FMC (Fana Media Corporation)
48.5K subscribers
44.6K photos
231 videos
20 files
16.9K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Download Telegram
ኮሚሽኑ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ለሚገኙ ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከጥቅምት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል አካባቢዎች ለሚገኙ 1 ሚሊየን 84 ሺሕ 486 ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ አስተባባሪ ሳሙኤል አበበ እንደገለጹት ባለፉት 2 ወራት በ210 ተሽከርካሪዎች የተጓጓዘ የስንዴ እንዲሁም የተለያዩ አልሚ ምግቦችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙ ዜጎች ካሉበት ችግር በመውጣት ወደ ቀደመ ኑሯቸው እንዲመለሱና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ቀጣይ ስራዎችን እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

በሳሙኤል ሃጎስ
የኤምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ለትራፊክ ክፍት ሆነ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ዛሬ ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍል እና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል።

ውስጠኛው የቀለበት መንገድ ክፍል ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ለመፍታት ተግባራዊ እየተደረጉ ከሚገኙ የመፍትሔ እርምጃዎች አንዱ በዋና ዋና የመስቀለኛ መንገድ መጋጠሚያዎች ላይ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ የመገንባት ሥራ ነው።

በዚሁ መሠረት በቦሌ ሚካኤል፣ በኢምፔሪያል እና በለቡ መጋጠሚያ መንገዶች ላይ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ ግንባታዎቹን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የኮከስ አባላት በክልሉ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ የተከናወኑ ተግባራት ምልከታ አደረገ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሴት ተመራጭ ኮከስ አባላት የኦሮሚያ ክልል የሴቶች እና ህጻናት ቢሮ በሴቶች ተጠቃሚነት ላይ የተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ምልከታ አደረገ፡፡

የክልሉ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ጀሚላ ሲንቢሩ በግማሽ የበጀት ዓመቱ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸዉን ለቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል፡፡

ከተግባራት ውስጥም ለችግረኛ ሴቶች 23 ሺሕ ቤቶች መሰራታቸውን ከ238 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የጤና መድህን ኢንሹራንስ መገዛቱንና ከ5ዐዐ በላይ ሴቶች መንጃ ፈቃድ እንዲያገኙ መደረጉን የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ኢኮኖሚያቻውን እንዲያሳድጉ እየተሰራ መሆኑንና ከ4 ቢሊዮን በላይ የመንግስት ወጪ መቀነስ መቻሉን የጠቀሱት ሃላፊዉ በቀጣይም ሰፋፊ ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ ኪሚያ ጁንዲ በማህበራዊ ትስስር የዜግነት አገልግሎት የጤና መድህን ተጠቃሚነት ላይ የተከናወኑ ተግባራትን በጥንካሬ አንስተው ተተኪ ሴት አመራሮችን በማፍራትና በፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ማድረግ ረገድ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0pu47QK4rPMigRmwTQqFqjZfZFUQeSB3aey7jUmu5ssGYwrtSGnV4XCyT5aduk6dHl&id=100064690148931&mibextid=Nif5oz
ከገጠመው የኩላሊት ህመም ጋር እየታገለ ለ5 ዓመታት ቆሞ በመማር በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀው ወጣት

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) ለ5 ዓመታት በመማሪያ ክፍል ውስጥ ቆሞ ከመማር፤በቤተ መጻሕፍት ውስጥ ተንበርክኮ እስከማንበብ የደረሰ ለትምህርት የተከፈለ መሰዋትነት፡፡

በበርካታ ውጣ ውረድ እና በተስፋ አስቆራጭ አጋጣሚዎች የተሞላ የተማሪ ግርማ ታሪክ በእሳት እንደተፈተነ ወርቅ ፍፃሜው አምሮለት 37 ኤ ፕላስ ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ተሻላሚ በመሆን ተመርቋል፡፡

የማይታመን ነገር ግን የሆነ የትምሀርት ዋጋን ልክ ያሳየ ይህ የተማሪ ግርማ ዳባ ይህወት ነው፡፡ወጣቶች ምንም ያህል ፈተና ቢገጥማቸው ፈተናውን አሸንፈው ውጣውረዱን ተሸግረው ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ የወጣት ግርማ ታሪክ የውሃ ልክ ነው፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት

ከኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ሙሎ እስከ ወላይታ ሶዶ የዘለቀው የወጣቱ ህይወት በጋሬጣ የተሞላ ቢሆንም ተማሪው አንድም ቀን ተስፋ ቆርጦ አያውቅም፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ለመማር የቀን ሥራ ሰርቷል በጥበቃ ሥራላይም ተሰማርቷል ከዚህ ሁሉ ውጣውረድ በኃላ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን አልፎ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ገባ፡፡

በትምህረት ላይ የሚገጥመው ፈተና ግን በዩኒቨረስቲም ተከተለው፤በሁለተኛ ደረጃ ትምሀረት ቤት እያለ የገጠመው የኩላሊት ህመም በዩኒቨርስቲ ውስጥ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ሲሆን ግርማ ግን የጽናት ሰው ነውና ጥርሱን ነክሶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ፡፡

እየከፋ የመጣው የኩላሊት ህመሙ ግን በክፍል ውስጥ ቁጭ ብሎ ትምህርቱን ከመከታተል፤በቤተ መጻሕፍት ለማንበብ ከፍተኛ ጫና አሳደረበት፡፡

... ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://rb.gy/e5drsf
የሲሚንቶ ፉብሪካዎች ምርታቸውን በሚያሳድጉበትና በግብዓት አቅርቦት ዙርያ ምክክር ተደረገ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) የሲሚንቶ ፉብሪካዎች ምርታቸውን ማሳደግ በሚችሉበትና በሲሚንቶ ግብዓት አቅርቦት ዙርያ ምክክር መካሄዱን የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ገለጹ፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በስራ ላይ ያሉ የሲሚንቶ ፉብሪካዎች የሲሚንቶ ምርታቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉን ጉዳዮችና የግብአት አቅርቦት ዙሪያ ከሲሚንቶ ፋብሪካ ኃላፊዎች እና የክልል ማዕድን ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ በቅርቡ ስራ ለመጀመር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ያለው የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ መሳተፉን ጠቅሰዉ ስራውን ለመጀመር የሚያስችሉ የግብአት አቅርቦት እንዲያገኝ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ አዲስ ለሚገነቡ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መደረግ ስላለበት ድጋፍ መወያየታቸዉንና በተለይ ክልሎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የፀረ-ሙስና ኮሚቴን አቋቋሙ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚቴን አቋቋሟል::

በዚሁ መሠረት:-

1. ፋጡማ መሀመድ........ስብሳቢ

2. እብራሂም ሁመድ...........አባል

3. አብዱ ሳሊህ..................አባል

4. አሊ ሳድቅ....................አባል

5. አህመድ መሀመድ...........አባል በማድረግ አቋቋሟል::

ኮሚቴው የተጣለባቸው ኃላፊነት ተገንዝበው ግዴታቸውን እንዲወጡ አደራ ብሏል።
ሊጉ አክሊሉ ታደሰን የሊጉ ፕሬዝዳንት አድርጐ መረጠ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አክሊሉ ታደሰን የሊጉ ፕሬዝዳንት አድርጐ መረጠ፡፡

አክሊሉ ታደሰ ከዚህ ቀደም ሊጉን በምክትል ፕሬዝዳንትነት የመሩ ናቸው፡፡

1 ሺሕ 200 ድምፅ ሰጪዎች እና 200 ያለ ድምፅ የተሳተፉበት ምርጫ ነው የተካሄደው::

ፕሬዝዳንቱ ለሚቀጥለው ሁለት አመት ተኩል ነው ሊጉን የሚመሩት፡፡

ፈዲላ አባቢያ እና ኦባንግ ኩማዳን ሁለቱም ሴት ም/ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል::

በሜሮን መስፍን
በምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ የሚፈጸም ማዋከብ ሊቆም ይገባል - የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) መገናኛ ብዙሃን በሚያከናውኗቸው የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራዎች ላይ በማንኛውም አካል የሚፈጸም ማዋከብ ሊቆም እንደሚገባ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።

ባለስልጣኑ ለዋልታ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ አጋዥና ተዋናይ መሆን የሚጠበቅባቸው የህፍሕ አካላት ለዚህ ስራ ተባባሪ እንጂ እክል እንዳይሆኑም ጥሪውን አቅርቧል።

ባለስልጣኑ በላከው መግለጫ ለመገናኛ ብዙሃን ስራ አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር በህግ የተጣለበትን ሃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር የምርመራ ዘገባ በሚያከናውኑ ባለሙያዎችና ተቋማት ላይ የሚፈጸም ማዋከብ መቆም እንዳለበት አሳስቧል።

በህገ መንግስቱ አንቀጽ 29 እና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 48 መሰረት መገናኛ ብዙሃን የህዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት መብት እንዳላቸው ባለሥልጣኑ አመለክቷል፡፡

መግለጫው የምርመራ ጋዜጠኝነትን ከማበረታታ አንጻርም እንደ መንግስት አቅጣጫ ተይዞ እንዲሰራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ጠቅሷል።

በመርህ ደረጃ የዜጎች መብት የተረጋገጠበት የዴሞክራሲ ባህል የሚጎለብትበትና ተጠያቂነት የሚሰፍንበት ስርዓት ለመገንባት የፍትህ አካላት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር መስራታቸው ጠቃሚ መሆኑንም ጠቁሟል የባለሥልጣኑ መግለጫ።

ይህ ሊረጋገጥ የሚችለው መገናኛ ብዙሃን ያለምንም መታወክና እንቅፋት ብቁ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ እንዲሰሩ መረጃ የማግኘት የመሰብሰብና የማሰራጨት መብታቸው ከማንም በላይ በፍትሕ አካላት ሲረጋገጥና ጥበቃ ሲደረግለት እንደሆነም አስታውቋል።
መንግሥት ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው- የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ብሎም የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ ተናገሩ።

በኢትዮጵያ የሚነሱ ማናቸውም ጥያቄዎችና አለመግባባቶች በዴሞክራሲያዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት መንግሥት ጽኑ አቋም ያለው መሆኑንም አረጋግጠዋል።

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግሥት የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

መንግሥት ለሰላምና ዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀው በየትኛውም አጋጣሚ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ልዩነቶችን በውይይት መፍታት የመንግሥት የማይናወጥ አቋም ስለመሆኑ አረጋግጠዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ የነበረው ችግር የተፈታበት መንገድና ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት መንግሥት ያሳየዉ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሃሳብ ልዩነት መኖር የሚጠበቅና ያለ ቢሆንም የውይይት መድረክ በማመቻቸትና በመነጋገር ችግሮችን መፍታት መለመድ ያለበት የዴሞክራሲ ባህል መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ብልጽግናን እውን ለማድረግ ያለ ልዩነት በጋራ መሥራት እንደሚገባ ነዉ ሚኒስትሩ ያስገነዘቡት።
ዋልታ ምሽት ከ #ዋልታ_ቴቪ በቀጥታ ታኅሣሥ 24/2015
https://fb.watch/hOKGg_QBW4/
ቦርዱ በዎላይታ፣ በጎፋ እና ጋሞ ዞኖች በሚገኙ 24 ምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ምዝገባ እንዲካሔድ ውሳኔ አሳለፈ

ታኅሣሥ 24/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዎላይታ፣ በጎፋ እና ጋሞ ዞኖች በሚገኙ 24 ምርጫ ጣቢያዎች በድጋሚ ምዝገባ እንዲካሔድ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚሁ መሠረት በድጋሚ ምዝገባ የሚካሔድባቸው ጣቢያዎች፦

• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ዱቦ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ዱቦ
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ዶላ ምርጫ ጣቢያ ሦስት ንዑስ ጣቢያ
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ቤታሎ ለ
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ጫማ ሄምቤቾ ምርጫ ጣቢያ አምስት
• በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ወርሙማ ሀ
• በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ማንቴ ጌራራ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ጌራራ ሦስት
• በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ቶሜ ጌሬራ ምርጫ ጣቢያ ቶሜ ጌሬራ አራት
• በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ዋጭጋ ቡሻ ምርጫ ጣቢያ ዋጭጋ ቡሻ 02
• ጎፋ ዞን ሳውላ ማዕከል ጃዉላ ጎሬ አዳ ምርጫ ጣቢያ
• ጎፋ ዞን ሳውላ ጃዉላ ውጋ መሸተላ ምርጫ ጣቢያ ሀ
• ጎፋ ዞን ሳውላ ማዕከል፣ ቡልቂ ከተማ ምርጫ ጣቢያ ቡልቂ 01 ሀ
• ጎፋ ዞን በኡባ ደብረ-ፀሐይ ማዕከል ገልጣ ሜላንቴ ምርጫ ጣቢያ ገልጣ ሀ
• ጎፋ ዞን በኡባ ደብረ-ፀሐይ ማዕከል በቶ ታዉን ምርጫ ጣቢያ ሁለት
• ጋሞ ዞን ብርብር በፋርጎሳ ምርጫ ጣቢያ
• ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0EgVH5S2L47wT4LCLUwNjrTQqzZsDzD8rXtom6qSYYUh5dj5LQ6nwepd9m3jnCcWgl&id=100064690148931&mibextid=Nif5oz