ትምህርት ሚኒስቴር
107K subscribers
315 photos
2 videos
81 files
60 links
ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support Us🙏
Download Telegram
Forwarded from Maraki News
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 271 የህክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ 240 በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ፣ ዘጠኝ በጥርስ ህክምና ዶክትሬት ዲግሪ እና 22 በአኔስቴዥያን ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

ከተመራቂዎች መካከል 198ኙ በማዕረግ፣ በከፍተኛ ማዕረግ እና በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ መሆናቸው ተገልጿል።
Forwarded from Maraki News
የአ.አ.ዩ. ተሸላሚ ተመራቂዎች

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬው እለት ካስመረቃቸው 249 የህክምና ተመራቂዎች መካከል ዶ/ር ሚካኤል አዘነ በህክምና ዶክትሬት 3.93 CGPA በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።

ከሴት ተመራቂዎች መካከል ዶ/ር ረድኤት ጌቱ በህክምና ዶክትሬት 3.87 CGPA በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆናለች።

የዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከህክምና ተመራቂዎቹ በተጨማሪ 22 በአኔስቴዥያን ዲግሪ የሰለጠኑ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ማስመረቁ ይታወቃል።
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Maraki News
#ማሳሰቢያ

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ስም የተለያዩ ቻናሎችን በመክፈት የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ ግለሰቦች እንዳሉና አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት በአካውንት ብር አስገቡ በማለት በብዙ ሺህ ብር እየጠየቁ ህብረተሰቡን እያታለሉ እንደሆነ ለተቋሙ የተለያዩ ጥቆማዎች እንደደረሰው አሳውቋል።

አስቸኳይ ጉዞ ለመሄድ፣ አስቸኳይ ሰነድ ያላችሁ፣ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት በአካል ብቻ በዋናው ቢሮ በመሄድ የምትስተናገዱ መሆኑን እና ክፍያም እዛው በቢሮው የምትከፍሉ ሲሆን አስቸኳይ ፓስፖርት በኦንላይን የማንሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

[የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት]
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ተማሪዎች ያስመርቃል።

የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት የ2016 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት የተማሪዎች ምርቃት የካቲት 16/2016 ዓ.ም እንዲከናወን ወስኗል።

ከቷቋሙ የጤና ሳይንስ እንስቲትዩትና ሌሎች የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች እንደሚመረቁ ተገልጿል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Forwarded from Maraki News
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመረጃ ማስተላለፊያ ገመድ ላይ ባጋጠመዉ ጉዳት አገልግሎቱ ተቋረጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት በቅርንጫፎች ፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ ፣ በሞባይል ባንኪንግ ፣ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ባንኩ አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከፍተኛ እርብርብ በማድረግ እየተሰራ በመሆኑ ደንበኞች በትዕግስት እንድትጠብቁ ሲል ጥሪ አስተላልፏል። ባንኩ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Maraki News
በሀገራችን ኢትዮጵያ ፈቃድ ካላቸዉ ኮሌጆች ዝርዝር ዉስጥ ኮሌጃችን ተራቁጥር 384 ላይ ይገኛል።
---ሊንኩን ተጭነዉ ማየት ይችላሉ --
https://bit.ly/43Z1Rck
--
ሜድስኬፕ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ እንጅባራ ካምፓስ
============================
ኮሌጃችን ለረጅም ዓመታት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች ባስተማሩ መምህራን ፣ስፔሻሊስት ሀኪሞችና የጤና ባለሙያዎች የተቋቋመ ኮሌጅ ሲሆን ለ 2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪና ዲፕሎማ በተመጣጣኝ ክፍያ በሚከተሉት የትምህርት መስኮች ምዝገባ ላይ እንገኛለን ።
--------------------------------------
በመጀመሪያ ዲግሪ
በመደበኛ፣በርቀት፣በኤክስቴንሽን መርሃ ግብር
- በፋርማሲ
- በነርሲንግ
- በማኔጅመንት
-------
በከፍተኛ ዲፕሎማ በመደበኛ፣በቅዳሜና እሁድ
=======
-በፋርማሲ
- በነርሲንግ
- በማኔጅመንት
- በአካዉንቲንግና ፋይናንስ
- በ አይሲቲ

አድራሻ:- እንጅባራ ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት
ወይም መናሃሪያ መዉጫ አስፓልት ተሻግሮ

ስ.ቁ:-09 95 22 22 94/ 09 62 79 18 08
Forwarded from Maraki News
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር መስተካከሉን ገልጿል።

በዚህም ተቋርጦ የነበረው አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመሩን አመልክቷል። ባንኩ ተፈጥሮ ለነበረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ይቅርታ ጠይቋል።
Forwarded from Maraki News
ኬንያ በዘረጋችው አዲስ አሰራር ኢትዮጵያውያን ዜጎች ያለ ክፍያ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ ፈቀደች

ኬንያ የሌላ ሀገር ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ ከፈቀደች በኋላ ከጀመረችው አዲስ የጉዞ ፈቃድ ማረጋገጫ ጥያቄ እና ክፍያ ኢትዮጵያውያን ነጻ እንዲሆኑ መወሰኗን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል።

ኬንያ ካለንበት የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ አንስቶ ከመላው አለም ወደ ሀገሪቱ መምጣት የሚፈልጉ ሁሉም ጎብኚዎች ለቪዛ ከማመልከት ይልቅ የኤሌክትሮኒክስ የጉዞ ፍቃድ ቀድመው እንዲያገኙ በማድረግ ክፍያ በመፈጸም ብቻ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ አዲስ አሠራር መጀመሯ ይታወሳል።

ሆኖም ግን ይህ የዲጂታል ስርዓት አሰራር ለበርካታ ዘመናት ወደ ኬንያ ያለ ቪዛ እና ክፍያ ወደ ሀገሪቱ ሲገቡ በነበሩት ኢትዮጵያውያን ላይ ወጪን እና በውስብስብ የጉዞ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ ቅሬታ እና ጥያቄን አስነስቶ ነበር።

ይህንን ተከትሎ የኬንያ መንግስት ወደ ሀገሪቱ ለመጓዝ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከአዲሱ የጉዞ ማረጋገጫ የክፍያ ሥርዓት ውጪ እንዲሆኑ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ የጉዞ ፈቃድ ማረጋገጫ ጥያቄ እና ክፍያ ነፃ እንዲሆኑ መወሰኑን አምባሳደር ባጫ በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

አምባሳደር ባጫ ወደ ኬንያ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ቪዛ እና ተያያዥ ክፍያ እንደማያስፈልጋቸውና የኬንያ መንስግስት ይህንን በማድረጉ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ነገር ግን ወደ ሀገሪቱ መጓዝ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በበይነ መረብ በኩል የሚሞላውን ፎርም ቀድመው መሙላት እንደሚጠበቅባቸውም ነው የተገለፀው።
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Maraki News
አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ድምፃዊው ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ተገልጿል ።

አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ በየካቲት 12 ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ለሊት ማረፉ ተሰምቷል።

ለመላው አድናቂዎቹና ወዳጆቹ መፅናናትን ተመኘን።

ተወዳጅ ከሆኑ ስራዎቹ ውስጥ ሀገሬን አትንኳት የሚለውን ከታች አያይዘናል።
ሰሞኑን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 98.62 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

ፈተናውን ከወሰዱ 363 የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 358 ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸው ተገልጿል።

በዘጠኝ የጤናና ህክምና ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደው፤ ከአካባቢ ጤና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሦስት እንዲሁም ከፋርማሲ ትምህርት ክፍል ሁለት ተማሪዎች ፈተናውን ሳያልፉ ቀርተዋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Forwarded from Maraki News
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እግረኞችን መቅጣት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ እስካሁን 89 እግረኞች የትራፊክ ደንብን በመተላለፍ እንዲቀጡ ማድረጉን ባለስልጣኑ አስታወቋል፡፡

በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እግረኞችን የሚቀጣ የህግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ነው ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያስታወቀው፡፡

በአዲስ አበባ ካሉት 11 ቅርጫፎችም በለሚኩራ ክ/ከተማ ቅርጫፍ ስራው መጀመሩን ቅርጫፍ ፅህፈት ቤቱ ለጣብያችን አስታውቋል፡፡

የለሚ ኩራትራፊክ ማኔጅመንት ቅርጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ምስጋና ፋንታሁ ቅጣቱ የተጀመረው በጎሮ አደባባይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ቦታው በከፍተኛ ሁኔታ የትራፊክ መጨናነቅ የሚስተዋልበት በመሆኑና እግረኞች በመኪና መንገድ ላይ በመግባት አደጋ እየደረሱ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ተቀጪዎች የትራፊክ ፍሰቱን እንዲያስተባብሩ እና በመንገድ ትራፊክ መረጃ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲያኙ በማድረግ የተጀመረው የቅጣት ሂደቱ በቀጣይ የገንዘብ ቅጣትን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎች እንደሚኖሩትም ተጠቁሟል፡፡

በጎሮ አደባባይ በተጀመረው ቅጣት እስካሁን 89 እግረኞች ደንብ ሲተላለፉ በመገኘታቸው ቅጣት ተላልፎባቸዋል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የገንዘብ ቅጣት መጣል ምቹ ሁኔታ ባይፈጠርም ከ40 ብር እስከ 80 ብር የሚደርስ ቅጣት በህግ ማዕቀፉ እንደተቀመጠ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከባለስልጣኑ ሰምቷል፡፡

በለሚ ኩራ የተጀመረው እግረኞችን የመቅጣት ስራ በሁሉም አካባቢዎች ቀጣይነት እንደሚኖረውም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕብረተሰብ ጤና፣ አጠቃላይ ነርሲንግ እና በሜዲካል ላቦራቶሪ የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ለአዲስ ፓስፓርት, ለነባር ቀጠሮ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለማግኘት የቲክቶክ ቪዲዮውን ይመልከቱ👇👇
https://vt.tiktok.com/ZSFrJKb5q/
https://vt.tiktok.com/ZSFrJKb5q/
Forwarded from Maraki News
ኦነግ ሸኔ በዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት አባቶችን መግደሉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኢኦተቤ ቴቪን ዋቢ በማድረግ ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ

1.  የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2.  የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3.  የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4.  በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል፡፡

የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ ጸጥታውን የሚያስከብረበት  መሣሪያች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
@Adis_media
@Adis_media
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ውስጥ 97.6 በመቶዎቹ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በሕክምና፣ ሜዲካል ላቦራቶሪ፣ ሚድዋይፈሪ፣ ነርሲንግ እና ሕብረተሰብ ጤና የትምህርት መስኮች ፈተናቸውን ከወሰዱ 253 ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 247 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል በሜዲካል ላቦራቶሪ የትምህርት መስክ ሦስት እንዲሁም በሕብረተሰብ ጤና የትምህርት መስክ ሦስት ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ አለማምጣታቸው ተገልጿል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister