Paradise
657 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#destiny

He couldn't go because he was afraid of the cemetery. He didn't go when his father died, he didn't go when his mother died, but one day people took him to the cemetery anyway.

#Stay@home

@USA2A

First we learn to read, then we read to learn🤷‍♂

#Stay@home

@USA2A
I Don't Care at All
Lucy Alvaro
🎼 I Don't Care At All from Mess
🎤 by Tough

If I stay with you, if I'm choosing wrong
I don't care at all
If I'm losing now, but I'm winning late
That's all I want
Now we need some space, 'cause I feel for you
And I wanna change
Growing up alone, it seems so short
I can't explain
Whatever happens in the future, trust in destiny
Don't try to make anything else even when you feel
I don't care at all
I am lost
I don't care at all
Lost my time, my life is going on
I will be so strong, looking for a new version of myself
Cause now all I want is to be a part of my new world
Whatever happens in the future, trust in destiny
Don't try to make anything else even when you feel
I don't care at all
I am lost
I don't care at all
Why not have it all
I am lone
I don't care at all
Lost my time, my life is going on

@USA2A AND @Lyrics09
ሰካራሙ_የመጨረሻ ክፍል ፲፭(15)

#ሶስና ብሎ ጠራና ነገ አብረን መዋል እንችላለን ወይ አለኝ
ደስ ይላኛል አልኩት
ልቤ ነገሩን እውነት ነው ብለው መቀበል እንኩዋን አልቻለም
እሁድ የቀን ቅዱስ
እሁድ የሰላም ቀን
እሁድ የእረፍት ቀን
እሁድ የደስታ ቀን
ምን ይዛው ሊመጣ ይሁን?
ምሽቱ አልነጋም አለኝ ነገን ለማየት ልቤ የበለጠ መጓጓቱን ቀጠለ ለካ ሰው ተስፍ
ሲኖረው ለመኖር እንደዚህ መጓጓት ይጀምራል
እኔ እኮ በፊት እንደዚህ አልነበርኩም ነጋ አልነጋም እያልኩ አልቀበጥርም ነበረ
ያው የእግዚአብሔር ፍቀድ የሆነ ነገር ሁሉ መሆኑ አይቀርምና ሌሊቱ ነጋ ጨለማው
በብርሃን ተለወጠ ልጁ በጥዋቱ ከእንቅልፍ ተነስቶ እኔን ከእንቅልፍ ቀሰቀሰኝ
ዝም ብዬ አልጋ ላይ ገደም ብዬ ነበረ እንጂ እኔም አልተኘሁም ነበረ
ቶሎ ብለሽ ልብስ ለባብሽ የምንሄድበት ቦታ አለ አለኝ
ግን እኮ በቅድሚያ ቁርስ መብላት አለብን አልኩት
አይደለም ሶስ በቅድሚያ ደርሰን መመለስ አለብን አለኝ
እሺ ብዬ ልብስ ለብሼ ወጣሁ
ነጠላ የለሽም ወይ አለኝ
አለኝ ግን አሁን ነጠላ ምን ያደርገል አልኩት
ካለሽ ነጠላ ልበሽ አለኝ
እሺ ብዬ ነጠላ ለብሼ ወጣሁ ከዛም አብረን የአስራ አምስት ደቂቃ መንገድ
በእግር ሄደን
ለካ ይዞኝ የሄደኝ ቤተክርስቲያን ነበረ
ለምን እንደሆነ አላውቅም በጣም ደስ አለኝ
ፀሎት ካደረግን በሓላ ቤተክርስቲያን ጊቢ ውስጥ አብረን ቁጭ አለን
ሶስ አለና ዛሬ እዚህ ለምን ይዤሽ እንደመጣሁ አውቀሻል ወይ አለኝ ?
እንዴ አንተ ካልነገርከኝ እኔ በምን አውቃለሁ አልኩት
ሶስ እኔ አንቺን እስካገኝ ድረስ ትርጉም የሌላት ህይወት እየኖርኩ ነበረ ህይወቴ ባዶ
ነበረች
ሰው ለመሆን ብዙ ሞክሬ ነበረ ነገር ግን ሰው መሆን አልቻልኩም
ደስተኛ ለመሆን እፈልግ ነበረ ግን ደስተኛ ለመሆን በጣም እፍራ ነበረ
አንቺን ካወኩሽ በሓላ ግን ነገሮች ሁሉ እየተቀየሩ መጡ
በርግጥ እኔ ከአንቺ ቀድሜ አንቺን ወድጄሽ ነበረ ነገር ግን እኔ የምቀርባቸው
ሰዎች ሁሉም በኔ ምክንያት ስለሚጎዱ አንቺን እንድትጎጂ አልፈለኩም
ነገር ግን አልቻልኩም
ዛሬ ፍቅሬን በፈጣሪ ፊት ለመግለጽ ነዉ ይዤሽ የመጣሁ አንቺን እንደ ሌሎቹ አይቼሽ ላጣሽ
አልፈልግም ለዛ ነው አለኝ
ሌላ አለም ውስጥ የገባሁ በህልሜም የሆነ መሰለኝ ህልም ነው እንዳልል
እኔ በህልሜ እንኩዋን እንደዚህ አይነት ንግግር ሰምቼ አላውቅም
በፈጣሪ ፊት ቃል ገባልኝ ከዛም ቀኑን ሙሉ ቤት ሳንመለስ መዝናኛ ቦታዎችን
እየሄደን አብረን ዋለን
ማታ አከባቢ በቃ አንተም መጠጥ ቤት ትሄዳለህ አይደለም እኔ ቤት መሄድ አለብኝ
አልኩት
ትንሽ ከሳቀ በሓላ ሶስ እኔ እኮ በፊት መጠጥ እጠጣ የነበረው የሚኖርለት ሰው
ስለሌለኝ ነው አሁን የምኖርለት ሰው አለኝ ህይወቴ የኔ ብቻ አይደለችም የአንቺም
ጭምር እንጂ ስለዚህ አንቺን የሚጎዳ ነገር ማድረግ አልፈልግም
ባይሆን አብረን ቤት እንሂድ አለኝ
ዋውውውውው ለካ ሰው ሆኖ ፍቅር የማይቀይረዉ የማይለወጥ ሰው የለም የብዙዎቹ ችግር በሰው
ላይ በበፊት ታሪክ ብቻ ይፈርዱበታል የበፊት ታሪኩን ስለሚያውቁ ብቻ ዛሬም ከእሱ
ይርቃሉ የበፊቱ ማንነቱን ብቻ አይተው መቅረብ ይፍራሉ
ህይወት ግን ትላንትም ዛሬም አዲስ ናት
ትላንት የትላንት ብቻ ናት ዛሬ መሆን አትችልም ትላንት መጥፎ የነበረ ሰው ዛሬ
ምናልባት ጥሩ ሰው ሆነው ሊገኝ ይችላል ትላንት ጥሩ የነበረ ሰው ምናልባት ዛሬ
መጥፎ ሰው ሆኖ ሊገኝ ይችላል
ትላንት ጠላትህ የነበረ ሰው ምናልባት ዛሬ ለክፉ ቀን ወዳጅ ሊሆን ይችላል
ትላንት ወዳጅህ የነበረ ሰው ምናልባት ዛሬ ጠላትህ ሊሆን ይችላል
ስለዚህ ሰውን መቅረብ ያለብን በዛሬው ማንነቱ ብቻ ነው
የሆነውን ሁሉ ለጓደኞቼ ተነገርኩ እነሱም በጣም ደስ አላቸዉ
ሄለንም ከወዛደሩ ልጅ ጋር በደስታ እያሰለፈች ነው
ከ9 ወር በሓላ ቅድስትም የልጅ እናት ሆናች
እኛም በዚህ አመት ለመጋባት አስባናል
እንግዲህ ፍቅር እንደዚህ ነው እኛ ይመጣል ብለን በጠበቅንበት መንገድ
አይመጣም ፍቅር ሁሉም ቦታ አለ ዋናው የልብ መዘጋጀት ነው።
#ተፈጸመ

አዲስ ትረካ እንድንጀምር ከፈለጋቹ በዚ ሀሳባቹን 👉👉 @Galaxy1bot 👈👈 አድርሱን

http://t.me/USA2A
#Doctor :በሽሮፕ or በኪኒን ልስጥክ.....

#Me🤔

#MoM: #በመርፌ 💉 ይሁንለት
😂😂

#stay@home

@USA2A
#ሚስቱ ከገዛ ጓደኛው ጋር ተኝታ አግኝቷት #በሽጉጥ ሲደፋው ምንአለችው....
:
እንዲ ከቀጠልክ ሁሉንም #ጓደኞችህን ታጣለህ #ፀባይህን አሳምር ሰውዬ!

#stay@home

@USA2A
ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

ሁሉንም የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ያለ ማንም ትዕዛዝ የሚፈጽመውና ለአጠቃላይ ጤናችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው አንጀታችን በብዙዎች 'ሁለተኛው አንጎል' በመባል ይጠራል።

የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት አንጀታችን ምግብ ከመፍጨት የበለጠ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያከናውናል።

ዶክተሮች እንዲውም አንጀት የአእምሮ ህመምን ለማከምና የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ለመገንባት የሚያደርገውን አስተዋጽ በግልጽ ለመለየት ምርምር ጀምረዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አውስትራሊያዊቷ ሜጋን ሮሲ በአንጀት ጤናና ህክምና ላይ በተለይ የሚሰሩ ዶክተር ናቸው። ስለምንበላቸው ምግቦችና በአንጀታችን ዙሪያ ማወቅ ስላሉብን ስድስት እውነታዎች ነግረውናል።

1. ራስ ገዝ የነርቭ ሥርዓት

ከሌሎቹ የሰውነት ክፍሎቻችን በተለየ መልኩ አንጀታችን በራሱ ጊዜ የሚያደርጋቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ከአንጎላችን እስኪመጣ አይጠብቅም።

አንጀታችንን የሚያዘው አንጎላችን ሳይሆን ''ኢንትሪክ የነርቭ ሥርዓት'' የሚባለው ሲሆን፤ ይህም በዋነኛነት የሚቆጣጠረው ከሥርዓተ-ልመት (የምግብ መፈጨትና መዋሃድ) ጋር የተያያዙ ሂደቶችን ነው።

ምንም እነኳን አንጀታችን ነገሮችን በራሱ ቢያናከውንም፤ ከማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት ጋር ግን መረጃዎችን ይለዋወጣል።

2. 70 በመቶ የሚሆኑት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሴሎች በአንጀታችን ውስጥ ይገኛሉ

እንደ ዶክተር ሮሲ ከሆነ ይህ እውነታ አንጀታችን ከበሽታ መከላከልና ከአጠቃላይ ጤንነታችን ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንዲሆን ያደርገዋል።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት የአንጀት ህምም ባጋጠመን ጊዜ እንደ ጉንፋን ላሉ በሽታዎች በቀላሉ ተጋላጭ እንሆናለን።



3. 50 በመቶ የሚሆነው የሰዎች አይነምድር ባክቴሪያ ነው

ግማሽ ያህሉ ከሰውነታችን የሚወደው አይነ ምድር ባክቴሪያ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ ባክቴሪያዎች ግን ጎጂ አይደሉም። ጎጂ ቢሆኑ እንኳን የአንጀታችን የመከላከል ብቃት ከፍተኛ ስለሆነ ብዙም የሚያሳስብ አይደለም።

ነገር ግን ይላሉ ዶክተር ሮሲ አንጀታችንን ሥራ ካበዛንበትና ካልተንከባከብነው ውጤቱ አስከፊ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ሰው በቀን ቢያንስ ሦስት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ጎራ ቢል መልካም ነው ባይ ናቸው።



4. የተለያዩ አይነት ምግቦች ስንመገብ አንጀታችን ደስ ይለዋል

አንጀታችን ውስጥ በትሪሊዮኖች የሚቆዎጠሩና ብዙ ጥቅም ያላቸው "ማይክሮብስ" የሚባሉ ጥቃቅን ነገሮች ያሉ ሲሆን እነሱ ደግሞ የተለያየ አይነት ምግቦች ወደ አንጀታችን ሲገባ የሥራ ፍጥነታቸው ይጨምራል።



እነዚህ ማይክሮብ የተባሉት ነገሮች የሥርዓተ ልመቱን ከማፋጠን አልፎ በምግቦች ውስጥ ያለውን ውሃ ለመምጠጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

''ማይክሮብስ'' በቤታችን እንደሚገኙ የቤት እንስሳት እንደማለት ናቸው። የእኛን እንክብካቤ ይፈልጋሉ በማለት ገልጸዋቸዋል ዶክተር ሮሲ።

5. የሆድ እቃችን ከጭንቀትና ስሜቶቻችን ጋር ግንኙነት አለው

ከሆድና አንጀታችን ጋር የተገናኘ ማንኛውም አይነት ህመም ሲሰማን መጀመሪያ ልናስበው የሚገባው ነገር በሰዓቱ ጭንቀት ውስጥ መሆን አለመሆናችንን ነው።

ለዚህም ነው በቅርቡ እየተሞከሩ ባሉ አዳዲስ የህክምና አይነቶች የአእምሮ በሽታና ቀላል ጭንቀቶችን ለማከም ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን ወደ አንጀት ማስገባት የተጀመረው።

የዘርፉ ባለሙያዎች እያደረጉት ባለው ጥናት ጤናማ የሆነ አንጀት ያላቸው ሰዎች ጤናማ ካልሆነ አንጀት ካላቸው ጋር ሲወዳደሩ ለጭንቀትና ሌሎች የአእምሮ በሽታዎች ያላቸው ተጋላጭነት የቀነሰ ነው።

6. የአንጀትዎትንና የሥርዓተ-ልመት ሂደቶችን ለማስተካከል የሚከተሉትን ያድርጉ

የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ይመገቡ

ጭንቀት ይቀንሱ

የሰውነት እንቅስቃሴ ያድርጉ

የአንጀት ህመም ካለብዎት የአልኮል መጠጦችን፣ ቡና እንዲሁም ቅመም የበዛባቸው ምግቦች አያዘውትሩ

ረጅምና ያልተቆራረጠ እንቅልፍ ያግኙ



#stay@home

@USA2A
ሕይወትዎን ቀለል ለማድረግ እነዚህን 10 መንገዶች ይጠቀሙ፤
========================================

1. በደንብ ካልተኙ ፣ ለአእምሮዎ “በደንብ ተኝቼያለሁ” ይበሉ ፡፡ የመታደስ ስሜት ይሰማዎታል። ይሞክሩት፡፡

2. እርስዎን የሚሰድብ አንድ ትኩረት ፈላጊ የሆነ ሰው ለማሸነፍ ይፈልጋሉ? ምላሽ አይስጡ በሌሎች ፊት ሙሉ በሙሉ እሱን ችላ ይበሉት። ይሄ የእሱን ምስል ይጎዳል እና እሱም ስለ እርስዎ ማንሳትን ያቆማል።

3. አንድ ሰው በትኩረት መከታተል ወይም አለመከታተሉን ማወቅ ይፈልጋሉ? የተናገሩትን በመጠኑ ትንሽ ቀይረው ይድገሙት ፡፡ እያዳመጠ ከነበረ የፊቱ ገጽታ ይለወጣል ወይም ደግሞ ጥያቄ ለማንሳት ይፈልጋል፡፡

4. አንድ ሰው በቡድን ውስጥ ለመስማማት ሲል እየዋሸ መሆኑን ማወቅ ይፈልጋሉ? በሚናገርበት ጊዜ ዓይኖቹን ብቻ ይመልከቱ ፣ ዓይኖቹ ለተናገረው ነገር የሌሎችን ማረጋገጫ የሚፈልጉ ከሆነ እያስመሰለ ነው ማለት ነው፡፡ አንድ ውሸታም / አስመስሎ በቡድኑ ውስጥ ለመገኘት የሚፈልግ ሰው ለሚናገራቸው ንግግሮች ሁል ጊዜ ማረጋገጫ ይፈልጋል ፡፡

5. ግምታዊና አፍራሽ ሃሳቦችን ማስወገድ ይፈልጋሉ? እነዚህ ጥያቄዎች ሲመጡብዎ አመክንዮአዊ ጥያቄ ይጠይቋቸው ፡፡ እንዲህ ሲያደርጉ አፍራሽ ሀሳቦችዎ ኃይላቸውን ያጣሉ እናም ቀስ በቀስ ድግግሞሻቸው ይቀንሳል ፡፡

6. በራስ የመተማመን ስሜት እንዲሰማዎት ይፈልጋሉ? ከአንድ ሌላ ሰው ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ያ ሰው ከእርስዎ የሚፈልገውን ሁሉ እንዳለዎት አድርጎ ይወስዳል ፡፡ ያን ጊዜ እርስዎ የሚፈልጉትን ስምምነት ለማድረግ ግድ ይሆናል ፡፡

7. ከአስቸጋሪ ሰዎች ጋር ተከራክረው ማሸነፍ ይፈልጋሉ? ከአስተያየታቸው ጋር የሚዛመዱ አሳማኝ ጥያቄዎችን ፈገግታ እያሳዩ ይጠይቋቸው፡፡ የዚያን ጊዜ ወይ ክርክራቸውን በአመክኖአዊ መልኩ ያዩታል ወይ ደግሞ ባለመስማማት ይስማማሉ፡፡ ይህ አይነቱ ድርጊት ያከስማቸዋል።

8. በአስደንጋጭ ሁኔታ ውስጥ ውጥረትን ለማስቀረት ይፈልጋሉ? በፊትዎ ላይ ፈገግታ ብቻ ያምጡ ፡፡ ወዲያውኑ ብርሃን እና ደስታ ይሰማዎታል።

9. የሆነ ነገር ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ? ስራውን ለመጀመር አዕምሮዎን ያሳምኑ ፡፡ አንዴ ማድረግ ከጀመሩት ደስ የሚል ሆኖ ያገኙትና ያጠናቅቁታል።

10. እርስዎን የሚያጠቁዎትን ሰዎች መዘወር ይፈልጋሉ? ምላሽ አይስጡ፣ አይጋፈጡ ፡፡ እነሱ እንዳሞኙዎት አድርገው ሊያስቡ ይችላሉ አንድ ቀን ግን እነሱንም በዚህ ጨዋታ ውስጥ ልክ የሚያስገባቸው ሰው ይኖራል፡፡

😊😊😊🌺🌺
#stay@home

@USA2A
🗣||የሰዉ ልጅ የሚችለዉን ያህል የሚጥር ከሆነ በእርግጠኝነት አንድ ቀን የእርሱን ለዉጥ ያየዋል።

ከትልቅ ለቅሶ ወደ ትንሽ ለቅሶም መለወጥ ትልቅ ለዉጥ ነዉና።

ለሚወዱት ሰው ያጋሩ🙏
#stay@home

@USA2A
I have just three things to teach:
Simplicity,
Patience,
Compassion.

These three are your greatest treasures.

✿ Simple in actions and in thoughts,
You return to the source of being.

✿ Patient with both friends & enemies,
You accord with the way things are,

✿ Compassionate towards yourself,
You reconcile all beings in the world.


SHARE! to a person that you care☺️☺️☺️
Join
👇👇👇
#stay@home

@USA2A