TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የገዛ ልጁን የደፈረው አባት በ15 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ።

በራሱ ልጅ ላይ #በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው አባት በፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

የድርጊቱ ፈፃሚ ሃይማኖት ስዩም የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ስላሴ ማሪያም ቤተክርስቲያን ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

ይኸው ግለሰብ ከታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2014 ዓ.ም ባሉ የተለያዩ ቀናት በራሱ ልጅ ላይ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅሟል።

ተከሳሹ የአስገድዶ መድፈር የፈፀመው በ15 ዓመት ልጁ ላይ ሲሆን ልጁን በማስገደድ በተደጋጋሚ ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት እና በዚሁ ምክንያትም ተበዳይ ያረገዘች በመሆኑ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር እና በዘመዳሞች መካከል የሚፈጸም የግብረ ስጋ ግንኙነት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ሴቶች እና ህጻናት ምድብ ችሎት የቀረበው ተከሳሽ የክሱ ዝርዝር በችሎት ተነቦለት የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸሙ ሲጠየቅ ድርጊቱን አንድ ጊዜ ብቻ በማስገደድ የፈጸመ መሆኑን አምኖ ነገር ግን እርግዝናውን እንደማይቀበል ክዶ ተከራክሯል።

ዐቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ዐቅርቦ ክሱን በበቂ ሁኔታ ያስረዳ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የመከላከል መብቱ ታልፎ የጥፋተኝነት ፍርድ ተወስኖበታል፡፡

በዚሁ መሰረት ፍርድ ቤቱ የካቲት 14/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ15 ዓመት ከ8 ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

More @tikvahethmagazine
#GERD🇪🇹

" ግብፅ #የቅኝ_ግዛት ዘመን አስተሳሰቧን ይዛ በመቀጠል ወደ ስምምነትና ትብብር የሚወስደውን መንገድ ዘግታለች " - ኢትዮጵያ

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን አዲስ አበባ ውስጥ የሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ሂደትን የተመለከተ መመሪያ ላይ የሦስትዮሽ ድርድር ሲያካሂዱ ነበር።

ድርድሩ ያለ ስምምነት ነው የተጠናቀቀው።

ኢትዮጵያ ምን አለች ?

- ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ እና በፍትሐዊ ድርድር የሶስቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ የመፍትሔ ሀሳብ ላይ ለመድረስ ያላትን ቁርጠኝነት ይዛ እንደምትቀጥል ገልጻለች።

- አራት ዙር ድርድር ተካሂዷል ፤ ይህ ድርድር የተካሄደው በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና በፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ የጋራ መግባባት ነው።

- በአራት ዙሮች ኢትዮጵያ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ልዩነቶችን ለመፍታትና የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት አድርጋለች።

- ግብፅ #የቅኝ_ግዛት ዘመን አስተሳሰቧን ይዛ በመቀጠል ወደ ስምምነትና ትብብር የሚወስደውን መንገድ ዘግታለች።

- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ አሞላል እና ዓመታዊ አሰራር መመሪያ እና ደንቦች ላይ የተደረገው ድርድር በሶስቱ ሀገራት መካከል መተማመን ለመፍጠር እንጂ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ የኢትዮጵያን መብት ለመንጠቅ ያለመ አይደለም።

- ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ ላይ በመመስረት የአሁንና የመጪውን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት ጥረቷን አጠናክራ ትቀጥላለች።

- አራተኛው ዙር ድርድር ከተጠናቀቀ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ቻርተር እና የአፍሪካ ህብረት ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌን የሚጻረር መግለጫ ግብጽ አውጥታለች። ኢትዮጵያ በግብፅ በኩል የቀረበባትን የተሳሳተ መረጃ አትቀበለውም።

ግብፅ ምን እያለች ነው ?

* " ኢትዮጵያ የሦስቱንም አገራት ጥቅም ሊያስጠብቅ እና ሊያስማማ የሚችል የሕግም ሆነ የቴክኒክ መፍትሄዎችን ለመቀበል ዝግጁ አይደለችም " የሚል ነገር ይዛ ብቅ ብላለች።

* " የግድቡን አሞላል እና ኦፕሬሽን በቅርበት በመከታተል መብቴን አስከብራለሁ " ስትልም ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥታለች።

* ግብፅ " በግድቡ ምክንያት የትኛውም አይነት ጉዳት ቢደርስብኝ በዓለም አቀፍ ቻርተሮች እና ስምምነቶች መሠረት የውሃ ድርሻዬን እና ብሔራዊ ደኅንነቴን የመጠበቅ መብቴ የተጠበቀ ነው " ስትልም መግለጫ አውጥታለች።

🇪🇹 ኢትዮጵያ #በተደጋጋሚ ጊዜ አንዳቸውም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በአባይ ግድብ ምክንያት ጉዳት እንደማይደርስባቸው ይልቁንም እነሱኑ እንደሚጠቅም አሳውቃለች።

@tikvahethiopia
#የመምህራን_ቅሬታ #ምላሽ

ለ487 ' የአዲአርቃይ ወረዳ ' መምህራን የ22 ወራት የደረጃ ዕድገት ደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ማሳደሩን የሰሜን ጎንደር ዞን መምህራን ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ፤ " በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን "  የሚል ምላሽ ሰጥቶናል።

የሰሜን ጎንደር ዞን የመምህራን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሀብታሙ አቸነፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

- የመምህራንን #የመልካም_አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ የሆነ የፖለቲካ የመንግሥት አመራር ባለመፈጠሩ ምክንያት 487 የአዲአርቃይ ወረዳ መምህራን ከጥር 1/2014 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ በጊዜ ቆይታ የደረጃ እድገት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ይህ በመምህራን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የቅሬታ ምንጭ ሆኖብናል።

- ለመምህራን ከጥር 01/2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2015 ዓ.ም የደረጃ እድገታቸው እንደሚያድግና ለእድገታቸው የሚሆን በጀት ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም በሥማቸው ተይዞ ነበር። ይህንን በጀት ' አዘዋውረን ለሰላም ማስከበር አውለነዋል' ነው የሚለው የአስተዳደር ምክር ቤቱ።

- ጥያቄያችንን #በተደጋጋሚ አቅርበን ምላሽ የሚሰጥ የመንግሥት አካል አላገኘንም።

- ባለፈው ዓመት በወረዳው ላይ በነበረ አንድ ጉባኤ ' የመምህራን ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ ነው፣ በአዲሱ በጀት ዓመት ጥያቄውን እመልሳለሁ ' የሚል ምላሽን ሰጠ #አስተዳዳሪው። በዚህ ዓመት ደግሞ ፦
* ሀምሌ፣
* መስከረም፣
* ጥቅምት ወራት ላይ ተጠየቀ አሁን የመጨረሻው ውሳኔ ' እኔ በጀቱን አላውቅም ፣ በወቅቱ የነበረውን አስተዳዳሪ በጠየቃችሁ ፣ እኔ አሁን የምከፍልበት ኮንዲሽን የለም ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው ፤ በዚህ መምህራን በጣም #ተበሳጭተው ነው ያሉት።

- መምህራን አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው ለመጠየቅ ሲሄዱ 'እናስራችኋለን፣ እንመታችኋለን' የሚል ተፅእኖ አለ።

- በወቅቱ የነበረው ችግር የሁላችንም ችግር ቢሆንም ደመወዝ ቀጥታ ተከፋይን አንስቶ ' ለሰላም ማስከበር ' በሚል ላለአስፈላጊ ጥቅም ማዋል ተገቢ አይደለም። ላለአስፈላጊ ጥቅም ነው የዋለበት ያልኩት ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኮማንድ ፖስት የትዕዛዝ አቅጣጫ ተሰጥቶ የነበረው ሁሉም ደመወዝ ለሰላም ማስከበር ይሆናል የሚል ሳይሆን፣ 'የሥራ ማስኬጃ 40%ን ተጠቀሙ' የሚል ስለነበር ነው።

- እንደ 'ሰሜን ጎንደር ዞን' ብዙ ወረዳዎች ተሳትፈዋል በጦርነቱ። ጠለምት ተሳትፏል፣ ዳባት ተሳትፏል ነገር ግን አንድም ከበጀት ጋር የተያያዘ ደመወዝ የተነሳበት ወረዳ የለም። በዞናችን አሥር ወረዳዎች አሉ ሙሉ በሙሉ የደረጃ ዕድገታቸውን እየከፈሉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። #አዲአርቃይ ግን እንዲህ አይነት ችግር ገጥሞናል።

- ያልተከፈለውን የደረጃ እድገት ምን ያህል እንደሆነ አላሰላሁትም፣ ግን ቢያንስ ለ487 መምህራን ዝቅተኛ 800፣ ከፍተኛ እስከ 2,000 ብር የደረጃ እድገት ያገኛሉ። ነገር ግን ይኸው እንግዲህ አሁን ጥር ወር ሲገባ 2 ዓመታት ሊሆነው ነው ሳይከፈል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ " የመምህራኑን #የደረጃ_እድገት ደመወዝ ለምን እስካሁን ድረስ አልተከፈለም ? " ሲል የአዲአርቃይ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አረቡ ጆርጌ ጠይቋል።

አቶ አረቡ ጆርጌ " አሁን ያለበት ሁኔታ በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን " ሲሉ መልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " መምህራኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እንዳልተከፈላቸው፣ በመጨረሻም በጀቱ ለሌላ ጥቅም እንደዋለ " እንደገለፁለት ለኃላፊው #በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

በተጨማሪ ፦

* ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለምን ገንዘቡን አልከፈላችሁም ?

* አሁን ለመክፈልስ ምን የታሰበ ነገር አለ ? ብለን ጠይቀናቸዋል።

ኃላፊው " ኦሬዲ ጠይቀዋል በጀት ተይዞ እንደሚከፈል ብቻ ነው የነገርናቸው እንጂ ለዚህ የተመደበ #ለሌላ ጥቅም የዋለ ገንዘብ የለም " ብለዋል።

" መከፈሉ ግዴታ ነው፣ እንደ ተቋም እንደ አስተዳደር ምክር ቤትም ' አይከፈልም ' የሚል ማስተባበያ አይኖረንም ምክንያቱም ደመወዝ ስለሆነ " ያሉት ኃላፊው፣ " ለሁለት ዓመታት ያክል የገቢ መሰብሰብ ችግር ስለነበር በጦርነቱ ምክንያት በጀቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና ነው ያሳደረው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስለዚህ እኛም አሁን የያዝነው ፕሮግራም ሙሉውን እንኳ ባይከፈል እየተከፈለ (የአመቱን ወደ 6 ወራት፣ የ6 ወራቱን ወደ ሦስት ወራት እየተደረገ በጀት እየያዝን እንከፍላለን እንጂ አይከፈልም የሚል አቋም የለም። ተገቢነትም የለውም " ብለዋል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia