#መድኃኒት_ተወልዶልናል
ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና #አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ #ተወልዶላችኋልና።
🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮችና የDawurootsuwa Gospel Tube ቤተስቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
#መልካም_በዓል_ይሁንላችሁ
እየሱስ ተወልዶልናል እያልን እስቲ COMMENT ላይ እንጽፋለን፤ በ LIKE ደስታችሁንም ግለጹልን ❤🥰
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ🥳
🎄4
Forwarded from 🎸Frenymusic🎸
ሕፃኑ መድኅን!
ዓለም ከፍ ባለ ድቅድቅ ጨለማ ተሞልታ ነበር፤ ሁሉ ነገር ዝምጭጭ ብሏል። ከአራት መቶ በላይ ለሚሆኑ አመታት ከዚህቀደም የተለመዱት ድምፆች ሁሉ ቆመዋል። ከሰማይ ክፉምመልካምም መልእክት ተሰምቶ አያውቅም። ብቻ ሁሉእንዳመጣለት፣ እንደመሰለው ይመላለስ ነበር። መንፈሳዊሥርዓቶችም ቢሆኑ እንዲያው ለወጉ ልማዱን ተከትሎይከወናሉ እንጂ፣ ይህ ነው የሚባል መንፈሳዊ እርካታአልነበረም።
በዚህ መካከል ተስፋ ቢስነት፣ የደኅንነት ምሥራች እጦት፣ የመንፈሳዊ ዓለም ዳፈና በሁሉ ስፍራ ገንኖ ነበር። ሌላኛውመደበኛ ሕይወት ግን እንዳለ ቀጥሏል። በዚህ መሐል ታዲያ፣ምድር በታሪክ የማይደገም አንድ ድንቅ ክስተት አስተናገደች።
በአንዱ ስፍራ እረኞች በሌሊት መንጋቸውን እየጠበቁ ነበር። በብርሃን የተንቆጠቆጠ መልአክም ድንገት በመሐከላቸውተገለጠ። ነገሩ ያልተለመደ እና አስፈሪ ስለነበር፤ በታላቅ ፍርሀትተሞሉ።
ክስተቱ ለምድር ብቻ ሳይሆን ለሰማይ ሰራዊቶች ሁሉ የደስታምክንያት ነበር፤ በመሆኑም ለሰዎች በሆነው በዚህ ምሥራች፣በሕፃኑ መድኅን ሰበብ ታላቅ ዝማሬ ሆነ።
ሕፃኑ መድኅን የዓለሙ አዳኝ ሆኖ ከተገለጠ እንኾ ሁለት ሺህአመት አለፈ። የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ለዓለም ተስፋ የኾነውእውነተኛው ብርሃን ዛሬም በትኩስ ጉልበት ያድናል። ዛሬምይኽ የምሥራች ትኩስ ነው። ዛሬም ተስፋ ላጡ፣ በማን ያድነናልጭንቅ ውስጥ ላሉ፣ በድቅድቅ ጨለማ ለተዋጡ የዛሬ ሁለትሺህ አመት የተወለደው ክርስቶስ ጌታ እውነተኛ ተስፋ፣ ብቸኛአዳኝ፣ የማይደበዝዝ ብርሃን ነው። ወደ እርሱ የሚመጡትንፈጽሞ ያድናቸዋል። ዛሬም ወደእዚህ እውነተኛና ብቸኛ ተስፋኑ ብለን ጥሪ እናስተላልፋለን!!
#ደስታ_ለዓለም #tesfa #hope

🥰2
ደስታ ለዓለም - Freny Music
Freny music
MERRY CHRISTMAS😊🎄🎄
Share with your families and friends🎄🎄
💒sʜᴀʀᴇ 🔔ᴊᴏɪɴ 🔔
👇👇 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇
Channel:@Freny_music🍀🍀
@Freny_music🍀🍀
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️
ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
Share with your families and friends🎄🎄
💒sʜᴀʀᴇ 🔔ᴊᴏɪɴ 🔔
👇👇 🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇
Channel:@Freny_music🍀🍀
@Freny_music🍀🍀
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️
ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
🎄3❤2
የአለሙ ቤዛ
ቀድሞ በነብያት ፣ለህዝቡ እንደማለ
እቤዣችኅለዉ ፣አይዟችሁ እንዳለ
እንደተናገረው ፣እንደተስፈ ቃሉ
ቤዛችን ተወልዷል ፣ሃሌሉያ በሉ
እሰይ የምስራች ፣ሆነልን ደስታ
በጨለማ ስኖር ፣ሆነን የሞት ሽታ
በደዌ ተይዘን ፣በኀጢአት በሽታ
በዲያብሎስ ቀንበር ለምንንገላታ
መዳኒት መቷል ፣ መድሃኒአለም ጌታ
መልካም በአል 🎄🎄🎄
ቀድሞ በነብያት ፣ለህዝቡ እንደማለ
እቤዣችኅለዉ ፣አይዟችሁ እንዳለ
እንደተናገረው ፣እንደተስፈ ቃሉ
ቤዛችን ተወልዷል ፣ሃሌሉያ በሉ
እሰይ የምስራች ፣ሆነልን ደስታ
በጨለማ ስኖር ፣ሆነን የሞት ሽታ
በደዌ ተይዘን ፣በኀጢአት በሽታ
በዲያብሎስ ቀንበር ለምንንገላታ
መዳኒት መቷል ፣ መድሃኒአለም ጌታ
መልካም በአል 🎄🎄🎄
❤4
አንዳንዶች የሚያውቁት የሽቶውን ዋጋ ነው፤ ማርያም የምታውቀው የኢየሱስን ዋጋ ነው፤ ውድ የምትሉት ነገር አላቹህ ሰብራቹህ አፍስሱለት🙇።
❤3
❤3
እምነት ቢሞላ ዕውቀት ቢከበኝ
ልሳን መናገር ትንቢት ቢኖረኝ
ሥጋዬን ለእሳት ብሰጥ ፈቅጄ
ባልነፍግ ለድሆች ያለኝን ከእጄ
ፍቅር የሌለው እልፍ ደግነት
ጌታ የሌለበት መንፈሳዊነት
ወዴት ወዴት ነው ይህ ከንቱ ጉዞ
በሃሜት ታዝሎ በቂም ተይዞ
ዞሮ ለማን ነው ይህ ጥል ግርግር
አቤል ከቃየል የማይሆን አጥር
ጐራ ለይቶ ይቅር ማድሩ
የእውነት ፍቅር ይግባ መንደሩ
የባላንጣችን ደስታው ይደፍርስ
በፍቅር ዘምተን ሰላም እንመለስ
የቁርሾን ዘመን ይበቃ ብለነው
መዘናጠሉ ነው ወዲያ እንጣለው
ፍቅር ይበቀለው
ልሳን መናገር ትንቢት ቢኖረኝ
ሥጋዬን ለእሳት ብሰጥ ፈቅጄ
ባልነፍግ ለድሆች ያለኝን ከእጄ
ፍቅር የሌለው እልፍ ደግነት
ጌታ የሌለበት መንፈሳዊነት
ወዴት ወዴት ነው ይህ ከንቱ ጉዞ
በሃሜት ታዝሎ በቂም ተይዞ
ዞሮ ለማን ነው ይህ ጥል ግርግር
አቤል ከቃየል የማይሆን አጥር
ጐራ ለይቶ ይቅር ማድሩ
የእውነት ፍቅር ይግባ መንደሩ
የባላንጣችን ደስታው ይደፍርስ
በፍቅር ዘምተን ሰላም እንመለስ
የቁርሾን ዘመን ይበቃ ብለነው
መዘናጠሉ ነው ወዲያ እንጣለው
ፍቅር ይበቀለው
H̶a̶n̶n̶a̶ T̶e̶k̶l̶e̶
❤4
“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
❤3
#ቅጠሉን_ሳይሆን_ስሩን_አጠጡ
አንድ ሰው በቤቱ አቅራቢያ ብዙ ቅጠሎች ያሉት እጅግ ያማረ በየዕለቱ ይንከባከበው የነበረ አንድ ዛፍ ነበረው።ጠዋት እና ማታም ወደ ዛፉ ጥላ እየሄደ ጥሩ ጊዜ ያሳልፍ ነበር።ከዕለታት አንድ ቀን ግን ይህንን ዛፍ አሻቅቦ ሲመለከተው አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን በማየቱ እጅጉን ሃዘን ገባው።
ምንም እንኳን ዛፉ ላይ ለመውጣት አስቸጋሪ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ ላይ እየተሰቀለ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው።ተመልሰው ነፍስ ይዘሩ ይሆናል በማለት ሽቅብ ወደ ላይ በመንጠልጠል ቅጠሎቹን እየወለወለ ውሃ ያርከፈክፍባቸው ነበር...ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆይቶ፤ የተቻለውን ሁሉ ቢያደርግም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመጠውለግ እና ከመድረቅ አልዳኑም። በመጨረሻም ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመ፤የደረቁት የዛፉ ቅጠሎችም ሙሉ በሙሉ መርገፍ ጀመሩ።
ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ሥር ውሃ እንደማጠጣት የጠወለጉት ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን ሙሉ በሙሉ ገደለው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ሥሩን ውሃ ቢያጠጣው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎቹም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር።
በሕይወታችን የማንፈልጋቸው ነገሮች ዕለት በዕለት በማህበራዊ ኑሮአችን ከሰዎች ጋር አላግባባ ያሉን መጥፎ ባህሪያት ለመቅረፍ የሚያቅተን ትኩረታችን ሁሉ ከሥር ከመሰረቱ ሳይሆን ከላይ በሚታየው ማንነታችን ለማሸነፍ ስለምንጣጣር ነው።ለመለወጥ እንወስንና ልባችንን ሳናጠራ፣ውስጣችንን ለእድሳት ሳናዘጋጅ ከላይ ያለውን ማነንነታችንን ለመቀየር እንጋጋጣለን።
ስለዚህ ከላይ ባለው ማንነታችን ላይ ጊዜአችንን ከምናጠፋ የውስጥ ማንነታችንን ለመለወጥ እንዘጋጅ ፊታችንን ሳይሆን ልባችንን ለማጥራት እንወስን።
መልካሙን ተመኘሁ!!!

እድለኛ ሴት ማለት ቆንጆ ወንድ ያገባች ሳትሆን
#ወደ_እግዚአብሔር የሚያስጠጋትን ያገባች ነች
እህቴ ልመርቅሽ🖐🏼
#If_you_are_Christian_girl ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን እንደወደደ የሚወድሽን ባል ይስጥሽ🙌

ከጌታ ጋር
መኖር አይደለም
መሞት ያመጣል
ከኢየሱስ
ጓደኛ አይበልጥም
ከኢየሱስ
አብሮ አደግ አይበልጥም
ከኢየሱስ አብሮ
የኖረ ሰው አይበልጥም
ኢየሱስ
ከምንም ይበልጣል 🙏
መኖር አይደለም
መሞት ያመጣል
ከኢየሱስ
ጓደኛ አይበልጥም
ከኢየሱስ
አብሮ አደግ አይበልጥም
ከኢየሱስ አብሮ
የኖረ ሰው አይበልጥም
ኢየሱስ
ከምንም ይበልጣል 🙏
🙏3❤1
9፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ ረድኤታቸውና መታመኛቸው እርሱ ነው።
10፤ የአሮን ቤት ሆይ፥ በእግዚአብሔር ታመኑ ረድኤታቸውና መታመኛቸው እርሱ ነው።
11፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ ረድኤታቸውና መታመኛቸው እርሱ ነው። መዝ 115
በእግዚአብሔር ተመኑ ❤️

❤2
#መሠረታዊ_የክርስትና_ትምህርት
(ክፍል 1)
ምዕራፍ አንድ - መጽሐፍ ቅዱስ
ትምህርት 1 – የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥ
« ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና» (1ተሰ 1፡5)
➢ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለበት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ መለኮታዊ ሥልጣንና ኃይል ያለው መጽሐፍ ነው (2ጢሞ 1:19-21)
➢ መጽሐፍ ቅዱስን ከ40 በላይ የሚሆኑ ጸሐፊዎች በመንፈስ ቅዱስ በመመራት የጻፉት ሲሆን 66ቱ መጻሕፍት ተጽፎ የተጠናቀቁበት ዘመን በአጠቃላይ ሲታይ 1500 ዓመታትን ፈጅቶበታል፡፡
➢ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ1400 እስከ 400 ዓ.ዓ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ሲሆን አዲስ ኪዳን ደግሞ ከ45 እስከ 100 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ነው፡፡
➢ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ነገሥታት፣ ካህናት፣ ገበሬዎች፣ ነቢያት፣ ምሑራን፣ ዓሣ አጥማጆች፣ ግብር ሰብሳቢዎች፣ ሐኪሞች ወዘተ... ሲሆኑ ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
➢ ጥንት ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት ከተክሎችና ከእንስሳት ቆዳ በተሠሩ /ፓፒረስና ብራና/ ጥቅልል ላይ ሲሆን በ1456 ዓ.ም ጆሐን ጎትን በርግ በተባለ በአንድ ጀርመናዊ ሰው ለዚህ ሥራ ተብሎ የጽሕፈት ማተሚያ መሣሪያ ከተፈለሰፈበት ጊዜ ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስ በወረቀት ታትሞ መውጣት ጀመረ፡፡ /2ጢሞ 4:17-20: 2ጢሞ 4:13/
➢ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎችንና ቁጥሮችን በመለየት ያዘጋጀው እንግሊዛዊ ጳጳስ ስቲፈን ላንግተን በ13ኛው ምዕተ ዓመት ነበር፡፡
➢ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ግዕዝ ቋንቋ መተርጎም የተጀመረው በ4ኛው ምዕተ ዓመት ሲሆን የተጠናቀቀውም በ7ኛው ምዕተ ዓመት ነው፡፡
➢ መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ለመጀመሪያ ጊዜ የተተረጎመው አብርሃም /አባ ሮሜ / በ19ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡
➢ አዲስ ኪዳን በአማርኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ የወጣው በ1829 ዓ.ም ሲሆን ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ በ1840 ዓ.ም ታተመ፡፡
➢ እስከ ዛሬ 2017 ዓ.ም ድረስ አዲስ ኪዳን በ3756 የዓለም ቋንቋዎች የተተረጎመ ሲሆን ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ በ1726 የዓለም ቋንቋዎች መተርጎሙን የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ፡፡
➢ «ካኖን» /Canon /:- የመጻሕፍት መመዘኛ ወይም መለኪያ ነው። ቃሉ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ መለኪያ ወይም መስፈሪያ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አንድ መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል ወይም የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ በካኖን መመዘኛ ማለፍ አለበት።
እነዚህም መለኪያዎች (መመዘኛዎች)፡-
የጸሐፊውን ሥልጣን ማወቅ – አንድ መጽሐፍ ከሐዋርያት በአንዱ ወይም ከሐዋርያት ጋር በቆየው አገልጋይ እጅ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
የመጽሐፉ ሐሳብ ከፍተኛ መንፈሳዊ ምስጢር ያለው ሆኖ የብሉይና የአዲስ ኪዳን ትምህርት ግንኙነት ሊኖረው ይገባል፡፡
መጽሐፉ በአብዛኛው አብያተክርስቲያናት ተቀባይነት ሊያገኝ ይገባል፡፡
መጽሐፉ በግልፅነት የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
በዚህ መሠረት፣
❖ በካኖናዊነት የተመዘኑና ተቀባይነት ያገኙ 39 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በ5ኛ መቶ ዓ.ዓ (በዕዝራ የተሰበሰቡና የተቀናበሩ መሆናቸውን ብዙ የታሪክ ጸሐፊዎች ያምናሉ፡፡
❖ 27ቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ዝርዝር በካኖን መመዘኛ ያዘጋጀው በ397 ዓ.ም በካርታጎ /cartago / የተሰየመው የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ጉባኤ ነው፡፡
1.2 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አመዳደብ
መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ 66 መጻሕፍትን የያዘ ሲሆን ብሉይኪዳንና አዲስ ኪዳን በመባል በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይክፈላል
ሀ/ የብሉይ ኪዳን 39 መጻሕፍት
የሕግ/የኦሪት/ መጻሕፍት...........................5
ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም
የታሪክመጻሕፍት................................12
ከኢያሱ እስከ መጻሕፍት አስቴር
የግጥምየቅኔ/መጻሕፍት...........................5
ከኢዮብ እስከ መኃልየ መኃልይ
የትንቢትመጻሕፍት...............................17
ለ/ የአዲስ ኪዳን 27 መጻሕፍት
❖ ወንጌላት...........................................4
ከማቴዎስ እስክ ዮሐንስ ወንጌል
❖ ታሪክ............................................--1
የሐዋርያት ሥራ
❖ መልዕክቶች.......................................21
ከሮሜ እስከ ይሁዳ መልዕክት
❖ የትንቢትመጽሐፍ………………… 1
የዮሐንስ ራዕይ
ሐ/ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ጥቂቶቹ፡-
ሙሴ /እረኛ ወይም የሕዝብ መሪ / ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም
ኢያሱ /የጦር መሪ/ – መጽሐፈ ኢያሱ
ሰለሞን /ንጉሥ/ -መጽሐፈ ምሳሌ መክበብ መኃልየ
ዳንኤል /ጠቅላይ ሚኒስቴር/ – ትንቢተ ዳንኤል
ኤርምያስ /ነቢይ/ – 1ኛ እና 2ኛ ነገሥት
ዕዝራ /መሪ / - መጽሐፈ ዕዝራና ነህምያ 1ዜና
ሳሙኤል /ነቢይ/ – መሳፍንትና ሩት
ኢሳይያስ / ነቢይ / – ትንቢተ ኢሳይያስ
ማቴዎስ /ቀራጩ / – የማቴዎስ ወንጌል
ሉቃስ /ሐኪም/ – የሉቃስ ወንጌልና ሐዋርያት ሥራ
ጳውሎስ /ምሑር/ – 14ቱ የጳውሎስ መልዕክቶች
ጴጥሮስ /ዓሣ አጥማጅ/ – የጴጥሮስ መልዕክቶች
ዮሐንስ /ዓሣ አጥማጅ/ – ዮሐንስ ወንጌል፣ ዮሐንስ መልዕክቶችንና
ዮሐንስ ራዕይ
መ/ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠራባቸው ስሞች:-
የእግዚአብሔር ቃል ሐዋ 13:48 ዘዳ 28:1 ኤር 42:6
የጌታ ቃል ሐዋ 13:49 2ተሰ 3:7
የሕይወት ቃል ፊል 2፡16 ዮሐ 1፡1
የእውነት ቃል ኤፈ 1፡13
የምሥራቹ ቃል ሮሜ 10:14-16 ኢሳ 61፡1
የመስቀሉ ቃል 1ቆሮ 1:18
የሕግ ቃል ወይም የሕግ መጽሐፍ ዘዳ 28:58 ኢያ 1:8
ቅዱሳን መጽሕፍት 2ጢሞ 3:15
የክርስቶስ ወነንጌል ሮሜ 1:9 2ቆሮ 4:3-4
የትንቢት ቃል ራዕ 1:3 2ጰጥ 1፡19
የጸጋው ቃል - ሐዋ 20:32
1.3 የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን
መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለሰዎች ያዘጋጀውን ዘላለማዊ የመዳን ዕቅዱን ይናገራል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ባሕርይም በቀጥተኛ መገለጥ ከእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት /አነሳሽነት/ በቅዱሳን ሰዎች መጻፉ ነው፡፡
/2ጴጥ 1:19-21 2ሳሙ 23:2)
ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በሚከተሉት ነጥቦች እንመለከታለን
« ከእኛ የሰማችሁትን የእግዚአብሔርን ቃል በተቀበላችሁ ጊዜ በእናንተ በምታምኑት ዘንድ በእርግጥ እንደሚሠራ እንደእግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ እናመሰግናለን»
1ተሰ 2፥13
👉ማንም ለገዛ ፈቃዱ ሊተረጉም ሊቀነስና ሊጨምር አይችልም፡፡ /2ጴጥ 1፥20-21 ራዕ 22፥18-19 ዕብ 4፥2 ዕብ 12፥32 መዝ 30፥5-6/
👉የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለበት ነው /2ጢሞ 3፥17/
👉የሕይወትና የእምነት ብቸኛ መመሪያ ነው /መዝ 119፥9-11፤105/
👉የማይለወጥ፣ የማይሻርና የማይደክም ፍጹም የሆነ እርስ በርሱ የማይጋጭ ነው፡፡ /ሉቃ 16፥17 ማቴ 24፥35/
👉በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚሰጡ የፀጋ ስጦታዎችን ሁሉ ይፈትናል፡፡ ቃሉን ሊተካ የሚችል መገለጥም ሆነ ስጦታ የለም፡፡/1ተሰ 5፥19-21/
👉ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረና ያፀና ደግፎም የያዘ ነው፡፡ /ዕብ1፥3 ቆላ 1፥3፤ 2ጴጥ 1፥2-21/
👉የመሥራት ሥልጣን አለው/ኢሳ 45፥23 55፥11 ኤር 23፥29፤ዕብ 4፥12/
👉የመንቀልና የመትከል ሥልጣን አለው /ኤር 1፥9-10/

❤3👍1
ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ.pdf
1.6 MB
@sʜᴀʀᴇ 🔔ᴊᴏɪɴ 🔔
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ ✓ Channel:@PathOfTruthHope
@PathOfTruthHope
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️
ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ ✓ Channel:@PathOfTruthHope
@PathOfTruthHope
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️
ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
👍3💯1
ለልብ ይናገራል ፣
እኔም ለልቡ አወራለሁ ፣
በመገኘቱ ሁልጊዜ እደሰታለሁ ፣
እርሱ ይስቃል ፣
እኔም አብሬው እስቃለሁ ፣
ዉዴ ይወደኛል ፣
እኔም ውዴን እወደዋለሁ ።
GOOD NIGHT MESSAGE ❤️
❤2👏1
ፍቅራችሁን check አድርጉ፤ ቅዱሱ መፅሀፍ ሲናገር ፍቅር የማይገባ ነገርን አያደርግም ይላል፤ በዚህ ዘመን የአንዳንዶች ፍቅር በስሜት፤ በጥቅም ላይ ይመሰረታል፤ አስተውሉ ወደድኳችሁ የሚል ሁሉ ላይወዳችሁም ይችላል፤ እዛው ቅዱሱ መፅሃፍ ላይ የአምኖን እና የትዕማርን ታሪክ እናገኛለ፤ አምኖን ትዕማርን እስኪታመም እስኪጨነቅ ሰውነቱም እየከሳ እስከሚሄድ ድረስ አፈቀራት ይላል፤ ነገር ግን ይሄ ፍቅር የተመሰረተው በስሜት ላይ ነበር፤ አምኖን የታመመ በማስመሰል ትዕማርን እንድታስታምመው በማድረግ ማንም በሌለበት አስገድዶ ደፈራት🥺፤ ከዛም በኋላ ፍቅሩ ወጣለት ቃሉ እንዲያውም በፊት ካፈቀራት አስበልጦ ጠላት ይላል፤ በስተመጨረሻም የእሷን እጣ ፈንታ አበላሸ፤ እርሱም በዚህ ስራው ተገደለ።
ሁሌም ይሄን እስታውሱ ፍቅር በማንም ላይ የማይገባ ነገርን አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅራችሁን መርምሩ፤ ፍቅር ያከብራል እንጂ አያዋርድም፤ ፍቅር ይጠነቀቃል እንጂ አያጠቃም፤ ፀጋ ይብዛላችሁ🙌።
🇯🇴🇮🇳🙏

Telegram
የእውነት መንገድ👣
✝️ Welcome to Path of Truth! ✝️
Discover the true way, walk in love, and grow closer to Jesus. 🌟

🙏2❤1👍1