ከደቡብ ሱዳን ተነስተዉ በሱርማ ወረዳ ከብት ለመዝረፍ የሞከሩ አርብቶአደሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ከደቡብ ሱዳን መነሻቸዉን አድርገዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኘዉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የአርብቶ አደሮችን ከብቶችን ዘርፈዉ ለመሄድ የሞከሩ 46 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ
የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የክልልና የአካባቢዉ ፖሊስ በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊው ገልጸዋል።
የተዘረፉ 250 ከብቶች እና 21 የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች መያዛቸዉንና የተመለሱ ከብቶችም ለባለቤቶች የተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
ዘራፊዎቹ አሁን ላይ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል።
መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
@TikvahethMagazine

👏98❤8🤔3😢2
ቀጣዩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሊቀ-መንበር ማን ይሆናል ?
አፍሪካ ህብረት የሊቀ-መንበርነት ምርጫ በወርሀ የካቲት በ አዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህ ምርጫ በየአራት አመቱ የሚካሄድ ሲሆን፣ ተመራጩም የአፍሪካ ህብረት ህጋዊ ተወካይና ዋና የአፍሪካ ህብረት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንዲሁም ኮሚሽኑ የገንዘብ ነክ ጉዳይ የበላይ ሀላፊ ይሆናል።
በ2025 አ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው 38ተኛው ጉባኤ አዲስ ሊቀ-መንበር ይመረጣል ተመራጩም ሊቀመንበር የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሙሳ ፋኪ ማህማትን የሚተካ ይሆናል።
በዚህ የምርጫ ፉክክር የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትር ራይላ ኦዲንጋ ለዘንድሮም ምርጫ ከፍተኛ ግምት አግኝተዋል።
ራይላ የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ- ልማት ልዩ መልክተኛ ( special Envoy) ሆነው ከ 2018 እስከ 2024 አገልግለዋል።
ራይላ ለአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበነት ቦታ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ፉክክር ይገጥማቸዋል ተብሎ ይታሰባል።
ከዚህም መካከለሰ የ59 ዓመቱ የጅቡቲው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር መሀሙድ አሊ የሱፍ ሌላው ለምርጫው ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ናቸው።
የ55 ዓመቱ የ ቀድሞው የማዳጋስካር ሪቻርድ ራንድሪያ ማናድራቶ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሚኒስቴር ለዋና ሥራ አስፈፃሚነት በምርጫው ይወዳደራሉ።
እነዚህ ተወዳዳሪዎች ዛሬ በአፍሪካ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ አፍሪካን በሚመለከት ያላቸውን እቅድ የፖሊሲ ጉዳዎች እና ቅድሚያ የሚሰጡዋቸው ሀሳቦች ላይ ክርክር ያካሂዳሉ።
የምርጫ ክርክሩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን እንዲሁም በሌሎች የኦላይን እና የቀጥታ ስርጭት አማራጮች ከምሽት 1 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ድረስ የሚተላለፍ ይሆናል።
#Mjadala
#TheAfricaWeWant
#AddisAbaba

❤20🕊3👍1
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update
በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ እንዲሁም ከዚያ በፊት ወደ አገር ለመመለስ ጠይቀው የመውጫ ቪዛ ሲጠባበቁ የነበሩ 316 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በቤይሩት-ሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጀነራል ጽ/ቤት አስታውቋል።
ከተመለሱት ዜጎች ውስጥ 167 ዜጎች በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉና በሊባኖስ ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር ረቡዕ ታህሳስ 2 ቀን ወደ አገር እንዲመለሱ የተደረጉ ሲሆኑ 17 እናቶችና 22 ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሊባኖስ ረዥም ዓመታት ሲኖሩ የነበሩ ሰነድ አልባ ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ባቀረቡት በጥያቄያቸው መሠረትት ደግሞ 149 የሚሆኑት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።

👏46❤9😨1
Forwarded from Concept Hub Ethiopia
#ሐሳብአለኝ
ሐሳብ አለኝ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 በነገው ዕለት ለአንባቢያን ይደርሳል፤ ይጠብቁን!
#አዳዲስድምጾች: የሐሳብ መሪነትና ሙያዊ ብቃት የሚንጸባረቅበት መድረክ
#EmergingVoice : A hub for thought leadership and professionalism
#TikvahFamily 🩵
@Concepthubeth

❤35👏2
ኮንሰፕት ሀብ (Concept Hub) የሐሳብ መድረክ ነው።
ዛሬ በይፋ እንድታነቡት የምንጋብዛችሁ "ሐሳብ አለኝ" የተሰኘው ዲጂታል መጽሔት እና በብሎግ አማራጭ የቀረቡት የጹሑፍ ሥራዎች ወጣቶች እድሉ ቢኖራቸው ለሚሰሩት ሥራ ጥቂቱ ማሳያ ነው።
ወጣቶች ተቀባይ ብቻ አይደሉም። ከሌሎች የሚማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ሁሉ ሐሳባቸውን የሚገልጹበት፤ የሚሞክሩበትና ፈጠራቸውን የሚያጎለብቱበት መድረክም ያስፈልጋል።
ይህ መድረክም ወጣቶች ሐሳባቸውን እንዲያካፍሉ፤ ለማኅበረሰባቸው ጠቃሚ የሚሉትን ሐሳብ እንዲያዋጡ፤ አዲስ እይታና የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ነው።
በተጨማሪም፥ ወጣቶችን እንዲጽፉ፤ ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ፤ የመፍትሔ ሐሳቦችን እንዲያፈላልጉና ለማኅበረሰብ ለውጥ እንዲሰሩ እድሉን መስጠትና ያስፈልጋል ይህ መድረክም ለዚህ የታሰበ ነው።
የተለያዩ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች፤ ወጣት ባለሞያዎች፤ ወጣት መምህራንና ጸሐፊያን፤ ጋዜጠኞች፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ባለሞያዎች፤ የሰብዓዊ መብትና የአከባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ሌሎች ብዙ ወጣት ሞያተኞችን አሉን ይህ መድረክ ማኅበረሰብ የሚጠቅም ሐሳባቸውን የሚያካፍሉበትም መድረክ ጭምር ነው።
ኮንሰፕት ሀብ ኢትዮጵያ (Concept Hub Ethiopia ) በቲክቫህ ኢትዮጵያ የተጀመረ ተነሳሽነት ሲሆን በዲጂታል መጽሔት ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በወጣቶች የሚደረጉ ውይይቶች፤ ዶክመንተሪዎች፤ የዲጂታል አጫጭር ሥልጠናዎች ወደፊት ይዞ ይመጣል።
🖥 www.concepthub.net

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏16❤9👍1😢1
#ተለቀቀ
"ሐሳብ አለኝ" ቅጽ 1 መጽሔት በዚህ Telegram Mini App ላይ ያገኙታል 👉 @ConceptHubeth_bot
ይጎብኙን www.concepthub.net
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
"ሐሳብ አለኝ" ቅጽ 1 መጽሔት በዚህ Telegram Mini App ላይ ያገኙታል 👉 @ConceptHubeth_bot
ይጎብኙን www.concepthub.net
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
👏26❤9😨1
𝐍𝐞𝐰 𝐓𝐫𝐚𝐢𝐧𝐢𝐧𝐠 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐀𝐧𝐧𝐨𝐮𝐧𝐜𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭 📣📣📣
"National Customs Procedure" Second Round Training
For More Information join our channel @EFFSAAtrainingcenter
and Registration,
📱 +251 903 182525
📞 +251 115 589045
📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)

ኢትዮጵያዊን ሥራ ፈጣሪዎች በየግሬት ሪፍት ቫሊ ኢኖቬሽን ሰሚት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የፈጠራ ሥራዎችን ለማጎልበት የግሬት ሪፍት ቫሊ ኢኖቬሽን ሰሚት ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ከጥር 23- 24 በስካይላይት ሆቴል በሚዘጋጀው በዚህ ዝግጅት በግብርና፣ በጤና እና በትምሕርት ዘርፍ የማኅበረሰብ ልማትን ለሚያፋጥኑ የላቁ የፈጠራ ውጤቶች $750,000 የአሜሪካ ዶላር በሽልማት መልክ ይበረከታል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ሊቀ-መንበርሉሊት እጅጉ "ይህ የፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች በተዘጋጀላቸው በመቶ ሺዎች የአሜሪካ ዶላር የሚገመት ሽልማት ለሀገር ምሰሶ በሆኑ ዘርፎች ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት መላ እንዲፈጥሩና ችግር እንዲፈቱ ያስችላቸዋል" ብለዋል።
ሉሊት እጅጉ ግሬት ሪፍት ቫሊ ኢኖቬሽን ሰሚት/ጉባዔ ለፈጠራ ባለሙያዎች አስቸኳይ ጥሪ ያቀርባል ያሉ ሲሆን "ተስፋ ሰጪ የፈጠራ ሐሳብ ባለቤቶች ለውድድር እንድታመለክቱ፤ አጋሮች ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋልን" ብለዋል።
አመልካቾቶ የተጀመሩ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች፣ ወይም በትንሹ አዋጭነታቸው የታየ ደረጃ ላይ ቢሆን ይበረታታሉ ተብሏል። በተጨማሪም የሽያጭ ዝርዝር ስትራቴጂክ እቅድ ሊኖራቸው ይገባል ተብሏል።
ለማመልከት ስለ ቢዝነሱ 5-10 ስላይድ፤ ከ 10 ገጽ ያልበለጠ ዝርዝር የቢዝነስ እቅድ፣ የፋይናንሺያል ሞዴል እና ትክክለኛ የንግድ ፍቃድ ማዘጋጀት አለባቸው ተብሏል።
በግብር፣ በጤና እና በትምሕርት ዘርፎች ልዩ ፈጠራ ያላችሁ ኢንተርፕርነሮችና ሥራ ፈጣሪዎች፣ የስታርትአፕ አንቀሳቃሾች ይህን ዌብሊን https://www.grvsummit.com በመጠቀም የመወዳደሪያ ሐሳባችሁን እስከ እሁድ, ታኅሣሥ 9 2017 ዓ.ም. ድረስ እንድታስገቡ ይሁን።
በተጨማሪም ጉባዔው የፓነል ውይይቶች፣ ወርክሾፖች፣ ኤግዚቢሽን እና ከኢንዱስትሪ ባለድርሻዎች ጋር የትውውቅ መድረክ የተዘጋጁበት በመኾኑ ተሳታፊዎች ልምድ እንደሚቀስሙበትና ተጠቃሚ እንደሚኾኑበት ይሆናል ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ info@grvsummit.com መልዕክት መላክ ይቻላል ተብሏል።

👏20❤6
"በሰርግ መልሳችን ቀን ግን ይሆናል ብዬ አሰቤ አላዉቅም ነበር" - ዶክተር በየነ አበራ
በሰርጉ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች ከጠሩት የመልስ ፕሮግራም ላይ ላይ ተነስቶ በመሄድና የተሳካ ቀዶ ጥገና በማድረግ እናትና ልጅን የታደገዉ ዶክተር በብዙዎች ምስጋና ተችሮታል።
ይህ የሚያስመሰግን ተግባር የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው።
በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር በየነ አበራ በትላንትናው ዕለት በሰርጉ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች በጠሩት የመልስ ዝግጅት ላይ ነበር።
በዚህ ዝግጅት ላይ እንዳለ ነው እንግዲህ ከሚሰራበት ሆስፒታል የስልክ ጥሪ የደረሰው። የስልክ ጥሪውም እናትና ልጅን እንዲታደግ የቀረበ ነበር።
ዶክተር በየነ ስለሁኔታው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ "መልስ በሀገራችን ባህልና ወግ ትልቅ ቦታ እሚሰጠዉ አዉቃለሁ በዕለቱ አማቾቼ አክብረው ጠርተዉን ፕሮግሙ እየተካሄደ ነበር ስልክ የተደወለልኝ" ሲል ያስረዳል።
"የመጀመሪያዉ ዙር አላነሳሁም! በድጋሚ ሲደወልልኝ አነሳሁት አንዲትን እናት ምጥ እንዳስቸገራትና ቀዶ ሕክምና የግድ እንደሚያስፈልጋት ተነገረኝ፤ አላመነታሁም!" በማለት የመልስ ዝግጅቱን አቋርጦ ለመሄድ መወሰኑን ነግሮናል።
ይህንን ጉዳይ እንዴት ለሙሽሪት እንዳስረዱና እንዳሳመኗት ጠይቀናቸዋል፤ እሳቸው ሲመልሱም፦
"በፍቅር ሕይወታችን ወቅት የትዳር አጋሬን በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ እነግራት ነበር፤ በሰርግ መልሳችን ቀን ግን ይሆናል ብዬ አሰቤ አላዉቅም ነበር" ሲሉ ሁኔታውን ይግልጻሉ።
ከዚያም "ለሙሽራዋ ባለቤቴና ለሚዜዎቼ ነገርኳቸዉና ወደ ሆስፒታሉ አመራሁ። የሙሽራዋ ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝ ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም፤" ያሉት ዶክተር በየነ "ቤተሰቦቿን ግን ተመልሼ ይቅርታ ለመጠየቅ ወስኜ ነበር ወደ ሆስፒታል የሄድኩት" ይላሉ።
አክለውም "ወደ ሆስፒታሉ ስደርስ የቀደ ጥገና ቲሙ ዝግጁ ስለነበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌ ቀዶ ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል" ብለዋል።
ዶክተር በየነ አበራ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሕክምና ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የስፔሻሊቲ መርሐግብራቸዉን ደግሞ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል።
ዶክተር በየነ አበራ እናመሰግናለን 👏
#TikvahEthiopia

👏770❤160🕊8🤔4😨3😡2
Ethiopian Incorporated : Transforming the way Businesses Run in Africa የተሰኘ መፅሀፍ ከቀናት በፊት ተመርቋል።
መፅሀፉ በአይ ኢ ኔትዎርክስ መስራች እና ዋና ስራ-አስፈጻሚ አቶ መርዕድ በቀለ የተጻፈ ነው።
ደራሲዉ አቶ መርዕድ በጣት ከሚቆጠሩ አፍሪካዊያን መሃል አንዱ በመሆን በ24 ዓመቱ ፤ በጊዜዉ የነበረዉን ዉስን የኢንተርኔት አቅርቦት እና ስለ ኢንተርኔት የነበረዉን የተገደበ ግንዛቤ ሳይገድበዉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ያደረገዉን CCIE ሰርተፊኬት ሊቀበል ችሏል፡፡
የ IE Network Solutions መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆነዉ አቶ መርዕድ በቀለ፣ በአሁን ሰዓት ከ200 በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠረ ካምፓኒ ባለቤት ነው።
ከቀናት በፊት ያስመረቁት መፅሀፍ ከዳበረ የስራ ፈጣሪነት እና የድርጅት አመራርነት በመነሳት የተጻፈ መሆኑ ተገልጿል።
መጽሀፉ በየትኛዉም የዕድሜ ክልል ላሉ ይስማማል የተባለ ሲሆን በተለይ ደግሞ የራሳቸዉን ድርጅት ለመፍጠር ህልም ኖሯቸዉ መንገዱን ማወቅ ለሚሹ ፣ በኢትዮጵያ ቢዝነስ በመስራትና ለማደግ ለሚሹ ፣ ለተለያዩ ድርጅት ባሌቤቶች እና ስራ ፈጣሪዎች እንዲሁም የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ገበያ አንድ እርምጃ ከፍ ማድረግ ለሚሹ የተጻፈ ነው ተብሏል።
@tikvahethmagazine

👏99❤21👍2😡2
ድብቁ የወሲብ ገበያ: ቴሌግራም ያቀጣጠለው የወሲብ አብዮት
ቴሌግራም በሀገራችን ኢትዮጵያ ሰፊ ተጠቃሚዎች ካሉት መተግበሪያዎች አንዱ ነው። ቴሌግራም ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችን ከደንበኞች ጋር ለማገናኘት፣ ለትምህርትና ለመረጃ ልውውጥ አወንታዊ ሚናን ይጫወታል።
በአንጻሩ ደግሞ ላልተረጋገጡ መረጃዎችና የሤራ ትንተና፣ ማንነትን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች፣ ለህገወጥ ንግዶች፣ ለገንዘብ ማጭበርበርና ለመሳሰሉት ተጠቃሚዎችን ማጋለጡን የተለያዩ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።
ምንተስኖት ደስታ በሥነ-ሕብረተሰብ (ሶሲዮሎጂ) ከሐረማያ ዩንቨርስቲ የተመረቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት በስንቅ ዩዝ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክት ማናጀር ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
በቴሌግራም ከሚታማባቸው ጉዳዮች አንዱ ስለሆነው ልቅ የወሲብ ገበያ ከኢትዮጵያ አንፃር የዳሰሰበትን ጹሑፍ በሐሳብ አለኝ ቅጽ 1 ዲጂታል መጽሔት ላይ አስነብቦናል።
ምንተስኖት በጹሑፉ በዚህ ላይ ከሚሳተፉ፤ ይኸው ተግባር ሱስ ከሆነባቸው ወጣቶችን ቃለመጠይቅ በማድረግና እና የተለያዩ ቻናሎችን በማጥናት ጥሩ ጹሑፍ አቅርቦልናል።
በዚህም፦
- ለዲጂታል ወሲብ አገልግሎቶች ከ500 - 3000 ብር እንደሚጠየቅ፤
- የህፃናት ወሲብ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ተፈላጊ ስለመሆኑ፤
- ስለባህል ህክምናና ማስታወቂያዎቹ፤
- ከመንግስት እና ከቤተሰበሰ ስለሚጠበቀው ነገር በጹሑፉ አንስቷል።
አንብቡት 👉 https://concepthub.net/article/4

😢121❤29👏21🤔15😡9😨5👍1🕊1
"በሰቆጣ ቃልኪዳን እስካሁን መድረስ የቻልነው ሀገሪቱ ካሏት ወረዳዎች ከአንድ አራተኛ በታች ነው " - ዶ/ር ሲሳይ ሲናሞ
በኢትዮጵያ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት በእድሜያቸው ሊደርሱበት የሚገባው ቁመት ላይ ያልደረሱ ወይም መቀንጨር ያጋጠማቸው ህጻናት ቁጥር 39 በመቶ ሲሆን 11 በመቶ ህጻናት ደግሞ መቀጨጭ እንዳጋጠማቸው ጥናቶች ያመላክታሉ።
ይህንን ሃገራዊ የህጻናት የመቀንጨር ምጣኔን ለመቀነስ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች ውስጥ የሰቆጣ ቃልኪዳን አንዱ ነው።
ይህ ቃልኪዳን የህጻናትን የመቀንጨር ምጣኔ መቀነስ ቢችልም እየተተገበረ የሚገኝባቸው ወረዳዎች ቁጥር ግን ሃገሪቱ ካሏት አጠቃላይ ወረዳዎች ሩቡን ያህል ብቻ መሆኑን በሰቆጣ ቃልኪዳን የፌደራል ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ክፍል ሲኒየር ፕሮግራም ማናጀር የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ ሲናሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የመቀንጨርን ምጣኔን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 2022 ዜሮ ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራበት ያለው የሰቆጣ ቃልኪዳን በአሁኑ ሰዓት በ 334 የኢትዮጵያ ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
ቃልኪዳኑ የሁለተኛ ምዕራፍ የአምስት አመት የማስፋፊያ ትግበራ ላይ ነው።
ዶ/ር ሲሳይ "ሃገራዊ የመቀንጨር ምጣኔ መረጃው 39 በመቶ ነው። እንደ ሰቆጣ ቃልኪዳን በአርባ ወረዳዎች ጀምረን ገና ዘንድሮ ነው 334 ወረዳዎች መድረስ የቻልነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም በሀገሪቱ ካሉ ወረዳዎች አንድ አራተኛ በታች ነው የሚሉት ዶ/ር ሲሳይ፥ "የኢትዮጵያ ወረዳዎች ከ 1,100 በላይ ናቸው የሰቆጣ ቃልኪዳንን ተጽዕኖ ለማየት በጣም ብዙ ስራ መስራት አለብን" ብለዋል።
ለዚህም ተግባራዊ የሚሆንባቸውን አካባቢዎች ከፍ አድርገን በርካታ ወረዳዎችን ካልደረስን ይህንን ሀገራዊ ቁጥር በፍጥነት መቀነስ አንችልም፤ ነገር ግን በልዩነት ይሄ ሥራ በተሰራባቸው አካባቢዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት አለ ሲሉ አክለዋል።
የሰቆጣ ቃልኪዳን ከ 7.8 ሚሊየን በላይ የሆኑ ህጻናትን እስከ 2022 ዓ/ም ድረስ ከመቀንጨር በመታደግ ሙሉ እድገታቸው ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ በ 2007 ዓ/ም ቃል የተገባበት ስምምነት መሆኑ ይታወቃል።

❤25👏5🕊5👍3🤔3😢2😡2
#EEU
° "የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኖች ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለባቸውን የኋላ ክፍያ በታህሳስ ወር በሚወጣው ቢል ላይ ተጨምሮ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡ " የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የተጠቀሙ ደንበኖች የፍጆታ ሂሳብ ላይ እና አዲስ ደንበኛ ማገናኘትን ጨምሮ ደንበኞች በሚፈፅሟቸው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
በዚህ መሠረት ደንበኞች ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ በሚከፍሉበት ወቅት የፍጆታ መጠናቸው ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ ከሆነ እላፊ የመጣው የፍጆታ መጠን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተሰልቶ ሂሳባቸው ላይ የሚደመር ይሆናል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ የሚደረገው ከህዳር ወር የክፍያ ደረሰኝ ጀምሮ ሲሆን፤ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኖች ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለባቸውን የኋላ ክፍያ በታህሳስ ወር በሚወጣው ቢል ላይ ተጨምሮ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
ዓመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያን በተመለከተ
ወርኃዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ መጠናቸው ከ50 ኪሎ ዋት ስዓት በላይ የሆኑ ደንበኞች 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ጋር የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ እየከፈሉ ይገኛሉ ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) ዓመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ መብት የተሰጠው ሲሆን ሁለቱ ተቋማት ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ስርዓትን በመጠቀም በየወሩ እንዲሰበሰብ ህዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።

😡51❤10🤔5🕊3