FMC (Fana Media Corporation)
48.4K subscribers
44.6K photos
231 videos
20 files
16.9K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
የዓለም ሠራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ)

ሚያዝያ 23/2015 (ዋልታ) በየዓመቱ እ.ኤ.አ ግንቦት አንድ የሚከበረው የዓለም አቀፍ ሰራተኞች ቀን እየተባለ መከበር ከጀመረ 134 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ለመሆኑ ታሪካዊ መነሻው እና ዓላማውስ ምን ነበር የሚለውን ስናይ ብዙ አስደናቂ እና አወዛጋቢ መረጃዎችን እናገኛለን፡፡

የዓለም ሰራተኞች ቀን በፈረንጆቹ ግንቦት አንድ እንዲከበር ውሳኔ ላይ የተደረሰው እ.ኤ.አ በ1889 በዓለም አቀፍ የሶሻሊስት ቡድን እና በሰራተኞች ማህበራት ውሳኔ ሲሆን በ1886 በችካጎ የተቀሰቀሰው የሄይማርኬት የሰራተኞች የመብት ጥያቄ አድማን ለማስታወስ በማሰብ ነው፡፡

የሄይማርኬት አድማ ግንቦት 1886 በችካጎ ከተማ ተቀሰቀሰ፡፡ በዕለቱ ከ400 ሺሕ በላይ ሰራተኞች የስምንት ሰዓት የስራ ጊዜ በመጠየቅ የስራ ማቆም አድማ መቱ፡፡ ከፖሊስ ጋር ተጋጩ፣ ሰዎች ተገደሉ፡፡ በግጭቱ ወቅት በፖሊስ ላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ሰባት ሰራተኞች ተይዘው ስድስቱ የሞት ፍርድ ሲፈረድባቸው አንዱ በ15 ዓመት እስራት ተቀጣ፡፡ ውሳኔው ኢፍትሃዊ ነው በሚል ብዙ ሰራተኛ ቅር ተሰኘ፡፡ ሁነቱም በታሪክ የሄይማርኬት ክስተት ወይም ጉዳይ (Haymarket Affair) ተብሎ ይታወሳል፡፡
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02QqR1a1JRZos5heNbtLJDVUWb9zAQnutnXhR8P76hbHsU8shnPUvnWCZxvLyFPmFTl
የሃላላ ኬላ ሪዞርት ግንባታ የተፈጥሮ ሃብቶችን በማልማት በቱሪዝም ሃብት ተጠቃሚ ለመሆን ሁነኛ ማሳያ ነው - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

ሚያዝያ 23/2015 (ዋልታ) የሃላላ ኬላ ሪዞርት ግንባታ የኢትዮጵያን እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶች በማልማት የአገሪቷን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ በቱሪዝም ሃብት ተጠቃሚ ለመሆን ሁነኛ ማሳያ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር-ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሃላላ ኬላ ሪዞርት መርቀው የከፈቱ ሲሆን ሪዞርቱ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።

በምረቃ መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የሃላላ ኬላ ሪዞርት የተፈጥሮ ፀጋዎችን በማልማትና በመጠቀም በኩል ለሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች አርአያ የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

የሪዞርቱ ግንባታ የኢትዮጵያን እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶች በማልማት ገጽታዋን ከመቀየር ባለፈ በቱሪዝም ሀብት ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ሁነኛ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02nUM9NrxfTr9VchKfToscWo2szmHgEzWUDc9A99h1vmyADghFj2CfsFdkg6kpnZpSl
የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነው ሃላላ ኬላ የምሽት ገጽታ በፎቶ
በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በጃዊ ወረዳ በተለያዩ ምክንያቶች ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎች እርቅ በመፈፀም ወደ ቤታቸው ተመለሱ

ሚያዝያ 23/2015 (ዋልታ) ሚያዝያ 1/2015 ዓ.ም ከመንግስት ጋር ቅሬታ በመፍጠር ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎች በሀገር ሽማግሌዎች አደራዳሪነት እርቅ ፈፅመው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።

እርቅ ፈፅመው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ሲያደራድሩ ከነበሩት የሀገር ሽማግሌዎች መካከል የጃዊ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ያረጋል አለነ እንደገለፁት ሰላም ለዜጎች መኖር ቁልፍ መሣሪያ ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጫካ የገቡት ዜጎች ከመንግስት ጋር ያላቸውን ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በማድረጋቸውና በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ስምምነት ፈፅመው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉን የቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

የተጀመረው ድርድር በዚህ የሚቆም ሳይሆን ከወረዳ ወረዳ፣ ከዞን ዞንና ከክልል ክልል ድረስ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሀገር ሽማግሌዎች ተግባሪን አጠናክረው ለመቀጠል አቅደው እየሠሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

መጋቢ ሀዲስ ያረጋል አለነ ሁሉም ዜጎች የሰላም አስፈላጊነትን በተገቢው መንገድ ተረድተው ለሰላም ዘብ እንዲቆሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid025iVi1MMxjxsis7Kw8XsVA1C9ccpnYePCqZFZv1scbMcvnxEghiMkUgxD1nncF81Dl&id=100064690148931&mibextid=Nif5oz
የጋራ ግብረ ኃይሉ የራሳቸውን አደረጃጀት ፈጥረው መንግሥትን በሕገ ወጥ መንገድ ለመተካት ያሰቡ አካላትን ተልዕኮ ለማክሸፍ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ቀጥሏል

ሚያዝያ 24/2015 (ዋልታ) የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የራሳቸውን አደረጃጀት ፈጥረው መንግሥትን በሕገ ወጥ መንገድ ለመተካት ያሰቡ አካላትን ተልዕኮ ለማክሸፍ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ቀጥሏል።

የሀገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በኃይል ለማፍረስና እኩይ የፖለቲካ ፍላጎት ለማሳከት ከፍተኛ አመራሮችን በመግደል፣ በኅብረተሰቡ ወስጥ ሽብርና ፍርሃትን በመፍጠር እኩይ ፍላጎታቸውን ለማሳካት በሕገ ወጥ መንገድ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጽንፈኛ የሽብር ቡድኖችን እንቅስቀሴና ድርጊት እያመከነ ነው።

በዚህም መሠረት ባለፈው ጊዜ ከወሰዳቸው ርምጃዎች በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ጽንፈኛው ቡድን ሰሜን ወሎ ዞን ተኩለሽ ጫካ ቆፍሮ ያዘጋጀው ስቶር ውስጥ የቀበራቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ተተኳሾችን መያዙን የጸጥታና የደኅንነት ምንጮች ገልጸዋል ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02KbhfRd2HcKMqJ68hFM8WrU4VNKCg8RFKz3ym7sHKasptrHpySXsm2Q9n1JikH42pl&id=100064690148931&mibextid=Nif5oz
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከ #ዋልታ_ቴቪ ሚያዝያ 24/2015
https://fb.watch/kgoNbbX5BG/?mibextid=Nif5oz
የጠ/ሚ ዐቢይ የጽሑፍ ሥራዎችን የሚያሳይና የሚዳስስ የመጽሐፍ ዐውደ ርእይ ዛሬ በአብርሆት ይከፈታል

ሚያዝያ 24/2015 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጽሑፍ ሥራዎች የሚያሳይ እና የሚዳስስ የመጽሐፍ ዐውደ ርዕይ በአብርሆት ቤተ መዛግብት መዘጋጀቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተዘጋጁ ህትመቶችን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጽሁፍ ሥራዎችን የሚያሳይ እና የሚዳስሰው ይህ ዐውደ ርዕይ ከሚያዚያ 24 እስከ ሚያዚያ 29 ቀን 2015 ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ነው የተጠቆመው፡፡

በእነዚህ ቀናትም ዜጎች በአብርሆት ቤተ መዛግብት በመገኘት እንዲካፈሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ጀመሩ

ሚያዝያ 24/2015 (ዋልታ) “እኔም ድርሻ አለኝ” በሚል የመዲናዋ ወጣቶች ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ ግዢ ተሳትፎ የማስጀመሪያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የመዲናዋ ወጣቶች ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚውል ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ ነው የቦንድ ግዢ ተሳትፎ ማስጀመሪያ የተካሄደው።

“እኔም ድርሻ አለኝ” የቦንድ ግዢ ተሳትፎ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ከ550 በላይ ወጣቶች የታደሙ ሲሆን የ300 ሺህ ብር የቦንድ ግዢም ፈፅመዋል።

በቀጣይ ቀናትም ወጣቶቹ በከተማ የቦንድ ግዢ ንቅናቄም የሚያካሂዱ ይሆናል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን፤ የአዲስ አበባ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ምስክር ነጋሽ እንዲሁም የመዲናዋ ወጣቶች ተገኝተዋል።

በሰለሞን በየነ
የጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ-ንባብ በአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ተከፈተ

ሚያዝያ 24/2015 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሐይ ጳውሎስ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ-ንባብ በይፋ ከፍተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተዘጋጀውና ለ6 ቀናት የሚቆየው የመጽሐፍ ዐውደ ርዕይ የተከፈተ ሲሆን፤ አውደ ርዕይው ኢትዮጵያውያን የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ጽሑፎችን ማስተዋወቅ እንደሆነ ተነግሯል።

ቤተ-ንባቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በስራ ገበታ ላይ እያሉ ሶስት የሚደርሱ መጽሐፎችን ጨምሮ ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የተሰነዱ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የንግግር ዶክመንቶች የሚቀመጡበት መሆኑ ተጠቁሟል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሐፍቶችና ሌሎች ዶክመንቶች የራሱ የሆነ በሆነ ቤተ-ንባብ ማደራጀት መቻሉ፤ ታሪክን በመሰነድ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሆነ ተነግሯል።

በደረሰ አማረ
በመዲናዋ ከግንቦት ወር ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር አይቻልም

ሚያዝያ 24/2015 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይቻል የከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው የሞተር ብስክሌት መንቀሳቀሻ ፈቃድን በዲጂታል መታወቂያ (Digital ID) መተግበሪያ ስራ ላይ ሊያውል በሂደት ላይ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል።

በዚህም በመዲናዋ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ብስክሌት ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች የመንቀሳቀሻ ፈቃዳቸውን ጂፒ ኤስ ባስገጠሙበት ተቋም የዲጂታል መታወቂያውን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ ኤጀንሲው ጠይቋል፡፡

ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሞተር ብስክሌቶች ላይ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ያለ ዲጂታል መታወቂያ በሚንቀሳቀሱት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡