Forwarded from Vision-power Page (Tefera Muluneh)
Forwarded from Tefera Muluneh
*** ዛሬ አዲስ ሰው ነህ! ***
በሰው አካል ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ህዋስ በሰባት ዓመታት ውስጥ እራሱን ይተካል። ይህ ማለት ከሰባት ዓመታት በፊት የአንተ አካል የሆነ የአንተ ትንሽ አካል የለም ማለት ነው። ስቲቨን ሃል።
አየህ የማይቀየር ነገር የለም። የአንተ አካል እንኳ አንተ ባይታወቅህም በየጊዜው ይታደሳል። እናም ዛሬ ሌላ አዲስ ሰው ነህ። ግን … ግን በአስተሳሰብህስ? … በተግባርህስ? … ልማዶችህስ? … አዲስ ማንነትን ገንብተሃል?
ወዳጄ ሆይ አዲስ ማንነት ያስፈልግሃል! ራስህን መለወጥ ያስፈልግሃል! ምክንያቱም አንተ ዛሬ አዲስ ሰው ነህ!
ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!

👏16❤7👍7🙏2
*** ታሪክህን የመቀያየር መብት አለህ! ***
በማንኛውም ጊዜ የራስህን ህይወት እንዴት ማስኬድ እንዳለብህ በመወሰን ውጤቱን ልትቀይረው ትችላለህ።
ህይወትህ በየትኛም ደረጃ ላይ ሊገኝ ይችላል። መጨረሻውን የምትወስነው ግን አንተ ነህ። ይህንን ለማድረግ ውሳኔው እጅህ ላይ ነው! ህይወትህን ለመለወጥ አቅሙና ችሎታው አለህ!
እናም ወዳጄ ሆይ ያለህን አቅምና ችሎታ ተጠቅመህ አሁን ያለህን ህይወት የተሻለ እና ያማረ ይሆን ዘንድ እድሉ አለህ!

👍17🙏3❤2👏1
Forwarded from Vision-power Page (Tefera Muluneh)
03 Customer Handling ForPublic Leaders 2024.pdf
1.4 MB
👍6🥰2
Forwarded from Vision-power Page (Tefera Muluneh)
*** የአይቻልም ጉም! ***
አይቻልም የሚለው አባባል ልክ እንደ ጉም ነው። የክረምት ጉም የፈለገውን ያህል ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ቢመስልም ከርቀት የሚታይህን ያህል ጨለማ አይደለም። እየቀረብከው ስትሄድ እሱም እየራቀህ አጠገብህ ያለው ብርሃን እየሆነ ይሄዳል።
አይቻልም የሚለው አባባልም ልክ እንደጉም ስትቀርበው ይርቅሃል። አይቻልም የተባለው ነገር አጠገቡ ስትደርስ የሚቻል ነው። ያ የማይቻል የነበረው የሚቻል ይሆንና የማይቻል የሚባል ሌላ አዲስ ከርቀት ላይ ያለ ነገር ታገኛለህ እዚያም ከደረስክ የሚቻል ይሆናል።
ወዳጄ ሆይ ጉም ወደምትፈልገው እንዳትጓዝ እንደማያግድህ ሁሉ አይቻልም የሚለው አስተሳሰብ የምትፈልገው የስኬት ደረጃ ላይ ከመድረስ አያግድህም። እናም ወደፊት! …

👏12👍8❤2
Forwarded from Vision-power Page (Tefera Muluneh)
Leadership for Public Service-2025.pdf
3 MB
Businees Model Canvas Tef-2025.pdf
55.8 KB
For Entrepreneurship Trainees