቸው በተሳካ ሁኔታ ተበርክቶላቸዋል። የ2000 ብር፣ የ1500 ብር እና የ1000 ብር ሽልማት ከሰርተፊኬት ጋር ለአሸናፊዎች ሲበረከት ለተቀሩት ተማሪዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ሁለተኛውና አጓጊው ውድድር በሁለቱ የከተማችን ታላላቅ ሀይስኩል ተማሪዎቻችን መካከል የሚደረግ ሲሆን ይህም በዕለተ እሁድ 10/12/2018 ዓ.ል. የሚካሄድ ይሆናል። እነዚህም የወራቤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የዘሞ ባቴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ናቸው።

ይህንን ፕሮግራም ልዩ እና አጓጊ የሚያደርጉት ነጥቦች እንደሚከተለው ተጠቅሰዋል፦

🔠. የእገዛ ትምህርቱ ያለ ምንም ክፍያ ፍላጎት ለነበራቸው ተማሪዎች ሁሉ በነጻ ሲሰጥ የቆየ መሆኑ

🔠. የጥያቄና መልስ ውድድሩ በከተማችን (ወራቤ ከተማ)፣ በዞናችን (ስልጤ ዞን) ምናልባትም በክልላችን (ማዕከላዊ ኢ/ያ) ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዘኛ ትምህርት የሚደረግ ልዩ ውድድር መሆኑ

🔠. ውድድሩ የሚካሄደው በሁለቱ ሀይስኩል ተማሪዎች መካከል መሆኑ

🔠. የውድድሩ አሸናፊዎች ከሰርተፊኬት በዘለለ የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት መሸለማቸው

🔠. የውድድሩ አሸናፊ ሶስት ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው የ10,000 ብር፣ የ7,000 ብር እና የ5,000 ብር ከሰርተፊኬት ጋር እንደየደረጃቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተሸላሚ መሆናቸው እና ለተቀሩት ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት መበርከቱ ይህ ውድድር ከሌሎች ውድድሮች ልዩ የሚያደርገው ሆኗል።

በመሆኑም ይህ የጥያቄና መልስ ውድድር ቀጣይ ሳምንት በዕለተ እሁድ 10/12/2018 ዓ.ል. የሚደረግ በመሆኑ በትምህርት ስራ ተሳታፊ የሆናችሁ አካላት፣ የት/ቤት ዳይሬክተሮች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የከተማው ነዋሪዎች በክብር ተጋብዛችኋል።

የጥያቄና መልስ ውድድሩም የሚካሄደው በወራቤ ከተማ አዲሱ ፓርክ ውስጥ በሚገኘው አዳራሽ ይሆናል።

ተወዳዳሪ ተማሪዎች እስካሁን የተማራችሁትን እየከለሳችሁ ተዘጋጁ። ኢንሻአላህ በጣም ጥሩ እና አስደሳች ጊዜ የምናሳልፍ ይሆናል።

ለዚህ ቀን ሰላም ያድርሰን። መልዕክቱን በማስተላለፍ ተባበሩን። መልካም ጊዜ!

.
Main Channel
https://t.me/Werabesps 🚀
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial 🚀
.
DM
@Abboud1088 ☑
.
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
🚫 የምዝገባ መልዕክት 🚫
ሰላም

በ2018 ዓ.ል. ሲሰጥ በቆየው የእንግሊዘኛ እገዛ ትምህርት ላይ ተሳታፊ የነበራችሁ በጥያቄና መልስ ውድድሩ መሳተፍ የምትፈልጉ የሁለቱ ሀይስኩል ተማሪዎች ከአሁን ጀምሮ እስከ ነገ ሰኞ 04/12/2018 ዓ.ል. ድረስ ምዝገባ መካሄድ ስለጀመረ እንድትመዘገቡ ለማስታወስ እወዳለሁ።

በውድድሩ ለመሳተፍ የሚከተሉት መሥፈርቶች መሟላት አለባቸው፦
🔠. በእገዛ ትምህርት ፕሮግራሙ ቢያንስ 70% እና ከዚያ በላይ ተሳታፊ የነበረ/ች
🔠. የወራቤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና የዘሞ ባቴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነ/ች
🔠. በቴሌግራም አድራሻ (@Abboud1088) ላይ መመዝገብ

የምዝገባ አድራሻ እዚሁ በቴሌግራም ሲሆን በውስጥ መስመር መጥታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ። ለምዝገባ የምትመጡ ተማሪዎች ስትጽፉ በሚከተለው መንገድ ይሁን፦

የትምህርት ቤት ስም: XOXOXOXO
የተማሪ ስም: XOXOXOXO
የተማሪ ክፍል: XOXOXOXO

ለመመዝገብ ይህን አድራሻ ተጠቀሙ፦
@Abboud1088

በተቻለ መጠን መልዕክቱን በመማር ሲሳተፉ ለነበሩና ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ሁሉ አድርሱ። መልካም ጊዜ

.
Main Channel
https://t.me/Werabesps 🚀
.
Tutorial Channel
https://t.me/WSPSTutorial 🚀
.
DM
@Abboud1088 ☑
.
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የጥያቄና መልስ ውድድሩ ፕሮግራም

ውድድሩ የሚካሄደው በ3 ዙሮች ነው።
የመጀመሪያ ሁለት ዙሮች የሚካሄዱት በክላስ ውስጥ ሲሆን አላማውም ለመጨረሻው ዙር ከአንድ ትምህርት ቤት 4 ተማሪዎችን ማስቀረት ነው።

ሶስተኛው እና የመጨረሻው ዙር ውድድር የሚካሄደው አዲስ በተሰራው ፓርክ ሲሆን ከሁለቱም ሀይስኩሎች በጠቅላላው 8 ተማሪዎች ተወክለው የሚወዳደሩ ይሆናል።

ፕሮግራሙ እንደሚከተለው ይሆናል፦
(የቀን አቆጣጠር በኢ/ያ አቆጣጠር ነው የተጻፈው)

ረቡዕ 6/12/2018
የ ወራቤ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የውስጥ ውድድር የሚካሄድበት ዕለት (በ1 ዙር የሚፈለገውን የተማሪ ቁጥር ካላደረስን ሁለተኛው ዙር ከሰዓት ይደረጋል።)

ሐሙስ
የዘሞ ባቴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የውስጥ ውድድር የሚካሄድበት ዕለት (በ1 ዙር የሚፈለገውን የተማሪ ቁጥር ካላደረስን ሁለተኛው ዙር ከሰዓት ይደረጋል።)

አርብ
-

ቅዳሜ
ለመጨረሻው ዙር ተወዳዳሪ ተማሪዎች ውድድሩን በተመለከተ ገለጻ ይደረጋል።

እሁድ
ሶስተኛው ዙር ውድድር የሚካሄድበት ዕለት


ስለዘህ በቀሩት ሁለት ቀናት ዝግጅታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ይሁን።

መመዝገብ ፈልጋችሁ ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች አሁንም እየመዘገብኩ ስለሆነ በዚህ (@Abboud1088) መመዝገብ ትችላላችሁ።

መልዕክቱ ላልደረሳቸው ማድረሳችሁን አትርሱ። መልካም ጊዜ
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
🚫የገለጻ ቀን🚫
ሰላም

ከሁለቱም ሀይስኩሎች ለመጨረሻው ዙር ያለፋችሁ ስምንት (8) ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ከቀኑ 8:30 ሰዓት (በኢ/ያ አቆጣጠር) ወንዝ ዳር ፕሮጀክት ውስጥ በሚገኘው አዲሱ አዳራሽ እንድትገኙ ይሁን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🚫እሁድ 10/12/2018🚫
ሰላም ሰላም ሰላም

አመት ቀረ፣ ወር ቀረ፣ ሳምንት ቀረ እያልን ሰንብተን እነሆ ለታላቁ የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር 24 ሰዓታት ብቻ ቀሩን። አንድ ቀን ብቻ!
▪️እሁድ ከጠዋቱ 03:00 ሰዓት▪️📌

በከተማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ስዋሰው ውድድር እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

በተለይ የዘሞ ባቴ ሀይስኩል ተማሪዎችና የወራቤ ሀይስኩል ተማሪዎች በዕለቱ ተገኝታችሁ ተወዳዳሪ ጓደኞቻችሁን እንድትደግፉ 🏁፣ እንድታበረታቱ 💪 እና የሞራል ድጋፍ እንድትሰጡ👏 ተጋብዛችኋል።

መልዕክቱ ላልደረሳቸው ማድረሳችሁን አትርሱ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1
Forwarded from Werabe Comprehensive Secondary School (ㅤ 🇪🇹)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM