ሰንበት ተማሪ ሌላ ሰንበት ተማሪን በመንገድ ሲያገኝ ወይም በአጋጣሚ ሲተዋወቅ የጠፋ የእናቱን ልጅ እንዳገኘ ልቡ በፍቅር ስስት ይቃጠላል፡፡ ኹለት የማይተዋወቁ ሰንበት ተማሪዎች ቢገናኙ ለመግባባት ጊዜ አይወስድባቸውም፤ ልቡናቸው ቀድሞ ይግባባል፡፡ ስማቸውን እንኳን ሳይተዋወቁ ስለ መስቀል ጥናት ፣ ስለ ጥምቀት ፣ስለ ደብረ ታቦር ፣ ስለ ፍልሰታ ፣ ወዘተ… ያወራሉ፡፡ አባባሉስ ቢሆን ‹‹አንድ ዓይነት ላባ ያላቸው ወፎች በአንድነት ይበራሉ - Birds of the same feather fly together›› አይደል የሚለው?
ታክሲ ውስጥ ከጎን የተቀመጠው ሰው ሐመር ወይም መለከት መጽሔትን ከያዘ አለበለዚያም አንድ መንፈሳዊ መጽሐፍን እያነበበ ከኾነ ሰንበት ተማሪ አያስችለውም ‹‹ወንድሜን (እኅቴን) አገኘሁ›› ብሎ ሊያወራ ይቋምጣል፡፡ በክርስቲያናዊ አለባበስ ያሸበረቀችና አካሏን ከመራቆት የሸፈነች ‹እኅቱን› ካየም እንደዚያው፡፡ ሌላው ይቅርና አንገቱ ከክር ያልተራቆተ ሰውን ማግኘት ራሱ እንዴት እንደሚያስደስተው!
ሰንበት ተማሪ ‹ሰንበት ትምህርት ቤት› የተባለች ውድ እናት አለችው፡፡ ብዙ ወንድሞችና እኅቶችን የሰጠችው ይህችው እናቱ ናት፡፡ እርሷ ስትነካበት አይወድም፡፡ ሰንበት ተማሪ ሳይሆኑ ፣ የሰንበት ትምህርት ቤትን ቁስል ሳያውቁ ፣ በችግሯ ሳይቸገሩ ፣ በደስታዋ ሳይፈነጥዙ ፣ ጣዕሟን ሳያጣጥሙ ፣ መዐዛዋን ሳያሸቱ ፣ አካሏን ሳይዳስሱ ፣ ቁመናዋን ሳይመለከቱ እንዲያው በሩቁ ብቻ ገምተው የሚተቿት ሰዎች እጅግ ይገርሙታል።በአንጻሩም የእናቱን ዕድገት የሚሻ ነውና በፍቅር ቀርበው ‹‹ለምን እንዲህ አታደርጉም›› የሚሉትን እጅግ ያከብራል፡፡ ‹‹ምን እናግዝ›› ብለው አብረው ለማገልገል የሚፈቅዱትን እጅግ ይወዳል፡፡
እናቱን ካለ ምክንያት የሚተችና ዕድገቷን የማይፈልግ ከራሱ ወንድሞች እንኳን ቢነሣ ቁጣው ብርቱ ነው፡፡
የሰንበት ተማሪ የዘወትር ጥሪው ‹‹ኑ ኹላችንም በእናት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር አንድ ቤተሰብ እንሁን፤ እናት ሰንበት ትምህርት ቤትንም እንደግፍ›› ነው፡፡
✍ዲያቆን ሕሊና በለጠ

"ወእንዘ ትጸውሙ - ስትጾሙ" ማቴ፮፥፲፮
➥[ከገብርኄር የቀጠለ #ዘኒቆዲሞስ]➥
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
➠ ወእንዘ ንጸውም - ስንጾም አባቶቻችንን በማሰብ [እንደአባቶቻችን] ነው
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
❖ ታላቁ ጾማችን በሃይማኖት ስለመጽናት፣ በቅድስና ስለማደግ፣ በቤተክርስቲያን ስለመኖር፣ ቢወድቁ በንሰሀ ስለመነሳት አስተምሮን እንዳስተማረን ሆነን ጌታን መጠበቅ እንዳለብንና እርሱ ጌታችን ሲመጣ ዋጋን እንደሚከፍለን ከዘወረደ እስከ ገብርኄር ባሉት ሳምንታቱ አስረድቶናል።
"እንደዚህ ሆኖ መኖር እንደምን ይቻላል?" የሚል ካለ በወንጌል የተነገረንን ትምህርት ኖረው በተግባር ያሳዩንን አበው መመልከት እንደሚገባ የዓቢይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት ይጠቁመናል - #ኒቆዲሞስ!
❖ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን እንድንመለከት፣ እነርሱንም እንድንመስል ያስተምረናል
✟ "ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ" ኢሳ ፶፩፥፪
✟ " እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ" ፩ኛ ቆሮ ፲፩፥፩
❖ ቅዱሱ መጽሐፍ "ወሀሎ አሀዱ ብእሲ ... - ... አንድ ሰው ነበረ" እያለ ስለቅዱሳኑ የሚነግረንም እንድናዘክራቸው /እንድናስባቸው/ እና የእምነታቸውን ፍሬ እየተመለከትን በእምነት እንድንመስላቸው ነው [ዕብ፲፫፥፯]
ወንጌልን በተግባር ካሳዩን እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን ቅዱሳን አንዱ ኒቆዲሞስ ነው!
"ወሀሎ አሀዱ ብእሲ...ዘስሙ ኒቆዲሞስ - ...ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ" ዮሐ፫፥፩
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
❖ ኒቆዲሞስ በዓቢይ ጾም ሳምንታት
ኒቆዲሞስ #በዘወረደ - ኒቆዲሞስ በዘወረደ ሃይማኖት ጸንቶ የኖረ ነው። የጸናበትንም ሃይማኖት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ተምሯል ጌታም አምስቱን አዕማደ ምሥጢራት እንደወርቅ አንከብሎ እንደሸማ ጠቅልሎ አስተምሮታል (ዘርዝሮ ለማየት ቦታው አልፈቀደም)
ኒቆዲሞስ #በቅድስት - ኒቆዲሞስ ሊቅ፣ ባለጸጋ፣ ባለሥልጣን ቢሆንም እነዚህ ሁሉ እሾኽ ሆነው ሳያንቁት በትህትና ሆኖ የመምህሩንም ተግሳጽ ታግሶ ተምሯል። አይሁድ ስህተታቸውን ሲገልጥባቸው "መርምር፣ እይ" ሲሉት ታገሳቸው እንጂ ክፉ የሆነ የትዕቢትን መልስ አልመለሰላቸውም [ዮሐ፯፥፶፪]
ትህትና፣ ትዕግስት፣... የመሳሰሉ ዕንቁዎች የተገኙበት ኒቆዲሞስን እየተመለከትን በቅድስት እንኑር
ኒቆዲሞስ #በምኩራብ፦ ኒቆዲሞስ በዘወረደ ሃይማኖት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በገባበት ጸንቶ የኖረ ነው።
ቤተ ክርስቲያን የምዕመናን ህብረት ናትና ኒቆዲሞስን ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር በኅብረት ሆኖ እናገኘዋለን
ዛሬም በሃይማኖት ጸንተው በምግባር አሸብርቀው በአንዲቷ ቤተ ክርስቲያን ያሉ ፤ ዘወትር "ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር ማኅበረ ሥላሴ አንትሙ..." እያልን ከምንማጸንባቸው ቅዱሳን መካከል ነው- ኒቆዲሞስ!
ኒቆዲሞስ #በመጻጉዕ፦ አስቀድሞ በሌሊት መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ ፍርሃት የተባለ በሽታ ነበረበት። በዚህ ህመሙ ግን ተስማምቶ መጻጉዕ እስኪባል አልጠበቀም። እነ ቅ/ጴጥሮስን ሳይቀር ከማስካድ አድርሶ የነበረውን ይህንን ክፉ በሽታ ፍርሀትን ከራሱ አራቀው ነፍሱንም ከመጻጉነት አተረፋት
በዮሐ፫ ፍርሃት አይሎበት የነበረው ኒቆዲሞስ በዮሐ፯፥፶ ተሻሽሎ በዮሐ፲፱፥፴፱ ፍርሀቱን ፍጹም አስወግዶ እናገኘዋለን
ኒቆዲሞስ #በደብረዘይት፦ ኒቆዲሞስ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በተማረው አምኖ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ የተወለደ ነውና የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ ሊገባም ደብረ ዘይትን ይጠብቃል።
ኒቆዲሞስ #በገብርኄር፦ ኒቆዲሞስ ደብረ ዘይት(ዳግም ምጽአት)ን የሚጠብቀው በሀዘንና በጭንቀት አይደለም። እርሱ በጥቂቱ የታመነ ገብርኄር ነውና በብዙ ሊሾም በተስፋ የሚጠብቅ ነው። ኒቆዲሞስ በረከትን የሚሰጥ የህግ መምህር ስለሆነ ከኃይል ወደ ኃይል እየሄደ በጎ አገልግሎትን አገልግሏል። አገልጋዮች በሸሹባት በዚያች በዓርብ ቀን ነፍስ የተለየችው መለኮት የተዋሃደውን የጌታችንን ሥጋ ከመስቀል አውርዶ ገንዞ በመቅበር ያገለገለ በእውነት ታማኝ አገልጋይ- ኒ ቆ ዲ ሞ ስ!
❖ በአርአያ ኒቆዲሞስ ተጉዘን ሆሳዕና እያልን ከህጻናቱ ጋር ለመዘመር ያብቃን። ይቆየን።
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥

ከቅኔ መሀሌት ዘወረደ ወደ ቅድስት የጌታ ጾም(ከቅድስት-ሆሳዕና) ያደረሰን ከቅድስት የጌታ ጾም ወደ መቅደስ ሕማማት ያሸጋገረን ቸሩ አምላካችን
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐነ ለብርሃነ ትንሳኤሁ በሠላም

Forwarded from Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።
#ሥርዐተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት፡፡
#የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች
† #ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅዳስ የተፈጸመበት ሰኞ::
† #ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን::
† #ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን::
† #ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ::
† #ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ::
† #ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡
በሰሙነ ሕማማት የሚባሉትን በአጭሩ ስንቃኛቸው፡፡
(#ለዐርቡ_ጸሎት_እንደ_ዘማች_ስለሚያገለግል) ዐርብ ከምንለቀው የዐርቡ ጸሎት ጋራ አብረን የምንጠቀምበት ስለሆነ በቃል ጭምር አጥኑት፡፡
/ይህን ጽሑድ በአድካሚ ሁኔታ እንደ ንብ ቀስመንና ሰብስበን አዘጋጅተንላችኋል፤ ላልደሰረሰው አዳርሱ፤ ማተሚያ ቤት ያላችሁ አትማችሁ ስጡ፡፡/
፠የሰሙነ ሕማማት ጸሎት የሚደረገው በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት መሠረትነት 7ት ጊዜ ነው፡፡ ለዚሁ አገልግሎት ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ7ቱ ጊዜያት ከፋፍሎ የደረሰው መልክአ ሕማማትም አብሮ በዜማ ይደርሳል፡፡ (መልክአ ሕማማትን ለብቻው አዘጋጅተን ለጥፈንላችኋል)
#የጸሎቱ_አደራረስ_ሥርዐትም ከዚህ እንደሚከተለው ነው፤
፠ደወልና ቃጭል ይመታል፤
፠ጸሎታት(ሙሉ ውዳሴ ማርያምና ዳዊት)ና (የኦሪትና የነቢያት) ምንባባት ይደርሳል፤
፠የተአምር መቅድምና ምንባብ ይነበባል፤ የተአምራት መርገፍ በዜማ ይባላል፡፡
፠የወንጌል አቡን በቅብብሎሽ ይደርሳል፤
፠ምስባክ ይሰበካል ፥ ወንጌል ይነበባል፡፡
#1ኛ_ስግደት፤ ‹‹ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ›› እያለ ቃጭል ሲያሰማ 22ት ጊዜ ‹‹እግዚኦ ተሣሃለነ›› እየተባለ ይሰገዳል፡፡
#2ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለከ ኀይል ክብር ወስብሐት›› የሚለውን በቅብብሎሽ 6ት ፥ 6ት ጊዜ (በድምሩ 12)፤ 7ኛውን በኅብረት እየተሰገደ ይባላል፡፡
#3ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለአምላክ ይደሉ›› የሚለውን 1ኛውን ዙር በቅብሎሽ፤ 2ኛውን ዙር እያስተዛዘሉ፤ ከስግደት ጋራ ይባላል፡፡
#4ኛ_ስግደት፤ ‹‹ክርስቶስ አምላክነ…›› የሚለውን በመሪና ‹‹ንሰብሖ ..›› ወናልዕል ስሞ የሚለውን በቅብብሎሽ ብለው በዚያው ቀጥለው፤ ‹‹ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን›› የሚለውን በመሪ 21 ጊዜ፤ በተመሪ 20 ጊዜ (በድምሩ 41 ጊዜ) እየተሰገደ ይደርሳል፡፡
፠የየሰዓቱን (የሌሊት፣ የነግህ፣ የጠዋት 3 ሰዐት፣ የቀትር/6 ሰዐት/፣ የተሰዐት/9ኝ ሰዐት/፣ የሰርክ /11 ሰዐት/፣ የንዋም) መልክአ ሕማማት በዜማ ይደርሳል፡፡
፠ካህኑ ቡራኬ ሰጥቶ፤ ዲያቆኑ ደግሞ ‹‹ሑር በሰላም›› ብሎ ሕዝቡን ያሰናብታል፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem

#መልክአ_ሕማማት፤ (የ፯ቱ ጊዜያት ጸሎት)
*መልክአ ሕማማት ማለት ስለ ጌታችን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሕማም፥ መከራ፥ ስቃይ፥ የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፤ ደራሲው ታላቁ ሊቅና የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ መምህር #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_ ነው፡፡
*መልክአ ሕማማት በባለ 3ት መስመር አርኬ የተደረሰ ግጥማዊ ድርሰት ሲሆን፤ የተደረሰውም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት አንጻር በመሆኑ ‹‹#ጸሎት_ዘሰባዐቱ_ጊዜያት›› በሚል መጠሪያም ይጠራል፡፡ የእያንዳንዱ ጊዜ ድርሰትም በዋነኛነት 3ት ክፍሎችን የያዘ ነው፤ እነርሱም፤
1ኛ) ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/
2ኛ) ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/
3ኛ) ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/
**በ7ቱ ጊዜያት ጸሎት ማድረስ እንደሚገባን ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 118 ላይ ‹‹ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ ይላል››፤ አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህንኑ ደንግገዋል፡፡ /ዲድስቅልያ 37፣ ቀሌምንጦስ 1ና 7፣ አቡሊዲስ 25ኛና 27ኛ፣ ባስልዮስ 28ኛ አንቀጽ፣ ፍትሐ ነገሥት ገጽ 21/፡፡
፠ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መልክአ ሕማማትን ሲደርስም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት የተፈጸሙትን ድጊቶች ከ3ቱ የየጊዜያቱ የድርሰቱ ክፍሎች ምስጋና (የማርያም፣ የጌታ፣ የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና) ጋር እያመሠጠረና እያራቀቀ፥ እያስዋበና ምሥጢር እያመጣ፤ እንደ ወርቅ እያንከባለለ፥ እንደ ሸማ እየጠቀለለ፥ በግጥም እያስጌጠ፥ በቃላት እየሰደረ፥ በዜማ እያሸበረቀ፥ መንፈስን እየመሰጠ፤ ነው የደረሰው፡፡
#የ7ቱ_የጸሎት_ጊዜያት_የሚባሉትም፤
፠1ኛ) መንፈቀ ሌሊት(ሌሊት 6 ሰዐት)፤ ጌታችን የተወለደበት፥ የተጠመቀበት፥ የተነሣበትና ዳግመኛ የሚመጣበት ፥ … ሰዐት ነው፡፡
፠2ኛ) ነግህ (ማለዳ፥ ጧት)፤ ጨለማን አርቆ ብርሃንን የሚያመጣበት፥ አባታችን ቅዱስ አዳም የተፈጠረበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጲላጦስ አደባባይ ፊት ቁሞ የተመረመረበት፥ …. ሰዐት ነው፡፡
፠3ኛ) ሠለስት (ጠዋት ሦስት ሰዐት)፤ እናታችን ሔዋን የተፈጠረችበት፥ ነቢዩ ዳንኤል ጸሎት ያደረሰበት፥ እመቤታችን ከቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን ሰምታ የጸነሰችበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡
፠4ኛ) ቀትር (6 ሰዐት)፤ አጋንንት የሚሰለጥኑበት ሰዐት ስለሆነ እንዳይሰለጥኑብን፥ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሳተበት ስለሆነ እንዳንስት እንጸልያለን፡፡ በተጨማሪም ነቢዩ ሄኖክ ቤተ መቅደስን ያጠነበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡
፠5ኛ) ተስዓት (ዘጠኝ ሰዐት)፤ ቅዱስ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ የወጡበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው የለየበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡
፠6ኛ) ሠርክ (ዐሥራ አንድ ሰዐት)፤ ነቢዩ ኤልያስ መሥዋዕት የሰዋበት፥ ዕዝራ ጸሎትን ያቀረበበት፥ ሕዝቅያስ ጸልዮ ፀሐይን ወደ ዐሥር ደረጃዎች የመለሰበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ወደ በፈቃዱ ወደ አዲስ መቃብር የወረደበት፥ …… ሰዐት ነው፡፡
፠7ኛ) ንዋም (የመኝታ ሰዐት)፤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጌቴሴማኒ የጸሎትን ሥርዐት ያስተማረበት ፥ እንዲሁም ሌሊቱን በመላእክት ጥበቃ ከርኵሳን አጋንንት እንዲጠብቀን የምንጸለይበት …… ሰዐት ነው፡፡
#ለቡ(ልዩ ማስታወሻ)!! ይህ ታላቅ ጸሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስር ባሉ በሁሉም ገዳማትና አድባራት በሰሙነ ሕማማት የሚደርስ ሲሆን፤ በአንዳንድ ትላልቅ ገዳማት (እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ወደብረ ጎል አቡነ በጸሎተ ሚካኤል) ያሉ መነኰሳትና መናንያን ግን ከዓመት እስከ ዓመት ጸሎቱን በዜማ /በንባብ/ ያደርሱታል፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927