ትምህርት ሚኒስቴር
107K subscribers
315 photos
2 videos
81 files
60 links
ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support Us🙏
Download Telegram
ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 98.62 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

ፈተናውን ከወሰዱ 363 የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 358 ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸው ተገልጿል።

በዘጠኝ የጤናና ህክምና ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደው፤ ከአካባቢ ጤና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሦስት እንዲሁም ከፋርማሲ ትምህርት ክፍል ሁለት ተማሪዎች ፈተናውን ሳያልፉ ቀርተዋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Forwarded from Maraki News
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እግረኞችን መቅጣት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ እስካሁን 89 እግረኞች የትራፊክ ደንብን በመተላለፍ እንዲቀጡ ማድረጉን ባለስልጣኑ አስታወቋል፡፡

በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እግረኞችን የሚቀጣ የህግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ነው ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያስታወቀው፡፡

በአዲስ አበባ ካሉት 11 ቅርጫፎችም በለሚኩራ ክ/ከተማ ቅርጫፍ ስራው መጀመሩን ቅርጫፍ ፅህፈት ቤቱ ለጣብያችን አስታውቋል፡፡

የለሚ ኩራትራፊክ ማኔጅመንት ቅርጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ምስጋና ፋንታሁ ቅጣቱ የተጀመረው በጎሮ አደባባይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ቦታው በከፍተኛ ሁኔታ የትራፊክ መጨናነቅ የሚስተዋልበት በመሆኑና እግረኞች በመኪና መንገድ ላይ በመግባት አደጋ እየደረሱ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ተቀጪዎች የትራፊክ ፍሰቱን እንዲያስተባብሩ እና በመንገድ ትራፊክ መረጃ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲያኙ በማድረግ የተጀመረው የቅጣት ሂደቱ በቀጣይ የገንዘብ ቅጣትን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎች እንደሚኖሩትም ተጠቁሟል፡፡

በጎሮ አደባባይ በተጀመረው ቅጣት እስካሁን 89 እግረኞች ደንብ ሲተላለፉ በመገኘታቸው ቅጣት ተላልፎባቸዋል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የገንዘብ ቅጣት መጣል ምቹ ሁኔታ ባይፈጠርም ከ40 ብር እስከ 80 ብር የሚደርስ ቅጣት በህግ ማዕቀፉ እንደተቀመጠ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከባለስልጣኑ ሰምቷል፡፡

በለሚ ኩራ የተጀመረው እግረኞችን የመቅጣት ስራ በሁሉም አካባቢዎች ቀጣይነት እንደሚኖረውም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕብረተሰብ ጤና፣ አጠቃላይ ነርሲንግ እና በሜዲካል ላቦራቶሪ የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ለአዲስ ፓስፓርት, ለነባር ቀጠሮ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለማግኘት የቲክቶክ ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇
https://vt.tiktok.com/ZSFrJKb5q/
https://vt.tiktok.com/ZSFrJKb5q/
Forwarded from Maraki News
ኦነግ ሸኔ በዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት አባቶችን መግደሉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኢኦተቤ ቴቪን ዋቢ በማድረግ ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ

1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል፡፡

የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ ጸጥታውን የሚያስከብረበት  መሣሪያች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ውስጥ 97.6 በመቶዎቹ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕክምና፣ ሜዲካል ላቦራቶሪ፣ ሚድዋይፈሪ፣ ነርሲንግ እና ሕብረተሰብ ጤና የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን ከወሰዱ 253 ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 247 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል በሜዲካል ላቦራቶሪ የትምህርት መስክ ሦስት እንዲሁም በሕብረተሰብ ጤና የትምህርት መስክ ሦስት ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ አለማምጣታቸው ተገልጿል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Forwarded from Maraki News
በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ለስድስተኛ ክፍል 86 ሺህ 691 ተማሪዎች እንዲሁም ለስምንተኛ ክፍል 88 ሺህ 28 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ በሥነ-ልቦና የማዘጋጀት፣ ከኩረጃ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲይዙ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል። ተማሪዎች በስልክና በመሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲቀነሱና ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ወላጆች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል።
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Maraki News
የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

ውጤትዎን ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://result.ethernet.edu.et/

@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Maraki News
በአማራ ከልል ሶስት ከተሞች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አንዲቆም ተደረገ!

በአማራ ከልል ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት፣ ከሸዋሮቢት ወደ ደ/ብረሀን እንዲሁም ከደ ብረሀን -ሸዋሮቢት - ደሴ የትኛውም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከዛሬ የካቲት 16 ቀን ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መደረጉን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ።

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት የትራንስፖርት አንቅስቃሴ እንዲቆም የወሰነው፤ በቀጠናው “ፅንፈኛ ሀይሎች” ላይ እርምጃ እየወሰደ በመሆኑ “ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው” እና አካባቢውን በአጭር ቀናት “ከፅንፈኛ” ሀይሉ ነፃ ለማድረግ ኦፕሬሽን ስራ የተጀመረ በመሆኑ ነው ሲል ገልጿል። ኮማንድ ፖስት አክሎም “ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የፀጥታ ሀይሉም ውሳኔው ይፈፀም ዘንድ ክትትል እንዲያደርግ” በሚል የተወሰነ መሆኑን አስታውቋል።
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለሁሉም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ነው። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ2016 ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ከየካቲት 18/2016 ዓ/ም ጀምሮ መለቀቁን አሳውቋል።

ተፈታኞች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ሊንክ ማየት ይችላሉ።
Forwarded from Maraki News
"ከጠለሸው ሰማይ ከወረሰን ዳዋ
አለች አንዲት ጀንበር በቅርብ የምትወጣ ዳግማዊት ዓድዋ"

ክብር ለሚኒሊክ!
ክብር ለጣይቱ!
ክብር ኢትዮጵያን ብለው ለተሰዉ ጀግኖች አርበኞቻችን በሙሉ! #ዳን_አድማሱ

መልካም የአድዋ ድል ቀን🛡
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ያልተመዘገበ አይፈተንም!

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 3 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ይታወቃል። ምዝገባው የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅና በተቀመጠው ቀነ ገደብ ያልተመዘገበ ተማሪ ፈተና እንደማይቀመጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡


የግል፣ የርቀት እና በበይነ መረብ ተምረው የሚፈተኑ ተማሪዎች ምዝገባ በክፍለ ከተማ፣ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ የትምህርት ፅ/ቤቶች እንደሚካሄድ መዘገባችን ይታወሳል።

በ2016 በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ወጣቶች እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የፋይናንስ ማስተማሪያ ሞጁል በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል፡፡

ባለፈው ሳምንት ይፋ የሆነው ሞጁሉ፤ ፍላጎት ላላቸው ሰልጣኞች የግልና ሙያዊ ክህሎት ስልጠና በባንኮች እና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ባለሙያዎች ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ሞጁሉ የፋይናንስ ትምህርት ጥረቶችን ማዕከላዊ ለማድረግ እና ወጣቶችን እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የገንዘብ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ አስፈላጊው ዕውቀትና ችሎታ እንዲኖራቸዉ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

First Consult እና BRIDGE ከተባሉ ተቋማት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የስልጠናው ሞጁል፤ ብድር፣ ኢንሹራንስ እና ዲጂታል የገንዘብ አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ ትምህርቶች ማካተቱ ተገልጿል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Forwarded from Maraki News
ይመዝገቡ!

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቀርተዋል።

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

የመደበኛ እና ማታ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ 👉 በትምህርት ቤቶች

የግል | የርቀት | የበይነመረብ ተማሪዎች ምዝገባ 👉 በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ እና በትምህርት ጽ/ቤቶች

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል።
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Maraki News
በመውጫ ፈተና ሞባይል ስልክ ይዞ በመግባት፣ በመኮረጅና የተለያዩ የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሠረዙን እና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑንም ጠቅሷል።

ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119 ሺህ 145 ተፈታኞች ፈተናውን መውሰዳቸው ተጠቁሟል።

ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ ከጀመራቸው ሪፎርሞች አንዱ የሆነው መውጫ ፈተና ተመራቂዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ተገቢውን እውቀትና ክህሎት መቅሰማቸውንና ብቁ መሆናቸውን ዒላማ ያደረገ በመሆኑ ፈተናው በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከ12 እስከ 20 ሺህ ብር ድረስ በእጃቸው ይዘው የተገኙ ተማሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉ። - ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጋጥሞኛል ካለው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ምሽት የማይገባ ገንዘብ ከኤ.ቲ.ኤም. ማሽን ወጪ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ማኅበረሰብ አካላት ገንዘብ ወጪ ሲያደርጉና ወደ ሌላም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ ያወጡና ያስተላለፉ እንዲመልሱ ተቋማት እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ የነበረ መሆኑን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጥበቃና ደህንነት ዳይሬክተር ኮማንደር አባዲር ዩያ ገልጸዋል፡፡

ያጋጠመውን የንግድ ባንክ ሲስተም ችግር ተጠቅመው የራሳቸው ያለሆነ ገንዘብ ከATM ለማውጣት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተማሪዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ጥበቃና ደህንነት ተማሪዎች ከዋናው ግቢ እንዳይወጡ ቁጥጥር ሲያደርግ እንደነበረ አመላክተው፣ ሆኖም በተለያዩ ምክንያትና መንገድ የወጡ ተማሪዎች ከግቢ ውጪ ካሉ ማሽኖች ብር የወሰዱ መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

በተማሪ እጅ ይገኛል ተብሎ የማይገመት ከ12 እስከ 20 ሺህ ብር ድረስ በእጃቸው ይዘው የተገኙ ተማሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር አባዲር ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም ንግድ ባንክ ያጋጠመውን ችግር ተከትሎ ተሳስተው ገንዘብ የራሳቸው ያደረጉ ተማሪዎች በአስቸኳይ ብሩን ሳያጠፉ እንዲመልሱ አሳስበዋል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 3-30/2016 ዓ.ም መከናወኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም ፈተናውን ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ መካሔዱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ተካሒዶ መጠናቀቁን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሳምንት እንደሚከናወን ጠቁመዋል፡፡

የፈተና ዝግጅት ሥራው ተማሪዎቹን በአግባቡ ለመመዘን በሚያስችል መልኩ ጠቀሱት ኃላፊው፤ በቀጣይ የፈተናው ሕትመት ይጀመራል ብለዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ወደፊት ይፋ ይሆናል ተብሏል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister