Zoma Herbal ዞማ ኸርባል
1.26K subscribers
25 photos
2 videos
7 links
Supernatural in nature; It also scientifically produces a variety of plants in our country, preserving its natural content; It is an organization that produces health and beauty products that are suitable for our country and our society
Download Telegram
Channel photo removed
ዞማ ኸርባል
በተፈጥሮ ይዘቱ ላቅ ያለ፤ እንዲሁም ተፈጥሯዊ ይዘቱን ጠብቆ በሀገራችን የሚገኙ የተለያዩ እፅዋቶችን ሳይንሳዊ በሆነ የሚመረት፤ ለሀገራችንና ለህብረተሰባችን ተስማሚ የሆነ የጤና እና የውበት መጠበቂያ ቅባቶችን የሚያመርት ድርጅት ነው
ለበለጠ መረጃ +251942500000
+251943500000
Zoma Herbal
Supernatural in nature; It also scientifically produces a variety of plants in our country, preserving its natural content; It is an organization that produces health and beauty products that are suitable for our country and our society.
For more information call + 251942500000
+251943500000
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዞማ ኸርባል ለሁሉም ይስማማል!
እንኳን ለ125ኛው የጥቁር ህዝቦች ኩራት፣ የአንድነት ተምሳሌት ለሆነው የአድዋ ድል በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡
ስለ ዞማ የነጭ ሽንኩርት ቅባት ጥቅም ምን ያህል ያውቃሉ?
- ፎሮፎርን ያስወግዳል
- ፀጉርን ይመግባል
- ራሰበረሀነትን ይከላከላል
- ፀጉራችን እርጥበቱን ይዞ እንዲቆይ ያደርጋል
- ለፀጉር እድገት ይጠቅማል
- ቆዳችን ወዙን ጠብቆ እንዳያረጅ ያደርጋል
- ከቆዳችን ላይ ብጉርን ያስወግዳል
የዞማ ኸርባልን ምርቶች በወኪልነት ማከፋፈል ለምትፈልጉ
አድራሻ 22 ማዞሪያ
ለበለጠ መረጃ በስልክ 0942 50 00 00 ወይም በ0943 50 00 00 ይደውሉ።
ዞማ ኸርባል፤
ለሁሉም ይስማማል!!
ስለ ዞማ የዝንጅብል ቅባት ጥቅም ምን ያህል ያውቃሉ?
- የፀጉራችን ቀዳዳዎች እንዲከፈቱና ፀጉራችን ፈጣን እድገት እንዲኖረው ያደርጋል
- የፀጉር መሳሳትን በመከላከል ፀጉራችን ወፍራምና ጠናካራ እንዲሆን ያደርጋል
- ፎሮፎርን ይከላከላል
- በከፍተኛ ሙቀት የሚመጣ የፀጉርን መበጣጠስ ይከላከላል
- የጭንቅላት ድርቀትን ይከላከላል
- ፀጉራችን ወዙን ጠብቆ እንዲቆይ ያደርጋል

የዞማ ኸርባልን ምርቶች በወኪልነት ማከፋፈል ለምትፈልጉ
አድራሻ:- ቁጥር 1. 22 ማዞሪያ
ቁጥር 2. መርካቶ ምዕራብ ሆቴል
ለበለጠ መረጃ በስልክ 0942 50 00 00 ወይም በ0943 50 00 00 ይደውሉ።
ዞማ ኸርባል፤
ለሁሉም ይስማማል!!
የቀይ ሽንኩርት የጤና በረከቶች
• አለርጂን ይከላከላል፤ ቀይ ሽንኩርት አስም በሽታ የመሳሰሉ የአለርጂ ውጤቶች ከሆኑ በሽታዎች ለመከላከል የሚያስችል ኩረሰቲን (Quercetin) የተባለ ንጥረ ነገር ይገኝበታል፡፡ በትንሹ አንጀትና በደም ውስጥ ረጅም ጊዜ በመቆየት ለአለርጂ ምክንያት የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ያስወገዳል፡፡
• ምግብ የመፍጨት ስርዓትን ያቀላጥፋል፤ ቀይ ሽንኩርት ኢኑሊን (Inulin) የተባለ የምግብ መፈጨት ስርዓትን የሚያቀላጥፍ ንጥረ ነገር ይዟል፡፡ ኢኑሊን ለምግብ መፈጨት ጠቃሚ የሆኑ ባክቴሪያዎች በማመጣጠን የተቀላጠፈ ምግብ መፈጨት ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል፡፡
• ጤናማ የጸጉር ዕድገትን ያፋጥናል፤ በቀይ ሽንኩርት ውስጥ አሉ ከሚባሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች መካከል ሰልፈር (Sulfur) ይገኝበታል፡፡ ሰልፈር ለጸጉር ዕድገት አስፈላጊ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ቀይ ሽንኩርት በሳምንት ሁለት ጊዜ ለሁለት ወራት መቀባት የጸጉርን ዕድገት ያፋጥናል ይላሉ በዘርፉ የተካሄዱ ጥናቶች፡፡
• ጉንፋንና ከመተንፈሻ አከላት ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ይከላከላል፤ በመተንፈሻ አካላት ውስጥ የሚፈጠርን ፈሳሽና የማቃጠል ባህሪ የሚከላከል ቅባት በቀይ ሽንኩርት ውስጥ ይገኛል፡፡ በተለይም ቀይ ሽንኩርትን ጉንፋን ሲጀምር አከባቢ መጠቀም ጉንፋኑ ሊያባብሱ የሚችሉ ሙከስ (mucus) ፈሳሾች እንዳይመነጩ ያደርጋል፡፡
• ጤናማ አጥንት እንዲኖረን ያደርጋል፤ ቀይ ሽንኩርት አጥንታችን እየሳሳ እንዳይሄድ ያደርጋል፡፡ በተለይም ዕድሜያቸው በገፉ ሰዎች የሚከሰተው ኦስቲዮፕሮሲስ (osteoporosis) የተሰኘው የአጥንት መሳሳት በሽታ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ . . . .
• ጤናማና የጠራ ቆዳ እዲኖረን ያደርጋል፤ በደም ህዋሳት ውስጥ ጤናማ የደም ዝውውር እንዲኖር በማድረግ በቆዳችን ላይ እንፌክሽኖች እንዳይፈጠሩ ያደርጋል፡፡ በተለይም ቀይ ሽንኩርትን በጥሬው መመገብ በቆዳችን ላይኛውም ሆነ ታችኛው አካል ቁስለት ካለ ለመፈወስ ይጠቅማል፡፡
• የኮልስትሮል መጠንን ለመቀነስ፤ ቀይ ሽንኩርት የኮልስትሮል መጠንን መቀነስ የሚያስችሉ ክሮሚያም(chromium)፣ ቫይታሚን ቢ (Vitamin B) እና ሰልፈር (Sulfure) የተባሉ ንጥረ ነገሮች አሉት፡፡ ቀይ ሽንኩርትን በአተክልት ውስጥ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች ሁሉ በውስጡ ስለሚገኙ ቀይ ሽንኩርትን አዘውትሮ መጠቀም ለልብ በሽታ የሚዳርገውን ኮልስትሮልን ለማስወገድ ይጠቅማል፡፡
• የስኳር በሽታን ለመከላከል፤ ቀይ ሽንኩርት በደማችን ውስጥ የሚገኘውን ግሉኮስ (Glucose) ምጣኔ ለማስተካከል አስፈላጊ የሆነው ክሮሚያም(chromium) ንጥረ ነገር የያዘ በመሆኑ ስኳር በሽታን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡
• የካንሰርን በሽታን ይከላከላል፤ ቀይ ሽንኩር ሰልፋይድ (Sulfide) የተባለ ንጥረ ነገር አለው፡፡ ሰልፋይድ የተለያዩ የካንሰር አይነቶችን ቀድሞ ለመከላከል ይረዳል፡፡
• ጠቅላላ የአፍና የጥርስ ጤናን ለመጠበቅ ይረዳል፤ ቀይ ሽንኩርት ባክቴሪያን የመከላከል አቅም ስላለው ለጥርስ መበስበስና በአፍ ውስጥ ያሉ ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል፡፡ ቀይ ሽንኩርትን በጥሬው ለ3 ደቂቃዎች ማኘክ በአፋችን ውስጥ ያሉ ባክቴሪያና ጀርሞችን እንደሚያጠፋ በቅርቡ የወጣ ጥናት ያመለክታሉ፡፡
ፎሮፎር ምንድነው?
#ፎረፎር ማለት የራስ ቅል ቆዳን የሚያጠቃ ፈንገስ ነው።
መገለጫውም የራስ ቅል ቆዳን በመፈርፈር የማሳከክ ስሜት መፍጠር ነው።

• ይህ አይነት ችግር በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰትና በጣም የተለመደ ሲሆን ሰዎችን የሚያሳፍርና ለማከም አስቸጋሪ የሆነ በሽታ ነው።

• ትክክለኛ ምክናየቱ አይታወቅም። በፎረፎር የመያዝ እድልን የሚጨምሩና ጎልቶ እንድታይ የሚያደርጉ ነገሮች ግን አሉ።
እነሱም ንፅህናን አለመጠበቅ (አለመታጠብ፡ አለማበጠር): የራስ ቅል ቆዳ ድርቀትን አለመከላከልና የተፈጥሮ የራስ ቅል ቆዳ ቅባትን ታጥቦ አለማስወገድ ፎረፎር ጎልቶ እንዲታይ ያደርጋሉ።

• በሽታ የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ ህመሞች፡ ምንነታቸው ያልታወቀ የፀጉር ቅባቶችን መጠቀምና የኑሮ አለመመቸትም ለፎረፎር ጎልቶ መታየት ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።

#ፎረፎርን ለማጥፋትና በማይታይ ደረጃ ለማድረስ የሚከተሉትን ያድርጉ

1. ጭንቀትንና ውጥረትን ያስወግድ

2. ፀጉረወትን ጧት ጧት ሁል ጊዜ ይታጠቡ

3. የማይታወቅ ቅባት አይጠቀሙ

4. የተፈጥሮ የራስ ቅል ቆዳ ቅባትን ታጥበው ይቀንሱ

5. የራስ ቅል ቆዳ ድርቀትን ይከላከሉ

6. እራስዎትን (ፀጉረዎትን) ለትንሽ ደቂቃ(3-5 ደቂቃ) ከረር ላለ የፀሀይ ጨረር አጋልጡት

7. የነጭ ሽንኩርት ዘይት (Garlic oil) ወይም ቲ ትሪ ዘይት (tea tree oil) ይቀቡ

8. እንዳጠቃላይ እራስዎትን ይጠብቁ። የተመቻቸ ኑሮ ፎረፎርን በእጅጉ ያጠፋልና

#የሚታዘዙ መድሀኒቶችም አሉና የጤና ባለሙያ ያማክሩ።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን
እንኳን ለታላቁ እና ተናፋቂው የረመዳን ፆም
በሰላም አደረሳችሁ
ያለ እድሜያችን የሚከሰተው የፀጉር ሽበት ምክንያቱ ምንድን ነው?

እድሜ እየገፋ ሲሄድ ሜላኒን የተባለ የቀለም መመረት እየቀነሰ ስለሚሄድ ፀጉራችን በተፈጥሯዊ መንገድ ወደ ነጭነት እየተቀየረ ይሄዳል።
ስለሆነም ነጭ ፀጉር ከእድሜ መግፋት ጋር የሚያያዝ ይሆናል።

ይሁን እንጂ ያለጊዜው የሚመጣ የፀጉር ቀለም ለውጥ (ሽበት) በአሁኑ ወቅት በለጋ እድሜ ላሉ ወጣቶች ጭምር አሳሳቢ ችግር እየሆነ መጥቷል።

እናም ይህ ችግር የሚከሰትበትን ምክንያት ማወቅ የመፍትሄ አቅጣጫዎቹን ለመጠቆም ስለሚረዳ መነሻዎቹን እንመልከት።

1. ከባድ ጭንቀት
በመልካም የኑሮ ደረጃም ሆነ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኝ በህይዎት ጉዞው ውስጥ ደረጃው ቢለያይም ለጭንቀት የተጋለጠ ነው። ይህ በበርካታ ሃሳቦች የመዋጥና የመጨናነቅ ስሜት ከፍ ሲልም ያለጊዜው ለሚመጣ ሽበት ይዳርጋል።

2. ስነ ባህርይ (genetics)
ፀጉራችን ወደ ነጭነት የሚቀየርበት ጊዜ በዘርም ይወሰናል። ስለሆነም አባቶቻችን አልያም አያቶቻችን ያለጊዜው በሚከሰት ሽበት ተጠቅተው ከነበረ እኛም በዚሁ ሂደት ውስጥ የማለፍ እድላችን ሰፊ ይሆናል።

3. ያልተመጣጠነ ምግብ
የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ለፀጉር ነጭ መሆን ምክንያት ይሆናል። ለዚህም እንደ አሳ፣ የበግ ስጋ፣ እንቁላል፣ ቅቤ እና ወተት እና የወተት ውጤቶችን መጠቀም ካልተፈለገና ካለጊዜው ከሚመጣ የፀጉር ቀለም ለውጥ ይታደጋል ተብሏል።

4. መጥፎ ልማዶች
ሲጋራ ማጨስ፣ መጠጥ ማዘውተርና መሰል ያልተገቡ ልማዶች ለፀጉር መንጣት አስተዋፅኦ እንዳላቸውም ይነገራል።

5. ፈሳሽ ነገሮችን አብዝቶ መውሰድ
ሻይ፣ ቡና እና ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን ከልክ በላይ መውሰድም ለችግሩ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል::
“ክርስቶስ ተንስአ እሙታን”
ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

"ፀጉር እንክብካቤ ይፈልጋል፤ በተለይ የተፈጥሮ ይዘቱን ለመጠበቅ፡፡"

እነሆ ዞማ መፍትሄ አለው!

የዞማ ኸርባም ምርቶችን ለማግኘት በጀሞ 1 እና በመገናኛ ባዛር ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆንኑን እየገለፅን፤ በክ/ሀገር አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ አምቦ፣ ደብረ ብርሃን ላይ ያገኙናል፡፡

ለማንኛውም አስተያየትና መረጃ ለማግኘት
0942 50 00 00 / 0943 50 00 00 ወይም 0118 22 23 05 ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

ዞማ ኸርባል ለሁሉም ይስማማል!
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የደስታ ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን!

ዞማ ኽርባል፤ ለሁሉም ይስማማል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዘና ብላችሁ ዋሉ

በዞማ ኸርባል ስፖንሰር አድራጊነት ከቀረቡት የ9ኛው ሺ ድርማዎች መካከል የተመረጡትን ተጋበዙልን

የዞማ ኸርባልን ምርቶች በወኪልነት ማከፋፈል ለምትፈልጉ

አድራሻ:-
ቁጥር 1. 22 ማዞሪያ
ቁጥር 2. መርካቶ ምዕራብ ሆቴል

ለበለጠ መረጃ በስልክ 0942 50 00 00 / 0943 50 00 00 ወይም 011 822 2305 ይደውሉ።

ዞማ ኸርባል፤ለሁሉም ይስማማል!!
የዞማ ኸርባል ምርቶችን ሄሎ ማርኬት ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

8420
ላይ በመደወል ወይም መልዕክት በመላክ የዞማ ኸርባል የፀጉር ቅባት ብለው ይዘዙ!

መጠን፡ 250 ml

ከታች ያለውን የቴሌግራም ቦት እንደ አማራጭ ማዘዣ ይጠቀሙ
https://t.me/helloo_market_bot?start=113410001
*በህይወት ውስጥ የስልጠናዎች ማነስ*

1. ተነሳሽነት ይቀንሳል
2. አቅጣጫ የሌለው ህይወት እንመራለን
3. የማንፈልገውን ኑሮ እንድንኖር ያስገድደናል
4. ስህተትን በመደጋገም ስኬታማ ላንሆን እንችላለን
5. አጥጋቢ ያልሆነ ህይወት ይኖረናል
6. ሚዛናዊ ያልሆነ የኑሮ ዘይቤ ይኖረናል
7. የህይወት ችግሮችን መፍታት ያስቸግረናል
8. ስኬታማ ለመሆን ያንተንና/ያንቺን የሌሎችን ግዴታ ለይቶ ማወቅ ይከብደናል
9. ከስኬት ወደኃላ ያሰቀሩንን አመሎች/ባህሪዎችን ማወቅ ያቅተናል
10. ሁሉም ነገር ላይ በጭፍንነት ይሳካል ብለን እንድንሞክር እና በተደጋጋሚ እንድንወድቅ ያደርገናል።