Tutorial for highschool students
174 subscribers
24 photos
25 videos
13 files
98 links
Educational channel
You can dm me at:
t.me/Abboud1088
Download Telegram
Forwarded from Tikvah-University
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡

ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?
ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።

በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።

#Ethiopia #NationalExam #Grade12 #ኤፍኤምሲ

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ስለ ኩረጃ ምን አሉ ?

" ትምህርት እውቀት ሲሆን ሰርተፊኬት ደግሞ ያንን እውቀት የምንለካበት ነው።

በስርቆት ፣ በማጭበርበርና በኩረጃ የሚገኝ ነገር እውቀት ሳይኖር ሰርተፊኬት ማግኘት ነው። ይህ ደግሞ እውቀት አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ሰርተፊኬቱ እውቀት አለህ ስለሚለው ምንም ሳያቅ ሰርተፊኬት በእጁ ስላለው ብቻ እውቀት አለኝ ብሎ የሚያምን የህብረተሰብ ክፍል ይፈጠራል፤ ይህም ህብረተሰቡን በጣም ይጎዳል።

በተለይ በትምህርት ዘርፉ ተንሰራፍቶ የነበረውን ማጭበርበር፣ ስርቆትና ኩረጃ ተማሪዎች ብቻ የሚያደርጉት ቢሆን ኖሮ የልጆቹ ችግር ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን ይህን የሚያደርጉት ፦
- ተማሪዎች፣
- የትምህርት ቤት አስተዳደሮች፣
- የክልል ባለስልጠናት እና ሌሎችም ' የኛ አካባቢ ልጆች እንዲያልፉ ' በሚል የሚያደርጉት በመሆኑ ከፍተኛ የሞራል ውድቀት ውስጥ የተገባበት ነበር።

በመሆኑም ወደፊት ትውልዱን በጥራት ማስተማር አለብን ካልን ከመሰረቱ ችግሩን መፍታትና በኩረጃና በማጭበርበር የሚገኝ እውቀት እንደሌለና ይህም ሀገር እንደሚጎዳ በሁሉም ዘንድ መተማመን መፍጠር ያስፈልጋል።

በዚህም ይህንን ስብራት ለማስተካከል በተወሰደው የለውጥ እርምጃ ተማሪዎች በትምህርት ዘርፉ በቀላሉ አጭበርብሮና ኮርጆ ማለፍ የለም የሚለውን በማወቅ ፦
° በሥርዓቱ ማጥናት፣
° ቤተ መጽሃፍት መግባት፣
° ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም፣
° በትርፍ ጊዜያቸው ቲቶሪያል መማርና ለትምህርታቸው በቂ ትኩረት መስጠት  ጀምረዋል።

መምህራንም በአግባቡ ተዘጋጅተው ማስተማርና ተማሪዎችን በሚገባ ማዘጋጀት፣ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንም ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ከክፍል ክፍል በትክክል ተመዝነው እንዲያልፉ ማድረግ ጀምረዋል።

በየክልሉ ያለው የትምህርት መዋቅርም በኩረጃ ' የኔ አካባቢ ይህን ያህል አለፈ ' ከሚል የቁጥር ጨዋታ ወጥተው በትክክል የትምህርት ምዘና በየደረጃው በማድረግ ልጆች ባላቸው እውቀት ብቻ ተመዝነው የሚያልፉበት ሥርዓት እየፈጠሩ ይገኛል። ለአብነት ፦ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በአግባቡ እየተገበሩ ነው።

ይህንን ማስቀጠል ከተቻለ የምዘናና የፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን በሚገባ ያስተካክለዋል።

የገጠመውን የሞራል ክስረት በሚገባ አስወግዶ ትምህርት በእውቀትና በችሎታ ብቻ የሚለው በጀመርነው አግባብ ወደ ኋላ ሳይመልሰው ማስረጽ ከቻልን ለምናደርገው የትምህርት ጥራት መሻሻል እንደ መነሻ ይሆናል።

በአጠቃላይ የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ማስተካከል ከተጀመረ ጀምሮ በተወሰዱ እርምጃዎች ከአሁን በኋላ በሁሉም ዘንድ ግልጽ በሆነ መንገድ በማጭበርበርና በኩረጃ የሚገኝ ነገር እንደሌለ እና ተምሮና ተግቶ በማጥናት ብቻ ውጤት እንደሚገኝ በተማሪዎችና በማህበረሰቡ ዘንድ መተማመን ተፈጥሯል። "

#MoE

@tikvahethiopia
ውድ የተከበራችሁ ቤተሰቦች

እንኳን ለዒዱል አድሓ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ለሁላችሁም ፍክትክት ያለ መልካም ዒድ እመኝላችኋለሁ። 🎉🎉
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም ወዳጆች

አሁን 10ኛ ክፍል የሆናችሁ ቀጣይ አመት (2018 ኢ.አ.) 11ኛ ክፍል የምትገቡ ተማሪዎች እስኪ ይህችን ቃለ መጠይቅ ሙሉ። በቀጣይ አመት Natural Stream ነው መቀላቀል የምትፈልጉት? ወይስ Social Stream ነው መቀላቀል የምትፈልጉት? ከዚህ መልሳችሁ በኋላ ለምርጫ እንዲመቻችሁ ሰፊ ዳሰሳ እናደርጋለን። መልሳችሁን ስትሰጡ በተቻለ መጠን ውስጣችሁን ለማዳመጥ ሞክሩ።
Final Results
34%
A. Social Stream
66%
B. Natural Stream
🥰3
ሰላም ለሁላችሁም

ከ4 ቀናት በፊት በተባባልነው መሠረት አሁን 10ኛ ክፍል ያላችሁ ቀጣይ አመት 2018 እ.ኢ.አ. 11ኛ ክፍል የምትቀላቀሉ ተማሪዎች ሰፋ ያለ ውይይት እናካሂዳለን። በውስጥ መስመር ስትጠይቁኝ ለነበራችሁና እንዲሁ ስለምትቀላቀሉት stream ለማወቅ ጥሩ ግንዛቤ እንደምታገኙበት ተስፋ አደርጋለሁ። ቢረዝምም ታግሳችሁ አንብቡት።

በመጀመሪያ ደረጃ ለዚህ ላበቃችሁ አላህ ምስጋና ይድረሰው። በመቀጠል ለዚህ ለበቃችሁ ወንድምና እህቶቼ እንኳን ለዚህ በቃችሁ። በቀጣይ ለምትቀጥሉት የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ጊዜያችሁ መልካም ጊዜ እመኝላችኋለሁ።

ወደ ሐሳባችን ስንመለስ..

ይህን ሐሳብ ስትጠይቁና ስትወያዩ ሁላችንም የምንገነዘበው ነገር አለ። እርሱም ይህ ምርጫችሁ አዲስ ወደሆነ ምዕራፍ መግቢያችሁ መሆኑንና እንደ ቀልድ የምትወስኑት ውሳኔ እንዳልሆነ ነው።

ይህ ምርጫችሁ ወደፊት የምትማሩትን ብቻ አይደለም የሚወስነው፤ ሙሉ አስተሳሰባችሁንና ማንነታችሁን የሚቀይር ውሳኔ ነው። ወደ ስራ አለም ስትቀላቀሉም በተማራችሁት የምትሰሩ ከሆናችሁ ስራችሁንም ይወስናል። ስለዚህ ሐሳብ ቢገባችሁ አይገርምም።

በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ መሀል ያለውን ልዩነት ከሞላ ጎደል ታውቁታላችሁ ተብሎ ቢታሰብም በትምህርት ደረጃ ያለውን ልዩነትና ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትቀላቀሉ ያለውን ልዩነት ትንሽ ልበላችሁ። ከትምህርት አይነቶቹ እንጀምር።

#Natural_Science (የተፈጥሮ ሳይንስ)
Biology
Chemistry
Physics
በዋናነት ሜዳው ላይ የሚጫወቱ ተሰላፊዎች ናቸው።

#Social_Science (ማኅበራዊ ሳይንስ)
History
Geography
Economics
በዋናነት የተሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው።

በሁለቱም ምድብ በኩል ያሉ ተጫዋች የትምህርት አይነቶች ቀላል የሚባሉ ባይሆኑም በተፈጥሮ ሳይንስ በኩል ያሉት ግን ትንሽ ከበድ ያለ አስተላለፍ የሚጠቀሙ ተጫዋቾች ናቸው። እንዴት እንደሆነ በሚቀጥሉ አንቀጾች እናነብባለን።

-> Maths & English በሁለቱም በኩል የሚጫወቱ 'ጆከሮች' በመሆናቸው አንድ ተማሪ 'ናቹራል'ም 'ሶሻል'ም ቢቀላቀል የሚቀሩለት አይሆንም። ለዚህ ነው ከላይ ካሉት ጋር የለያየኋቸው።

"የቱን ምድብ ልምረጥ?" ብላችሁ ስታስቡ ታሳቢ ማድረግ ያሉባችሁን ነጥቦች እንመልከት።

1. ፍላጎት እና ጠንካራ ጎን
አንድ ተማሪ የተፈጥሮ ሳይንስ ምድብ ለመግባት Maths, Chemistry, Physics and Biology ላይ ጎበዝ መሆን ይጠበቅበታል። ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ ማወቅ የሚፈልግ እና ነገሮችን መሞካከር የሚፈልግ ተማሪ የተፈጥሮ ሳይንስ ቢገባ የተዋጣለት ይሆናል።

በተቃራኒው አንድ ተማሪ ወደ ማኅበራዊ ሳይንስ ለመግባት language, History, Geography, Economics ላይ ጎበዝ መሆን ይጠበቅበታል። ረጅም ሰዓት ማንበብ የሚወድ፣ መጻፍ የሚወድ፣ ክርክር/ውይይት የሚወድ፣ የሚመራ እና በነዚህም የተካነ ከሆነ ማኅበራዊ ሳይንስ መንገዱ ነው።

ከላይ ከተጠቀሱት 6 የትምህርት አይነቶች ስትማሩት ድካም የማይፈጥርባችሁ፣ ደስታ የሚሰጣችሁ፣ ቶሎ ለመረዳት አጭር ጊዜ የሚፈልግባችሁ የትምህርት አይነት የቱ ነው? ይህንን ለይታችሁ እወቁ።

2. ወደፊት መሆን ከምትፈልጉት አንጻር መመልከት
አንድ ተማሪ እስከ 10ኛ ክፍል ሲማር ወደፊት ምን መሆን እንደሚፈልግ በራሱ ፍላጎት አቅጣጫ እንዲይዝ እየተቀረጸ ነው የሚሄደው። ልጆች ሳለን ምን መሆን እንደምንፈልግ ስንጠየቅ "ዶክተር፣ ፓይለት፣ ኢንጂነር፣ መምህር፣ ነርስ፣ ሹፌር፣ ፕሬዘደንት..." እያልን ነበር የምንመልሰው። ይህ መልሳችን የተጠና መልስ ሆኖ አይደለም። ከጓደኞቻችን ሰምተን፣ በቤተሰብ ፍላጎት 'እንዲህ ነው የምትሆንልኝ/የምትሆኚሊኝ' ተብለን፣ መልስ የለንም ላለመባል እና የመሳሰሉ ውሃ የማይቋጥሩ ምክንያቶችን ይዘን ነበር የምንመልሰው።

ነገር ግን በሂደት እስከ 10ኛ ክፍል ስንደርስ በልጅነት ከተመኘነው ይልቅ ፍላጎታችንን ያገናዘበ ምርጫ ለመምረጥ እንወስናለን። ዶክተር እሆናለሁ እያለ ያደገ ተማሪ የታሪክ ተመራማሪ መሆን ይፈልግና ያርፈዋል። ምናልባትም እየተመከረ ኢንጂነር መሆን ይፈልግ የነበረው ተማሪ ለአቅመ-ውሳኔ ሲደርስ ሰዎች ይመክሩት ከነበረው ባሻገር ፍላጎቱም ከኢንጂነሪንግ ትምህርቶች አንዱ እንደሆነ ተረድቶ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በዚያው ዘርፍ የሚከታተል ይኖራል።

ስለዚህ ወደፊት መሆን ከምትፈልጉት ነገር አንጻር ነው ዛሬ ላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ወይም የማኅበራዊ ሳይንስ መምረጥ ያለባችሁ።

----
የተፈጥሮ ሳይንስ የመረጠ ተማሪ
በሁሉም #የጤና_ዘርፍ መማር ይችላል።
Doctor, Nurse, Pharmacist, Medical Lab, HO...

አጠቃላይ የምህንድስና/ኢንጂነሪንግ ትምህርቶች
Mechanical Engineering
Civil Engineering
Electrical Engineering
Chemical Engineering
Biomedical Engineering
Biotechnology Engineering
Software Engineering ...

ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶች
Software engineering
Computer Scientist
Architect

በመምህርነት የሳይንስ መምህር መሆን ይችላል።

----
ማኅበራዊ ሳይንስ የመረጠ ተማሪ

የህግ ባለሞያ
ጠበቃ
ዳኛ...

ቴክኖሎጂ ላይ
IT
Tech Marketing...

Business ላይ
Economist (Economics)
Marketer (Marketing)
Manager (Management)
Accountant (Accounting)
Diplomat...

በመምህርነት
History/Civics/Language teacher መሆን ይችላል።

3. የስራ ጫና እና ጭንቀት መቋቋም መቻል
እንደ አጠቃላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ከማኅበራዊ ሳይንስ የበለጠ የትምህርት ጫና አለው።
ቶሎ የመድከምና የመሰላቸት ባህሪ ያለበት ተማሪ ተዕግስትን የሚፈታተኑ ትምህርቶችን የያዘ ዘርፍ ነው። ትዕግስት ይጠይቃል።

በዩኒቨርሲቲ አለም ረጅሙ የትምህርት ጉዞ ያለው በህክምናው/Medicine አለም ነው። 7 አመታትን የሚረዝም ጊዜ ይፈልጋል። ሌሎች የጤና ዘርፎች እንኳ ሁሉም ማለት በሚያስችል መልኩ 5 አመታትን ነው የሚፈልጉት።

ማኅበራዊ ሳይንስ በአንጻራዊነት አጭር የትምህርት ጊዜ የሚወስድ ነው። እንደ የህግ ትምህርት እና ኢኮኖሚክስ ረጅሙን አመት የሚፈልጉ ከመሆን ባለፈ የህግ ትምህርት ከህክምናው ትምህርት ባልተናነሰ እጅግ በጣም ረጅም የንባብ እና የሽምደዳ ጊዜ የሚጠይቅ ትምህርት ነው።

ስለዚህ የተፈጥሮ ሳይንስ የመቀላቀል ፍላጎት ካላችሁ ጫናን ለመቋቋም ትከሻችሁን ጠንከር አድርጉ። ውጤታችሁም አሪፍ ይሆናል። ከከባድ ጫና ነጻ ሆናችሁ መማር ካሰባችሁ ማኅበራዊ ሳይንስን ተቀላቀሉ።

መገንዘብ ያለብን ዋና ነጥብ፡ በሁለቱም ምድብ ብትሄዱ ሁሉም የትምህርት መስኮች ማንበብን የሚፈልጉ፣ የእንግሊዘኛ እውቀትን የሚጠይቁ፣ ቢያንስ የ4 አመታት ቢበዛ የ7 አመታትን ትዕግስት የሚጠይቁ ናቸው። አቋራጭ የሚባል መንገድ የለም!

እድሜ ለፕሮፌሰሩ ዛሬ ዛሬ አንድ ተማሪ ትምህርት ቤትም ዩኒቨርሲቲም የሚገባው የመማር ፍላጎት ካለው ብቻ ነው። ለቀልድ የሚመጣ ተማሪ በገባበት በር ተመልሶ ይወጣል። በየእርከኑ ጥብቅ ቁጥጥር ስላለ 'ቀልጄ እመረቃለሁ' የለም። Exit Exam ስለሚጠብቃችሁ በደንብ ማንበብ ይኖርባችኋል።

ከላይ ካሉ የምርጫ አመክንዮዎች ባሻገር ጫናን የመቋቋም አቅማችሁን ማገናዘብ ይኖርባችኋል።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል።
❤1
ክፍል ሁለት



4. ተፎካካሪ የሚበዛባቸው ትምህርቶች

በሁሉም አገራት ያሉ ሰዎች የየራሳቸው ተወዳጅ የትምህርት መስኮች አሏቸው። ወደ አፍሪካ በተለይም ኢትዮጵያ ስንመጣ እንደ ህክምና፣ የህግ ባለሞያነት እና ምህንድስና ቦታ የሚሰጣቸው ትምህርቶች የሉም። ይህ በተማሪዎችም በተማሪዎቹ ወላጆችም ዘንድ የሚታይ እውነታ ነው።

በዚህ ጫና ምክንያት ተማሪዎች በጣም ጎበዝ ከሆኑ እና ውጤታቸው አሪፍ ከሆነ ህክምና እና ምህንድስና የመማር ፍላጎታቸው ከፍ ያለ ይሆናል። በዚህም ዘርፍ የተመረቁ ተማሪዎች ከሌሎች ምሩቃን የተሻሉ እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ። ይህ አስተሳሰብ ሁሌ ትክክል ነው ማለት አይቻልም። አንድ ተማሪ ጎበዝ ስለሆነ ብቻ ሐኪም መሆን አለበት የሚባለው እሳቤም የተሳሳተ ነው።

ወደ ዩኒቨርሲቲም ስትገቡ ፉክክሩ ስለሚከር እነዚህን ትምህርቶች በቀላሉ ማግኘት ከባድ ይሆናል። ስለዚህ ከአሁኑ ዶክተር፣ ኢንጂነር እና የህግ ባለሞያ የመሆን ህልም ያላችሁ ተማሪዎች ከሌሎቹ የትምህርት መስኮች የበለጠ መልፋት እንዳለባችሁ ተገንዘቡ። ካልሆነ በተፈጥሮ ሳይንስም በማኅበራዊ ሳይንስም ጫና የሌለባቸውን ከህልማችሁ ጋር የሚቆራኘውን በማሰብ መምረጥ ትችላላችሁ።

5. የቤተሰብና የኅብረተሰብ ጫና
ከ4ኛው ጋር ተቀራራቢ ሐሳብ የያዘ ነጥብ ነው። ቤተሰብም ይሁን ኅብረተሰቡ ቅድም ለተገለጹ ሶስት የትምህርት መስኮች የሚሰጠው ቦታ ከፍ ያለ ነው። ብዙ ወላጆች የልጆቻቸውን ህልም ሳይሆን የራሳቸውን ህልም ነው በልጆቻቸው ላይ የሚጭኑት። በዚህም ብዙ ስኬት የራቃቸውን ሰዎች በየአካባቢያችን እንመለከታለን።

ወልደው በልፋት ላሳደጉን ወላጆች ምርጫቸውን ብንከተል ክፋት የለውም። ነገር ግን ይህ የወላጆች ስህተት ብዙ ባለ ተሰጥኦ አዕምሮን ገድሏል። ሊስተካከልም ይገባዋል። ወላጆች ልጆቻቸው ደስተኛ ሆነው የሚፈልጉትን ትምህርት ተምረው በዚያም ስኬታማ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ቢያበረክቱ የተሻለ ነገን መመልከት እንችላለን።

በተፈጥሮ ሳይንስም በማኅበራዊ ሳይንስም ተምረው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች አሉ። "ዶክተር ስለሆነ ስኬታማ ይሆናል። አካውንታንት ስለሆነ ስኬታማ አይሆንም።" የሚባል ነገር የለም። ስኬቱ የሚወሰነው በተማሪው ያላሰለሰ ጥረት ብቻ ነው። የህክምና ትምህርት ጀምረው ያቋረጡ ሰነፎችን አይተናል። አካውንቲንግ ተምረው ቆራጥ በመሆን ሰርተውበት ስኬት በራቸውን ያንኳኳላቸውን ጎበዞች አይተናል። የትም መሄድ ሳይጠበቅብን እዚሁ ከተማችን ላይ በቂ ምሳሌዎች አሉን። ስም አልጠራም።

ለናንተ የማስቀምጠው ምክረ-ሐሳብ፡
የወላጆቻችሁ ምርጫ ከናንተ ምርጫ ከተጣጣመ እንኳን ደስ አላችሁ። ነገር ግን ምርጫቸው ከምርጫችሁ ከተለያየ ሁለት መንገድ አላችሁ።
አንደኛ- ፍላጎታችሁን ገድባችሁ ፍላጎታቸውን ማሟላት። የመረጡላችሁን የማትፈልጉትን ትምህርት ለመውደድ እና እየተላመዳችሁት መሄድ። በዚህም ቢያንስ የነርሱን ደስታ ታገኛላችሁ።
ሁለተኛ- ይህን ትምህርት የምትማሩት እናንተ እንጂ ወላጆቻችሁ ወይም ኅብረተሰቦቻችሁ አይደሉም። የናንተ አዕምሮ የትኛውን ቢቀበል እንደማይከብደው የምታውቁት እናንተ ናችሁ። በትምህርቱ አለም ማሳካት የምትፈልጉትን ህልም የምታውቁት እናንተ ናችሁ። የራሳችሁን ህልም እንጂ ሰው የቀረጸላችሁን ህልም መኖር ግዴታችሁ አይደለም።

ስለዚህ እንደተማረ ወጣት ወላጆቻችሁን ቁጭ አድርጋችሁ ለወላጅ በሚገባው ክብር አሳማኝ ነጥቦቻችሁን በማንሳት ማወያየት። ባይቀበሏችሁ ሁሌም ቢሆን ሁሉንም ማስደሰት አይቻልምና የራሳችሁን ውሳኔ መወሰን።

ክፍል ሶስት በቅርብ ደቂቃዎች ይለቀቃል።
እስኪ ይህን መጠይቅ ሙሉ።
ስትማሯቸው ደስታ የሚሰጧችሁን፣ ቶሎ ለመረዳት ብዙ ጊዜ የማይፈልጉባችሁን እና አሪፍ ውጤት ያመጣችሁባቸውን ትምህርቶች ምረጡ።
Maths and English በሁለቱም በኩል ስለማይቀሩላችሁ ምርጫዎቹ ውስጥ አይካተቱም።
Final Results
47%
A. Chemistry, Physics, Biology
53%
B. History, Geography, Economics, Citizenship
ክፍል ሶስት


6. የጓደኛ/የክፍል ጓደኛ ጫና
ይህ ነጥብ ከ5ኛው ጋር ቢነሳ ችግር አልነበረውም። ነገር ግን የነገሩን ክብደት ለመጠቆም ስለፈለግኩ ነው ለብቻው ላነሳው የወሰንኩት።

የሰው ልጅ በምድር ሲኖር ከቤተሰቡ ባለፈ ጓደኛ ያስፈልገዋል። ልክ እንደቤተሰብ የሚቀርበው፣ አንዳንዴም አለፍ ብሎ ከቤተሰቡ የበለጠ የሚቀርበው ጓደኛ ሊኖረው/ሊያስፈልገው ይችላል።

በዘመናችን ትንሽም ይሁን ብዙ፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ ጓደኛ የምናፈራበት ወሳኙ ቦታ ትምህርት ቤት ነው። የህይወት መስመራችንን የማያበላሹ ምግባረ-መልካም ጓደኞች መያዛችን አስፈላጊ ነው።

ይህ ሐሳብ ከ Stream መረጣ ጋር ምን አገናኘው?
ተማሪዎች ምድባቸውን በሚመርጡበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የጓደኛ ግፊት ይደርስባቸዋል። "እኔ ሶሻል ስለምገባ አንተም ከኔ ጋር ሶሻል ግባ።" "እርሷ ናቹራል ስለገባች እኔም ናቹራል እገባለሁ።" አይነት አስተሳሰቦች አሉ።

አንዳንዴም ሰነፉ ተማሪ የተፈጥሮ ሳይንስ ላይ ጎበዝ ተማሪዎች ይበዛሉ በሚል እሳቤ በጎበዝ ተማሪዎች ላይ ጥገኛ ኮራጅ ሆኖ ዩኒቨርሲቲን ለመቀላቀል የሚዳክር አለ። ይህም የተሳሳተ እና መታረም ያለበት እሳቤ ነው። ማንም ከማንም አይበልጥም። ሁሉም እኩል ነው። እርሱ አንብቦ ከገባው አንተም አንብበህ ትረዳለህ። ልዩነቱ ትኩረትና ጊዜ መስጠቱ ላይ ነው። ስለዚህ ለዩኒቨርሲቲ የምትዘጋጁበትን መሠናዶ ጊዜ ሰጥታችሁ በደንብ ለማንበብ ተዘጋጁ።

ከፍ ስንል ደግሞ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በሁለት ተቃራኒ ጾታ መካከል በሚፈጠር የፍቅር ግንኙነት (ክብርን የሚያጠፋ፣ እድሜና ጉልበትን የሚያባክን ግንኙነት ብለው ይሻላል) በዚህ የምድብ መረጣ ላይ አስተዋጽኦ ሲያደርስ ይታያል። "እኔ ናቹራል ስለምገባ አንቺም ናቹራል ግቢ።" "እሷ ሶሻል ስለገባች እከተላታለሁ።" የሚሉ 'ሞኞች' አሉ።

ወዳጆች! በተፈቀደው መንገድ ያልተፈጠረ መጣመር አስቀያሚ ከሆነ መለያየት አይታገድም። + ጊዜያዊ ስሜታችሁን ተከትላችሁ የማትፈልጉት Stream ውስጥ እንዳትገቡ እመክራለሁ። በኋላ መለያየት ሲመጣ "እርሷን/እርሱን ብዬ የማልፈልገውን ትምህርት እየተማርኩ የሚል ጸጸት ይከተላችኋል። ከአሁኑ ቀልድ ላይ የሆናችሁ ጓዶች ቀልድና ቁም ነገር እየለያችሁ።

7. ናቹራል=ጎበዝ ❌ ሶሻል=ሰነፍ ❌
ማኅበራዊ ሳይንስ የሰነፎች የተፈጥሮ ሳይንስ የጎበዞች አድርጎ በማሰብ ትምህርት የሚከብዳቸው ተማሪዎች ወደ ሶሻል የመዘንበል ሁኔታ ይታያል። በርግጥ ከማኅበራዊ ሳይንስ ይልቅ የተፈጥሮ ሳይንስ ከበድ ይላል። ሆኖም ግን ማኅበራዊ ሳይንስም ቀላል የሚባል አይደለም። በመሠረቱ በየትኛውም ምድብ ብትገቡ ረጅም ጊዜ ሰጥታችሁ ለማንበብ ዝግጁ ያልሆናችሁ ካላችሁ ከወዲሁ ትምህርቱን እንድታቋርጡት አሳስባችኋለሁ!

ከላይ እንደጻፍኩላችሁ በሁለቱም ምድቦች የሚገኙ የትምህርት መስኮችን ተምረው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች አሉ። በተደጋጋሚ እንደጻፍኩት ዋናው የግል ጥረት ነው።

አንድ ተማሪ ጠንካራ ጎኑን እንደሚለየው ሁሉ ደካማ ጎኑንም ለይቶ ማወቅ አለበት። ተማሪው የእንግሊዘኛ ቋንቋ እውቀት ከሌለው ማኅበራዊ ሳይንስ ባይገባ እመክራለሁ! ተማሪው የሒሳብ ችሎታ ከሌለው የተፈጥሮ ሳይንስ ባይገባ እመክራለሁ።

8. የምትማሩት ለገንዘብ ነው? ወይስ ለማወቅ ነው?
ብዙ ሰዎች ጋር የሚስተዋል አንድ ችግር አለ። "ይህን ተምሬ ሀብታም እሆናለሁ።" የሚሉ ሰዎች ቁጥር ትንሽ አይደለም።

ወዳጆች.. ስንማር ዋና አላማችን መሆን ያለበት #በእውቀት_ራሳችንን_ማዳበር_ነው ።
ሀብታም ለመሆንማ እዚሁ ከተማችን ላይ ያሉ ባለ ፋብሪካዎች ጋር ሂዱና ከነዚህ ሁሉ ባለፋብሪካዎች ዲግሪ ያለው ስንት ሰው ነው ብላችሁ ጠይቁ። ከ100 ውስጥ 10 ባለ ዲግሪ አታገኙም። ምናልባትም አንዳንዶቹ ከ8ኛ ክፍል ያቋረጡ ናቸው። ትምህርት ለሀብት ሳይሆን ለእውቀት ነው የሚፈለገው። ጥሩ እውቀት ከጨበጥንበት በዚያ ገንዘብ መስራት አይከብድም።

9. ወደፊትን በመመልከት ዛሬን መወሰን
አለማችን እየሄደችበት ያለው መንገድ እጅግ ተለዋዋጭና ሊገመት የሚከብድ ነው። ቢሆንም ጭላንጭሎችን መመልከት ችሎ ለዚያ መዘጋጀት ያስፈልጋል። "ኢትዮጵያ ይሁን አለማችን ለሚቀጥሉት ከ10-20 አመታት የትኛውን ስራ ነው የሚፈልጉት?" ብለን መጠየቅ አለብን።

ይህን ለመመለስ የኢትዮጵያን ሁኔታ ማጤን ይጠበቅብናል። የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ አካባቢዎች ወደ ከተማነት መቀየር /Urbanisation ፣ የአየር ጸባይ፣ የዲጂታል አለም እድገት፣ ከሌሎች አገራት ጋር ያለን መስተጋብር.... ተመልክተን የወደፊቱን በትንሹ መተንበይ እንችላለን። ከነዚህ ነገሮች በመነሳት ለወደፊቱ ተፈላጊነታቸው የሚጨምሩ ስራዎች እነማን ናቸው?
Health and Medical Sectors (Natural Science)
- ሰው ባለበት ቦታ ከጤና ጋር በሽታ አለ። በሽታ እስካለ ድረስ በቂ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ያስፈልጉናል። በአገራችን ያለው የሐኪም፡ታማሚ ስብጥር እጅግ አስደንጋጭ ነው። አንድ ሐኪም በትንሹ ለ10,000 - 20,000 ታማሚ የሚመደብበት እጅግ የወረደ የህክምና ስርዓት ያለበት አገር ውስጥ ነው ያለነው። (1:20000) ስለዚህ ምንም በማያጠራጥር ሁኔታ ብቁ የሆኑ ሐኪሞች (ሆድ ውስጥ መቀስ ረስተው የማይሰፉ¡) ለአገራችን አስፈላጊ ነው።

Infrastructure and Engineering (Natural Science)
- የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ የመኖሪያ ቤት፣ የህንጻ፣ የመንገድ፣ የንጹህ ውሃ መስመር፣ የኤሌክትሪክ... እንዳጠቃላይ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ይበራከታሉ። ስለዚህ በዚህ ዘርፍ በቂ እውቀትን ከስራ ፍላጎት የያዘ ሰው ተፈላጊ የማይሆንበት ምክንያት የለም። (መጥፎ የሚባል የአገራችን የቢሮክራሲ ስርዓት መኖሩ እንዳለ ሆኖ ነው ታድያ!)

Information and Digital Technology (Natural Science)
- ለዚህ ሐሳብ ብዙ መተንተን አይጠበቅብኝም። አገራችን እንደ ኤሊ ቢሆንም ወደ ዲጂታል እና ቴክኖሎጂ አለም እየገባች ነው። ይህን ትምህርት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ባትማሩት እንኳ በግል ከመማር ውጭ ሌላ ምርጫ አይኑራችሁ።

Agriculture (Natural + Social Sciences)
- ሰው የሚባል ፍጥረት እስካለ ድረስ ግብርና ቁጥር አንድ ተፈላጊ ነገር ከመሆን አይወገድም። በተጨማሪም ብዙ ግድቦችን እየገነባን ስለሆነ በውሃ ሳይንስ ላይ እጅግ በጣም ብዙ ባለሞያዎች ያስፈልጉናል። ስለዚህ ቶሎ ተምሮ ለዚህ የበቃ እውቀትም ገንዘብም ማፈሱ የማያጠራጥር ነው።

Business, Finance and Entrepreneurship (Social Science)
- አገሪቱ እያደገች በሄደች ቁጥር በቢዝነሱ፣ በንግዱ አለም ... ያለው ሁኔታ እያደገ ይሄዳል። የገበያውን ሁኔታ የሚረዱ፣ ድርጅትን በብቃት የሚመሩ ትንታግ ለስራ የነቃ አዕምሮ ያላቸው የተማሩ ወጣቶች ተፈላጊነት ይጨምራል።

Law, Policy and Governance (Social Science)
- የአገሪቱ ህዝብ በጨመረ ቁጥር፣ እድገት በጨመረ ቁጥር በዚያው ልክ ህግና ደንብን የሚያረቁ፣ ህግን የሚያስከብሩ፣ አስተዳደሩን ለማጠናከር የሚበጁ በስራቸው ብቁ የሆኑ አካላት ተፈላጊ ይሆናሉ።

Education (Social and Natural Sciences)
-አገራችን በአፍሪካ ትልቁ የወጣት ቁጥር ካሉባት አገራት ተርታ ትመደባለች። ያሉንን ታዳጊ ሀይሎች ለማስተማር በትምህርትና ትምህርት ነክ የትምህርት መስኮች ተፈላጊ ሆነን መገኘት ከቻልን ራሳችንንም አገራችንንም እንጠቅማለን።
❤2
Media, Communication & Arts (Social Science)
- Journalists, Public Relation Specialists, Language Translators...

Tourism & Hospitality (Social Science)
- Tour Guides, Travel Experts, Hotel & Hospitality Managers....
በሰፊው ያስፈልጋሉ።

ጠቅለል ስናደርገው

Sector                         Stream
Health                          Natural  
Engineering                Natural
Tech                             Natural
Agriculture                  Both
Business                     Social
Law & Governance    Social
Education                    Both
Environment               Natural
Media                           Social
Tourism                       Social

ወደ ማጠቃለያ ሐሳብ እንሂድ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመቀላቀል
ረጅም ሰዓት መስጠት፣ ጥልቅ የሆነ ትኩረት፣ በተደጋጋሚ ልምምድ የሚፈልጉ ትምህርቶችን የያዘ ምድብ ነው።

የማኅበራዊ ሳይንስ ለመቀላቀል
በጥልቀት ማሰብ፣ ጥናቶችን ማካሄድ፣ ጠንካራ የቋንቋ እውቀት ያስፈልጋችኋል።

በሁለቱም ምድቦች ስመ-ጥር ስኬታማ ሰዎች አሉ። አንዱ የጎበዝ አንዱ የሰነፍ ተብሎ አይለይም። የግል ጥረት ቁጥር አንድ አስፈላጊው ነገር ነው። አገራችን በሁለቱም ምድቦች የተማሩ ሰዎች ያስፈልጓታል።

ሶሻል የምትገቡ ተማሪዎች እንደ አላህ ፈቃድ በቀጣይ ሁለቱ አመታት ከኔ ጋር ሰፊ ጊዜ እናሳልፋለን። ናቹራሎች ምናልባት በEnglish ዳግም ልንገናኝ እንችል ይሆናል። ለሁላችሁም መልካም ጊዜ እመኛለሁ።

በመረጣችሁት ምርጫ አላህ መልካሙን ሁሉ ይግጠማችሁ። የተሳካ መንገድ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። የሰው ልጅ በትምህርት አለም ላይ ስለዘለቀ ብቻ ሳይሆን ከትምህርትም ርቆ መጽሐፍ ሊለየው አይገባም። የትኛውም አይነት ድሎት እና ስልጣኔ ላይ ብንሆን ካላነበብን፤ አዕምሯችንን ካልመገብን ጎዶሎ ሆነን ነው የምንቀረው። ስለዚህ የ'አንብብ' ትውልዶች ማንበብ የስልጣኔ መነሻ እንደሆነ ተረድተን ንባብን ባህላችን እናድርግ።

ሰላም ለሁላችሁም!
❤1
Forwarded from STEM with Murad 🇪🇹
‎የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ — 2025

1 Addis Ababa University
2 University of Gondar
3 Bahir Dar University
4 Jimma University
5 Mekelle University
6 Hawassa University
7 Haramaya University
8 Adama Science and Technology University
9 Arba Minch University
10 Jigjiga University
11 Addis Ababa Science and Technology University
12 Ambo University
13 Dilla University
14 Unity University
15 Debre Berhan University
16 Wollo University
17 Debre Markos University
18 Wolaita Sodo University
19 Madda Walabu University
20 Worabe University
21 Wachamo University
22 Debre Tabor University
23 Wolkite University
24 Ethiopian Civil Service University
25 Arsi University
26 Samara University
27 Assosa University
28 Dire Dawa University
29 Wollega University
30 Mattu University
31 Mizan-Tepi University
32 Kotebe Education University
33 Adigrat University
34 Woldia University
35 Oromia State University
36 Bule Hora University
37 Aksum University
38 Bonga University
39 Rift Valley University
40 Oda Bultum University
41 Raya University
42 Injibara University
43 Selale University
44 Debark University
45 Kebri Dehar University
46 Gambella University
47 Mekdela Amba University
48 Dembi Dolo University
49 Jinka University
50 Borena University
Un Ethiopian Police University
‎
‎(According to UNIRANKS® — Top-Ranked Universities in Ethiopia - 2025)
❤2