ፈ ተ ና🌺
❣ :¨·...............:¨·.❣
♥️ ክፍል 5
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
ውጪ እንኳን ላድር አምሽቼ የማላውቅ ልጅ ዛሬ ሊያውም ከማላፈቅረው ወንድ ጋር ተኝቻለሁ ግም ምን ልበል ልናደድ ወይስ ደስ ልሰኝ ምንም አላውቅም ቀስ ብዬ የለበስኩትን ልብስ አየሁት እናም እንደለበስኩት ነው እኔ ከማንም ወንድ ጋር ተኝቼ አላውቅም ያም ማለት ድንግል ነኝ ግን ምንም አይነት ደም አይታየኝም ግራ ገባኝ ወንድ ልጅ ነው አብሬው እስከመተኛት ደርሼ ምንም አላረግንም ማለት አይታሰብም ... ነቅቶ የተፈጠረውን እስኪነግረኝ ጓጓው ... እኔ በጭንቀት ተጣጥፌ ወንበር ላይ ተቀምጬ እንዳቀረቀርኩ ነቃ በስስት ተመለከተኝ አይኖቼ እምባ አቀረሩ አንድ ጥያቄ እንዳለኝ ያወቀ ይመስል ለመናገር ጉሮሮውን ጠራረገ ከዛም ትላልቅ
አይኖቹን በሁለት እጆቹ ያሻቸው ጀመር ሲነቃ ደፍርሰው ከነበረው በላይ ደፈረሱ ደና አደርሽልኝ ቆንጆ አለ ይሄኔ ያላባት ያሳደገችኝ እናቴ ሳልነግራት አድሬ ምን ያህል እንደምትጨነቅ እና ሉሌ ከሌላ
ወንድ ጋር መማገጤን ሲያውቅ ምን ሊለኝ እንደሚችል አስቤ እራሴን ጠላሁት የማረባ ሴት መሆኔ ታወቀኝ ... ዝምታዬ ያስፈራው ናቲ ከተኛበት አልጋ ወርዶ ከተቀመጥኩበት ወንበር ላይ አንስቶ አልጋው ላይ በጀርባዬ አስተኛኝ የልብ ምቴ ጨመረ ግን ካንደበቴ ቃል አሎጣም ... ክንዱን አንተርሶኝ ከጎኔ
ተኛ ... ደንግጠሻል? አለኝ አይ አልደነገጥኩም አልኩት እሺ ማታ
ምን እንደተፈጠረ ታስታውሻለሽ ሲል ጠየቀኝ አ...ይ አልኩ እሺ እነግርሻለሁ ሲል ቀጥሎ የሚለውን ለመስማት ካንገቴ ቀና አልኩ ከዛም እ...እኔ ማወቅ የምፈልገው አንድ ነገር ነው እናም ወሲብ
ፈፅመናል? ብዬ ጠየኩት ከት ብሎ ሳቀ ይበልጥ ግራ ገባኝ ... ዝም ብዬ ተመለከትኩት ልክ ስቆ ሲጨርስ ... በፍፁም አለኝ ኮራ ብሎ አላመንኩትም ... ብፈልግ እንኳ ሰክረሽ አላደርግም አለኝ ይሄኔ በልቤ ፈጣሪን አመሰገንኩ... ከዛ ቀን ቡሃላ እኔም ዱርዬ የምባል አይነት ሴት ሆንኩ መጠጥ
እጠጣለው ሺሻ ቤት ቤቴ አርጌዋለው ታድያ እናቴም በኔ ማዘኗን ቀጥላለች ናቲ በርግጥም ብዙ ግዜ መክሮኛል ከሱ ጋር ስሆን መጠጥ እንኳ ብዙ አይፈቅድልኝም ሺሻም ፈፅሞ አላጨስም ግን ከሱጋ የምሆነው ውስን ጊዜአቶችን ነው ምክንያቱም እሱ ስራ አለው... በዚ መልኩ ወራት አለፉ እናም ከዛ በላይ ክብሬን ማስጠበቅ አልቻልኩም ከናቲ ጋር አንሶላ ተጋፈፍን ... ይሄኔ ከዚ ቡሃላ ፍቅር
የለም ብዬ አመንኩ እናም ስራ ፈልጌ ተቀጠርኩ ግን እቤት የምገባው ከምሽቱ 4፡00 ቡሃላ ነው ማንም ሰው ሲመክረኝ
ያናደኛል ናቲ ፍቅረኛዬ ይሁን ወንድማዊ ጓደኛዬ ምኑንም አላውቀው ግን አብረን ማደር አዘወተርን ... ፍቅረኛ እይዛለው 3ወር ሳይሞላ እጣላዋለሁ ሌላ ፍቅረኛ
እይዛለው ከዛም ከሱጋም እፋታለው ህይወቴ በዚ መልኩ እየቀጠለ ልክ ባመቴ ልኡል ደወለ ስልኩን ሳየው የደነገጥኩት መደንገጥ አሁን ድረስ ትዝ ይለኛል ግን አላነሳሁለትም የሚገርመው ግን ስራ ቦታዬን አፈላልጎ መጣ ሳየው የማደርገው ጠፋኝ ፍቅር እንዳዲስ አገረሸብኝ ግን ህይወቴ የተበላሸው በሱ
ስለነበር ዳግም መጎዳት አልፈለኩም ግን ሊተወኝ አልቻለም ደጋግሞ ይቅርታ ጠየቀኝ... አንድ ቀን ከስራ ስወጣ ልኡል ከእናቱ ጋር እየጠበቀኝ አገኘሁት ደንግጬ ቆምኩ እናቱም የኔ ቆንጆ ደሞ ስታምር ብለው ይስሙኝ ጀመር ግራ ገብቶኝ ዝም አልኩ ልጄን ከአጉል ሱስ አወጣሽልኝ የጠፋውን ልጄን መለስሽልኝ እደጊልኝ አሉኝ አይናቸው የደስታ እምባ አቅርሮ... እኔ በሱ ምክንያት ህይወቴ ተመሰቃቅሎ እናቴ በኔ ሀሌም ታዝናለች ልኡሌ ደግሞ በኔ ተለውጧል ግን እንዴት
ቢያፈቅረኝ ኖሮ ሌላ ሴት እንዳለው አይደብቀኝም ነበር ይሄን ያህል ግዜም አይጠፋም ነበር... ወደኋላ ተመልሼ ሳስብ እንባዬ ይምዘብ ጀመር ከዛም
እናትና ልጅ በቆሙበት ትቻቸው ሮጥኩ.....
꧁༺༒༻꧂
✎ ክፍል ስድስት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
@Tiburning
@tiburning
@tiburning
Contact👉 @tiburning
🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳
❥❥________⚘_______❥❥

COVID - 19 #UPDATE 🌍❗️
በቫይረሱ የተጠቁ 8,326,000 +
•በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ 448,000 +
•ከቫይረሱ ያገገሙ 4,357,000 +
•አሁን ቫይረሱ የሚገኝባቸው 3,521,000 +
•በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኙ 3,466,000 +
•በአስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ 54,000 +
አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችና ጥቆማወችን በዚህ አድርሡኝ ፡-
@Tiburning@Tiburning