FMC (Fana Media Corporation)
48.4K subscribers
44.6K photos
231 videos
20 files
16.9K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለስራ ጉብኝት ጣሊያን ሮም ገቡ

ጥር 29/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሥራ ጉብኝት ጣሊያን ሮም ገብተዋል፡፡

ኢትዮጵያና ጣሊያን ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ የሁለትዮሽ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው፡፡

(ምንጭ ፡ኢቢሲ)
የኢትዮጵያን እና የጣልያንን ወዳጅነት አጠናክረን እንቀጥላለን- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ጥር 29/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እና የጣልያን ግንኙነት ለብዙ ዘመናት የቆየ እና ፍሬያማ የሆነ አጋርነት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጣልያን ሮም መግባታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ "ዛሬ ጠዋት በፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ለተደረገልን አቀባበል ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን እና የጣልያንን ግንኙነትም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሚኒስትሮች ልዑክ ቡድን በሮም ጣሊያን የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት÷ በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል ስላለው ግንኙነት መክረዋል፡፡

በተጨማሪም በሌሎች ወቅታዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮቴል ኢኖቬሽን የተሰኘ ፕሮግራም አስጀመረ

ጥር 29/2015 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮቴል ኢኖቬሽን የተሰኘ ፕሮግራም ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡

መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን ጀማሪ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ቢዝነሶችና ባለሙያዎች የሚበረታቱበት ነው ተብሏል።

ፕሮግራሙ ጀማሪ የስራ እድል ፈጠራ ላይ የሚሰማሩ ተቋማትን የሚያበረታታና የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታ ከመሆኑ ባሻገር ለማህበረሰቡ መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሂወት ታምሩ ገልፀዋል።

ኢትዮቴል የተሰኘው ፕሮግራም ለ250 ኩባንያዎች የስራ እድል የሚፈጥር ነውም ተብሏል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ ለ100 ኩባንያዎች የስራ እድል የሚፈጥር እንደሆነም ነው የተገለፀው።

ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ለ150 ኩባንያዎች የስራ እድል የሚፈጥር እንደሆነም ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።

ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ የቢዝነስ ሀሳቦች የሚጎለብቱበትና ስራ ላይ እንዲውሉ በጥናትና ምርምር ደረጃ በማሳደግ የሚተገበር ነው ተብሏል።

የቴሌኮም ዘርፉ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን የገለፁት ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ኢትዮቴል ኢኖቬሽን ፕሮግራም የተቋማትን ትብብርን የሚያበረታታ መርሐ ግብር መሆኑን ነው ገልጸዋል፡፡

መርሐ ግብሩ እንዲጀመር የቴሌኮም መሰረተ ልማት የሟሟላት አስቻይ ሁኔታ መፈጠሩንም ስራ አስፈፃሚዋ ጠቁመዋል።

ክህሎት ያላቸውን ወጣቶችን የሚያበረታታ እና የስራ እድል የሚፈጥረው ይህ መርሐ ግብር አገር በቀል እውቀቶችንና የምርምር ስራ የሚያከናውን እንደሆነ ነው የተገለፀው።

በሱራፌል መንግስቴ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያዩ

ጥር 29/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት ትብብር እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የ180 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የያዘውን የ2023-2025 የኢትዮጵያ እና የጣልያን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የፋይናንስ ስምምነቱ በኢኮኖሚ ልማት በተለይ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች እና በጤና እና በትምህርት መሠረታዊ አገልግሎት አቅርቦት፣ ቁልፍ በሆኑ ተግባራት ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የአሥር ዓመት የልማት ዕቅዳችንን ለማስቀጠል የሚደግፍ መሆኑም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ጠቁሟል፡፡

ሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነትን መግለጻቸውም ተመላክቷል፡፡
ዋልታ ምሽት ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ጥር 29/2015
https://fb.watch/iwTy0KFOKr/
ከ3ሺ 771 የምርጫ ጣቢያዎች ከአንድ ምርጫ ጣቢያ በስተቀር ምርጫው ተካሂዷል

ጥር 29/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን አስታውቋል።

የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በምርጫ አሰጣጥ ሂደት ያጋጠሙ የአሰራር ግድፈቶች እና የቁሳቀስ ጉድለቶች እንደነበሩ የጠቀሱ ሲሆን ቦርዱ በሰጠው ፈጣን ምላሽ የምርጫ ሂደቱ እንዳይስተጓጎል ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ምርጫው በ3ሺ 771 ምርጫ ጣቢያዎች በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን የገለፁት ዋና የቦርድ ሰብሳቢዋ በቡርጂ ማእከል ዳሊኦ ቀበሌ ዳሌኦ ምርጫ ጣቢያ ላይ የድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይ ከምርጫ ጣቢያው ሰራተኞች ውጪ የተሳተፈ መራጭ የለም ይህም ህብረተሰቡ ከቀበሌው አስተዳደር ጋር ባለ ያልተፈታ ቅሬታ መሆኑን ምርጫ ቦርዱ መረጃ ደርሶታል ብለዋል።

በአራት ምርጫ ጣቢያዎች 18 ዓመት ያልሞላቸው ዜጎች በመራጭነት ተመዝግበው መገኘት፣በሶስት ምርጫ ጣቢያዎች የመንግስት አስተዳደር አካላት ተፅዕኖ ለማድረግ መሞከር ያሉ የአሰራር ግድፈቶች እንዳጋጠሙ ለማስተካከል ጥረት መቻሉን ተናግረዋል።

የማህተም መርገጫ፣ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች እጥረት ያሉ የቁሳቁስ ጉድለቶች የገጠሙ ሲሆን ይህንን በፍትነት ማስተካከል ተችሏል ነው ያሉት።

በአጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን እና ካለፉት ምርጫ የተሻለ ለቀጣይ ምርጫዎችም ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይ በ11ዱም መዋቅሮች የምርጫ ውጤት የሚገለፅ ሲሆን ይህ ሂደት ሲጠናቀቅ የመጨረሻው የተረጋገጠ ውጤት በምርጫ ቦርድ እንደሚገለፅም በመግለጫው ተጠቅሷል።

ትዕግስት ዘላለም
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በቱርክዬ እና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

ጥር 30/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክዬ እና ሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባወጡት መግለጫ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልጸው በአደጋ ለተጎዱትም ብርታትን ተመኝተዋል።

በደቡባዊ ቱርክዬ እና በሰሜን ሶሪያ 7.8 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተከሰተ ሲሆን ከ4 ሺሕ 300 ሰው በላይ ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ከ #ዋልታ_ቴቪ ጥር 30/2015

https://fb.watch/ixEHo1SirR/
የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ ተደረገ

ጥር 30/2015 (ዋልታ) በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ውሳኔ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና አስተባባሪ መቅደስ መኮንን ለኢዜአ እንዳሉት የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቋል።

ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺሕ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ለህዝብ ይፋ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ህዝብ ውሳኔ በክልሉ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች ትናንት መካሄዱን አስታውሰዋል።

በየደረጃው የተሰማሩ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ታዛቢዎችና የጸጥታ አካላት የምርጫውን ሥነ ሥርዓት ለማስፈጸም በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀሳቸውንም ገልጸዋል።
በጋምቤላ ክልል ከነገ ጀምሮ የስራ ሰዓት ለውጥ እንደሚደረግ ተገለጸ

ጥር 30/2015 (ዋልታ) በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ከነገ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፒተር ሆው እንዳሉት በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለስራ ምቹ ባለመሆኑ ከነገ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል።

በለውጡ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የስራ ሰዓት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ተኩል እንደሚሆን አስታውቀዋል።

ከሰዓት በኋላ ደግሞ ከ9 እስከ 11 ተኩል የነበረው ከ10 እስከ 12 ሰዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን አመልክተዋል።

የስራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሽና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር አስረድተዋል።

በለውጡ መሰረትም የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች በተጠቀሰው የስራ ስዓት መስሪያ ቤታቸው በመገኘት የተለመደ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ማሳሰባቸውን ከጋምቤላ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
የቀን 6፡00 ዜና ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ጥር 30/2015

https://fb.watch/ixP9zqeSJi/