የእውነት መንገድ👣
165 subscribers
33 photos
8 videos
1 file
19 links
✝️ Welcome to Path of Truth! ✝️
Discover the true way, walk in love, and grow closer to Jesus. 🌟
Download Telegram
ምስጋና አያኖርህ የፍጥረታት ቅኔ
ማንም ሳይፈጠር ኖረህ ነበር ያኔ
ፍጡር ያምልክህ እንጂ ለሕይወቱ ብሎ
የማንም ውዳሴ አያኖርህ ችሎ
ባይወጣም እልልታ ከፍጥረታት ዓለም
አንተን የሚያኖርህ አምልኮ እኮ አይደለም
ፅኑ ምሰሶ ነህ የሕይወት መገኛ
ከቶ አይደለህም የአምልኮ ጥገኛ
5🥰2
የዛሬው ቀን

የደስታ !
ሁሉም ነገሮች መልካም የሚሆኑበት !

መከናወን የሚሆንበት !

የልበችሁን መሻት የሚተገኙበት!

መልካም የሆኑ ነገሮች ወደ እናንተ የሚመጣበት !

የእናንተ ነገር ሞገስ የሚያገኝበት !

እንኳንም ይሄ ቀን ተሰጠኝ የየምትሉበት ቀን ይሁንላችሁ 🙏❤️
6🥰1🙏1
ሮሜ 12 (Romans)
2፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
3🙏1
እግዚአብሔርን በመጠበቅ የሚባክን ጊዜ የለም

መልካም ምሽት 🙏❤️
4💯1
የባረከኝ መልዕክት 👇🏼👇🏼


#ምንጩን_ለመናገር_የማታፍሩበት_በረከት_ይስጣችሁ
ሶምሶን ለእናትና አባቱ ማር አምጥቶ አበላቸዉ ፥ ነገር ግን ከየት እንዳመጣ አልነገራቸዉም ይላል። ምክንያቱም ናዝራዊ ስለሆነ አትንካ ከተባለ ቦታ ከሞተ አንበሳ ሆድ ነዉ ያመጣዉ። ስለዚህ ማሩን እንጂ ምንጩን አልነገራቸዉም።
ብዙ ሰዎች እጃቸዉ ላይ መልካም የሚመስል ነገር ንብረት፣ ገንዘብ፣ አገልግሎት አለ ነገር ግን ምንጩን አይነግሩህም ለመናገርም ያፍሩበታል።
በየትኛዉም ሰዓት ምንጩን ለመናገር የማታፍሩበት ከእግዚዓብሄር እጅ የምትቀበሉት በፅድቅ የተገኘ በረከት ይስጣችሁ።

መልካም
ዕለተ ዋዜማ ☀️😎
🥰31
ትንሽ ምክር .....ለቻናሎቻችን ቤተሰቦች
ገናን ስታከብሩ መረዳት ያለባችሁ ነገር
የ ኢየሱስን መወለድ

ኢየሱስ ምድር ላይ መምጣቱ

ኢየሱስ ለሰው ያለዉን ፍቅር

ኢየሱስ ለአለም ብሎ እራሱን መስጠቱን


እነዚህ እና ሌሎችን ኢየሱስ ለእኛ ብሎ የሆነውን እያሰብን እናክብር


መልካም የገና በአል ይሁንልን 🎄🎄🎄🎄
🎉21
የእውነት መንገድ👣 pinned «ትንሽ ምክር .....ለቻናሎቻችን ቤተሰቦች ገናን ስታከብሩ መረዳት ያለባችሁ ነገር የ ኢየሱስን መወለድ ኢየሱስ ምድር ላይ መምጣቱ ኢየሱስ ለሰው ያለዉን ፍቅር ኢየሱስ ለአለም ብሎ እራሱን መስጠቱን እነዚህ እና ሌሎችን ኢየሱስ ለእኛ ብሎ የሆነውን እያሰብን እናክብር መልካም የገና በአል ይሁንልን 🎄🎄🎄🎄»
🔥🔥🔥❄️❄️❄️⭐️⭐️⭐️🤭🤭🤭
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
— ኢሳይያስ 9፥6


❄️ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን የልደት መታሰቢያ በአል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ🙏

🎏🎏
መልካም🎏🎏
🔔በዓል🔔


🇯‌🇴‌🇮‌🇳‌ 🤏❄️
🎄3🥰1
#መድኃኒት_ተወልዶልናል



ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና
#አትፍሩ
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ
#መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ #ተወልዶላችኋልና

🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮችና የDawurootsuwa Gospel Tube ቤተስቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄
#መልካም_በዓል_ይሁንላችሁ


እየሱስ ተወልዶልናል እያልን እስቲ COMMENT ላይ እንጽፋለን፤ በ LIKE ደስታችሁንም ግለጹልን 🥰

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ
🥳
🎄4
Forwarded from 🎸Frenymusic🎸
ሕፃኑ መድኅን!

ዓለም ከፍ ባለ ድቅድቅ ጨለማ ተሞልታ ነበር፤ ሁሉ ነገር ዝምጭጭ ብሏል። ከአራት መቶ በላይ ለሚሆኑ አመታት ከዚህቀደም የተለመዱት ድምፆች ሁሉ ቆመዋል። ከሰማይ ክፉምመልካምም መልእክት ተሰምቶ አያውቅም። ብቻ ሁሉእንዳመጣለት፣ እንደመሰለው ይመላለስ ነበር። መንፈሳዊሥርዓቶችም ቢሆኑ እንዲያው ለወጉ ልማዱን ተከትሎይከወናሉ እንጂ፣ ይህ ነው የሚባል መንፈሳዊ እርካታአልነበረም።
በዚህ መካከል ተስፋ ቢስነት፣ የደኅንነት ምሥራች እጦት፣ የመንፈሳዊ ዓለም ዳፈና በሁሉ ስፍራ ገንኖ ነበር። ሌላኛውመደበኛ ሕይወት ግን እንዳለ ቀጥሏል። በዚህ መሐል ታዲያ፣ምድር በታሪክ የማይደገም አንድ ድንቅ ክስተት አስተናገደች።

በአንዱ ስፍራ እረኞች በሌሊት መንጋቸውን እየጠበቁ ነበር። በብርሃን የተንቆጠቆጠ መልአክም ድንገት በመሐከላቸውተገለጠ። ነገሩ ያልተለመደ እና አስፈሪ ስለነበር፤ በታላቅ ፍርሀትተሞሉ።
ክስተቱ ለምድር ብቻ ሳይሆን ለሰማይ ሰራዊቶች ሁሉ የደስታምክንያት ነበር፤ በመሆኑም ለሰዎች በሆነው በዚህ ምሥራች፣በሕፃኑ መድኅን ሰበብ ታላቅ ዝማሬ ሆነ።

ሕፃኑ መድኅን የዓለሙ አዳኝ ሆኖ ከተገለጠ እንኾ ሁለት ሺህአመት አለፈ። የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ለዓለም ተስፋ የኾነውእውነተኛው ብርሃን ዛሬም በትኩስ ጉልበት ያድናል። ዛሬምይኽ የምሥራች ትኩስ ነው። ዛሬም ተስፋ ላጡ፣ በማን ያድነናልጭንቅ ውስጥ ላሉ፣ በድቅድቅ ጨለማ ለተዋጡ የዛሬ ሁለትሺህ አመት የተወለደው ክርስቶስ ጌታ እውነተኛ ተስፋ፣ ብቸኛአዳኝ፣ የማይደበዝዝ ብርሃን ነው። ወደ እርሱ የሚመጡትንፈጽሞ ያድናቸዋል። ዛሬም ወደእዚህ እውነተኛና ብቸኛ ተስፋኑ ብለን ጥሪ እናስተላልፋለን!!

#ደስታ_ለዓለም #tesfa #hope
🥰2
ደስታ ለዓለም - Freny Music
Freny music
MERRY CHRISTMAS😊🎄🎄

Share with your families and friends🎄🎄
💒sʜᴀʀᴇ 🔔ᴊᴏɪɴ 🔔
    👇👇  🔺🀄️🀄️ሉ  👇👇

Channel:@Freny_music🍀🍀
@Freny_music🍀🍀
       
     ♡ ㅤ   ⎙ㅤ    ⌲        ✉️   
     ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
🎄32
የአለሙ ቤዛ
ቀድሞ በነብያት ፣ለህዝቡ እንደማለ
እቤዣችኅለዉ ፣አይዟችሁ እንዳለ
እንደተናገረው ፣እንደተስፈ ቃሉ
ቤዛችን ተወልዷል ፣ሃሌሉያ በሉ

እሰይ የምስራች ፣ሆነልን ደስታ
በጨለማ ስኖር ፣ሆነን የሞት ሽታ
በደዌ ተይዘን ፣በኀጢአት በሽታ
በዲያብሎስ ቀንበር ለምንንገላታ
መዳኒት መቷል ፣ መድሃኒአለም ጌታ

መልካም በአል 🎄🎄🎄
4
አንዳንዶች የሚያውቁት የሽቶውን ዋጋ ነው፤ ማርያም የምታውቀው የኢየሱስን ዋጋ ነው፤ ውድ የምትሉት ነገር አላቹህ ሰብራቹህ አፍስሱለት🙇
3
የማይሆነው ሆነ ግርግም አካባቢ
መና ተወለደ ዘላለም አጥጋቢ
ረሀብ ያለብን በሞት የገዛን
ወረደልን ህይወት በፍቅር ሊገዛን

#Exodus
3
#የማለዳ_ቃል 🌤☀️

“እኔ እግዚአብሔር
#ጠባቂው_ነኝ፤ ሁልጊዜ #አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጐዳው #በሌሊትና #በቀን #እጠብቀዋለሁ።”
  — ኢሳይያስ 27፥3

መልካም ቀን !
2🙏1
እምነት ቢሞላ ዕውቀት ቢከበኝ
ልሳን መናገር ትንቢት ቢኖረኝ
ሥጋዬን ለእሳት ብሰጥ ፈቅጄ
ባልነፍግ ለድሆች ያለኝን ከእጄ
ፍቅር የሌለው እልፍ ደግነት
ጌታ የሌለበት መንፈሳዊነት
ወዴት ወዴት ነው ይህ ከንቱ ጉዞ
በሃሜት ታዝሎ በቂም ተይዞ
ዞሮ ለማን ነው ይህ ጥል ግርግር
አቤል ከቃየል የማይሆን አጥር
ጐራ ለይቶ ይቅር ማድሩ
የእውነት ፍቅር ይግባ መንደሩ
የባላንጣችን ደስታው ይደፍርስ
በፍቅር ዘምተን ሰላም እንመለስ
የቁርሾን ዘመን ይበቃ ብለነው
መዘናጠሉ ነው ወዲያ እንጣለው
ፍቅር ይበቀለው


H̶a̶n̶n̶a̶ T̶e̶k̶l̶e̶
4
ልባርካችሁ እርግማን የምትመስል ግን ምርቃት የሆነ በረከት

እግዚአብሔር የሌለበት በር የተዘጋ ይሁን


መልካም ቀን
🙏2
“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
3
#የማለዳ_ቃል ☀️🌤

“አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።”
  — መዝሙር 25፥4

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው!

መልካም ቀን !
🙏3