ከውጭ ይገቡ የነበሩ ሴራሚክ፣ ግራናይት፣ ብረት እና እምነበረድ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን ሚኒስቴሩ አስታወቀ
ጥር 4/2015 (ዋልታ) ባለፉት 6 ወራት ከውጭ ይገቡ የነበሩት ሴራሚክ፣ ግራናይት፣ ብረት እና እምነበረድ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት መቻሉን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው የግማሽ አመት አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
በመግለጫው ሴራሚክ፣ብረት፣ግራናይት፣እምነበረድ እና ሲሚንቶ በሀገር ውስጥ በማምረት በዚህኛው 6 ወር ከውጭ አለማስገባቱን ገልጿል።
በተለይም ብረትን ከውጭ ለማስገባት በአመት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይወጣ እንደነበር የገለጸው ሚኒስቴሩ በ6 ወሩ ምንም ብረት ከውጭ አለመግባቱን አስታውቋል።
በቃልኪዳን ሀሰን

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት 6 ወራት ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
ጥር 4/2015 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 70 ሚሊዮን ደንበኞችን በማፍራት በአጠቃይ ከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ለባለድርሻ አካላትና ለሚዲያ ባለሙያዎች እያቀረበ ይገኛል።
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 70 ሚሊዮን ደንበኞችን በማፍራት 33 ነጥብ 8 ቢሊየን አጠቃላይ ገቢ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 8 ነጥብ 18 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን ተቋሙ አስታውቋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተቋማችን የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና ደንበኞች በአገልግሎት አሰጣጥ እንዲረኩ ለማድረግ ሰርተናል፤ ውጤታማም ሆነናል ብለዋል።
ተቋሙ ከመደበኛ አገልግሎት አሰጣጥ ባሻገር የተጀመረው የቴሌ ብር አገልግሎት፤ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት በተጨማሪም የፋይናንስ አካታችነት ለማረጋገጥና ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልፀዋል፡፡
ከቴሌ ብር 27 ነጥብ 2 ሚሊዮን ደንበኞች ማፍራት መቻሉንና 166 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የግብይት መጠን በማንቀሳቀስ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ማስገኘት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪ 18 ባንኮችን ጨምሮ በርካታ የግልና የመንግስት ተቋማት ከቴሌ ብር ጋር በጋራ መስራት ላይ መሆናቸውንም አንስተዋል።
በተለይም ወጪን በአግባብ በመጠቀም ረገድ ትልቅ ስራ መሰራቱን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ከዚህም 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ ቅነሳ መደረጉን ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም መሪ የተሰኘ የሶስት አመት የእድገት ስትራቴጂ ቀርፆ ወደ ስራ የገባ መሆኑን ሀምሌ 1 ቀን 2014 ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
በሳራ ስዩም

አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩዋትን ሀገር አስከብረን ለትውልድ እናስተላልፋለን - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
ጥር 4/2015 (ዋልታ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕርዳር የሚገኘውን የሰሜን ምዕራብ እዝ ደረጃ ሦስት ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።
እንዲሁም የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊውጂን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር ጄኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሀገርን ለማጽናት የተዋደቁ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ሕዝባችንን ይዘን የማንፈፅመው ተልዕኮና የማንወጣው ግዳጅ የለም፣ የተሰዋነው እና የቆሰልነው ለሕባችን ደኅንነት ነው፣ ለሕዝብ አንድነትና ክብር ነው ብለዋል።
አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩዋትን ሀገር አስከብረን ለትውልድ እናስተላልፋለን ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

አገልግሎቱ ለ28 ሆስፒታሎች በቅደመ ክፍያ ውል መድሃኒቶችን ሊያቀርብ ነው
ጥር 4/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለ28 ሆስፒታሎች በቅደመ ክፍያ ውል መድሃኒቶችን ሊያቀርብ መሆኑን አስታውቋል።
አገልግሎቱ ውል የተገባለት የመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓት ትግበራ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ከ28 ሆስፒታሎች ጋር አካሂዷል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አብዱልቃድር ገልገሎ (ዶ/ር) ፤ የተጀመረው የአሰራር ስርዓት በኢትዮጵያ የሚታየውን የመድኃኒት አቅርቦት ችግር 80 በመቶ የሚፈታ መሆኑን ገልጸዋል።
አገልግሎቱ በተለይ 150 የህይወት አድንና ሌሎች መድሃኒቶችን ለ28 ሆስፒታሎች በቅደመ ክፍያ ውል ለማቅረብ ከስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
በዚህም አሰራር 95 በመቶ የአቅርቦት ፍላጎትን ተደራሽ ለማድረግ ግብ እንደተቀመጠ አስታውቀዋል።
በተጨመሪ በሙከራ ደረጃ ሲሰራበት የቆየው የፈጣን ለውጥ አምጪ እቅድ ስርዓትን በሆስፒታሎች የሚጀመር መሆኑ ገልጸዋል።
በጤና ፕሮግራም የሚሰጡ የቲቪ፣ የኤች አይ ቪ፣ ማላሪያ እና የክትባት መድሃኒቶች በመሠረታዊ መድሃኒት የአሰራር ስርዓቱ ላይ እንዲዘረጉ ይደረጋል ብለዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፈረንሳይና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
ጥር 4/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እና ከጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ጥልቅ እና ፍሬያማ ውይይታችን ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላትን ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነትን የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት እያከናወነች ያለችውን ዘርፈ ብዙ ማሻሻያ፣ ቁልፍ ውጤቶችንና ተያያዥ ችግሮችን ለሚኒስትሮቹ አካፍለዋል።
ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላት ግንኙነት ለበርካታ አሥርት ዓመታት ቆይቷል።
ባለፉት አራት ዓመታት ከሁለቱም ሀገራት ለተደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍ እመስግነዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮችም ለውጡን ለማስቀጠል የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሰራር የሀገሪቱን ዕዳ ዝቅ ማድረግ እንደቻለ ተገለፀ
ጥር 4/2015 (ዋልታ) ነዳጅ ከጅምላ ድጎማ ወጥቶ የታለመለት ድጎማን ተግባራዊ በማድረጉ በወር 15 ቢሊዮን ብር የነበረውን ዕዳ ወደ 3 ቢሊዮን ብር ዝቅ ማድረግ መቻሉን የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ገለጸ፡፡
ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶችን በከፍተኛ ዋጋ አስገብታ በዝቅተኛ ዋጋ ለገበያ በማቅረቧ ለ187 ቢሊዮን ብር ዕዳ ዳርጓታል፡፡
በነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ስታንዳርድ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ለሜሳ ቱሉ ለዋልታ እንደገለጹት ከዚህ ችግር ለመውጣትና መንግስት የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት ከጅምላ ድጎማ በመውጣት አነስተኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ የታለመለት የነዳጅ ድጎማን አሰራር ተግባራዊ አድርጓል፡፡
የታለመለት የነዳጅ ድጎማ መንግስት ባለፈው ዓመት ከመወሰኑ በፊት ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ 70 ቢሊዮን ብር የነበር ሲሆን ዓለማቀፉ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት በወር 15 ቢሊዮን ብር ዕዳ ደርሶም እንደነበር ተገልጿል፡፡
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ በመደረጉ ከሰኔ 2014 ጀምሮ የእዳው መጠን ከ15 ቢሊዮን ብር ወደ 3 ቢሊዮን ብር ዝቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ለ5 ዓመት የሚቆይ ሲሆን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ከተስተካከለ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ከአቅም በላይ ሆኖ ማስፈጸም ካልተቻለ እንዲሁም መንግስት በቢሊዮን የሚቆጠር ወጪ እያወጣ ህብረተሰቡ ግን በአግባቡ ካልተገለገለ በጥናት ላይ ተመስርቶ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡
በተስፋዬ አባተ

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
ጥር 4/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባኤርቦክ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪ ኮሎናን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
በዚህም የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጋር በነበራቸው ውይይት የሀገራቱን ረጅም ዘመን የዘለቀ ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በመንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሚደረገው መልሶ ግንባታ ተግባራት ሁለቱ ሀገራት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሚኒስትሮቹ አረጋግጠዋል፡፡
የመልሶ ማቋቋምና የመደገፍ ስራዎች ሴቶችን ታሳቢ በማድረግ ላይ ያተኮሩ መሆን እንዳለባቸውም በውይይታቸው ተነስቷል።

ሀገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኤግዚቢሽንና ባዛር በሐዋሳ ዛሬ ይከፈታል
ጥር 4/2015 (ዋልታ) በሀገሬ ምርት እኮራለሁ ውስጥ አምራቾች እገዛለሁ በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ 6 ቀናት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኤግዚቢሽንና ባዛር በሐዋሳ ዛሬ ይከፈታል::
በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 224 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እና 22 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉ ታዉቋል።
በተጨማሪም የተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጨምሮ የተለያዩ የህብረት ሥራ ማህበራትና የአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም ከአንድ ማዕከላት የተውጣጡ 28 ተቋማት በኤግዚቢሽንና ባዛሩ እንደሚሳተፉ ታውቋል ።
በኢንተርፕርይዞች እና በሸማቾች መካከል ዘላቂ የገበያ ትስስር መፍጠርን ዓላማው ባደረገው በዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር ስድስት ሚሊዮን ብር የገበያ ትስስር ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከኤግዚቢሽንና ባዛሩ ጎን ለጎን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢ-ኮሜርስ ልምድ ያላቸው የግል ዘርፍ ተዋናዮች እንዲሁም ከንግድና ዘርፍ ማህበራት የተወጣጡ ተሳታፊዎች በተገኙበት በዘመናዊ የኢንተርፕራይዞች የግብይት ሥርዓት እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።
ኤግዚቢሽንና ባዛሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ፣ ክህሎት እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

አርቲስት ማሪቱ ለገሰ የክብር ዶክተሬት ድግሪዋን ተረከበች
ጥር 4/2015 (ዋልታ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ ከሰባት ዓመታት በፊት ሰጥቷት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪዋን በዛሬው ዕለት አስረክቧል።
ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ማሪቱ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ላበረከተችው አስተዋጽኦ በ2008 ዓ.ም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷት እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለትም አርቲስቷ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዋ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተረከበች መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሥነ ሥርዓቱም ላይ የተለያዩ የዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎችና የአርቲስቷ አድናቂዎችና ወዳጆች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
አርቲስት ማሪቱ ለገሰ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተሻገረው የሙዚቃ ህይወቷ አራቱን የሙዚቃ ቅኝቶች በመጫወት ትታወቃለች፡፡
በተለይም የአምባሠል ቅኝት አጨዋወቷ የመጠሪያዋ ቅጽል ስም እስከመሆን አድርሷታል ።
በተጨማሪም አርቲስቷ ዓመቱን ሙሉ የባህል አልባሳት በመልበስ በባህል አምባሳደርነትም ትታወቃለች።

በሐሰተኛ መታወቂያ የመንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በሚሉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው
ጥር 4/2015 (ዋልታ) ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በማለት ኅብረተሰቡን እያጭበረበሩ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለዋልታ በላከው መረጃ እንዳመለከተው ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የደኅንነትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን የሚሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በተለያዩ መንገዶች ክትትል ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በዚህ የማጭበርበሪያ ስልት የሚጠቀሙ አካላት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል፡፡
ሰሞኑን በተደረጉ ጥብቅ ክትትሎችም ፈለቀ ዴብሳ ደማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ አስፋው አዳማ ሙታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፣ ሳምሶን ገነነ መንገሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ ተስፋ ሀተው ገምቴሳ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ሰበታ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ዮሰን በቀለ ትክሳ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክፍለ ከተማ ሐሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን መታወቂያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማትንም ሐሰተኛ መታወቂያ በመጠቀም ለሕገወጥ ድርጊት የሚያውሉ ግለሰቦች በጸጥታ አካላት የተቀናጀ ሥምሪት ተይዘዋል፡፡