ትምህርት ሚኒስቴር
104K subscribers
293 photos
2 videos
81 files
50 links
ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support Us🙏

ማስታወቂያ ለማስነገር በዚህ ያናግሩን
@Adis_probot
Download Telegram
2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል።

የዘንድሮው የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና ከሰኔ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲሰጥ ቆጥቷል።

በዛሬው ዕለት የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች የኬሚስትሪ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ከታህሳስ ጀምሮ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 78 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ለስምንት ቀናት የተሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑ ይታወቃል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድረሻ አከላት ጋር መክሯል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የትምህርት ሥርዓቱ ን ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለ ምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፌዴራል እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ፈተናው የተሳካ እንዲሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው÷የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ተቋሙ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮዎችና የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን÷በቀጣይ ሁሉንም ተማሪዎች በኦንላይን ለመፈተን ሙከራ ይደረጋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ይፋ ይደረጋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ከሰኔ 14 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በዛሬው እለት ይጠናቀቃል።

የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እና በድጋሜ ተፈታኞች ለሦስተኛ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

የህክምና እና ፋረማሲን ጨምሮ በተለያዩ ትምህርት አይነት ፈተናዎች ዛሬ እየተሰጡ ነው፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው ዛሬ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ ይደረጋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ2016 ዓ.ም የፋርማሲ ትምህርት ክፍል እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በድጋሚ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በጠዋትና በከሰዓት በሁለት ፈረቃ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ያሳወቀ ሲሆን ።

ሆኖም ከተፈታኞች ቁጥር አንጻር ፈተናው በተጠቀሰው ቀን ጠዋት ከ2:30 ሰዓት ጀምሮ ለግማሽ ቀን ብቻ የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ የሚከተለው ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

1. በዚህ ፈተና የሚቀመጡት ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች (First seater) እና ፣

2. ከዚህ በፊት የመውጫ ፈተና ተፈትነዉ የማለፊያ ውጤት ያላገኙ ተፈታኞች (re-takers) ናቸው።

ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን የመውጫ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ተማሪዎች መውጫ ያዘጋጀው መሆኑ ታውቆ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል እጩ ተመራቂዎች በጤና ሚኒስቴር የሚዘጋጀውን የላይሰንሰር ፈተና በሌላ ጊዜ እንደሚሰጣችሁ እንድትገነዘቡ እያሳወቅን ጊዜው ወደፊት በሚወጣ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Your exam result is on loading....
❤️Join our channel to see it first
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@examresultet
@examresultet
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል።

በራያ ዩኒቨርሲቲ ከተፈተኑት 325 ተማሪዎች 97.55% በማሳለፍ እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡ ማሳያ ነው።

በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Your exam result is on loading....
❤️Join our channel to see it first
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@examresultet
@examresultet
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት።

ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ደጋግሞ በመሞከር ውጤት መመልከት ይቻላል።

ውድና የተከበራችሁ ተማሪዎች በኮሜንት መስጫው ውስጥ ሀሳብ መቀያየር እና ጥቆማ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል ?

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ላይ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

ከግል ተፈታኞች ውጤት ጋር በተያያዘ ያልተጠናቀቁ ነገሮች በመኖራቸው ውጤቱ ይፋ አለመደረጉን በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልገሎት የዴስኩ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ቀሪ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳለቁ የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ይደረጋል ብለዋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የዘንድሮ የ12ኛ ክፋል ብሄራዊ ፈተና ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ገልፀዋል።

በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ።

የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ።

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦
- በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ 
- በሲቪል ሰርቪስ
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 
- በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ
- በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ።


እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ።

የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
አገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት ነው እየተሰጠ ያለው።

የመጀመሪያ ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትላንት ሐምሌ 2 በቀድሞ ትምህርት ካሪኩሉም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የትግራይ ክልል ተማሪዎች አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጀመራቸው ይታወሳል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የመጀመሪያው ዙር አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከረዕቡ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በዛሬው የሦስተኛ ቀን ፈተና፣ በጠዋቱ መርሐግብር የታሪክ ትምህርት ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና ይሰጣል፡፡

ሁለተኛው ዙር ፈተና ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አድርገዋል።

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://aa.ministry.et/account#/student-result

በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው በቀጣይ ጥቂት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219  በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ አስታውቀዋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል !

የ8ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ተለቋል። ወንድም ሴትም 50ና ከዚያ በላይ ያመጡ ናቸው ወደ ሚቀጥለው ክፍል የሚያልፉት። የአካል ጉዳተኞች ማለፊያ ነጥብ 45 እና ከዚያ በላይ ነው።

78 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞቻችን አልፈዋል።

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል። ”__

የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መመልከቻ : https://aa.ministry.et/account#/student-result
(መለያ ቁጥርና ስም ያስገቡ)
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
በወረቀትና በኦንላይ የሚሰጠውን የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ይሆናል።

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ ከ 9-11/ 2016 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በበይነ መረብ (Online) እና በወረቀት ፈተናው ይሰጣቸዋል።

ፈተናውን የምትወስዱ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በሙሉ መልካም እድልን እንመኝላችኋለን።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister