FMC (Fana Media Corporation)
48.5K subscribers
44.6K photos
231 videos
20 files
16.9K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ይገምቱ ይሸለሙ!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ።

ሁለቱ ክለቦች ወደ ዋንጫ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ልዩነት ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ጨዋታ በማንችስተር ሲቲ ኢትሃድ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይደረጋል።

ማን ያሸንፋል?

የጨዋታውን ትክክለኛ ግምት ላስቀመጡ ሶስት ተከታዮቻችን የሞባይል ካርድ ሽልማት እናበረክታለን።
20ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው በመካከለኛ ዘመን (2016 - 2020) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የተወያየው በመካከለኛ ዘመን /2016-2020/ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ሲሆን ማዕቀፉ በዋናነት የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎችና ታሳቢዎች ጋር ተጣጥሞ የተዘጋጀ መሆኑን፣ የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየትና ለማመላከት የሚያገለግል የበጀት ዕቅድ መሳሪያ ሆኖ የ2016 የፌዴራል መንግስት ዝርዝር በጀት የሚዘጋጅበትን ጥቅል የገቢ ትንበያ፣ የወጪ ጣሪያ፣ የክልላዊ መንግስታት የበጀት ድጋፍ ጣሪያ እና የፊሲካል ጉድለት መጠንን የሚያመላክት ሆኖ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ አረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ማዕቀፉ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት የተጋረጠውን የፊሲካል ስጋት ለመቅረፍ እና የፊሲካል ጤናማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የፋይናንስ አጠቃቀም ስልት ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያስችል መሆኑን በማመን፣ የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲመጣጠን ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ግምት ውስጥ በማስገባት ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ ስረዓተ ቀብር ተፈፀመ

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) የአንጋፋው የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ አቀንቃኝ ዘሪሁን ወዳጆ የቀብር ሰነ-ስረዓት በመንበር ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ዘመድ ወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተፈፀሟል።

አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ በ1949 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን ለ48 ዓመታት በአፋን ኦሮሞ የተለያዩ ይዘት ያላቸው ሙዚቃዎች በማቀንቀን ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደረግ ቆይቷል።

አርቲስቱ ባጋጠመው ህመም ምክንያት በህንድ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ከቀናት በፊት ህይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በፌናን ንጉሴ
ፍርድ ቤቱ ህገ መግስቱን በኃይል ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው የተጠረጠሩት የነ ፕሮፌሰር ሲሳይ አጉቾን መዝገብ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ረ/ ፕሮፌሰር ሲሳይን ጨምሮ በአምስት ተጠርጣሪዎች ላይ የሰራውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ከነገ በስቲያ ለሚያዚያ 20 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተጠርጣሪ በሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቾው፣ ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያብን ፣ አማሃ ዳኘው፣ ሰለሞን ልመንህ እና ሄኖክ አዲስን በሚመለከት መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው የስምንት ቀን ውስጥ የሰራውን የምርመራ ስራ በዝርዝር ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አቅርቧል።

በዚህም ተጠርጣሪዎች ህገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ በማሰብ በአማራ ክልል ሁከትና ብጥብጥ አመፅ በማስነሳት በንብረትና በሰው ላይ በደረሰ ጉዳት ተሳትፎ እንዳላቸው የሚገልፁ በጥናት የተዘጋጀ የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘቱን አብራርቷል።

ለበጎ አድራጎት እርዳታ በሚል ሰበብ በግልፅ አባላት ተመልምሎ አጣዬ አካባቢ ስልጠና ሲሰጡ እንደነበር የተገኘው ማስረጃ በግልፅ ያሳያል በማለት ለችሎቱ አስረድቷል።

የተለያዩ የገንዘብ ዝውውሮችን ለማጣራት ለባንኮች ደብዳቤ መጠየቁን እና በተጠርጣሪዎች እጅ የተገኘ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን፣ የተያዙ ቦንቦችንና የጦር መሳሪያዎችን እንዲሁም ሰለሞን ልመንህ እጅ የተገኙ የበርካታ የወጣቶች መታወቂያዎችና ሰነዶችን ህጋዊነት የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

እንደ አጠቃላይ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር የሚገናኝ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችን መሰብሰቡን አስረድቷል።
ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በኡጋንዳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ

ሚያዝያ 18/2015 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኡጋንዳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል።

በአራት የአፍሪካ አገራት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአራተኛ ሃገር ጉብኝታቸውን በኡጋንዳ ማድረግ ጀምረዋል።

ሚኒስትሩ ኡጋንዳ ሲደርሱ የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሄነሪ ኦኬሎ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኡጋንዳ ቆይታቸውም ከሃገሪቱ ኘሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም በኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሰራዊት ያበረከቱ ሃገራት ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዋልታ ምሽት ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ሚያዝያ 18/2015
https://fb.watch/k91hKfHzW9/
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ እና ሀገሪቱን ለማገዝ መወሰኑን ኢትዮጵያ በበጎ እደምታየው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሚያዚያ 18/2015 (ዋልታ) የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ኢትዮጵያ በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትልቅ እምርታ ማስመዝገቧን እ.ኤ.አ ሚያዚያ 24 ቀን 2023 መግለጫ ማውጣቱን ጠቅሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ ከህብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ብዙ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን እና ይህ የህብረቱ ውሳኔም ወደላቀ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው ሚኒስቴሩ ጠቅሷል፡፡

ህብረቱ መደበኛውን የባለብዙ- አመላካች አመታዊ ፕሮግራምን እንደገና ለማንቀሳቀስ መወሰኑ፣ አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የማረጋጋት ጥረት እንዲደግፉ ማበረታታቱን እና አበዳሪ ተቋማትም የእዳ አከፋፈል ሽግሽግ እንዲያደርጉ ጥሪ ማድረጉን ኢትዮጵያ በበጎ እንደምትቀበለው አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላሟን በማጠናከር፣ በጦርነቱ የተጎዳውን የህብረተሰብ ክፍል መልሶ በተማቋቋም፣ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን እና የአየር ንብረት ለውጥን ሊቋቋም የሚችል እድገትን ለማሳካት ጥረት በምታደርግበት ወቅት ወዳጅ አገሮች ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ መሆናቸውንም መግለጫው ያመለክታል፡፡

የአውሮፓ ህብርት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ፣ በቀይ ባህር እና አካባቢው ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አጋር መሆኗን እና አገሪቱ ወደ ዘላቂ ሰላም የምታደርገውን ጉዞ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከ #ዋልታ_ቴቪ ሚያዝያ 19/2015https://fb.watch/k9OoqarDdu/
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራው የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን ወደ መቀሌ ተጓዘ
ሚያዚያ 19/2015 (ዋልታ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ሌሎች ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን ወደ መቀሌ ተጓዘ።
በቡድኑ ውስጥ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የአፋር ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሶማሌ ክልል፣ የሲዳማ ክልል ይገኙበታል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀርና ሚኒስትሮች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አብረው መጓዛቸውን የዘገባው ኢ.ፕ.ድ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለሰሜኑ ጦርነት የሠላም ስምምነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና መርሀ-ግብር ሲከናወን የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ወደመቀሌ በማቅናት መቀራረቡን እንዲያጠናክሩ ተናግረው እንደነበር የሚታወስ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ልዑክ ወደ መቀሌ ገቡ
ሚያዚያ 19/2015 (ዋልታ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ልዑክ ወደ መቀሌ ገብተዋል።
የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮቹ እና የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በመቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመቀሌ ከተማ ነዎሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የርዕሳነ መስተዳደሮቹ የመቀሌ ጉዞ ለትግራይ ክልል አጋርነታቸውን ለማሳየት እና በመልሶ ግንባታ ሂደት የድርሻውን ለማበርከት ዓላማ ያደረገ ነው።
የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባዎች ወደ መቀሌ ሲያቀኑ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።
ከሰሞኑ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው ‘ጦርነት ይብቃ፤ ሰላምን እናፅና’ በሚል መሪ ቃል በተካሄደ መርሐ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በመቀሌ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መናገራቸው ይታወሳል።
አርጀንቲና ከቻይና ለምታስገባቸው ምርቶች በዶላር ሳይሆን በዩዋን ልትከፍል ነው
ሚያዚያ 19/2015 (ዋልታ) አርጀንቲና ከቻይና ለምታስገባቸው ምርቶች በዶላር ሳይሆን በቻይና መገባበያ በዩዋን ልትከፍል መሆኑን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሰርጂዮ ማሳ ገለጹ፡፡
ውሳኔውም እየቀነሰ የመጣውን የአርጀንቲናን የዶላር ክምችት ለማቃለል ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡
አርጀንቲና በሚያዝያ ወር ብቻ ወደ 1 ቢሊየን ዶላር ግምት ያላቸው የቻይና ምርቶችን በዩዋን ለመክፈል ያቀደች ሲሆን በቀጣይ በየወሩ ወደ 790 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ግምት ያላቸው ምርቶችን በዩዋን እንደምትከፍልም ተጠቁሟል፡፡
ቻይና ከዶላር ውጭ የንግድ ልውውጥ ሥምምነት ከሩሲያ፣ ፓኪስታን፣ ብራዚል እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ጋር ማድረጓ ይታወቃል፡፡
የቀን 6፡00 ዜና ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ሚያዝያ 19/2015https://fb.watch/k9YTnuvATd/