TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ5 ሰዎችን ህይወት አልፏል!

ከሀዋሳ ወደ አርሲ ነጌሌ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ #የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የምዕራብ አርሲ ዞን የትራፊክ መምርያ አስታወቀ ።

ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 ላይ በውጭ ሀገር ሆነው ለሲዳማ ህዝብ እኩልነት ሲታገሉ የቆዩትን እነ ፕሮፌሰር #ወላሳ_ላዊሶነንና ሌሎች የመብት ተሟጓቾችን ለመቀበል ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችን የያዘ ላንድ ኩሩዘር ከአርሲ ነጌሌ ወደ ሻሻመኔ በመጓዝ ላይ ከነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና ጋር አርሲ ነጌለ ወረዳ ቀርሳ #እላላ_ቀበሌ በመጋጨታቸው የደረሳ አደጋ መሆኑን የምዕራብ አርሲ ዞን የትራፊክ ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር #ጎሴ_ድኮ ገልፀዋል፡፡

በዚህ አደጋም የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰዉ ከባድ የአካል አደጋ ደርሷል፡፡

የተጋጩት ሁለቱ መኪናዎች ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ የገለፁት ኢንስፔክተሩ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነዉ ብሏል፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️ትላንት በምዕራብ አርሲ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ #የአምስት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ዘግበን ነበር። በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው አንድ ወጣት በህክምና ባለሞያዎች ህይወቱን ለማትረፍ የተደረገው ጥረት #ሳይሳካ ቀርቷል። በዚህም በትላንቱ የመኪና አደጋ በአጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈው ዜጎች ቁጥር #ስድስት (6) ሆኗል።

በTIKVAH-ETH ስም ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነጆው ጥቃት ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር፦
.
.
ትናንት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ በተባለ ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት #የአምስት ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቆ ነበር።

ማክሰኞ ዕለት በታጠቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት አምስት ሰዎች ሰንራይዝ በሚባል በአካባቢው የማዕድን ማውጣት ሥራ ላይ ለተሰማራ ኩባንያ የሚሰሩ እንደነበር ታውቋል።

በጥቃቱ የተገደሉት ሦስት ኢትዮጵያዊያን እና ሁለት የውጪ ሀገራት ዜጎች ሲሆኑ እነሱም የህንድና የጃፓን ዜግነት ያላቸው እንደሆ የአካባቢው ኮማንድ ፖስት አባል የሆኑት አቶ #አደም_ኢስማኤል ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከተገደሉት አራቱ ወንዶች ሲሆኑ አንዷ የውጪ ዜጋ ሴት ናት።

እነዚህ የጥቃቱ ሰለባዎች ከማዕድን ኩባንያው ጋር ይሰሩ የነበሩ ሲሆን አንደኛው የኩባንያው ባለቤት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

አቶ #አለማየሁ_በቀለ ይህንን የማዕድን ማውጣት ሥራ ለመጀመር #ሦስት ዓመታትን የፈጀ ጥናት ማከናወኑንና የምርት ሥራውን ለመጀመር በተቃረበበት ወቅት ከአራት ባልደረቦቹ ጋር በታጣቂዎቹ መገደሉን የቅርብ ጓደኛው አቶ አቦማ አምሳሉ ለቢቢሲ ተናግሯል።

አቶ አለማየሁ ከአንድ ወር በፊትም በሥራው አካባቢ በድንጋይ በተፈጸመ ጥቃት በመኪናው ላይ የመሰባበር ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፤ ከአካባቢው ወጣቶችና ህብረተሰብ ጋር ለመግባባትና ከሥራው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ለመወያየት ዕቅድ እንደነበረው ጓደኛው አቶ አቦማ ያስታውሳል።

አቶ አለማየሁ በቀለ ተወልዶ ያደገው ጊምቢ ውስጥ ሲሆን ነዋሪነቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነበር። እንዲሁም ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት፤ የመጀመሪያ ልጁም ገና አምስት ዓመቱ እንደሆነ አብሮ አደግ ጓደኛው ጨምሮ ገልጿል።

ከአቶ አለማየሁ ጋር አብረው በጥቃቱ ከተገደሉት አንደኛው የመኪናው ሹፌር ሲሆን ሌሎቹ ግን በማዕድን ሥራው የሚረዱት ባለሙያዎች ነበሩ። ጃፓናዊቷና ሕንዳዊው ሥራውን ለማቀላጠፍ በዕውቀትና በልምዳቸው እንዲያግዙት የቀጠራቸው ባለሙያዎች እንደሆኑም ተገልጿል።

ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የወጡ መረጃዎች የድርጊቱ ፈጻሚዎች ማንነታቸው እንዳልታወቀ የያመለከቱ ቢሆንም አመሻሽ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ታጣቂዎቹ "ኦነግ ሸኔ" የተባለው ቡድን አባላት መሆናቸውን ገልጸዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ጀነራል ረታ በላቸው እንደተናገሩት፤ አምስቱን ሰዎች በመግደል መኪናቸውን ያቃጠሉት "በአካባቢው እየተዳከመ የመጣው የሸኔ ቡድን አባላት ናቸው" በማለት የጸጥታ ኃይሉም አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።

ግድያውንና ምክትል ኮሚሽነሩ የተናገሩትን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ የኦነግ ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ ቶሌራ አደባን ቢቢሲ ጠይቆ "የድርጅቱን ወታደሮች በተመለከተ የዕርቅ ኮሚቴው የያዘው ጉዳይ በመሆኑ ሃሳብ መስጠት አንችልም" ብለዋል።

ነገር ግን በተፈጸመው ግድያ እጅጉን ማዘናቸውንና አስፈላጊው ማጣራት መደረግ እንዳለበት አቶ ቶሌራ ጨምረው ተናገረዋል።

ቀደም ባሉት ጊዜያት በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና የጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ የኦነግ ስም በሚነሳበት ጊዜ ድርጅቱ በሚሰጠው ምላሽ ላይ መንግሥት ላይ ክስ ያቀርብ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከዚህ ተቆጥቧል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ። የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ዛሬ በሰሜን ሸዋ " መሀል ሜዳ " ላይ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። " ብለዋል። ዶ/ር ዐቢይ የግድያውን ሁኔታ በተመለከተ #ዝርዝር_መረጃ…
" አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገድለዋል " - የአማራ ክልል መንግስት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባወጣው የሀዘን መግለጫ በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው ግድያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ፤ የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን ሠርተው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን ሲመለሱ በመንዝ ጓሳ ላይ መሆኑንና ግድያው የተፈፀመው በታጠቁ ኢ-መደበኛ ኃይሎች እንደሆነ ገልጿል።

ከእሳቸው በተጨማሪ በግል ጥበቃዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ጥቃት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን እስካሁን #የአምስት_ሰዎች ሕይወት ስለማለፉ መረጃው እንደደረሰው ክልሉ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ክልሉ በመግለጫው፥ "ይህንን የሽብር ሥራ እየሠሩ ያሉ እንዲህ አይነት ኃይሎች ላይ የክልሉ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል፡፡ የጥቃቱን አድራሾችም ለሕግ ያቀርባል " ብሏል።

አክሎም፥ "የጥፋት ኃይሎች ከዚህ በላይ ዓላማ ያላቸው እና ክልሉን የማፍረስ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በኋላ የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ እናረጋግጣለን " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia