Top Mereja
22.9K subscribers
9.2K photos
290 videos
32 files
668 links
Download Telegram
‹‹…እኔም ኮሎኔል ነኝ። ከእኔ እኩል ኮለኔል የሆነ የነሱ ሰው በአራት ከተሞች አራት አምስት ትልልቅ ህንጻዎች ሰርቷል። እኔ ግን ልጆቼን አንድ ሱሪ ከገዛሁ በሚቀጥለው ደግሞ ጠብቄ ሸሚዝ እገዛለሁ። እንዲህም ሆኖ ለሀገሬ ስል ይሁን ብዬ 20 አመት ጉድጓድ ውስጥ ሆኜ ስጠብቃቸው እነሱ ግን በመጨረሻ እንድሞት ፈለጉ!"

- ከህወሀት ግድያ ያመለጠው የሰሜን እዝ አባል ኮለኔል ደሳለኝ ሳህለ


@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
የህግ የበላይነትን ለማስፈን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል ‼️

🗣የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት

ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ እስካሁን 280 ጸረ ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ነው የገለጹት።የህወሐትን ተልዕኮ በማስፈጸም በዞኑ ውስጥ ዜጎችን በመግደል፣ በማፈናቀልና ንብረት በማውደም የተሰማሩ ቡድኖችን ለማጽዳት እርምጃው ይቀጥላል ብለዋል ኮሎኔል አያሌው ።

ቀጠናው የአጎራባች ሃገራት አዋሳኝ ስለሆነ ለጠላት ሰርጎ ለመግባት አመቺ መሆኑና የጸረ ሰላም ሃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀላቀላቸው ለይቶ ለማውጣት የአንዳንድ አመራሮች ቁርጠኝነት ማነስ ሁኔታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማረጋጋት አስቸጋሪ እንዳደረገውም ተናግረዋል።

ይሄን የጥፋት ተልዕኮ ለመደምሰስ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የክልሉ ልዩ ሃይል ፖሊስ በመቀናጀት የዘመቻ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡ ጠላትን አጋልጦ እንዲሰጥ የፖለቲካ አመራሩ እየሰራ ይገኛልም ነው ያለው።

ባለፉት ሁለት ቀናት ህግን ለማስከበር በተደረገው የተቀናጀ ዘመቻ በማንዱራ 17፣ በዳንጉር 4 እና በጉባ 2 በአጠቃላይ 23 ጸረ ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገነነው መረጃ ያመለክታል።

#Via መተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
"ወታደራዊ ዘመቻው ከ1 ሳምንት ባጠረ ቀን ያልቃል "‼️

በትግራይ ክልል ወሳኝ የሚባሉ ቦታዎች በመከላከያ ሰራዊት ነፃ መውጣታቸውን የገለፁት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ሕግ የማስከበር ወታደራዊ ዘመቻው በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ገለፁ፡፡ከፍራንስ 24 ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ሚኒስትሩ ዘመቻው ከአንድ ሳምንት ባጠሩ ቀናት ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተስፋ መደረጉን ነው የጠቀሱት፡፡

ንፁሃን እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ያሉት አህመድ ሽዴ አሁን ላይ ዘመቻው በመቐለ እና ዙሪያዋ ባለ ጠባብ ቦታ የሚከወን መሆኑን አስተድተዋል፡፡ በሌሎቹና ከሕወሓት ነፃ በሆኑ ቦታዎች የሰብኣዊ አገልግሎቶች እንዲደርሱ ክፍት መደረጉንም አንስተዋል፡፡

#Via አሐዱ ቴሌቪዥን

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
ጁንታው ዋሻው ገብቶ መዘገብ ጀመረ‼️

DW ደምጸ ወያኔ ከ5 ቀናት ቡሃላ ዋሻ ወስጥ ከሚገኘው ስትዱዮ የተለመደውን ፕሮፖጋንዳ ማስተላለፍ ጀምሯል።

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ‼️

በንጹኃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በማይካድራ ከተማ መፈፀሙ ይታወቃል።

ይህን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እንደሆነ ገልጾ ነበር።

ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ያደረገ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው በመገኘት አረጋግጠዋል።

በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው ተገኝተዋል።

በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል።

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
#ሰበር_ዜና‼️

ሰራዊቱ መቀሌን እና የወንጀለኛው ጁንታ ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎችን ያዘ!

የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን እና የወንጀለኛው ጁንታ ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ።

የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ ለመከላከያ ሰራዊት ወገንተኝነቱን አሳይቷል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት ሀውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲቀየህ፣ ማይመሳኖን እና ውቅሮን ከጁንታው ታጣቂ ሃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ አድርጓል። የህወሃት ጁንታ በሰላም እጁን እንዲሰጥ መንግስት የሰጠውን የ72 ሰዓታት ጊዜ ሊጠቀም ባለመቻሉ ከትናንት ጀምሮ የህግ ማስከበር ስራው ቀጥሏል።

በመከላከያ ሰራዊት ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ሀሰን ኢብራሂም ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ የህግ ማስከበር ሂደት በውጤታማነት ቀጥሎ ተጨማሪ የትግራይ ክልል ከተሞችን ከጁንታው ታጣቂ ነፃ ማድረግ ተችሏል። በዚህም በአድዋ ግንባር የተንቀሳቀሰው ሰራዊት ሃውዜን፣ አብርሃ ወአፅበሃንና ውቅሮን የተቆጣጠረ ሲሆን አጉላን በግማሽ ቀን መቆጣጠሩን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በመቀሌ አቅራቢያ ወደሚገኘው መሰቦ ተራራ እየገሰገሰ ሲሆን ይህም መቀሌን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ጠቁመዋል። በሁለተኛው ግንባርም በአዲግራት በኩል ሳንቀጣ እና አልነጃሺን በመቆጣጠር ውቅሮ ገብቷል።
በሶስተኛው የራያ ግንባር ደግሞ አዲቀይህን የተቆጣጠረ ሲሆን ሄዋናና በመቆጣጠር ሁሉንም ምሽጎች ሰባብሮ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
የሕወሓት ታጣቂዎች በመቀሌ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞችን በሌሊት ወደ አልታወቀ ስፍራ ወስዶ እየሰወራቸው መሆኑን የአይን ምስክሮች ለኢሳት ተናገሩ ‼️

ከእስር ተለቀው በእግራቸው ወደ አማራ ክልል የገቡ ሰዎች እንደ ገለጹት “ለእናንተ የሚሆን የእለት ምግብ ማቅረብ አልችልም፤” በሚል በቀላል እስራት የተቀጡ እስረኞችን እየለቀቀ መሆኑን እና በርካታ እስረኞችን ግን ወደ አልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ ነው ።

በመቀሌ ማረሚያ ቤት ውስጥ ብቻ ከ5 ሺህ በላይ እስረኞች መኖራቸውን እና በከባድ ወንጀል ተጠርጥረው በቀጠሮ የሚመላለሱ እና ውሳኔ ያገኙ ታራሚዎች በሌሊት ትፈለጋላችሁ በሚል እየተወሰዱ መሆኑን ነው የገለጹት ።

በቡድኑ ታጣቂዎች በእስር ቤቱ ውስጥ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ የገለጹት እነዚህ የአይን ምስክሮች ተደብድበው የሞቱ እስረኞች እንዳሉም ተናግረዋል።


@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
በራያ ግንባር የተሰለፈው ሰራዊት መቀሌን ለመቆጣጠር 2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

አበበ ሰማኝ (ከሄዋኔ) ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም

በራያ ግንባር ተሰልፎ አስቸጋሪ የመሬት ገፆችን በማለፍ የድል ባለቤት የሆነው መከላከያ ሰራዊት ከ2 ቀናት በኋላ መቀሌ ከተማን እንደሚቆጣጠር የግንባሪ መሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደብሌ ተናገሩ።

በራያ ግንባር ተሰልፎ የጠላትን አከርካሪ በመስበር ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በአንድ ብኩል ከጨርጨር እስከ መሆኒ በሌላ በኩል ደግሞ ከቆቦ አለማጣ ኩኩፍቱ እና መሆኒ በማድረግ ግዳጁን በሁለት አበይት አቅጣጫዎች ሲፈፅም ቆይቷል።

ምንም እንኳን የገጠምነው ሃይል የጎበዝ አለቃ ወታደር ቢሆንም አካባቢው ካለው ተራራማ የመሬት ገፅ አንፃር ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፈን የሚከፈለውን መስዋዕትነት በመክፈል በአሁኑ ሰዓት ከመቀሌ በ30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሄዋኔ ከተማን ተቆጣጥረናል ብለዋል።

በቀጣይ ግዳጅ ላይ የምንሰራቸው ማይ ነብሪ እና አዲ ጉዶም የተባሉ ከተማዎችን መቆጣጠር ነው ያሉት ጀነራል ባጫ እነዚህን ተልዕኮዎች በሚገባ በመፈፀም በቀጣይ 2 ቀናት ውስጥ መቀሌ ከተማን እንቆጣጠራልን ሲሉ ተናግረዋል።

ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ በበኩላቸው ጁንታው ቡድን ለረጅም ጊዜ እዋጋበታለሁ ብሎ የገነባቸው ኮንክሪት ምሽጎች ከ3 ቀናት መራራ ውጊያ በኋላ ሲደመሰሱ ካለአማራጭ ቦታውን ልቆ እንዲሸሽ ተደርጓል ብለዋል።

የመከላከያ ሃይሉ የከባድ መሳሪያ ምድብተኞች በተመረጡና ኢላማቸውን በጠበቁ ተኩሶች የጠላትን የማድረግ አቅም ማዳከም ተችሏል ያሉት ጀነራል አለምሸት በዚህም የጁንታው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ወደ አዲጉዶም ሸሽቷል ብለዋል።


@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
የመከላከያ ሰራዊቱ የራያ ግንባር ሒዋነ ከተማን ከጁንታው እጅ ማስለቀቁን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ፡፡

ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሁን ላይ የጁንታው ቡድን ወደ ዐዲ ጉደም መሸሹን ተናግረዋል፡፡
ሰራዊቱ አካባቢውን በተቆጣጠረበት ወቅት የጥፋት ሃይሉ ይጠቀምባቸው የነበሩ 6 ታንክ እና ሁለት ዙ23ን ጨምሮ በርካታ መሳሪያዎች መደምሰሳቸውንም ነው የተናገሩት፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ አስቸጋሪ መልክዓ ምድሩን በብቃት በማለፍ የጁንታውን ቡድን መደምሰሱንም አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሰራዊቱ የጥፋት ሃይሉ ሲሸሽ ያወደማቸውን ድልድዮችና መሰረተ ልማቶች እየጠገነ በጁንታው ቡድን ላይ ድል ማስመዝገቡንም አውስተዋል፡፡ አሁን ላይ ሰራዊቱም ወደ መቐለ የሚያደርገውን ግስጋሴ መቀጠሉን ጠቅሰው ሰራዊቱ ከተማዋን በአጭር ጊዜ እንደሚቆጣጠርም ገልጸዋል፡፡

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
#BREAKING‼️

የህወሀት ቡድኑ በርካታ ሮኬቶችን ወደ ኤርትራ ከተሞች አስወነጨፈ!

የህወሃት ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውን ጦርነት አለም አቀፍ ለማድረግ በወጠነው ሴራ የመጨረሻ የተስፋ መቁረጥ ሙከራ ዛሬ ማታ አድርጓል ተብሏል።

በበርካታ የኤርትራ ከተሞች ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል፡፡ ኤርትራ ፕረስ በአስመራ የወደቁ ሮኬቶች በተጨናነቁ የመኖሪያ መንደር አቅራቢያ ባለ አቅራቢያ እንደወደቁ ማረጋገጥ ችሏል።

ይሁን እንጂ በሰው ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት የለም ብሏል። ኤርትራ ፕሬስ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰው እንደሚያቀርብ አስታውቋል።


@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
አየር ኃይል የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችንና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለተለያየ የስራ ጉዳዮች በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰራተኞችን ወደየአካባቢያቸው የማመላለስ ስራ ጀምሯል።


@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
አስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የትግራይ ቴሌቪዥን እና የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ስርጭታቸው ተቋርጧል‼️


@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
#UPDATE‼️

ምሽት ወደ ኤርትራ የተተኮሱት ሮኬቶች 2 መሆንናቸውን ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ስምኦን ሃጎስ (ከኣስመራ) ገልጿል።

ጥቃቱ ወደ አስመራ እና ከአስመራ በደቡብ በኩል 40 ኪሎ ሜትር ወደ ምትርቀው #ደቀምሓረ የተፈፀመ ነው ብሏል።

አንዱ አስመራ ፤ አንዱ ደቀምሓረ ነው የወደቀው። በሰውም ይሁን ንብረት ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ መረጋገጡን ጋዜጠኛው ጨምሮ ገልጿል።


@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙህመድ እና የሶማሊ ልዩ ሀይል አዛዥ ኮማንደር አህመድ መሀመድ መከላከያ ሰራዊት ለግዳጅ ለቆ የወጣውን ድንበር በመጠበቅ ላይ ያሉ የክልሉ የልዩ ሀይል አባላትን ጎበኙ‼️

ልዩ ሀይሉ በድንበር ጥበቃ እና ሰላም በማስከበር የመከላከያን ቦታ ሸፍኖ መስራቱን በጎበኙበት ወቅት ሰራዊቱ ያለበትን ጥንካሬ እና ብርታት አድንቀዋል።

ሰራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ እና በላቀ አፈፃፀም እየተወጣ መሆኑን የጠቆሙት በቦታው ያሉ የሰራዊቱ አመራሮች ወደ ቦታው ከመጡ ግዜ ጀምሮ በጁንታው የህወሃት ቡድን ተልእኮ ተሰጥቷቸው ወደ መሀል ሀገር ሊዘልቁ የሞከሩ ከ10 በላይ የአልሸባብ አባላትን በቀጥጥር ስር ማዋላቸውን ተናግረዋል።

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
በኦሮሚያ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከኅዳር 30 እስከ ታኅሣሥ 2 እንደሚሰጥ ተገለጸ ‼️

በክልል ደረጃ የሚሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና በኦሮሚያ ከኅዳር 30 እስከ ታኅሣሥ 2 የሚሰጥ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
በክልሉ ከመዋዕለ ሕፃናት ውጪ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ እንደሚጀምርም ተገልጿል።
የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት መጀመሪያ ጊዜ ለሁለት ሳምንታት መራዘሙ ነው የተገለጸው።

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል።

በራያ አላማጣ ከተማ ከአንድ የመንግስት ቢሮ ውስጥ በርካታ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል።በስፍራው አስተያየታቸውን የሰጡት ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ እንደገለፁት ይህን መታወቂያ የሚጠቀሙት ግለሰቦች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀልና የሽብር ጥፋት ለማድረስ ነው ብለዋል።ይህ የትህነግ ድርጊት በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀል በመፈፀም የአማራን ህዝብ ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ለማጋጨት ያሴሩት ሴራ ነው ሲሉ ምክትል ኮማንደሩ ተናግረዋል።ሁሉም የሀገራችን ህዝብ እና የፀጥታ አካላት መታወቂያ በሚያዩበት ጊዜ በደንብ ማስተዋል ይገባል።አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Via Amhara Police Commission
@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia
የጁንታው ቡድን ልዩ ሃይል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የጦር መሳሪያ በማስቀመጥ ህብረተሰቡን ያስቆጣ ተግባር ፈጽሟል – መከላከያ ሰራዊት

የጁንታው ቡድን ልዩ ሃይል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የጦር መሳሪያ በማስቀመጥ ህብረተሰቡን ያስቆጣ ተግባር መፈጸሙን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡
“በራያ ግንባር የተሰለፈው የመከላከያ ሰራዊት በሚያከናውነው የህግ ማስከበር ተልዕኮ ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን እየተጋተ የሚገኘው የጁንታው ቡድን የማይደፈረውን ነገር ፈጽሟል” ብሏል።
በዚህም በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያስቆጣ አረመኔያዊ ተግባር መፈጸሙንም ሰራዊቱ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል ።
አቶ በሀይሉ በርኸ ” ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመድፍ ጥይት እና ቢ ኤም መሳሪያ አምጥተው አስቀመጡ ለምን ስንላቸው ቤተክርስቲያኑ አይመታባችሁም ከተመታም የጥይት ሳጥን እንሰጣችሁና እሱን ሸጣችሁ ታስጠግኑታላችሁ አሉን ” ብለዋል ።
አቶ በሀይሉ “ቤተ ክርስቲያኑ ፈርሷል ውስጡ ያለው ፅላትም ይኑር አይኑር የምናውቀው ነገር የለም ፥ ወያኔ ለሃይማኖት እኩልነት እቆማለሁ ሲል የነበረ ድርጅት ዛሬ ግን ስጋወደሙ የምንቀበልበትን የእምነት ቦታ አርክሶብናል” ሲሉ በሃዘንና በቁጭት ስሜታቸውን እንዳጋሯቸውም ነው ያስታወቀው።
በየትኛውም ፖለቲካዊ እይታ ህዝብን ያልያዘ ሃይል የድል ባለቤት ሊሆን አይችልም ያለው ሰራዊቱ፥ ከሞቱ መቃብር አፋፍ ላይ የሆነው ትህነግ ግን በራሱ ልክ በተሰፋው የሴራ ፖለቲካ ተተብትቦ በሰው ህሊና ሊፈፀሙ አይደለም ሊታሰቡ የማይችሉ ተግባራትን ከመፈፀም አልቦዘነምም ነው ያለው።
ለሁሉም በመላው ህዝብ ድጋፍ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጀግንነት ዘራፊውናከሃዲው ቡድን ያለች

@AddisMerejaEthiopia
@AddisMerejaEthiopia