Excellent training on Team Dynamics and Team Coaching Skills concluded today. Great participants, highly motivated and energetic. Keep on, all, the learning and the great work you are doing!
Always inspired to meet new people on trainings. There is so much connection and sharing to enjoy.
Networking at the opening of our team dynamics and team coaching training, which started today at Ellily Hotel.
👍5
አማርኛ Group እና Team - ቡድን የሚል ተመሳሳይ ፍቺ ያስቀምጥላቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁለት ቃላቶች ልዩነታቸው ሰፊ ነው፡፡
Group ስብስብን የሚገልጽ ሲሆን Team ውህደትና ቅንጅትን ሲያሳይ በጋራ አብሮ የመስራትና ከፍ ያለ ውጤትና ዕሴት የመፍጠርን ፍልስፍና ያካትታል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ Team የሚለው ቃል ዕጅግ የላላ ትርጉም ተሰጥቶት Group የሚለውን ቃል በሚገልጽ መልኩ አብረው የሚሰሩ የሰዎችን ስብስብ ለመግለጽ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ይህ ፍጹም ስህተት ነው፡፡ ለምሳሌ የአመራር ቲም (Leadership Team) ወይንም የበላይ ቲም (Senior Management Team) የሚሉ አገላለጾች አባላቱ ፍጹም በቲም የመስራት ዝንባሌ በማይታይባቸው ሁኔታዎች ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ቲም ከቡድን በበርካታ መስፈርቶች በዕጅጉ የተለየ ነው፡፡ ሰዎች በGroup ሲሰሩ ግላዊ ውጤታቸው ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን Team ግን ለጋራ ውጤት በጋራ ተጠያቂነት ላይ ያተኩራል (እዚህ ላይ የሩጫና የእግር ኳስ ስፖርቶችን እንደምሳሌ መውሰድ ይቻላል)፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግም የሚከተሉት ጎልተው የሚወጡ ልዩነቶች ናቸው፡፡
• ትብብርና ቅንጅት የሚጠይቅ የጋራ ዓላማ
• በሚሰሩት ስራ የሚኖራቸው መተሳሰር፤ ለምሳሌ የአንዱ ስራ በሌላኛው ላይ የተመሰረተ መሆን
• እርስ በርስ ባላቸው የጋራ መደጋገፍ
• ለጋራ ጥረታቸውና ድክመታቸው በጋራ የሚወስዱት ኃላፊነት ናቸው፡፡

👍7
ጤናማ ግጭት (ብሎ ነገር አለ?)
በሰዎች የእርስ በርስ ግንኙነት ውስጥ ግጭት ልናስወግደው የማንችለው ለዕድገትና ለለውጥ አስፈላጊ የሆነ ክስተት ነው፡፡ ግጭት ችግር የሚሆነው ጤናማ ካልሆነ ብቻ ነው፡፡ መተማመን ባለበት ሁኔታ የሚከሰት ማንኛውም ልዩነትም ሆነ ግጭት ጤናማ ሲሆን መተማመን በሌለበት ሁኔታ ግን ግጭት ጤናማ አይሆንም፡፡
ጤናማ ግጭቶች ሁሉም ወገን አሸናፊ የሚሆንባቸው ናቸው፣ ጤናማ ባልሆኑ ግጭቶች ውስጥ ግን ሁልጊዜም ቢሆን አሸናፊና ተሸናፊ ይኖራል፡፡ ይህ ደግሞ ባብዛኛው ቂምና በቀልን የሚያስከትል ሲሆን ግጭቶች እንዲቀጥሉ ምክንያት ይሆናል፡፡
ግጭቶች ጤናማ እንዳይሆኑ እንቅፋት የሚሆኑብን ባሀርያት የትኞች ናቸው
• መፈረጅ ጤናማ ያልሆኑ ግጭቶች ዋና ምንጭ ነው
• አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን፣ ውይይቶችንና ግንኙነቶችን መሸሽ ጤናማ ባልሆኑ ግጭቶች ሁሉም ወገን ተሸናፊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
• ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር መሻት ይህ ባህርይ ልዩነቶች ሲፈጠሩ ከመወያየት ይልቅ የራስን ፍላጎት በሌላኛው ወገን ላይ በመጫን ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል፡፡
• ሌላኛው ተለማማጭነት ሲሆን ይህ ዓይነቱ ባህርይ የራሳችንን ፍላጎት ወደጎን በመተው ሌሎችን ለማስደሰት የእነሱን ፍላጎት ብቻ ለሟሟላት መጣር ሲሆን ማናም ቢሆን በዘላቂነት ጥቅሙንና ፍላጎቱን አሳልፎ ስላማይሰጥ በአንደ ወቅት የግጭት ምክንያት ይሆናል፡፡
ግጭቶች ጤናማ እንዲሆኑ የሚያግዙን ባህርያት የትኞች ናቸው?
1) Empathy/ ራስን በሌሎች ቦታ አድርጎ መመልከት
ይህ ባህርያ ያላቸው መሪዎች በጤናማ ግጭት ወቅት አስቀድመው መረዳት የሚፈልጉት ነገር ቢኖር የሌላኛው ወገን ፍላጎት ምን እንደሆነ ማወቅ ነው፡፡
ይህም ተግባቦትን በመፍጠር ግጭቶች ጤነኛ እንዲሆኑና ሁሉም ወገን አሸናፊ እንዲሆን የሚያስችሉ ውጤቶችን በጋራ ለማምጣት ያግዛል፡፡
2) በመቀራረብ አማራጮችን ማሰስ
በመቀራረብ ሁሉም ወገኖች በጋራ አማራጭችን በመፈለግ አዲስና የሁሉንም ፍላጎት የሚያሟላ ሀሳቦችን ማምጣት ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ባህርያት ግጭቶች ጤናማ እንዲሆኑ የሚያግዙ ሲሆን በውጤቱም ሁሉም አካል አሸናፊ እንዲሆንና በሂደቱም መተማመን እንዲፈጠርና የበለጠ እየዳበረ እንዲሄድ ያደርጋሉ፡፡