ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለአረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ጎዳና ተዳዳሪዎች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ
ታኅሣሥ 29/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአረጋዊያን፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለጎዳና ተዳዳሪዎች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ማጋራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የክርስቶስን ልደት ስናከብር ይቅር ባይነት፣ እርቅ እና ሰላምን ይዘን መሆን አለበት - ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ
ታኅሣሥ 29/2015 (ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓልን ስናከብር የይቅር ባይነት፣ ሰላም እና እርቅ ስሜት በውስጣችን ሊኖር እንደሚገባ የደቡብ ኦሞ ዞን ሀገረ ስብከት እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ አሳሰቡ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም በስጋ ሲመጣ ክፉን ድርጊት ሁሉ ለማስቀረት፣ ሰላምን በምድር ላይ ለማስፈን፣ ፍቅር ለማሳየት እና አንድነትን ለመስበክ ነው ብለዋል።
በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ነፃነታችንን፣ ሰላማችንን እና አንድነታችንን እያከበርን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባዋል ብለዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም ለሰላማችን እና ለአንድነታችን ሁሉም ኃላፊነቱንና ድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓልን ለማክበር በላሊበላ ከተማ የተገኙት ብፁዕነታቸው በበዓሉ ላይ ለታደሙ የውጭ ጎብኝዎችና ዲፕሎማቶች ባስተላለፉት መልዕክት ኢየሱስ ክርስቶስ በግርግም ውስጥ መወለድ የሰው ልጅን ከወደቀበት እንዲነሳና እና ዘላለማዊ ሕይወትን እንዲያገኝ በማሰብ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ካለን ማካፈል ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር የሚለውን ወርቃማ እሴታችን የምናሳይበት መሆኑን ገለጹ
ታኅሣሥ 29/2015 (ዋልታ) ካለን ማካፈል ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር የሚለውን ወርቃማ እሴታችን የምናሳይበት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብራሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡
የገናን በዓል በማስመልከት በብላቴ ኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አካባቢ ላሉ 120 አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ወቅት ያለንን ማካፈል የኖርንበት የኢትዮጵያዊነት ባህላችንና እንደ ተቋም ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር የሚለውን ወርቃማ እሴታችን የምናሳይበት ነው ብለዋል።
ሠራዊቱ ለሀገር ሰላም ሲል ውድ ህይወቱን የሚገብር፤ ህዝቦቿ ሲቸግሩ ካለው የሚያካፍል የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ ነው ሲሉም አክለዋል።
ሠራዊታችን የሰላማችን ዘብ የቸገረን ጊዜ ረዳታችን ነው ፤ የገናን በዓል በማስመልከት ለተደረገልን ድጋፍ እናመሰግናለን ሲሉ ድጋፍ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ድጋፉን የ40ኛ ዙር 1ኛ ብርጌድ ተመራቂ የኮማንዶ አባላት ያሰባሰቡ ሲሆን ከወላይታ ዞን እና ሲዳማ ክልል ውስጥ ካሉ 5 ቀበሌዎች ለተውጣጡ ነዋሪዎች መበርከቱን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ከንቲባዋ በዓሉን በአሙዲ የምገባ ማዕከል የከረዮ የጌጃ ሰፈር ወገኖች ጋር አሳለፉ
ታኅሣሥ 29/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን በአሙዲ የምገባ ማዕከል የከረዮ የጌጃ ሰፈር ወገኖች ጋር ማሳለፋቸውን ገለጹ።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው "ከምገባ ማዕከሎቻችን አንዱ በሆነው አሙዲ የምገባ ማዕከል በዓሉን ከምንወዳቸውና ከምናከብራቸው የከረዮ_ የጌጃ ሰፈር ወገኖቻችን ጋር በአብሮነት በደስታ አሳልፈናል" ብለዋል፡፡
ወገኖቻችንን በመመገብ እየተጋችሁ ያላችሁ በጎ አድራጊዎች፣ አመራሮችና እናቶች ከልባችን እናመሰግናለን፤ በዓሉ የይቅርታ፣ የአብሮነት፣ የደስታ፣ ያማረና የሰላም ይሁንልን ሲሉም አክለዋል።

ደሃና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የመደጋገፍ ተግባር መጠናከር እንዳለበት ተገለጸ
ታኅሣሥ 29/2015 (ዋልታ) መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ደሃና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የመደጋገፍ ተግባር መጠናከር እንዳለበት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ለዚህም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ግብረሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ሚኒስትሯ ኢርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ ከኢቢ አካዳሚ ጋር በመቀናጀት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራትና የድጋፍ መርኃግብር አካሂዷል።
በዚህም ከ400 በላይ ለሚሆኑ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ማዓድ የተጋራ ሲሆን ሚኒስትሯ ኢቢ አካዳሚ ያደረገውን በጎ ድጋፍ አመስግነው በቀጣይ ይህንኑ ልምድ ለሌሎች በማጋራት በጎ ድጋፍ የሚያደርጉ አካለትን በማብዛት ችግሮቻችንን በጋራ መቅረፍ እንችላለን ብለዋል፡፡
ኢቢ አካዳሚ ትምህርት ቤት አመራሮች ይህን ዝግጅት ላለፉት 13 ዓመታት ከትምህርት ቤቱ ክበባት፣ መምህራንና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በማሰባሰብ የሚያዘጋጁ መሆኑን ገልጸው የዘንድሮውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር መርኃግብሩ እንደተዘጋጀ መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በላሊበላ የተከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ
ታኅሣሥ 29/2015 (ዋልታ) በላሊበላ በድምቀት የተከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አስታውቋል።
ዓለም አቀፍ ቅርስ በሆነው ላሊበላ በድምቀት የተከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ያለምንም ፀጥታ ችግር መጠናቀቁን ነው የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የገለጸው።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር እንግዳው ሆዴነው በየዓመቱ የሚከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በላሊበላ ከተማ በደመቀ መልኩ ተከብሮ መዋሉን ተናግረዋል።
በበዓሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የእምነት አባቶች፣ በሀገሪቱ ከአራቱም አቅጣጫዎች የመጡ እንግዶችን ጨምሮ የውጭ አገር ዜጎችና አምባሳደሮች በድምቀት አክብረውት መዋላቸውን ገልጸዋል።
በዓሉ በሰላም ለማክበር አስቀድሞ በተካሄደ የተቀናጀ የቅድመ ዝግጅት ስራ በዓሉን በሰላማዊ መንገድ ማክበር መቻሉን መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።

የገናን በዓል በላሊበላ ያከበሩ አንባሳደሮች በቆይታ መደሰታቸውን ገለጹ
ታኅሣሥ 29/2015 (ዋልታ) የገና በዓልን በላሊበላ ተገኝተው ያከበሩት የቻይና እና የአሜሪካ አምባሳደሮች በበዓሉ አከባበርና በአብያተ ክርስቲያናቱ መደናቃቸውን ገለጹ።
በኢትዮጵያ የቻይና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዣዎ ዢዩዋን "ለሁለት ቀናት የዩኔስኮ ቅርስ የሆነውን ላሊበላን ስጎበኝ ወዳጅ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረገልኝ እንክብካቤና እና መስተንግዶ ተደምሚያለሁ" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ በዓሉ ላይ የታደሙት ፊዮና ኤቫንስ በበኩላቸው በኢትዮጵያ መንግስት ግብዣ የላሊበላ አቢያተ ክርስቲያት መጎብኘታቸውን ገልጸው ለሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጥገና ድጋፍ በማድረጋችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።