TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬇️

በቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የአካል ጉዳት፣ #ዘረፋና ንብረት እንዲወድም ከመስከረም 1 ቀን 2011 ጀምሮ በመቀስቀስ እና #ገንዘብ በማከፋፈል ግጭቱ እንዲነሳ በማድረግ የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦችን የፌደራል ፖሊስ ፍረድ ቤት አቀረበ።

በፌደራልና በኦሮሚያ ፖሊስ ለሁለት ተከፋፍሎ የሚከናወነው ምርመራ የቀጠለ ሲሆን፥ ትናንት ከሰዓት በኋላ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ ችሎት 1ኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት ስድስቱ ተጠርጣሪዎች ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆባቸዋል።

#ተጠርጣሪዎቹ ሳምሶን ጥላሁን፣ ዓለሙ ዋቅቶላ፣ ቡልቻ ታደሰ፣ ሀሺም አህሚድ፣ ሽፈራው ኢራና እና ኢሉ ዳንኤል ሲሆኑ፥ ነዋሪነታቸው በቡራዩ፣ ገፈርሳና ከታ አካባቢ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹ #የተጠረጠሩበት በቡራዩና አካባቢዋ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደም እና ዘረፋ የተጠረጠሩ ናቸው በማለት መነሻ መረጃ እንዳገኘባቸው አስረድቷል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ድርጊቱን አልፈፀምንም ሲሉ አስረድተዋል።

ክርክራቸውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራውን በ14 ቀናት ውስጥ አጠናቆ እንዲቀረብ በማዘዝ ለመስከረም 24 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው ካሉ ግለሰቦች መካከል 45 ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ዛሬ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ በረከት ስምዖን #ኮምፒውተር#ስልክ እና #የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት #ውድቅ አድርጎባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ ከዚህ በፊት ምስክሮችንና የሕግ ባለሞያዎችን ምክር ለማገኘት እንዲረዳቸው የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት እንዲሟላላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ሆኖም ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ኮምፒዩተሮችና የስልክ አገልግሎት በማረሚያ ቤቱ ስለሚገኙ ተጠርጣሪዎቹም በዛው እንዲገለገሉ በማለት የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄውን ዛሬ ወድቅ ማድረጉን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ እንደሌሎች ጠጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርበውን ማንኛውንም ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ እለት የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ #ተጠርጣሪዎቹ ለመጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia