የጊንር ጽጌ ተዋህዶ ሰ/ት ቤት
304 subscribers
886 photos
16 videos
12 files
19 links
ይህ ቻናል ዓላማውን የሰንበት ት/ ቤቱን ጠቃሚ መረጃዎች እና መልእክት ማስተላለፍ አድርጎ ጥር 19/2012ዓም ሌሊት 6:50 ላይ ተከፈተ፡፡
Download Telegram
+++ቅዱሳን መላእክት+++

✥ ቅዱሳን መላእክት የምንላቸው በአንዲት ርትዕት ሃይማኖት ጸንተው ያለግዳጅ ወደውና ፈቅደው የሚላላኩትን/የሚያገለግሉትን ነው። ርኩሳን መላእክትም አሉና

📖 "...ከእርሱም ጋር #ቅዱሳን_መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል...እናንተ ርጉማን፥ #ለሰይጣንና_ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ" እንዲል ማቴ፳፭ ፥፴፩ - ፵፩

✥ ርኩሳን መላእክትን አናከብራቸውም አናመሰግናቸውምም ይልቁንም እንነቅፋቸዋለን "እክህደከ ሰይጣን እንተ ይእቲ ስምዕየ ማርያም" እያልን ድንግልን ምስክር አድርገን እንክዳቸዋለን!!! ነቢየ እግዚአብሔር እንዳመለከተንም "አቤቱ፥ የሚበድሉኝን በድላቸው፥ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው" እያልን እንጸልይባቸዋለን [መዝ ፴፭፥፩]

#በአንጻሩ ቅዱሳን መላእክትን እናከብራቸዋለን እናመሰግናቸዋለን እንሰግድላቸዋለን እናምናቸዋለን!!!

እንደ ጻድቁ ሎጥ "ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ" [ዘፍ፲፱፥፪] እያልን እንደ ሰዶም ካለ መቅሰፍት ይጠብቁን ዘንድ ወደ እነርሱ እንጸልያለን::

✥ ቅዱሳን መላእክትን የምናከብራቸው እስከምን ድረስ ነው?

መጽሐፍ ለአገልጋዮች "እጥፍ ክብር ይገባቸዋል" ብሏልና [፩ኛጢሞ፭፥፲፯] በእጥፍ ክብር እናከብራቸዋለን!!!

ሐዋርያው ጨምሮ "ስለ ሥራቸውም በፍቅር #ከመጠን_ይልቅ ታከብሩአቸው ዘንድ እንለምናችኋለን" በማለት እንደነገረን [፩ኛተሰ፭፥፲፪-፲፫] ከመጠንም ይልቅ እናከብራቸዋለን

✥ መላእክት እንዲህ የሚከበሩት ስለ ሥራቸው ነው።

"ለመላክነሂ ኢናከብሮ ለእመ አስረጸ ክንፈ፤ ለኦፍ ወለትንንያ እስመ ቦሙ ክንፈ... - መላክን ክንፍ ስላወጣ አናከብረውም ወፍና ትንኞችም ክንፍ አላቸውና" እንዳለ ባለቅኔው

ስለ በጎ ስራቸው ግን እናከብራቸዋለን
"በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል" [ሮሜ፪፥፲]

✥ ህዝበ እስራኤል ባሕረ ኤርትራን በተሻገሩ ጊዜ በሙሴ እንዳመኑ ሁሉ [አግዚአብሔር እንዲያሻግራቸው አግዟቸዋልና]

"እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፥ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ በእግዚአብሔርም
#በባሪያውም_በሙሴ_አመኑ" ዘፀ፲፬፥፴፩

እኛም መዳንን እንወርስ ዘንድ በሚያግዙን (ዕብ ፩፥፲፬) በቅዱሳን መላእክት እናምናለን!!!

#የቅዱስ_ገብርኤል_ጠብቆቱ_አይለየን !!!
#ጌታችን_የተወለደባት_ቀን

"ይህች ቀን ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ቀን ናት፡፡

ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን፤ ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!

ይህች ቀን የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!

ይህች ቀን ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ቀን ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡

ይህች ቀን የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን።

ይህች ቀን የትሕትና ቀን ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት።

ይህች ቀን የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት።

የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!

ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው።"
ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባሕርይ ተገኘ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመሆኑም ከባሕርዩ አልተለወጠም።

የመለኮቱ መገኘትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ፤ የማይታመም እርሱ ከባሕርየ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ሥጋን ተዋሐደ።

ዳግመኛም በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ሥጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋሕድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ ተዳሰሰ፤ ሀጢአትን የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተሸፈነ።

ብልህ ሸክላ ሠሪ የሚሠራውን የለዘበ ጭቃ በአገኘ ጊዜ ከእርሱ መልካም ዕቃ እንዲሠራ እንደዚህ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንጹሕ ሥጋዋን ንጽሕት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ሥጋ ሊዋሐደው ፈጠረ።

እንደ ወደደ ከድንግል ነፍስን ሥጋን ፈጥሮ ለበሰ፤ እርሱንም ተዋሕዶ ዛሬ ተወለደ፤ ሕጸጽ ያለበት ነው ብሎ ባሕርያችንን አልተወውም፤ ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ቃል ከምልአቱ አልተወሰነም፤ ሥጋ የፈጣሪ አካል ባሕርይ በሆነ ጊዜ ፍጹም አምላክነትን አገኘ እንጂ።

ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ሕፃን ሆኖዋልና እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን፤ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሠሥ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሠሠ፤ ኃጢአትን የሚሸፍን እርሱን፤ በጨርቅ ሸፈኑት፤ ይህን ወዶአልና።

ክብርን ተለይቶ የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው የጸጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ሥጋንም የባሕርያ ገዥ ሊያደገው ወደደ፤ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው።

ስለዚህ ሥጋዬን ተዋሐደ፤ ወንጌልን ሲያስተምር እሰማው ዘንድ ሥጋዬን በተዋሕዶ ገንዘብ አደረገ፤ መንፈስ ቅዱሰን ሰጠኝ፤ ተቀበልኩ ለኔም ፍጹም ሕይወትን ገንዘብ አደረግሁ እርሱ ያከብረው ዘንድ ሥጋዬን ተዋሐደው የሚያድነኝ መንፈስ ቅዱስን ሰጠኝ።

እንደ ሰው በሰው ዘር አልተወለደም አምላክ ሲሆን ሰው ሆነ እንጂ ሰው ሆኖ ዛሬ ከድንግል ተወለደ በዘር ከመወለድ በራቀ በእኛ ባሕርይ ዲያብሎስን ድል ነሣው፤ ሁሉን ለፈጠረ ጌታ ንጽሕት ልዩ በሆነች ልደት መወለድ ተገባው።
ቀድሞም አዳምን ካልታረሰች ምድር ፈጠረው፤ ዳግመኛ ሔዋንን ከአዳም ያለ እናት ፈጠረ አዳም ያለ እናት ሔዋንን እንዳስገኘ እንዲሁ ዛሬ ድንግል ክርስቶስን ያለ ኣባት ወለደች።

ነቢይ ስለ እርሱ ሰው ሲሆን መርምሮ ያውቀው ዘንድ የሚችል ማነው? አለ ለወንዶች የሚከፈለው ዕዳ በሴቶች ላይ ነበረ፤ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና፤ ስለዚህም ድንግል ግን ያለ ዘርዐ ብእሲ ክርስቶስን ወለደች፤ የሔዋንን ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስለአስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደች ድንቅ በሚሆን አንድነት ይህ አንድ የፍጥረት እኩልነት ይታወቅ ዘንድ።

ከአዳም ጐን ጐድን አጥንት እንደነሣ አዳምንም አካል እንዳልጎደለው እንዲሁ ከድንግል የምትናገር፤ የምታውቅ ነፍስ ያለችው ሥጋን ነሣ፤ ማኅተመ ድንግልናዋ አልተለወጠም፤ አዳም የጎድን አጥንት ከእርሱ ከተነሣ በኋላ አካል ሳይጎድለው ፍፁም ሆኖ ኖረ፤ ድንግልም ሕፃን ክርሰቶስ ከእርሷ ከተወለደ በኋላ እንዲሁ ያለመለወጥ በድንግልና ጸንታ ኖረች።
እንደ እኔስ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢሆን ብዙ ሰዎች ዕሩቅ ብእሲ ባሉት ነበር አምላክነቱንም በካዱ ነበር እንዲህስ እንዳይሉት ከድንግል ተወለደ፤ በወለደችውም ጊዜ ድንግልናዋን ያለመለወጥ አጸና፤ ድንቅ በሚሆን ፅንሷ ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትሆን ዘንድ።

ጣዖት የሚያመልክ ወይም አይሁዳዊ በውኑ ክርስቶስ እንደሰው ሁሉ ያለ ሰው ነውን ወይስ ከሰው ሁሉ እርሱ ይበልጣል? ብሎ ቢጠይቀኝ አዎን ከሰው ሁሉ እርሱ ይበልጣል ብዬ እመልስለታለሁ ለቃል ምስክር ከምትሆን ከድንግል በኅቱም ድንግልና መወለዱን ምስክር አድርጌ እናገራለሁ።

ፍጡራንን ሁሉ ወስኖ ገቶ የሚኖር ኃጢአትን ሞትን ድል የነሣ እርሱ ነው፤ የእናቱን ማኅፀን የፈጠረ ድንግልናዋንም ያጸና እርሱ ነው፤ ዘር በሌለበት ልደት ተወልዷልና እርሱ በማይመረመር ግብር በወደደው መልክ ሥጋን ፈጥሮ ተዋሐደ።
ከድንግል በተወለደ ጊዜ ድንግልናዋን ያለመለወጥ አጸናው፤ ቀድሞ ሔዋን ድንግል ነበረችና ዲያብሎስ አሳታት እንጂ ድንግል ማርያምን ግን ገብርኤል አበሠራት።

ነገር ግን ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃየልን ወለደች፤ ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች።

ዳግመኛም ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ጽኑዕ መለኮት ከባሕርዩ አልተለወጠም፤ አምላክ ለሦስትነት እንደሚገባ ተወለደ።
ሰዎች ትተውት ነበርና፤ በሰው አምሳልም ጣኦትን ሠርተው አምልከው ነበርና ፈጣሪያቸውንም አሳዝነውት ነበርና፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ቃል በሰው ባሕርይ ተገለጠ፤ ጣኦት እልም ድርግም ይል ዘንድ መመለክም ለእርሱ ብቻ ይሆን ዘንድ ክብር ጌትነት ከሀሊነት ለዘላለሙ ገንዘቡ የሚሆን እርሱ ነው።

ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (ስለ ልደት ከሚያነሳው ከፍል የተወሰደ)
በጊንር ያላችሁ አማንያንና ጥሙቃን ሁላችሁ ጥምቀትን በአንድነት እየዘመርን ታቦተ ህጉን እንድናጅብ ታስቦ የአንድነት የመዝሙር ጥናት ተጀምሯልና ዘወትር ሠርክ 11:00 በጽጌ ተዋህዶ አዳራሽ ተገኝታችሁ እንድታጠኑ ይሁን።
ጌታችን የዕዳ ደብዳቤአችንን በቀደደ ጊዜ (በተጠመቀ ጊዜ) "እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ " ማቴ 3:16

ዛሬም የሰማያትን ምስጢር እናስተውል ዘንድ ከኃጢአታችን ዕድፍ በንሰሀ ለመታጠብ በቸርነቱ ያድለን
መልካም በዓል
ጥምቀተ ፳፻፲፮።
በሠላም በደስታ እንድናሳልፍ ለረዳን ለአምላከ ጊዮርጊስ ምን እንላለን - ተመስገን!!!
ጥር 18 ለሚከበረው ለቅዱስ ጊዮርጊስ  ዓመታዊ ክብረ በዓል  እንኳን  አደረሳችሁ🤗......  ሌሊት  አባቶች  ማኅሌት  ከሚቆሙት  አንዱን  እዩልኝማ  😊

ሰላም ለአማዑቲከ ወለንዋየ ውስጥከ ክዕዋት ፣ አመ አጾሩከ በምክያድ ምስለ አስካለ ወይን ወዘይት፥ጊዮርጊስ ክቡር መክብበ ሰማዕት ፥ በእንተ አባላቲከ እለ ተከፍላ ኃበ አሠርቱ ክፍላት፥ ኢይሰስል እምኔየ ዘለከ ረድኤት።

#(ትርጉም)

በመንኮራኩር  እንደ ዘይት እና እንደ ወይን እየረገጡ ስለጨመቁት 🤯 የሆድ እቃህ  ጊዮርጊስ ሆይ  ሰላም  እላለሁ

የሰማዕታት  ሁሉ ራስ  የሆንክ ጊዮርጊስ  ሆይ አስር ቦታ (በመጋዝ) ስለተከፈሉት  ሰውነትህ 🥺 ስትል  ለኔ የምታረገውን  እርዳታ  ቸል  አትበል።🙏

የዚህ  ተራዳኢ  ሰማዕት  በዓለ ንግሱ እዚሁ በደብራችን መካነ ሰማዕት  ነገ (ቅዳሜ)  ይከብራል።   የቻልን በማኅሌቱ  ያቃተን በበዓሉ እንገኝ❤️
"ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች" ሉቃ1 : 29

+++ድንግል ሆይ #አበውን_ተከትለን ትህትናሽን እናደንቃለን #በድርጊትና #በንግግር ብቻ ያይደለ #በሀሳብሽም ትሁት ነሽና!!!

+++ርኅርኅት ሆይ ወደ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ #በፍጥነት መውጣትሽን እያሰብን እንደነቃለን ሉቃ1:39

+++ንግሥት ሆይ አንቺኮ ንጉሡ እግዚአብሔርን የተሸከምሽ ታቦት ነሽ!!! ታዲያ ስለምን ዘመድሽን አልጠራሻትም? ወደ ርሷ መሄድሽ ሳያንስ ስለምን ወደ ኤልሳቤጥ ይወስዱሽ ዘንድ አጃቢ አልፈለግሽም? ዣንጥላስ ለምን አላዘረጋሽም?

+++ቅድስት ኤልሳቤጥ ሆይ እውነተኛዋ ታቦት ወዳንቺ መጥታለችና ነቢይ ዳዊት በታቦተ ጽዮን ፊት እንዳደረገ (2ኛ ሳሙ6:9) "...ወደኔ ትመጪ ዘንድ እንደምን ይሆንልኛል" እያልሽ በትህትና ልትዘምሪ ይገባል አንቺው እንዳልሺው የጌታሽ እናት ናትና!!! (ሉቃ1:43)

+++ድንግል ማርያም ሆይ መልአኩ ያውም የመላእክት አለቃ አምላክን ትወልጃለሽ እያለ ራስሽን ባሪያ ማለትሽ ይደንቃል!!!

+++ወንጌላዊው ደግሞ ሀሳብሽን ነግሮ አስገረመን

+++ቅዱስ ሉቃስ ሆይ የእመቤታችንን ሀሳቧን ትጽፍ ዘንድ እንደምን አወከው?!

#በዓይን_የሚታየውን_ተአምሯ ሲጻፍ "እንዴት?" ብለው አልቀበል የሚሉ ስሁታንስ ይኽን ነገርኽን እንዴት ይመለከቱት ይሆን?!

ይሄኔኮ አንተንም እብድ ብለውህ ይሆናል መች ያፍሩና #ቅዱስ_ጳዉሎስ ግን "እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው" ብሎ ይሞግትልሃል (2ኛቆሮ5 : 13) እንግዲህ መናፍቃን ምጉታቸው ከማን ጋር እንደሆነ ይወቁት!!!

#ሊምረው_የወደደውን_የእናቱን_ፍቅር_ያሳድርበታልና_የእመቤታችን_ፍቅሯን_ያሳድርብን !!!

እንኳን አምላክን ለወለደች በትህትናዋ ለተደነቀች ለድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት አደረሰን🙏
ዝም  እንበል!

እግዚአብሔር ይሰራል።

“ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።” ዮሐ 5፥17  ብሎ  እንደተናገረ ።

በዚህ  ረቂቅ  መለኮታዊ እቅድ ውስጥ የሰው ተሳትፎ በመጀመሪያ  ሊሆን የሚገባው ለእቅዱ  ከፊት ለፊት እየቀደሙ  በምላሳችን  ጋሬጣ  ከማበጀት  ይልቅ  ዝምምምም  ማለት ነው። 

“ከዚህም ወራት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰችና፦ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል ስትል ራስዋን አምስት ወር ሰወረች” ሉቃ 1፥24-25

አይ  እናታችን! 

ይብስተ በረከት ፤ ዑጸተ ማህጸን ፤  ጡተ ደረቅ  ስትባል የነበረች  ምስኪን :  እናንተ ብትወልዱ  በተገባ ልማድ በጊዜያችሁ   እኔ ብወልድ  በመለኮታዊ ተአምር በብስራተ መልአክ ...  ብላ  ልመካባችሁ  ሳትል ሰወረችው። (በርግጥ ይህ  በጽንስ ጊዜ ፎቶ መነሳት  ሱስ ለሆነባቸው ተግሳጽም ጭምር ነው።) 

የሷ  ዝም ማለት  የሷ  ጊዜ መስጠት  ድንግል  ማርያምን  እያስፈጠነ ከመቅደስ ወደ ተራራማው ሀገር  እንድትሄድ እና እንድትጎበኛት  ሆነ። 

እኛም  ሁልጊዜ  ዕለት  ዕለቱን  "ወበሳድስ ወር...በስድስተኛው ወር..."  እያልን  ለመጸለይ  አንዷ  ምክንያት  ሆነችን።


   'አቤቱ ለአፋችን  መዝጊያን  አኑር'
🌹🌹🌹የሰርግ መዝሙር 🌹🌹🌹

ርዕስ፦ ❤️ሙሽሮቹ አንድ ናቸው❤️
ግጥም፦ አብርሃም አድማሱ ዘጊንር
ዜማ፦ ማኅበረ ቅዱሳን (ቤተክርስቲያን አንዲት ናት በሚለው ዜማ)

❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖

አንድ ናቸው ሙሽራዎቹ አንድ ናቸው(*2)
ክርስቶስ በደሙ አንድ ያደረጋቸው
ማንም ለወደፊት ማይነጣጥላቸው
ሙሽሮቹ አንድ ናቸው
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
በቅብዓ ሜሮኑ በካህናት ጸሎት
አንድነት ይጸናል ጠፍቶ ሁለትነት
ከሰማያዊው ማዕድ በአንድነት ቆርበዋል
አንዱ ክርስቶስ አንድ አድርጓቸዋል(*2)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ቤተ ክርስቲያንን ጌታ እንደወደዳት
አንተም እንደ እርሱ ሚስትህን ውደዳት
አጋዥህ ናትና ለመንፈሳዊነት
ከማዕበል መትረፊያ ወደብህ ሚስትህ ናት(*2)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
እንዲሆን ቤታችሁ የሠላም የፍቅር
ለባልሽ ታዘዢው አንተም ያዛት በፍቅር
ዘውድ ሁኚው ለራስሽ ለሕይወትሽ አጋር
ክብሩ ለራስሽ ነው አካልሽን ማክበር(*2)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ለጸሎት ለመትጋት በአንድነት ተባብረን
ልዩነት አጥፍተን በአንድ መንፈስ ሆነን
የዓለምን ፈተና እንድናልፍ ተጋግዘን
ትዳርን የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን(*2)
❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥
አታዉኪኝ ነፍሴ
<unknown>
መዘምራን ዘ ጽጌ ተዋህዶ ዘወትር እሁድ በጉባዔ እንዲህ የሚያለመልም ዝማሬን ያቀርባሉና ኑ ዘፈን ያደነቆራት ነፍሳችንን በዚህ እናሳርፋት
የተወደሽ እህታችን #ሠርክዓለም_ጌታ እና የተወደድክ ወንድማችን #ኤርምያስ_አድማሱ (#ተሰማ) እንኳን ደስ አላችሁ❤️‍🔥

❤️‍🔥የካቲት ፫- ፳፻፲፮ ዓም ጫንጮ ሥላሴ❤️‍🔥

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሠርክ ዓለም ውበቷ በሁሉ ተሰማ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በሦስቱ ጉልቻ የጣድነው ምጣዱ ተሰማ
እንጀራው ውብ ሆኖ ለሁሉ እንዲስማማ
ሠርኬ ትጋግርበት ብለዋል እማማ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ከቀጮ ከአቤ ተግቶ የተማረ
ተሰማ ጎበዙ ነጥብ አስቆጠረ
ከትዳሩ ትምህርት ከቶ ስላልራቀ
በቅድስት ሥላሴ ዛሬ ተመረቀ
ወንድሜ ተሰማ ጎልቶ ተደመጠ
በንግሥናው ዙፋን ይኸው ተቀመጠ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ጽጌ ተዋህዶ በጣም ታድለሻል
ሠርክዓለም ልጆችሽ ያመሰግኑሻል
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት 8  በዚህች  ቀን በምድረ ሊብያ  በተንባላት (ISIS)  እጅ ሰማዕትነትን  የተቀበሉ የ21  ግብጻውያን ክርስቲያኖች  የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።  በጸሎታቸው  የምትገኝ በረከት ለሁላችን  ትድረሰን   አሜን።
አርምሞ - ዝምታ

ጥንቱን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን መላዕክትንም በዝምታ ፈጠረ። የተገቡ ሰማዕያን ሲኖሩ እንኳን በተገባ ንግግር "ለይኩን" "ለታውጽዕ ባሕር" ለታውጽዕ ምድር" እያለ በተመጠነ ተናገረ እንጂ በዚህ ገብቶ በዚያ ወጥቶ አላለም።

ለመላእክት የምስጋና እንጂ የወሬ ክፍለ ጊዜ የላቸውም

አዳም ለጸሎት እንጂ ለወሬ ቦታ አልነበረውም

ሔዋን ከእባብ ጋር ወሬ ብትጀምር ለወሬ በተከፈተ አፍዋ በለስን እስከመብላት ደረሰች የ5500 ዘመን መዘዝም አመጣች!

ይህን ያስተዋሉ አባቶቻችን "ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም" አሉ።

በእግዚአብሔር ስለተወደደው ያዕቆብ እንዲህ ተጽፏል

"ያዕቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፥ በድንኳንም ይቀመጥ ነበር" ዘፍ ፳፭፥፳፯

እግዚአብሔር እንደ ልቤ ያለለት ዳዊት

"በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ" ይላል መዝ ፴፱፥፩

ጸሎቱም "አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ" የሚል ሆነ (መዝ ፻፵፩፥፫)

ስለ ጌታችን ልዑለ ቃል ኢሳይያስ በትንቢት እንዲህ ተመልክቶ ነበር
"... አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም" ኢሳ ፶፫፥፯

በነቢዩ እንደሰማን እንዲሁ በወንጌል ተመለከትን!

የዚህችን ትዕግሥት አቅሟን በጥቂቱም ቢሆን ለመረዳት የሻተ ደራሲ
"ጸግወኒ ማዕጾ አፍ እንተ ይእቲ አርምሞ ለትዕግሥትከ ከመ አእምር አቅሞ" እያለ ዝምታ እንድትሰጠው ተማጸነ (መልክዐ ኢየሱስ፤ ለአፉከ)

ከሥራ ይልቅ በወሬ ለተጠመድን በማናውቀው እንኳ "መሰለኝ" እያልን ሀሳብ መስጠትን እንደ ብልኅነት እንደ ሊቅነት እንደ ዘመናዊነት ቆጥረን ወርቋን ዝምታ ጥለን ለአፋችን ጠባቂ ከማኖር ለተከልክለን ለኛ

ስለ ዝምታ ብለው ዕድሜ ልካቸውን ድንጋይ ጎርሰው የኖሩ አበው እለ አጋቶን ተግሳጾቻችን ናቸው!

በአባቶቻችን ዝምታ ደስ የተሰኘ አምላክ ዛሬ ተለውጦ በኛ ቀባጣሪነት ደስ ሊሰኝ አይችልም።

የዝምታን ወርቅነት የሚያስተውል ልቦና ይስጠን።

ዝምታ ቅድስና ናት በቀላል ገንዘብ የምናደርጋት አይደለችምና ተጋድሎ ትፈልጋለች

ቅድስና የሌለው እንደ እኔ ስለዝምታም ቢሆን ያወራል እንጂ ዝም ማለት አይቻለውም!

አይ አርምሞ! አይቴ ብሔራ ለአርምሞ? ያገኛችኋት እንደሆነ እባካችሁ መንገዷን አመልክቱኝ🙏
መዝሙር👇

ዘይቤ በነቢይ ወርዘውኩሂ ወረሳዕኩ ጻድቅሰ ዘይትገደፍ ኢርኢኩ #መካነ_ሰማዕት (*፪)
አድኃነኒ እስመ ይፈቅደኒ ወለሞትሰ ባህቱ ኢመጠወኒ ሊቀ ሰማዕት መድኃኒተ ኮነኒ ቅዱስ ጊዮርጊስ(*፪)

እንዳለ በነቢይ ጎለመስኩ አረጀሁም ጻድቅ ግን ሲጣል አላየሁም አላየሁም #መካነ_ሰማዕት(*፪)
አዳነኝ ስለወደደኝ ለሞትም አሳልፎ አልሰጠኝም ሊቀ ሰማዕት መድኃኒት ሆነኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ (*፪)
https://youtu.be/jc_u64-0pAI?si=IznRGA0diUxeR9BK

Tokkittiidha/አንዲት ናት/ 

Tokkittiidha Manni kiristiyaanaa tokkittiidha (2)
Qooqni, bifti fi sanyiin kan ishee hin qoodne
Kiristoos dhiiga Isaan kan ishee hundeesse
Manni kiristiyaanaa tokkittiidha

Imala gidiraaf nutoo haara miti
Kan kufe hin beeknu hirkatee fannootti
Waaqni qulqullootaa nu wajjin jiraati
Jabaadha amantootaa daandii dhugaarratti (2)

Waa'ee Tawaahidoo amantii abbootii
Dhaga'aa guddanne galmee qabsuuraatti
Har'as dhiyaatullee wareegamummaani
Callisuu hin dandeenyu dhugaan dhiibamnaani (2)

Isheenoo hin banne abiddaan qoramtee
Nutis kana beekna ifatti mul'atte
Godaanuun gubachuun hundumtuu yeroofi
Duuti ulfina keenya yoo ta'e dhugaafi (2)

Midhuudhaaf diigdanis  qulqulluu mana Isaa
Badii osoo hin qabaatiin ajjeestanis saba Isaa
Jiraatii afuurri Isaa Tawaahidoo waliin
Jedhe sagaleen Isaa hin baddu Ortodooksiin
Jedhe sagaleen Isaa hin baddu Tawaahidoon

Qubee biyyaaf boccee seenaa kan tursite
Hambaa kan dhaalchiste kawaala hojjettee
Haadha  afuuraati simattuu keessummaa
Kana hin dagatinaa Ortodooksiin biyyuma
Kana hin dagatinaa Tawaahidoon biyyuma  (2)