የእውነት መንገድ👣
166 subscribers
33 photos
8 videos
1 file
19 links
✝️ Welcome to Path of Truth! ✝️
Discover the true way, walk in love, and grow closer to Jesus. 🌟
Download Telegram
ለምን አልነገርሽኝም ?


ከሲኦል የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ !

ቤተልሔም ሰፈርዋ ስትደርስ ከምሽቱ 3 ሰአት ሆኖ ነበር፡፡
እጅግ ከምትወዳት ጓደኛዋ ከማኪ ጋ ነበር ያመሹት፡፡
ለሁለት የበሉት ትልቅ ፒዛ በጣም አጥግቧት ስለነበር
ቤትዋ የቀረበላትን ራት ይቅርብኝ ብላ ለምሽት
የምትመርጠውን የካሞሜል ሻይ ጠጥታ በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቷ ገባች፡፡

እንደ ልማዷ አጭር ፀሎት አድርሳ ፣
ፒጃማዋን ለብሳ ለእንቅልፍ ራስዋን አመቻቸች፡፡
የቤቲ እንቅልፍ ሁል ጊዜ ጣፋጭ ነው፡፡ ፀጉሯ ትራስ ከነካ እርሷ የለችም… ወደ ሌላ አለም ትሔዳለች! ደግሞ ህልሞች
ታልማለች…. ለዛውም የ 7Dህልሞች! በህልም የምትቀበላቸው መልዕክቶች መሬት ላይ ጠብ አይሉም፡፡

ሁሉም ሲፈፀሙ አይታለች፡፡ “ዛሬ ህልም አይቼ…” ብላ ከጀመረች ሁሉም ሰው በጉጉት ነው የሚሰማት፡፡
በዚህ ሌሊት ያየችው ህልም ግን እጅግ የተለየ ነው፡፡
አንድ ሰው ደብዳቤ ይዞላት ይመጣል…በህልሟ፡፡ ደብዳቤው
የተፃፈው ከታች
#ከሲኦል ሲሆን #የፃፈችላት ደግሞ አብራት
ያመሸችው ባልንጀራዋ ማኪ ናት፡፡ ደብዳቤው አንዲህ ይነበባል፡፡

“ውድ ጓደኛዬ ቤቲዬ! በድንገት ሳላስበው ዛሬ ሌሊት ወደማላውቀው ስፍራ መጣሁ፡፡
ሲኦል ነው ብለው ነግረውኛል፡፡ የምፅፍልሽ ከዛ ነው፡፡ በጣም የሚያስፈራ፣ የሚያስጨንቅ ቦታ ነው፡፡ በቅጽበት ከመንገድ ወደዚህ
ሲያመጡኝ ለምን ብዬ ጠይቄያለሁ፡፡ የሰጡኝም መልስ
“ከጠላት አላመለጥሽም….የጉብኝትሽን ወራት አላወቅሽም… የተከፈለለልሽን አልተረዳሽም!” የሚል ነው፡፡

😢አንቺ ግን ታውቂ ነበር አይደል? ተረድተሽም ነበር አይደል? ግን ለምን አልነገርሽኝም? ቤቲዬ! አንዳንቺ
የሚቀርበኝ ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም፡፡

ሚስጥረኛዬ አንቺ ነበርሽ! አንድ ቀን እንኳን ሳላገኝሽ ከዋልኩ ቅር ይለኝ... ትናፍቂኝ ነበር፡፡አሁንም በፍቅር ልውቀስሽ ብዬ እንጂ ተጣልቼሽ አይደለም፡፡

ቤቲዬ! ብዙ ቀን ሳውና አብረን ገብተናል… ጃዙኪ ውስጥ ተዝናንተናል፡፡ ስለ ብዙ ነገር አውርተናል… መካሪዬ ነበርሽ! ግን ቤቲዬ ልጠይቅሽ …

ለምን ስለ ክርስቶስ አልነገርሽኝም?
ፀጉራችንን፣ ጥፍራችንን ስንሰራ ሁሌም አጠገብ ላጠገብ
ሆነን ነበር፤ ለብዙ ሰአታት እናወራ ነበር፡፡ አንቺ ግን ታውቂ
ነበር አይደል…? መዳን ከቅድስት ማርያም በተወለደው
በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ? እስቲ አሁን እያነባሁ በፍቅር
ልጠይቅሽ… ቤቲዬ የኔ ቆንጆ… ለምን አልነገርሽኝም?
ምሳ አብረን ስንበላኮ ከ 3 እስከ 4 ሰአታት ይፈጅብን
ነበር፡፡ ስለሔድሽባቸው ከተሞች… ስለ ፓሪስ፣ ስለ ለንደን፣
ስለ ኒውዮርክ፣ ስለ ባንኮክ ስታወሪልኝ አፌን ከፍቼ ነበር
የምሰማሽ፡፡ ግን ቤቲዬ የኔ ጓደኛ… የኔ ማር… በመስቀል
ላይ ስለተሰራው ስራ ለምን አልነገርሽኝም? አያስፈልጋትም
ብለሽ ነው? በየ ጊዜው ከውጪ ስትመጪ ስጦታ
ታመጪልኝ ነበር፡፡ ዛሬ እንኳን ይዤው የነበረው ቦርሳ አንቺ
የሰጠሸኝ ነው… አንገቴ ላይ የነበረውም ሀብል እንዲሁ፡፡
ለእኔ ስጦታ መስጠት ደስታሽ ነበር፡፡ ግን ቤቲዬ! አህቴ!
መጸሐፍ ቅዱስ ለምን አልሰጠሸኝም?አልዋሽም!
መንፈሳዊ ወሬዎች ከሌሎች ጓደኞቻችን ጋ ሆነን ስታወሩ
ሰምቻለሁ፡፡ ስለ ታዋቂ ሰባኪዎች… ስለ ቄሶች ፣ ስለ
ፓስተሮች… ስለመጡላችሁ ትንቢቶች… ስላገኛችኋቸው
በረከቶች ስታወሩ ሰምቼ አውቃለሁ… ግን ለምን ስለ
መድሀኔያለም አልነገራችሁኝም? ለምን ከሞት
እንደሚያድን፣ ከሲኦል እንደሚታደግ አልተረካችሁልኝም?
ቤቲዬ! እሺ እል እኮ ነበር! ብታስረዱኝ እስማማኮ ነበር!
ዛሬ እንደሆነው ሰይጣን ያለ እድሜዬ አይቀጥፈኝም ነበር!
በደሙ እሸፈን ነበራ! መላዕክቱ ይጠብቁኝ ነበራ! አሁንማ
አበቃ! ጊዜው አልፏል አሉኝ… ወደዚህ ስፍራ አመጡኝ፡፡
በጣም ያስፈራል ቤቲዬ… ለማሰረዳት እንኳን ያስቸግራል!
ማንም ወደዚህ እንዲመጣ አልፈልግም፡፡
ጓደኛዬ ማሬ! ቤቲዬ ሚስጥረኛዬ! አንቺኮ ልብስሽን
ሲነኩብሽ አትወጂም ነበር፡፡ እኔ ግን ሌዘር ጃኬትሽን
ስለብስብሽ… ለዛውም ሳላስፈቅድሽ… ስካርፍሽንም
ለብሼ ስወጣ… በነዚያ ትላልቅ አይኖችሽ አየት ታደርጊኝና
ዝም ትይኝ ነበር፡፡ ሽቶሽ ሽቶዬ… ጥፍር ቀለምሽ ጥፍር
ቀለሜ… ሊፕስቲክሽ ሊፕስቲኬ ነበር፡፡ እንቺኮ የልብ
ጓደኛዬ… አሰተማሪዬ ነበርሽ፡፡ ሰለ ዳይት፣ ስለ ቫታሚኖች፣
ስለ ጂም … ያስተማርሽኝ አንቺው ነሽ፡፡

ግን ቤቲዬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን አልነገርሽኝም? በእርሱ ሀጢያትሽ
እንደተሰረየልሽ… የዘላለምን ህይወት እንደወረስሽ ለምን አላወራሸልኝም? ብዙ ቀን
#ሲኒማ ስንሔድ አንድ ቀን እንኳን
#ቤተክርስትያን እንሂድ ለምን አላልሽኝም?

ልቤ አዘነብሽ… ተቀየምኩሽ ጓደኛዬ… ቤቲዬ! ምንም እንኳን ባዝንብሽም
ሁሌም
ጨክኜ አንቺን ማኩረፍ አልችልም… ታውቂ የለ፡፡ መልካም
ህይወት ይሁንልሽ! አምላክሽ ያሰብሽውን ሁሉ ያሳካልሽ!
ሁል ጊዜ እወድሻለሁ! አንዳንድ ቦታ አልነበብ ካለሽ
ቀለሙን ያበላሸው የተንጠባጠበው እንባዬ ነው! ደህና
ሁኚልኝ! አክባሪ እህትሽ… ጓደኛሽ… ሚስጥረኛ ባልንጀራሽ
ማኪ ነኝ… ከታች… ከሲኦል!”

ቤቲ ከእንቅልፏ በታላቅ ድንጋጤ ነቃች፡፡ ህልም ነበር!
በህልሟ ያነበበችው የማኪ ደብዳቤ ግን በጣም አስደንግጧታል፡፡
ፊቷ ላይ ላብ ችፍ ብሏል!
እየተንቀጠቀጠች ስልኳን አንስታ ወደማኪ ደወለች፡፡
ስልኩ ተነሳ … ያነሳችው ግን ማኪ አልነበረችም፡፡ እነ
ማኪ ቤት ለቅሶ ይሰማል… “ጓደኛዬን ማኪን ፈልጌ ነው”
አለቻቸው እየተርበተበተች፡፡ ስልኩን ያነሱት እናትም
በሲቃ…😭 “ አዬ! ማኪንማ የመኪና አደጋ ነጠቀኝ! ጉልበተኛ
ሰይጣን ነጠቀኝ! ለማን አቤት ይባላል?” አሏት፡፡ የቤቲ
ሞባይል ከእጇ ወደቀ…. ማኪን?… የመኪና አደጋ?.....
በህልሟ ያነበበችው የማኪ ጥያቄ ይጮህባት ጀመር….😢😢
ለምን አልነገርሽኝም?… ለምን?… ጓደኛዬ… ቤቲዬ…
እህቴ… ባልንጀራዬ… ማሬ… ለምን አልነገርሽኝም?….

ለምን?..........................

⚠️ይህንን አንብቦ የሆነ ነገር የተሰማው ብቻ
#ለሁሉም ሰው #ሼር_ያድርግ

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄    ⌲   
@Truthofpath
@Truthofpath

♡ ㅤ   ⎙ㅤ    ⌲      🔕         ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
🙏3👏1
የእውነት መንገድ👣
ለምን አልነገርሽኝም ? ከሲኦል የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ ! ቤተልሔም ሰፈርዋ ስትደርስ ከምሽቱ 3 ሰአት ሆኖ ነበር፡፡ እጅግ ከምትወዳት ጓደኛዋ ከማኪ ጋ ነበር ያመሹት፡፡ ለሁለት የበሉት ትልቅ ፒዛ በጣም አጥግቧት ስለነበር ቤትዋ የቀረበላትን ራት ይቅርብኝ ብላ ለምሽት የምትመርጠውን የካሞሜል ሻይ ጠጥታ በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቷ ገባች፡፡ እንደ ልማዷ አጭር ፀሎት አድርሳ ፣ ፒጃማዋን ለብሳ ለእንቅልፍ…
ሁልጊዜ #በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ካልዳኑ #ከጓደኞቻችን ጋር ስንሆን በምናገኘው አጋጣሚ ሁሉ

ስለ
#እየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት : ስለ እኛ #ሀጢአት እና ስለ እኛ #በደል በመስቀል እንደ ሞተ #በሦስተኛውም ቀን እንደተነሳ
#መመስከር እና #መናገር አለብን ደግሞ ወደዚህ ህይወት ተቀላቅለው #ከጨለማ ወደ #ሚደነቅ_ብርሃን እንዲመጡ እና #በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው #የእግዚአብሔር ልጅ መሆን እንደሚችሉ
መመስከር እና መናገር አለብን ። 🥰

⚠️ይህንን_መልዕክት_ለሁሉም_ሰዎች
#ሼር_ማድረግ_እንዳይረሳ🙏🙏

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄    ⌲   
@Truthofpath
@Truthofpath

♡ ㅤ   ⎙ㅤ    ⌲      🔕         ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
🙏2
ያዳነኝ አውቀዋለሁ የሞተልኝ እየሱስ ነው ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታዬ ምስጋና ነው.🙏🙏


መልካም ቀን ይሁንልን ❤️
2
ተመስገን ተመስገን 🙏🙏🙏
ደስ የሚል ጠዋት🥰🥰
🥰
3
የእውነት መንገድ👣
ተመስገን ተመስገን 🙏🙏🙏 ደስ የሚል ጠዋት🥰🥰🥰
ኢሳይያስ 41 (Isaiah)
10፤ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
አጠገቤ ካለው ሰው ይልቅ
እርሱ ለእኔ ቅርብ ነው 🤎
🚨🚨⚠️⚠️⚠️⚠️🆕

📢ውድ የፍቅር ቃል ቤተሰቦቻችን,

እስከ ዛሬ ድረስ አብረን ብዙ ተጉዘናል፣ አብረንም እንደ ቤተሰብ ለ 1 ዓመት ከ 8 ወር በላይ አብረን ቆይተናል።

አሁን ግን አንድ አስፈላጊ ነገር ልነግራችሁ ነው!!

ይህም ከዝህ በፍት የነበረው
#content ከዚህ በኃላ አይቀጥልም🥺 ማለትም በፊት post ስናደርግ የነበረው #content አሁን ተቀይሮ መጥቶኣል......

መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ 14፥6 እንዲህ ይላል፦
“መንገድና እውነትና ሕይወት እኔ ነኝ፤ ከእኔ በስተቀር ወደ አብ የሚመጣ ማንም የለም።”


ይህ ጥቅስ እዉናተኛው ወደ እግዚአብሔር የምወስድ መንገድ የ እዉነት መሰረት እና ዘላለማዊ ህይወት በእርሱ መሆኑንና እኛ እውነተኛ ፍቅር በኢየሱስ ብቻ መገኘቱን ያሳያል፤ እርሱ መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት ነው!!

ስለዚህ አሁን በአዲስ
#content በ አዲስ የእውነትን መንገድ እና ሕይወትን እንከተላለን።

ዓላማው ማህበራዊ ወይም ዓለማዊ ፍቅር ሳይሆን፣ እውነተኛ ፍቅር – የኢየሱስ ፍቅር – ይሆናል።

እኔም ካዝ ባፍት እዉናተኛው ፍቅር እያለ ስለ ዓለም ፍቅር ብዙ ስሳብክ ቆይቻላው አሁን ግን ስለ እዉናተኛው ፍቅርና ማንጋድ እንሳብካለን
አሁንም አብረችሁን እንድትሆኑ በትልቅ ትህትና እጠይቀችኅለዉ....

የእውነት መንገድ (Path of Truth)

🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄    ⌲   
@Truthofpath
@Truthofpath

♡ ㅤ   ⎙ㅤ    ⌲      🔕         ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
የእኔ እህት ፈጣሪን እንጂ ተፈጣሪን
ለማስደሰት አትልበሺ ወዷ እህቴ 🥰

የእውነት መንገድ (Path of Truth)

🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄    ⌲   
@Truthofpath
@Truthofpath

♡ ㅤ   ⎙ㅤ    ⌲      🔕         ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
👍21🙏1
Forwarded from ✝️ᴘʀᴏᴛᴇsᴛᴀɴᴛ ᴡᴏʀsʜɪᴘ ✝️
Ethiopian Gospel Singer ...
Asrat Mulachew
#Cover_by_Asrat_Mulachew original song #Dereje_Kebede

sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ
    ♻️
@protestant_worships
    ♻️
@protestant_worships
2🙏2
#Careless እኮ ሆኜ አይደለም ግን life has
taught me to be calm አሁን እንደ
#እግዚአብሔር_ፈቃድ_ማለት_ተምሬአለሁ

#እግዚአብሔር ከፈቀደ ይሆናል ካልሆነም ይቀራል እሱ የተሻለ ሀሳብ አለዉ that's it 🤍

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄    ⌲   
@Truthofpath
@Truthofpath

♡ ㅤ   ⎙ㅤ    ⌲      🔕         ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
1👍1
እስቲ ሰላም ላሳደረን ፈጣሪያችን እናመስግን 🙏
..... ምክንያቱም ከነቁት መሀል ስላደረገን
🥰🙏🙏

𝓷𝓪𝓽𝓾
.......🫶
2
ሕይወት ምርጫ ናት‼️

"....... በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

‎ ዕብ 7:25 (AMH)
1👍1
ስሚኝማ የኔ ቆንጆ😊

ብዙ የዘገዩ የምመስሉ ፀሎቶች የተረሱ የምመስሉ እምባዎች ልኖሩሽ ይችላሉ ግን በዚህ ማለዳ አንድ ነገር ልንገርሽ ይህ ልብሽን ይደግፈዋል የኔን እንደደገፈው ሁላ ማለት ነዉ ፀሎቶችሽ እምባሽ ዋጋ አለዉ እንድሁ አልባከነም🥹


ሰው የፀለየውን ይረሳ ይሆናል፤
እግዚአብሔር ግን የሰማውን አይረሳም🙇
Amen🙏
🙏3
በቃ እራሳችንን እንሁን ምንም አይጎልብንም🥹
🤝2👍1
አቁሙ 😠

አቅማቹንና ነጋቹን እንደ ቀልድ እየበሉባቹ ካሉ ነገሮች
#ለምን ራሳቹን አታድኑም ? ቁም ነገር በሌለው ሳቅና ቀልድ በየቀኑ በየ social mediaw #ውድ_ጊዜያቹን እንዲሁ ማባከን ኪሳራ እንጂ ትርፍ ያለው አይመስለኝም....

በዚህ እንኳን ቀልዳቹበት ሰርታቹበት እንኳን መለወጥ በማይቻልበት ጊዜ አጉል ስንፍና ውስጥ መቆየታቹን አቁሙ ።

#Social_media ላይ ማፍጠጥ አቁሙ... #ላለመፀለይ ምክንያት መደርደራቹን አቁሙ.... ለውጣቹ ላይ ሙድ ከሚይዙ ጓደኞቻቹ ጋር ያላቹን ህብረት አቁሙ በቃ በህይወታቹ ላይ ወስኑ ትኩረታቹን ከሰዎች አስተሳሰብና ውሎ ላይ አንስታቹ ራሳቹ ላይ ማድረግ ጀመሩ፤ ጌታ እንጂ ጊዜ ምህረት አያቅም በጊዜያቹ ተጠቀሙ።

https://t.me/Truthofpath
👍42
ምን ይሻለናል ?

በተለይ አሁን ላይ ይሄን #አይምሯችንን #አጫጭር ነገር አስለምደነው  #ረጅም ነገር ላይ ትኩረት ሰጥቶ መቆየት እየከበደው ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ምን ያህል እየተጎዳን እንደሆነ የገባኝ የሁለት ደቂቃ #video እንኳን አላልቅ ብሎን በ 2× ማየት ስንጀምር ነው 😁

እኔ እንኳን አንዳንዴ ለእናንተ ይጠቅማቿል ብዬ ለማዘጋጀት የምሞክረው #መልዕክት  ሳላውቀው ይረዝምብኝና ተወዋለሁ ለምን አትሉኝም ? #ርዕሱን_ብቻ አንብበው ይተውት ይሆን በሚል 🥰 አሁን እንኳን ይህ #text ረዝሞበት ያልጨረሰው ይኖራል እኮ 😁😁 እስቲ ያነበባቹ #react አድርጉ.... ተው ወገን ወደ ቀድሞ መረጋጋታችን እንመለስ !

https://t.me/Truthofpath
👍41
እኛ ካየናቸውም ካላየናቸውም ክፉ ነገሮች ሁሉ የጠበቀን ያሻገረን እግዚአብሔር ይመስገን🙏

እስከዚች ቀን ያደረሰን ምህረቱን ያላራቀብን እግዚአብሔር ይመስገን 🙏 ስለሆነውም ስላልሆነውም እግዚአብሔር ይመስገን🙏

🥰እግዚአብሔር ይመስገን🥰

🥰እግዚአብሔር ይመስገን🥰

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄    ⌲   
@Truthofpath
@Truthofpath

♡ ㅤ   ⎙ㅤ    ⌲      🔕         ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
2
📣#በቤተክርስቲያን ውስጥ መደረግ የሌለባቸው #11 ወርቃማ ህጎች

ቤተክርስቲያን
#የእግዚአብሔር_ቅዱስ_ስፍራ_ነው፣ በቤቱ ስርአትና አክብሮት ሊኖር ይገባል!

1.
#ፕሮግራም_አታርፍድ እግዚአብሔር ለቀጠሮው አይዘገይም፤ አንተስ ለምን ታረፍዳለህ? በጊዜ መገኘት በረከትን ቀድሞ መቋደስ ነው። 📖 "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ" (መዝሙር 122:1)

2.
#ድምፅህን_ጠብቅ፤ አታውራ 🗣️ በአምልኮና በትምህርት ሰዓት ወሬና ጨዋታ ለእግዚአብሔር ቤት አይመጥንም። ስፍራው የዝምታና የጸሎት ነው። 📖 "ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌሶን 4:29)

3.
#ስልክህን_እረፍት_ስጠው 📱 በስብከት ወቅት ሶሻል ሚዲያ መጠቀምና ስልክ መነካካት መንፈሳዊ ትኩረትን ይሰርቃል። ስልክህ ሲደወልም አንስተህ አታውራ፤ ቅዱሱን ድባብ አታናጋ። 📖 "በላይ ያለውን አስቡ" (ቆላስይስ 3:2)

4.
#አለባበስህ_ስርአት_ይኑረው 👗 ሰውነትን ገልጦ የሚያሳይና#ሌሎችን _ለፈተና የሚዳርግ አለባበስ ከቤተክርስቲያን ቅድስና ጋር አይሄድም። ይህ ወንዶችንም ይመለከታል።

📖 "ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን" (1 ቆሮንቶስ 14:40)

5.
#አትተኛ፤ ንቃ! 😴 ቤተክርስቲያን የመንፈስ መታደሻ እንጂ መኝታ ቤት አይደለችም። ንቁ ሆነህ ቃሉን ተከታተል። 📖 "አንተ የምትተኛ ንቃ..." (ኤፌሶን 5:14)

6.
#ተመልካች_ብቻ_አትሁን፤ በመንፈስ ተሳተፍ 👀🔥 ሌሎች ሲያመልኩና በረከት ሲቀበሉ አንተ ዝም ብለህ አትመልከት። ዘምር፣ አምልክ፣ ስገድ፤ በመንፈስና በእውነት ከፈጣሪህ ጋር ተገናኝ። 📖 "እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።" (ዮሐንስ 4:24)

7.
#ቂም_ይዘህ_አትቆም_ቂም_ይዘህ አትጸልይ! ልብህ በቂምና በነገር ተሞልቶ አምልኮ የለም። አስቀድመህ ለበደሉህ ይቅርታ አድርግ፤ በንጹህ ልብም ፊትህ ቁም። 📖 "አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ" (ማቴዎስ 5:24)

8.
#ተስፋ ሰንቀህ ቅረብ ከእግዚአብሔር እጅ አንድ ነገር እንደምትቀበል አምነህ ሂድ። የምትጠብቀው ነገር ከሌለ የምታገኘውም አይኖርም። 📖 "አፍህን በሰፊው ክፈት እኔም እሞላዋለሁ" (መዝሙር 81:10)

9.
#አገልጋዮችን
_አታቅልል 🙅‍♂️
ከአገልጋዮች ጋር ባለህ መቀራረብ የተነሳ ቅጥ የሌለው ድፍረት አታሳይ። የእግዚአብሔርን ቅቡዓን ማክበር ለራስህ ስኬት መቆለፊያ ነው። 📖 "የቀባሁትን አትንካ" (መዝሙር 105:15)

10.# ለዲያቆናትና ለአገልጋዮች ታዘዝ 🙏 ዲያቆናት የሚተጉት ስርአትን ለማስጠበቅና አንተን ለማገልገል ነው። ትህትናንና ትብብርን አሳያቸው። 📖 "ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ..." (1ኛ ጴጥሮስ 2:17)

11.
#ፕሮግራም ሳያልቅ አትውጣ በጸሎትና በስብከት መሃል ጥሎ መውጣት ስርአተ አልበኝነትና ሌላውን መረበሽ ነው። እስከ መጨረሻው ታግሰህ በረከቱን ይዘህ ውጣ።

📖 "ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ" (መክብብ 5:1)

sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ
    ♻️
@Truthofpath
    ♻️
@Truthofpath
2🙏2👍1
Forwarded from ✝️ᴘʀᴏᴛᴇsᴛᴀɴᴛ ᴡᴏʀsʜɪᴘ ✝️
ዝም ይበል ሁሉ Zim Yibel
illasha fekadu
(#illasha_Fekadu)

sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ
    ♻️
@protestant_worships
    ♻️
@protestant_worships
2🥰1
እንችላለን !

#ለራሳችን የምንነግረው ነገር #ህይወታችንን ሊያስተካክለውም ሊያበላሸውም ይችላል።

#በህይወት ውስጥ ከባድ ነገር ቢገጥመን እንኳን በተቻለን አቅም ለራሳችን እንደማንችል መንገር የለብንም ምክንያቱም እያንዳንዱ #የምናወጣው_ቃል ለጆሮአችን ቅርብ ነው።

🎉ጣፋጭ ምሽት ተመኘን🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊


sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ
    ♻️
@Truthofpath
    ♻️
@Truthofpath
4💯1