በክልሉ በሁሉም ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በሲዳማ ክልል የሁለት ዓመት ጉዞ በሁሉም ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡ ተገልጿል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 2ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የፓናል ውይይት ላይ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙ ሲሆን ክልሉ በሁለት ዓመታት ውስጥ ያከናወናቸውን አስተዳደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የመሰረት ልማት ሥራዎች ለታዳሚው ቀርቧል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ባደረጉት ንግግር ልማታችንን ለማፋጠን ሕዝብን ያሳተፈ ሥራ መስራት ከፍተኛ ዋጋ እንዳለውና በዚህም ባለፈው ሁለት ዓመት ብዙ ውጤቶችን ያየንበት ነው ብለዋል።
በአገልግሎት ዘርፉ እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ደካማ አፈፃፀም መታየታቸውንም ገምግመናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ ሕዝቡ ችግርም መፍትሄም በእጃችን መሆኑን አውቆ በንቁ ተሳትፎ ከጎናችን መቆም አለበት ብለዋል።
የፓናል ውይይቱ ላይ የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት አራርሶ ገረመው (ፒኤችዲ) ውይይቶች በግልፅነት ላይ የተመሰረተ ሥራን ለማከናወን እና በሕዝብ እና በአስተዳደሩ መካከል ያለውን የጋራ መግባባት የሚያጠናክሩ ስለሆነ ፋይዳቸው የጎላ ነው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በመንግሥት የተሰሩትን የመሰረተ ልማት ሥራዎች ቦታው ድረስ በመሄድ መጎብኘታቸውን ጠቅሰው ከልማቱ ጎን ለጎን የፀጥታና ደኅንነት ሥራ እንዲጠናከርም ጠይቀዋል።
የክልሉ መንግሥት 2ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በነገው እለትም በተለያዩ ሁነቶች መከበር እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
አንተነህ ደጀኔ (ከሀዋሳ)

በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
"የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በመባል የሚታወቀው እና በተለያዩ ሀገራት የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በሀገራችን ተከስቶ ሁለት ሰዎች ተለይተዋል (ኳረንቲን ገብተዋል) የሚል መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቶ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ እንደሚገኝ የገለጸው ሚኒስቴሩ “በሽታው በሌሎች ሀገራት ቢከሰትም በሀገራችን እስከ አሁን በበሽታው የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን እናሳውቃለን” ብሏል።
ኃላፊነት የሚሰማቸው የሚዲያ ተቋማት ይህን መሰል ያልተረጋገጠ እና በሚመለከተው አካል ያልቀረበ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡም አሳስቧል።
ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እንዲሁም የማኅበረሰቡ የጤና ስጋት የሚሆኑ ወረርሽኞችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አስጀመሩ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ‘‘አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን አራተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በጋምቤላ ወረዳ ቀርሚ ቀበሌ አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመርኃ ግብሩ ላይ እንዳሉት በአራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።
ዕቅዱን እውን ለማድረግ አመራሩ መላውን የክልሉን ነዋሪ በማስተባበር ውጤታማ ሥራ ማከናወን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
ባለፉት ሦስት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሮች በተሰራው ሥራ በርካታ የተራቆቱ አካባቢዎችን በእጽዋት ማልበስ መቻሉን ገልጸዋል።
ዘንድሮም ካለፈው መልካም ተሞክሮ በመውሰድ እንደሚሰራ ጠቅሰው እስከ መስከረም አጋማሽ በሚዘልቀው የችግኝ ተከላ ሁሉም ሰው ቢያንስ 100 ችግኝ በመትከል ለዕቅዱ መሳካት የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አጃክ ኡቻላ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተራቁቶ የነበረ ከ15 ሺሕ ሄክታር መሬት በላይ ወደ ቀድሞ ይዘቱ መመለሱን ተናግረዋል።
በዘንድሮ መርኃ ግብር የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሴ ጋጂት በመርኃ ግብሩ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ተማሪዎች በስፋት እንደሚሳተፉ አመልክተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
የአኝዋሃ ዞን አስተዳዳሪ ኡቦንግ ኡጁሉ በበኩላቸው የሽብር ቡድኖችን እኩይ ሴራ በመመከት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስኬታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በክልሉ 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አስጀመሩ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የ4ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በኢሉ አባቦር ዞን ያዮ ጫካ ውስጥ አስጀምረዋል።
መርኃ ግብሩ "አሻራችን ለትውልዳችን ለትውልድ እንስራ ለኦሮሚያ እንትከል" በሚል መርህ ሃሳብ ነው የተካሄደው።
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በመርኃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ አንድ ሰው 300 ችግኝ መትከል እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ባለፉት 3 ዓመታት ከ9 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከሉን የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አበራ ወርቁ ተናግረዋል።
በክልሉ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በአንድ ቀን ከ4 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከል የታቀደ መሆኑም ተነግሯል።
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም በመርኃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።
ያዮ ጫካ በዩኔስኮ የተመዘገበ የተፈጥሮ ሀብት ሲሆን 167 ሺሕ 21 ሄክታር መሬትን ሸፍኗል።
አስቴር ጌታሁን (ከኢሉ አባቦር)

አፈ ጉባኤው መሻሻል የሚጠይቁ ጉዳዮች ውይይት እየተደረገባቸው ሲወጡ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ጠንካራ ምሰሶ ይሆናሉ አሉ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) ሕግ ሊወጣላቸውና መሻሻል የሚጠይቁ ጉዳዮች በጥናት እየተለዩ እና ጥልቅ ውይይት እየተደረገባቸው መውጣታቸው ለሀገረ መንግሥት ግንባታው ጠንካራ ምሰሶ እንደሚሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡
አፈ ጉባኤው ይህን ያሉት ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ጋር በበይነ መንግሥታት የፊስካል ግንኙነት ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረውን የምክክር መድረክ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
መድረኩ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የተጠናቀቀ ሲሆን የበይነ መንግሥታት የፊስካል ግንኙነት ጥናትና የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲሁም ውስን ዓላማ ያላቸው የድጎማ በጀት እና የፌዴራል መሠረተ ልማት ስርጭት ፍትሐዊነት የክትትል ሥርዓትን ለማስፈጸም ረቂቅ ደንብ ለውይይት ቀርበው ግብዓት መሰጠቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ሁለቱ ምክር ቤቶች በተሰጣቸው ሕገ መንግሥታዊ ስልጣንና ኃላፊነቶች መሠረት በጋራ መሥራታቸው የተጀመረውን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ለማጎልበትና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አንድነት ለማሳደግ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም አፈጉባኤው ገልጸዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ነገ ይጀመራል
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በነገው እለት በደብረብርሀን ከተማ ይጀመራል።
ስብሰባው ለ2 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዋናነት በሊጉ የተሰሩ ሥራዎችን በመገምገም ለቀጣይ ተግባራት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ተገልጿል።
በተለይም ምግቤን ከጓሮዬ በተሰኘው መሰል የወጣቶች ንቅናቄ የተሰሩ ሥራዎችን መስክ ድረስ ወርዶ በመጎብኘት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚደረግ ከሊጉ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህም ጎን ለጎን ከ6 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የ2014 የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ይካሄዳል ተብሏል።
በተጨማሪም የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ የወጣቶች ሊግ ጉባኤ የሚካሄድበት ቀን እና ቦታ በማእከላዊ ኮሚቴው ውይይት ተደርጎበት እንደሚወሰን የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዝዳንት እና የጽህፈት ቤት ኃላፊ አክሊሉ ታደሰ ገልፀዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ አህጉሪቷ በምግብ ራሷን እንድትችል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍ አሜሪካ ገለጸች
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ልማት ባንክ አፍሪካ በምግብ እራሷን እንድትችል የምግብ ምርቷን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍ አሜሪካ ገለጸች።
ባንኩ በአፍሪካ የሚገኙ ከ20 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ አነስተኛ ግብርና አምራቾች የአየር ንብረትን መቋቋም የሚችሉ ስንዴ፣በቆሎ፣አኩሪ አተር እና ሌሎች ዋና ዋና የሰብል ዘሮችን ማምረት እንዲችሉ እንዲሁም ለማዳበሪያና ለግብርና ሥራዎች አገልግሎት ይውል ዘንድ በግንቦት ወር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ማጽደቁ ይታወሳል፡፡
ይህም አፍሪካ ለቀጣዮቹ አራት የምርት ወቅቶች ወደ 12 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ 38 ሚሊየን ቶን የምግብ እህል ምርቶችን በፍጥነት እንድታመርት ያስችላታል ተብሏል፡፡
በተለይም በሩሲያ እና ዩክሬን ግጭት ምክንያት በአህጉሪቱ ላይ እያንዣበበ ያለውን የምግብ ቀውስ ለመከላከል ባንኩ የምግብ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳድግ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
በቡድን 7 አባል አገራት ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ባይደን https://www.facebook.com/489211707826282/posts/pfbid0QKef84N4rkmJRiMtQn9H2kn2k22JmKBCuqPFwMtMNFDP9DnRhKsFKcHWNa86Gigwl/

በኮትዲቯር አስተናጋጅነት የሚካሄደው አፍሪካ ዋንጫ የጊዜ ለውጥ መደረጉ ይፋ ሆነ
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኮትዲቯር አስተናጋጅነት የሚካሄደው ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ የጊዜ ለውጥ መደረጉ ይፋ ሆነ፡፡
በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ሊካሄድ አስቀድሞ መርኃ ግብር የተያዘለት ውድድሩ በኮትዲቯር ካለው ከባድ አየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የቀን ለውጥ መደረጉን ካፍ አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ እግር ካስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ደቡብ አፍሪካዊው ፓትሪስ ሞሴፔ ከአየር ሁኔታው ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ኃላፊነት አንወስድም ብለዋል፡፡
ይህን ተከትሎ የአፍሪካ ዋንጫ በፈረንጆቹ 2024 ጥር ወር ላይ ይከናወናል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያም በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ብርቱ ፉክክር እያደረገች ሲሆን ምድቧን በመምራት ላይ ትገኛለች።
በተያያዘ ዜና ካፍ የአፍሪካ ሱፐር ሊግ በቀጣዩ የውድድር ዓመት ነሐሴ ወር በታንዛኒያ እንደሚደረግ ይፋ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም ካፍ ባሳለፈው ውሳኔ የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ መርኃ ግብር በደርሶ መልስ አሸናፊው እንዲለይ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ፋሲል ከነማ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
ሰኔ 26/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደረገለት፡፡
አምና የሊጉ ሻምፒዮን የነበረውና በዚህ የውድር ዓመት ከሁለተኛው የውድድር አጋማሽ ጀምሮ ምርጥ ፉክክር ሲያደርግ የቆየው ፋሲል ከነማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
በሊጉ ባደረጋቸው 30 ጨዋታዎች 61 ነጥብ በመያዝ ያጠናቀቁት አፄዎቹ ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ክለቡ በውድድር ዘመኑ ላስመዘገበው ውጤትም የከተማ አስተዳደሩ 7 ሚሊየን 462 ሺሕ 500 ብር፣ ከክለቡ 2 ሚሊየን 487 ሺሕ 500 ብር በድምሩ 9 ሚሊየን 950 ሺሕ 500 ብር ለክለቡ ተጫዋቾችና ለአሰልጣኞች እንዲሁም ለአጠቃላይ ሰራተኞችና የቦርድ አመራሮች የማበረታች ሽልማት ተበርክቷል።
በአቀባበሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ ዘውዱ ማለደና ሌሎች የጎንደር ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ክለቡ በቀጣዩ የውድድር ዓመት በአፍሪካ መድረክ በክለቦች የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናልም ነው የተባለው፡፡
በሀብታሙ ገደቤ