ትምህርት ሚኒስቴር
109K subscribers
302 photos
2 videos
81 files
55 links
ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support Us🙏
Download Telegram
ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ተቋማት በፋይናንስ አጠቃቀማቸው እንጂ በአፈፃፀም ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት አልነበረም፡፡

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተቋማት በአፈፃፀማቸው ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር መተግበር እንደሚጀምር በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ 

በዚህም በተጠያቂነት የአሰራር ስርዓት መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች (KPI) ላይ ውል በማድረግ ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።

የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓቱ ተመዝነው የተሻለ አፈጻጻም ያስመዘገቡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕውቅና እንዲያገኙ እንዲሁም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ደግሞ የማስተካከያ ዕርምጃዎች የሚወስዱበት አግባብ የሚፈጠርበት መሆኑንም አስረድተዋል።
@Timihirt_Minister
የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መካከለኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናዎቹ በተጠቀሱት ቀናት በጠዋት እና ከሰዓት መረሐግብር እንደሚሰጡ ቢሮው ያወጣው የድርጊት ጊዜ ሰሌዳ ያሳያል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ጥያቄ አድርሰውናል።

12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ አሳውቋል።
@Timihirt_Minister
በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች እያንዳንዳቸው የአገልግሎት ክፍያ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

በዚህም ተፈታኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 በመጠቀም እስከ ማክሰኞ ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ተፈታኞች የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ antedefar@gmail.com እና lakbt2013@gmail.com መላክ ይኖርባቸዋል።

(ተጨማሪ መረጃ ከተያያዘው ደብዳቤ ይመልከቱ።)
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ፈተናው በኦላይን ይሰጣል

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።
@Timihirt_Minister
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ጊዜ ታወቀ

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5  ለማህበራዊ ሳይንስ ሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ  6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ 25 የክልል ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና በተጨማሪ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጡን ስኬታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ሚኒስትር ድኤታዋ ጠቁመዋል።

የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተገልጿል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
Forwarded from Maraki News
የ2025 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ ዛሬ ምሽት 1 ሰአት ላይ ይፋ የሚደረግ ሲሆን እንዴት ማየት እንደምንችል ሙሉ ቅደም ተከተሉን እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

1⃣ ይህንን ሊንክ ተጭነው ወደ ድረገፁ ይግቡ 👉https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx

2⃣ Continue የሚለውን ይጫኑ።

3⃣ ማመልከቻ ሲያስገቡ የተሰጠውን የማረጋገጫ ቁጥር ያስገቡ። ለምሳሌ. 20251O0DZWY3DOV9

4⃣ በኤሌክትሮኒክ ዲቨርሲቲ ቪዛ መግቢያ ላይ ጥቅም ላይ የዋለውን የመጨረሻ ወይም የአያት ስም ያስገቡ።

5⃣ የተወለዱበትን ዓመተ ምህረት ያሰገቡ።

6⃣ የሚመጣሎትን ፊደል እያዩ ሁሉንም ያስገቡ።

7⃣ በመጨረሻም ሁሉን የተሟላ መረጃ አስገብተው ሲጨርሱ Submit የሚለውን በመጫን ውጤቶን መመልከት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው / ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው"  በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንትጠነቀቁ አደራ እንላለን።

መልካም እድል
☑️ @MarakiNews ☑️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው በሁሉም ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ፕሮፌሽናል ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister