Real Business Ideas/ኑ ቢዝነስ እንስራ
46 subscribers
64 photos
2 videos
8 files
31 links
Do you want to be a millionaire?
Just join this channal
እውነት እላችዋለው ኑሮን እንበቀላት
Download Telegram
ኢትዮ-Info & Book:
#BREAKING

መጋቢት 3/2012 ዓ/ም የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በሀገራችን ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት (16) ደርሷል፡፡

#MoH

አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችና ጥቆማወችን በዚህ አድርሡኝ ፡-
@Tiburning
ኢትዮ-Info & Book:
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች 16 ደረሰዋል!

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-

ታማሚ 1 ፦

የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ ሲሆኑ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከኮንጎ ብራዛቪል የተመለሱ ናቸው፡፡ መጋቢት 13፣2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 6 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ታማሚ 2፦

የ61 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ በተገኘው መረጃ መሠረት ግለሰቡ የውጭ የጉዞ ታሪክ ባይኖራቸውም በስራ ባህሪያቸው ምክንያት ከአንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ጋር ግንኙነት ነበራቸዉ፡፡ ታማሚው ግለሰብ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም የህመም ስሜት ሲሰማቸው ራሳቻውን አግልለው እንደቆዩና መጋቢት 16፣ 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ሪፖርት ባደረገው መሰረት በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚው በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 24 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ታማሚ 3 ፦

የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የመጨረሻ ጉዞዋም መጋቢት 12፣ 2012 ዓ.ም እስራኤል ሀገር ደርሳ የተመለሰች ናት፡፡ ግለሰቧም በቀን 16፣ 2012 ዓ.ም በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ከታማሚዋ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 7 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን ማጣራት ሂደት
እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ታማሚ 4 ፦

የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ቢሆንም የበሽታው ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር የነበራት ግንኙነት እየተጣራ መሆኑ እና ግለሰቧም በቀን 17/2012 ዓ/ም በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል፡ በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡

#MoH

አሥተያየቶችን @Tiburning
#UPDATE

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቀረበው ጥሪ ተከትሎ በዛሬው እለት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡

በዚህም ፦

1. አርቲስት ቴዲ አፍሮ 1.2 ሚሊዮን ብር
2. ታፍ ኦይል 2 ሚሊዮን ብር
3. VSO 1.2 ሚሊዮን ብር
4. አማጋ ኃ/የተ/ግ/ማ 1 ሚሊዮን ብር
5. ለገሃር ሳይት ኮንትራክተርስ 3 ሚሊዮን ብር
6. ካን ቤቢ ዳይፐር 500 ሺ ብር
7. GMM ጋርመንት ኃ/የተ/ግ/ማ 500 ሺ ማስክ
8. ሚአን አግሮ ኢንዱስትሪ 20 ሺ ብር
9. የወልዋሎ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ 30 ሺ ብር
10. አንበሶ ወ/ገብርኤል መኖሪያ ቤታቸውን
11. ኢትዮጲስ ኮሌጅ ኮሌጃቸውን
12. ቤተልሄም ጥላሁን የመስርያ ቦተታቸውን
13. ውብሸት ተክሌ ዋቅጂራ ህንጻቸውን
14. አስራት ካሳዬ ሆቴላቸውን
15. ቫኮም ኢንጂነሪንግ 5 ኩንታል እህል
16. ካህናት አለምአቀፍ ቤ/ክርስቲያን የአምልኮ ስፍራ
17. ሂንዲያን ትምህርት ቤት ት/ቤታቸውን
18. ሄኖክ ፣ ፍትሃዊና ተመስገን እህልና የንጽህና መጠበቂያ
19. አድዋ ዱቄት ፋብሪካ 13ሺ ካሬ ስፋት ያለው አዳራሽ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን ጥሪ ተከትለው ድጋፍ እያደረጉ ላሉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከከንቲባ ፅህፈት ቤት!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መረጃ❗️

እንደ ዪኒስኮ ገለፃ ከሆነ በአለም ላይ 1.52 ቢልየን ልጆች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ትትምህርት ቤታቸው ተዘግቶ ትምህርት አቁመዋል።

[ ተስፋዬ ጌትነት ]

አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችና ጥቆማወችን በዚህ አድርሡኝ ፡-
@Tiburning_bot
COVID - 19 #UPDATE ❗️

በቫይረሱ የተጠቁ 550,000 +

በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ 24,000 +

ከቫይረሱ ያገገሙ 128,000 +

አሁን ቫይረሱ የሚገኝባቸው 395,000 +

በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኙ 374,000 +

በአስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ 20,000 +

አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችና ጥቆማወችን በዚህ አድርሡኝ ፡-
@Tiburning_bot
‼️ሁላችሁም አንብቡት‼️

ኧረ ሰወች አዲስ አበባን አንድ ነገር ይሠራለት።እኔ የኢትዮጵያዊን ጉዳት እግዜያብሔር አያሣየኝ አያሠማኝ ።ከቤት ሣልወጣ ውየ ምሽት ለብቻየ ጉዞ (walk)ለማድረግ ወጣሁ ሐበሻ በሙሉ በየመንገዱ ሥብሠባ አዳራሽ የሚመሥል ድብልቅልቅ ያለ መሥተጋብር ሠው እየተገፋፋ ይሔዳል።ምኑን ተጠነቀቁት፤ ምንም። አዝኜ ተመልሼ ገባሁ። የሚሠማ ህዝብ የለም።ስለቫይረሱ የማያወራ የለም።ጣሊያን ብዙ ሰው እንዲህ ሆነ አሜሪካ ስፔን ምናምን በቃ እንደታሪክ ያወራል።ወቅታዊነቱን አስከፊነቱን ጥንቃቄ ማድረግ ምኑም አይደለም።ኧረ ሰወች ምን ይሻላል አዲስ አበባ ሠው ። ኧረ የመንግስት ያለህ።ከሰፈራችን ጉልት ገበያ አለ በዚያ የሠው ብዛት ማለፊያ የለም።የመንገድ ዳር ህገወጥ ነጋዴው መውጫ መግቢያ የለም ሠው በሰው ተደራርቦ ነው የሚያልፍ እኔ ተስፋ ቆረጥኩኝ በህዝባችን። ግን ደግሞ በኑሮ ውድነት ፤ ከእጅ ወደአፍ ኑሮ ተገደደ።
እና አ.አ. ተው ተመከሩ፣ተው ራሳችንን እንጠብቅ የታላላቅ ሠውችን መመርያ እና ምክር ተግብረን ይሔን ጊዜ እንለፈው ። አካላዊ መራራቅ(physical distance) መፍትሔ ከሆነ ዋጋ የማይከፈልበት ዜዴ ነው እንተግብረው።ማስቸካከያ social distance መባል ግን የለበትም። ያም ሆነ ይህ አ.አ እባክሽ ከጣሊያን ተማሪ፣ ከስፔን ተማሪ።
/////ትዝብቴን ምክሬን የሠጠዋቹህ ምህረቱ ከአ.አ.///// Thanks a Lot.
በአፍሪካ_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭት_ወቅታዊ_መረጃ

✅እሑድ መጋቢት 20-2012 እስከ ጠዋቱ 01:00 ድረስ
✅እስካሁን በአፍሪካ 4,232 የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኝተዋል
✅በአፍሪካ 46 ሀገራት ላይ ቫይረሱ ተሰራጭቷል
✅በአህጉሪቱ የተመዘገበው ጠቅላላ ሞትም 133 ደርሷል
✅አገግመው ከሆስፒታል የወጡት 249 ደርሰዋል
✅ደቡብ አፍሪካ በርካታ ኬዝ የተገኘባት ሀገር ነች (1,187)
✅ግብፅ በቫይረሱ በርካታ ሰው የሞተባት ሀገር ነች (36)
✅19 የአፍሪካ ሃገራት ላይ የሞት ሪፖርት ተደርጓል
✅10 የአፍሪካ ሃገራት ከ100 በላይ ኬዝ አለባቸው
✅እስካሁን 8 የአፍሪካ ሀገር ላይ ቫይረሱ አልገባም

✅ግብፅ በ24 ሰዓት 40 ኬዝና 6 ሟች አስተናግዳለች
✅ደቡብ አፍሪካ በ24 ሰዓት 17 አዲስ ኬዝ አግኝታለች
✅አልጄሪያ በ24 ሰዓት 45 ኬዝና 3 ተጨማሪ ሞት አስተናግዳለች
✅ሞሮኮ በ24 ሰዓት 57 ኬዝና 2 ተጨማሪ ሞት አስተናግዳለች
✅ቱኒዚያ በ24 ሰዓት 51 ኬዝና 1 ተጨማሪ ሞት አስተናግዳለች
✅ቡርኪናፋሶ በ24 ሰዓት 27 ኬዝና 1 ሞት አስተናግዳለች
✅ጋና በ24 ሰዓት 4 ኬዝና 1 ተጨማሪ ሞት አስተናግዳለች
✅ዲ.ሪ.ኮንጎ በ24 ሰዓት 14 ኬዝና 1 ሞት አስተናግዳለች
✅ማሊ በ24 ሰዓት ውስጥ 7 ኬዝ ስታስተናግድ በሀገራ የመጀመሪያ የሆነ 1 የሞት ሪፖርትም አድርጋለች
✅በሀገራችን ትላንት አንዱ ታማሚ ሙሉ ለሙሉ ከቫይረሱ በማገገሙ እና ከዚህ ቀደም 2 ጃፓናውያን ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው መሄዳቸውን ተከትሎ በጠቅላላው አሁን በሀገራችን ያሉት ታማሚዎች ወደ 13 ዝቅ ብለዋል
✅ጎረቤት ሀገራትን ስንመለከት (ኬኒያ 38 ኬዝና 1 ሞት ፣ ጂቡቲ 14 ፣ ኤርትራ 6 ፣ ሱዳን 5 እና ሶማሊያ 3 ኬዞች አሉባቸው)

✅ በአፍሪካ እስካሁን ቫይረሱ ያልታየባቸው 8 ሀገራት እንዳሉስ ያውቃሉ?
√ ቦትስዋና
√ ቡሩንዲ
√ ኮሞሮስ
√ ሌሴቶ
√ ማላዊ
√ ሳኦ ቶሜ
√ ሴራሊዮን
√ ደቡብ ሱዳን

🔴 በአፍሪካ አጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ይህን ይመስላል
🇿🇦 1,187 ደ. አፍሪካ
🇪🇬 576 ግብፅ
🇩🇿 454 አልጄሪያ
🇲🇦 402 ሞሮኮ
🇹🇳 276 ቱኒዝያ
🇧🇫 207 ቡርኪናፋሶ
🇬🇭 141 ጋና
🇸🇳 130 ሴኔጋል
🇲🇺 102 ሞሪቲየስ
🇨🇮 101 ኮትዲቯር
🇨🇲 91 ካሜሮን
🇳🇬 97 ናይጄሪያ
🇨🇩 65 ዲ.ሪ. ኮንጎ
🇷🇼 60 ሩዋንዳ
🇰🇪 38 ኬንያ
🇺🇬 30 ኡጋንዳ
🇿🇲 28 ዛምቢያ
🇲🇬 26 ማዳጋስካር
🇹🇬 25 ቶጎ
🇲🇱 18 ማሊ
🇪🇹 16 ኢትዮጵያ
🇹🇿 14 ታንዛኒያ
🇩🇯 14 ጅቡቲ
🇬🇶 12 ኢኳቶሪያል ጊኒ
🇳🇪 10 ኒጀር
🇸🇿 9 ኢስዋቲኒ
🇬🇳 8 ጊኒ
🇲🇿 8 ሞዛምቢክ
🇳🇦 8 ናሚቢያ
🇸🇨 8 ሲሼልስ
🇬🇦 7 ጋቦን
🇿🇼 7 ዚምቧቡዌ
🇧🇯 6 ቤኒን
🇪🇷 6 ኤርትራ
🇨🇻 6 ኬፕ ቨርዴ
🇲🇷 5 ሞሪታኒያ
🇸🇩 5 ሱዳን
🇦🇴 5 አንጎላ
🇨🇬 4 ሪ.ኮንጎ
🇨🇫 3 ሴንትራል አፍሪካ
🇬🇲 3 ጋምቢያ
🇹🇩 3 ቻድ
🇱🇷 3 ላይቤሪያ
🇱🇾 3 ሊቢያ
🇸🇴 3 ሶማሊያ
🇬🇼 2 ጊኒ ቢሳው

🔵 በአፍሪካ ሞት ያስተናገዱ ሀገራት 15 ደርሰዋል

🇪🇬 36 ግብፅ
🇩🇿 29 አልጄሪያ
🇲🇦 24 ሞሮኮ
🇧🇫 11 ቡርኪናፋሶ
🇹🇳 8 ቱኒዚያ
🇨🇩 6 ዲ.ሪ. ኮንጎ
🇬🇭 5 ጋና
🇲🇺 2 ሞሪቲየስ
🇨🇲 2 ካሜሮን
🇳🇬 1 ናይጄሪያ
🇰🇪 1 ኬንያ
🇹🇬 1 ቶጎ
🇳🇪 1 ኒጀር
🇬🇦 1 ጋቦን
🇿🇼 1 ዚምቧቡዌ
🇸🇩 1 ሱዳን
🇨🇻 1 ኬፕ ቬርዴ
🇬🇲 1 ጋምቢያ
🇿🇦 1 ደ. አፍሪካ

───────────────────────────

√ የኮሮና ቫይረስን በጋራ እና በግል እንከላከል
✅የእጃችንን ንፅህና በአግባቡ እንጠብቅ
✅ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ አንገኝ
✅ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት እንጠብቅ
✅የተጨናነቁ የትራንስፖርት አመራጮችን አንጠቀም
✅የጤና ባለሞያዎችን ምክር ሁሌም እንተግብር
✅የጤና ሚኒስቴር መምሪያዎችን እንከታተል
✅ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ትክክለኛ መረጃ ከWHO ፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከህበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ያግኙ!

በተጨማሪ በነፃ የስልክ መስመሮች 8335 / 952 ላይ ደውለው መረጃዎችን ያግኙ

🦠 በከኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ውስጥ

√ ከፍተኛ ትኩሳት
√ ሳል
√ ለመተንፈስ መቸገር ዋነኞቹ ናቸው

#በቅድመ_ጥንቃቄ_እና_በፀሎት_እንበርታ

√ መረጃ አይናቅም ስለዚህ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ
─────────────────
───────────────────────────
#Corona_Virus_Update

የኮሮና ወረርሽኝ

- 654,147 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል
- 30,361 ሰዎች ህይታቸው አልፏል
- 139,591 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል


አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችና ጥቆማወችን በዚህ አድርሡኝ ፡-
@Tiburning
🖍COVID19 - በአሜሪካ ‼️

በኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 119,609
በኮሮና ቫይረስ የሞቱ 1,988 ሰዎች
ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ 3,224 ሰዎች
በኮሮና ቫይረስ ዛሬ 15,483 አዲስ ተጠቂዎች እና 152 አዲስ ሞት በዩናይትድ ስቴትስ ተመዝግቧል።

#SHARE

አሥተያየቶችን
@Tiburning
@Tiburning_bot
Forwarded from John's Sketch 🎨 (ᴊᴏʜɴ ☯)
Dear members whenever you get "🎨" button please touch it it takes no time to click but it means a lot to me
የታማሚዎች ሁኔታ፦

- በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሶስቱ (3) ግለሰቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡

- የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ እና የመጨረሻ በረራዋ ኮንጎ ብራዛቪል ነው፡፡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቷ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆና በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዘች መሆኗ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

- ሁለተኛው ታማሚ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የስራ ባህሪው ከተለያዩ ተጓዥ መንገደኞች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡

- ሶስተኛው ታማሚ የ32 ዓመት ወንድ ሲሆን ቀደም ብሎ በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ ክትትል ሲደረግለት የነበረ ሲሆን በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

- ሶስቱም (3) ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሌሎች ሰዎች የመለይት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#DrLiaTadesse
Forwarded from Kaldi's Consultancy (ነጋሪት ሚዲያ)
‱

🇪🇹 እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ 🇪🇹
🙏እንደምን አደራቹ የሀገሬ ልጆች🙏


"ወዳጄ ሆይ በህይወት እስካለህ ፊልም ታያለህ፡፡ህይወት ግን ፊልም አይደለችም፡፡ አንድ የፊልም ተዋናይ በሰባት ፊልም ላይ ሰባት ሴት ሊወድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰባት ፊልም ስለሰራ፡፡ አንተ ግን አንድ ህይወት ነው ያለክ፡፡ አንድ የመኖር እድል ደጋግመክ መኖር አትችልም፡፡ህይወት አንድ ግዜ ብቻ ነው፡፡ያለህን አንድ እድል በአግባቡ ተጠቀምበት፡፡"

💞 #መልካም_ቀን 💞

🇪🇹 #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር! 🇪🇹

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

አዘጋጅ ቃለአብ መንገሻ

© ነጋሪት ሚዲያ

@Negarit_media1
Forwarded from Kaldi's Consultancy (ነጋሪት ሚዲያ)
‱
ሕይወት እና መጥረቢያ!

ሁለት እንጨት ፈላጮች ሥራ ይቀጠራሉ…
ሥራው የግንድ ቁራጮችን መፍለጥ ነው፡፡ ሥራቸውን
የሚጀምሩት እኩል ሰዓት ነው፤ የሚያርፉትም እንዲሁ፡፡ ነገር
ግን… አንደኛው ፈላጭ ከሌላኛው በተሻለ ብዙ ግንዶችን
በመፍለጥ፣ ፍላጮቹን ከምሮ ሌላኛውን ያሳጣዋል(ሳ- ጠበቅ)
፡፡
ሁለት፣ ሶስት ቀናት… ተቆጠረ… ይሄ ትንሽ ግንዶችን ብቻ
የሚፈልጠው ፈላጭ በባልደረባው በጣም በመቅናቱ የተነሳ ከሱ
እኩል ብዙ ፍልጦችን ለመከመር ባለ በሌለ አቅሙ በፍጥነት
ቢፈልጥም በመጨረሻ እጁ ይዝልና ቀኑ ሲገባደድና ክምራቸው
ሲታይ አሁንም እንደተሸነፈ ነው፡፡
ታዲያ… በባልደረባው የቀናው ይሄ ፈላጭ ለዕረፍት ሲቀመጡ፣
እንዲህ ሲል ጠየቀው…
"መጥረቢያችን አንድ አይነት ነው፣ የሚሰጠን የግንድ አይነት አንድ ነው፣ የምንጀምረው፣ የምናርፈው እኩል ነው… እንዴት
ነው ያንተ ፍላጮች ሊበዙ የቻሉት?"
ሌላኛው ፈላጭ እንዲህ ሲል መለሰለት…
"ትክክል ነህ ወዳጄ! ሁሉ ነገር ላይ እኩል ነን! ነገር ግን
የምንበላለጠው ስናርፍ ብቻ ነው! አንተ በዕረፍት ሰዓታችን
መጥረቢያህን ወርውረህ ቁጭ ትላለህ፤ እኔ ግን የእረፍት
ሰዓቴን መጥረቢያዬን በመሳል/በመሞረድ ነው የማሳልፈው!
ልዩነታችንን የፈጠረውም እሱ ነው፡፡"
እስኪ ምሳሌዋን እናስፋት…
አየህ! የሁላችንም ልዩነት የሚፈጠረው እዚህ ጋር ነው!
በእረፍት ሰዓትህ ምንድን ነው የምታደርገው?
መጥረቢያህን ትሞርዳለህ ወይስ ዝም ብለህ ነፍዘህ
ትቀመጣለህ?
በስራህ ወይም በሞያህ መንገድ እራስህን ትሞርዳለህ ወይስ
በማይረባ ነገር በመሞዳሞድ ጊዜህን ታባክናለህ?
በዶለዶመ እውቀትና ልምድ ህይወትህን ትገዘግዛለህ ወይስ በሰላ መጥረቢያ ክርትፍትህ እያደረግህ መንገድህን ታቀናለህ?

እንጃ!
እኔ ግን ሁሌ እንደምልህ ልበልህ…
በየትኛውም መስክ ብትሆን ሥራህ የተቃና እንዲሁን ሁሌም
መጥረቢያህን ሳል።


👂መልካሙን ሁሉ የምንሰማበት ቀን ይሁንልን !

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

አዘጋጅ ቃለአብ መንገሻ

© ነጋሪት ሚዲያ

@Negarit_media1
Forwarded from ThinkUpAgi
3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የታየው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እድገት!

➡️ January 19: 100 cases
➡️ January 24: 1,000 cases
➡️ February 12: 50,000 cases
➡️ March 6: 100,000 cases
➡️ March 21: 300,000 cases
➡️ March 26: 500,000 cases
➡️ March 29: 700,000 cases
➡️ April 1: 900,000 cases

አሥተያየቶችን እዲሁም መረጃወችና ጥቆማወችን በዚህ አድርሡኝ ፡-
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

@ethio27info @ethio27info
አንድ ሰው በኮረና መጠቃቱን እንዴት ሊረዳ ይችላል... ፈጣን መመዘኛ...

አዲሱ ኮሮና ቫይረስ(Coronavirus) ለብዙ ቀናት ምንም አይነት የህመም ምልክት(sign of infection) ሳያሳይ ይቆያል።

እሱ/እሷ በቫይረሱ መያዛቸውን እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ?

የታይዋን ባለሞያዎች ዘወትር ጥዋት ጥዋት ቀለል ያለ እራስን በራስ ቼክ ማድረጊያ መላ አቅርበዋል።
🗣..በጥልቀት ወደውስጥ አየር እንሳብ አየሩን ከሳብን በኋላ ለ10 ሰኮንድ ትንፋሻችንን እንያዝ። ይህን ነገር ካለ ሳል፣ ያለመጥፎ ስሜት፣ ድርቀት፣ ወይም
ውጥረት፣ ወዘተ ካጠናቀቃችሁ በሳምባችሁ ጡንቻዎች ላይ መወጠር የለም ማለት ነው፣ ይህም ምንም አይነት ህመም(infection) እንደሌለብን ያሳያል።

ይህን ስታደርጉ ጥሩ ጊዜን ምረጡ ...ዘወትር ጥዋት ከውኑት ይህም
አየሩ ንፁህ አከባቢ መሆን አለበት።
ሌላው በCOVID-19 ጥብቅ የሆነው የጃፓን ዶክቶሮች ምክር : አፎቻችን እና ጉሮሮዋችን ከድርቀት ነፃ (moist) መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን።

በየ15 ደቂቃው በጥቂት በጥቂቱ ውሃ ፉት ማለት ይኖርብናል። ለምን?
ምንም እንኳን ቫይረሶቹ በአፋችን ቢገቡም፣ ውሃ እና ሌሎች ፈሳሾችን መጠጣታችን ከጉሮሮአችን ታጥበው ወደ ጨጓራችን ይገባሉ። አንዴ እዛ ከገቡ በጨጓራችን ውስጥ የሚገኘው አሲድ ሁሉንም ይገድላቸዋል።

በተደጋጋሚ በቂ ውሃ የማንጠጣ ከሆነ ቫይረሱ ከጉሮሮአችን በአየር ማስገቢያ ቱቦ በኩል ወደ ሳንባችን ገብቶ ያርፈዋል። ያ ደግሞ በጣም አደገኛ ነው።

🗣... ጠቃሚ ማስገንዘቢያዎች

1⃣. ከአፍንጫችን ፈሳሽ እና የሚያናፍጠን ከሆነ በጉንፋን(የተለመደው) ተይዘናል ማለት ነው።

2⃣. የኮሮና ቫይረስ(Coronavirus pneumonia) ደረቅ ሳል ሲኖረው ነገርግን በአፍንጫ በኩል የሚወጣ ፈሳሽ የለውም።

3⃣. አዲሱ ቫይረስ መቃጠልን መቋቋም አይችልም እና ከ26/27 ዲግሪ የሆነ የአየር አከባቢ ላይ መቆየት አይችልም። ፀሀይ ይጠላል።

4⃣. በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሲያስነጥስ ወደ መሬት ከመውደቁ አስቀድሞ ቫይረሱ 10 Feet(3.048 ሜትር) ይጓዛል ከዛን በኋላ አይነሳም።

5⃣. በሚወድቅበት ጊዜ በብረት እና ብረት ነክ ነገሮች ላይ የሚያርፍ ከሆነ ቢያንስ ለ12 ሰዓታት ሊቆይ ይችላል - ስለዚህ ብረት ነክ ነገሮችን ከነካችሁ በተቻላችሁ ፍጥነት ፀረ ባክቴሪያ በሆነ ሳሙና እጆቻችሁን ታጠቡ።

6⃣. ፋብሪካ ውስጥ ከ6-12 ሰዓት ይቆያል። የልብስ ማፅጃዎች በቀላሉ ይገለዋል።

7⃣. የሞቀ ውሃ መጠጣት ለሁሉም ቫይረሶች ማከሚያነት የተሻለ ነው። ቀዝቃዛ ፈሳሽ ነገሮችን ባንጠቀም የተሻለ
ነው።

8⃣. ቫይረሱ በእጆቻችን ላይ ከ5-10 ደቂቃ ስለሚቆይ እጆቻችንን በተደጋጋሚ እንታጠብ ... ይህን የምናደርገው አይኖቻችንን ልናሽ፣ አፍንጫችንን ልንይዝ ስለምንችል ነው።

9⃣. መጉመጥመጥንም እንደመከላከያ መጠቀም ይቻላል። ለብ ባለ ውሃ ውስጥ
ጨው ጨምረን መጠቀምም ቀላል መፍትሄ ነው።

1⃣0⃣. ያልበዛና በቂ ውሃ ከመጠቀም አንቆጠብ።

የበሽታው ምልክቶች

1⃣. በሽታው አስቀድሞ ጉሮሮን ስለሚያጠቃ ለ3/4 ቀናት የሚቆይ ህመም ይኖረናል።

2⃣. በመቀጠል ቫይረሱ በመተንፈሻ ቀዳዳ በመግባት በአየር ቧንቧ አድርጎ ወደ ሳንባችን በመግባት የሳንባ የምች(pneumonia) ያሲዘናል። ይህ ሂደት ከ5/6 ቀናት ውስጥ የሚከወን ነው።

3⃣. የሳንባ ምች ከመጣ በኋላ ከፍተኛ ትኩሳትና የመተንፈስ ችግር ይገጥመናል።

4⃣. የአየር መተላለፍያ ቱቦዎች መኮማተር ከተለመደው አይነት የወጣ ነው። ስንተነፍስ እየሰመጥን ያለን ይመስለናል። ይህ ከአቅም በላይ በመሆኑ አስቸኳይ ዕርዳታ ያስፈልገናል።

እባካችሁን ...
ይህን መረጃ #send እና #share በማድረግ ወገኖቻችንን እንታደግ።

Share ➠➠➠➠ @vo3as

Comment ➠➠ @yoyo5com
#COVID19 😷 #WORLD‼️
በመላው ዓለም በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊዮን መቃረቡን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አሁናዊ አሃዞች ያመላክታሉ።

እስከ ዛሬ ንጋት ድረስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 937,170 ሲሆን ከእነዚህም መካከል 212,000 የሚሆኑት በአሜሪካ የሚገኙ ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሟቾች ቁጥር 50 ሺህ ሊደፍን የቀረው ጥቂት ነው።

ዛሬ ንጋት ላይ በመላው ዓለም በወረርሽኙ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 47,235 ነው።

በአገራት ዝርዝር ደግሞ ከፍተኛውን የሞት ቁጥር ካስመዘገቡ አገራት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

ጣሊያን 13,155

ስፔን 9,387

አሜሪካ 5,116

ፈረንሳይ 4,043

ቻይና 3,316

ኢራን 3,036

ዩናይትድ ኪንግደም 2,357

እባካችሁ በተቻለ መጠን ከቤት አትዉጡ፣ ሁሌም ጥንቃቄ አይለያችሁ...ከፈጣሪ ጋር በህብረት ሆነን ይሄን ጊዜ እናልፈዋለን