Paradise
646 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#Doctor :በሽሮፕ or በኪኒን ልስጥክ.....

#Me🤔

#MoM: #በመርፌ 💉 ይሁንለት
😂😂

#stay@home

@USA2A
#ሚስቱ ከገዛ ጓደኛው ጋር ተኝታ አግኝቷት #በሽጉጥ ሲደፋው ምንአለችው....
:
እንዲ ከቀጠልክ ሁሉንም #ጓደኞችህን ታጣለህ #ፀባይህን አሳምር ሰውዬ!

#stay@home

@USA2A
ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

ሁሉንም የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ያለ ማንም ትዕዛዝ የሚፈጽመውና ለአጠቃላይ ጤናችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው አንጀታችን በብዙዎች 'ሁለተኛው አንጎል' በመባል ይጠራል።

የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት አንጀታችን ምግብ ከመፍጨት የበለጠ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያከናውናል።

ዶክተሮች እንዲውም አንጀት የአእምሮ ህመምን ለማከምና የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ለመገንባት የሚያደርገውን አስተዋጽ በግልጽ ለመለየት ምርምር ጀምረዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አውስትራሊያዊቷ ሜጋን ሮሲ በአንጀት ጤናና ህክምና ላይ በተለይ የሚሰሩ ዶክተር ናቸው። ስለምንበላቸው ምግቦችና በአንጀታችን ዙሪያ ማወቅ ስላሉብን ስድስት እውነታዎች ነግረውናል።

1. ራስ ገዝ የነርቭ ሥርዓት

ከሌሎቹ የሰውነት ክፍሎቻችን በተለየ መልኩ አንጀታችን በራሱ ጊዜ የሚያደርጋቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ከአንጎላችን እስኪመጣ አይጠብቅም።

አንጀታችንን የሚያዘው አንጎላችን ሳይሆን ''ኢንትሪክ የነርቭ ሥርዓት'' የሚባለው ሲሆን፤ ይህም በዋነኛነት የሚቆጣጠረው ከሥርዓተ-ልመት (የምግብ መፈጨትና መዋሃድ) ጋር የተያያዙ ሂደቶችን ነው።

ምንም እነኳን አንጀታችን ነገሮችን በራሱ ቢያናከውንም፤ ከማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት ጋር ግን መረጃዎችን ይለዋወጣል።

2. 70 በመቶ የሚሆኑት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሴሎች በአንጀታችን ውስጥ ይገኛሉ

እንደ ዶክተር ሮሲ ከሆነ ይህ እውነታ አንጀታችን ከበሽታ መከላከልና ከአጠቃላይ ጤንነታችን ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንዲሆን ያደርገዋል።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት የአንጀት ህምም ባጋጠመን ጊዜ እንደ ጉንፋን ላሉ በሽታዎች በቀላሉ ተጋላጭ እንሆናለን።



3. 50 በመቶ የሚሆነው የሰዎች አይነምድር ባክቴሪያ ነው

ግማሽ ያህሉ ከሰውነታችን የሚወደው አይነ ምድር ባክቴሪያ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ ባክቴሪያዎች ግን ጎጂ አይደሉም። ጎጂ ቢሆኑ እንኳን የአንጀታችን የመከላከል ብቃት ከፍተኛ ስለሆነ ብዙም የሚያሳስብ አይደለም።

ነገር ግን ይላሉ ዶክተር ሮሲ አንጀታችንን ሥራ ካበዛንበትና ካልተንከባከብነው ውጤቱ አስከፊ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ሰው በቀን ቢያንስ ሦስት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ጎራ ቢል መልካም ነው ባይ ናቸው።



4. የተለያዩ አይነት ምግቦች ስንመገብ አንጀታችን ደስ ይለዋል

አንጀታችን ውስጥ በትሪሊዮኖች የሚቆዎጠሩና ብዙ ጥቅም ያላቸው "ማይክሮብስ" የሚባሉ ጥቃቅን ነገሮች ያሉ ሲሆን እነሱ ደግሞ የተለያየ አይነት ምግቦች ወደ አንጀታችን ሲገባ የሥራ ፍጥነታቸው ይጨምራል።



እነዚህ ማይክሮብ የተባሉት ነገሮች የሥርዓተ ልመቱን ከማፋጠን አልፎ በምግቦች ውስጥ ያለውን ውሃ ለመምጠጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

''ማይክሮብስ'' በቤታችን እንደሚገኙ የቤት እንስሳት እንደማለት ናቸው። የእኛን እንክብካቤ ይፈልጋሉ በማለት ገልጸዋቸዋል ዶክተር ሮሲ።

5. የሆድ እቃችን ከጭንቀትና ስሜቶቻችን ጋር ግንኙነት አለው

ከሆድና አንጀታችን ጋር የተገናኘ ማንኛውም አይነት ህመም ሲሰማን መጀመሪያ ልናስበው የሚገባው ነገር በሰዓቱ ጭንቀት ውስጥ መሆን አለመሆናችንን ነው።

ለዚህም ነው በቅርቡ እየተሞከሩ ባሉ አዳዲስ የህክምና አይነቶች የአእምሮ በሽታና ቀላል ጭንቀቶችን ለማከም ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን ወደ አንጀት ማስገባት የተጀመረው።

የዘርፉ ባለሙያዎች እያደረጉት ባለው ጥናት ጤናማ የሆነ አንጀት ያላቸው ሰዎች ጤናማ ካልሆነ አንጀት ካላቸው ጋር ሲወዳደሩ ለጭንቀትና ሌሎች የአእምሮ በሽታዎች ያላቸው ተጋላጭነት የቀነሰ ነው።

6. የአንጀትዎትንና የሥርዓተ-ልመት ሂደቶችን ለማስተካከል የሚከተሉትን ያድርጉ

የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ይመገቡ

ጭንቀት ይቀንሱ

የሰውነት እንቅስቃሴ ያድርጉ

የአንጀት ህመም ካለብዎት የአልኮል መጠጦችን፣ ቡና እንዲሁም ቅመም የበዛባቸው ምግቦች አያዘውትሩ

ረጅምና ያልተቆራረጠ እንቅልፍ ያግኙ



#stay@home

@USA2A
ሕይወትዎን ቀለል ለማድረግ እነዚህን 10 መንገዶች ይጠቀሙ፤
========================================

1. በደንብ ካልተኙ ፣ ለአእምሮዎ “በደንብ ተኝቼያለሁ” ይበሉ ፡፡ የመታደስ ስሜት ይሰማዎታል። ይሞክሩት፡፡

2. እርስዎን የሚሰድብ አንድ ትኩረት ፈላጊ የሆነ ሰው ለማሸነፍ ይፈልጋሉ? ምላሽ አይስጡ በሌሎች ፊት ሙሉ በሙሉ እሱን ችላ ይበሉት። ይሄ የእሱን ምስል ይጎዳል እና እሱም ስለ እርስዎ ማንሳትን ያቆማል።

3. አንድ ሰው በትኩረት መከታተል ወይም አለመከታተሉን ማወቅ ይፈልጋሉ? የተናገሩትን በመጠኑ ትንሽ ቀይረው ይድገሙት ፡፡ እያዳመጠ ከነበረ የፊቱ ገጽታ ይለወጣል ወይም ደግሞ ጥያቄ ለማንሳት ይፈልጋል፡፡

4. አንድ ሰው በቡድን ውስጥ ለመስማማት ሲል እየዋሸ መሆኑን ማወቅ ይፈልጋሉ? በሚናገርበት ጊዜ ዓይኖቹን ብቻ ይመልከቱ ፣ ዓይኖቹ ለተናገረው ነገር የሌሎችን ማረጋገጫ የሚፈልጉ ከሆነ እያስመሰለ ነው ማለት ነው፡፡ አንድ ውሸታም / አስመስሎ በቡድኑ ውስጥ ለመገኘት የሚፈልግ ሰው ለሚናገራቸው ንግግሮች ሁል ጊዜ ማረጋገጫ ይፈልጋል ፡፡

5. ግምታዊና አፍራሽ ሃሳቦችን ማስወገድ ይፈልጋሉ? እነዚህ ጥያቄዎች ሲመጡብዎ አመክንዮአዊ ጥያቄ ይጠይቋቸው ፡፡ እንዲህ ሲያደርጉ አፍራሽ ሀሳቦችዎ ኃይላቸውን ያጣሉ እናም ቀስ በቀስ ድግግሞሻቸው ይቀንሳል ፡፡

6. በራስ የመተማመን ስሜት እንዲሰማዎት ይፈልጋሉ? ከአንድ ሌላ ሰው ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ያ ሰው ከእርስዎ የሚፈልገውን ሁሉ እንዳለዎት አድርጎ ይወስዳል ፡፡ ያን ጊዜ እርስዎ የሚፈልጉትን ስምምነት ለማድረግ ግድ ይሆናል ፡፡

7. ከአስቸጋሪ ሰዎች ጋር ተከራክረው ማሸነፍ ይፈልጋሉ? ከአስተያየታቸው ጋር የሚዛመዱ አሳማኝ ጥያቄዎችን ፈገግታ እያሳዩ ይጠይቋቸው፡፡ የዚያን ጊዜ ወይ ክርክራቸውን በአመክኖአዊ መልኩ ያዩታል ወይ ደግሞ ባለመስማማት ይስማማሉ፡፡ ይህ አይነቱ ድርጊት ያከስማቸዋል።

8. በአስደንጋጭ ሁኔታ ውስጥ ውጥረትን ለማስቀረት ይፈልጋሉ? በፊትዎ ላይ ፈገግታ ብቻ ያምጡ ፡፡ ወዲያውኑ ብርሃን እና ደስታ ይሰማዎታል።

9. የሆነ ነገር ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ? ስራውን ለመጀመር አዕምሮዎን ያሳምኑ ፡፡ አንዴ ማድረግ ከጀመሩት ደስ የሚል ሆኖ ያገኙትና ያጠናቅቁታል።

10. እርስዎን የሚያጠቁዎትን ሰዎች መዘወር ይፈልጋሉ? ምላሽ አይስጡ፣ አይጋፈጡ ፡፡ እነሱ እንዳሞኙዎት አድርገው ሊያስቡ ይችላሉ አንድ ቀን ግን እነሱንም በዚህ ጨዋታ ውስጥ ልክ የሚያስገባቸው ሰው ይኖራል፡፡

😊😊😊🌺🌺
#stay@home

@USA2A
🗣||የሰዉ ልጅ የሚችለዉን ያህል የሚጥር ከሆነ በእርግጠኝነት አንድ ቀን የእርሱን ለዉጥ ያየዋል።

ከትልቅ ለቅሶ ወደ ትንሽ ለቅሶም መለወጥ ትልቅ ለዉጥ ነዉና።

ለሚወዱት ሰው ያጋሩ🙏
#stay@home

@USA2A
I have just three things to teach:
Simplicity,
Patience,
Compassion.

These three are your greatest treasures.

✿ Simple in actions and in thoughts,
You return to the source of being.

✿ Patient with both friends & enemies,
You accord with the way things are,

✿ Compassionate towards yourself,
You reconcile all beings in the world.


SHARE! to a person that you care☺️☺️☺️
Join
👇👇👇
#stay@home

@USA2A
Zor Zor | ዞር ዞር - New Ethiopian Music 2020 (Official Video)
Kako Getachew
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​👤 Kako Getachew
🎵 Zor Zor | ዞር ዞር
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
Anything that you want is on the other side of fear!
#stay@home

@USA2A