❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
3.8K subscribers
7.07K photos
921 videos
98 files
4.8K links
« ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበ ትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ »
••••
« ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ
••••
ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው‼️
-------------------------------------------
Download Telegram
#በውስጧ_አድረህ_ስለቤተክርስቲያን_ተናገር
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
አቤቱ አምላካችን ሁሉን የያዝክ ለዓለሙ ሁሉ ነግሦ የሚኖር የቅዱስ ልጅህ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ ወንድሞቻችንን ድውያንን አድን፤ እኅቶቻችንን ድውያንን አድን። ያደሩባቸውንም አጋንንት አውጣ። በደዌ የተለዩትንም አረጋጋ። የታመመችውን ሰውነት ጎብኝ። ሁሉንም አድናቸው ይቻልሃልና። ድንቅ ተአምራትን የምታደርግ አንተ ጽኑ ነህና።

ሠላሳ ስምንት ዓመት ታሞ የነበረውን መጻጕዕን አዳንክ ፤ አልአዛርንም ከሙታን አስነሣህ ፤ ለእናቱ አንድ የነበረውንም ሰጠህ ፤ ደም ይፈሳት የነበረቸውንም አዳንክ ፤ ሐማተ ጴጥሮስንም ከሆድ ዝማ አድነህ አስነሣህ። እንደዚሁም ሁሉ ከእነዚህ በሽተኞች ላይ በጎ አምልኮትህን አድርግ፤ ነጠብጣበ ምሕረትህንም በእነሱ ላይ አውርድ። ከአንተ የሚገኝ ጠል ሕይወታቸው ነውና። እነሱም ተነሥተው ከእኛ ጋር ያመሰግኑ ዘንድ ፤ ስምህንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናደርግ ዘንድ። በአንድ ልጅህ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእሱ ያለ ክብር ፣ ጽንዕ ለአንተ ይገባል። ከእሱ ጋራ፣ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ምስጋና፣ ግዛት፣ጌትነት ያለህ ዛሬም ፣ ዘወትርም ለዘለዓለሙ።

የሁሉን ጌታ አምላካችንን ሁሉን የሚይዝ ፣ ለዓለሙ ሁሉ ነግሦ የሚኖር ፣ የገዥዎች ገዣቸው፣ የነገሥታትም ንጉሣቸው የሚሆን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት ዳግመኛ እንማልደዋለን። እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ስለኢትዮጵያ መንግሥት እንለምናለን። መንግሥቷም በእውነትና በሰላም ይጠብቅ ዘንድ፤ በሰልፍ ሁሉ ድል የሚያደርግ አምላካችን እግዚአብሔር ነው። እውነት ነው ፤ አቤቱ አምላካችን ሁሉን የሚይዝ ፣ ለዓለሙ ሁሉ ነግሦ የሚኖር የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት የገዥዎች ገዣቸው ፣ የነገሥታትም ንጉሣቸው ሆይ እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ አገራችን ስለኢትዮጵያ መንግሥት እንለምንሃለን ፤ እንማልድሃለን። በእውነትና በሰላም ጠብቅ ፤ እንደ ዓይን ብሌን በክንፍህም ጥላ ሰውረው ።

አቤቱ አገራችንን ኢትዮጵያን ይቅር በላት። ጠላቶቿን ከበታቿ አስገዛላት። በአገሪቱም በየአውራጃውም ሁሉ ብዙ ሰላምን ስጣት። ለረጅም ዘመናት፣ ለሰፊ ክረምት በደስታና በምሕረት ማመንን ሃይማኖትንም ጨምርላት። በውስጧ አድረህ ስለቤተ ክርስቲያን ተናገር። ሰላምን ስጣት። ስለእኛና ስለወገኖችህ ሁሉ በሰላም ዐርፈን እንኖር ዘንድ፣ እግዚአብሔርን በመፍራት እንኖር ዘንድ፣ በበጎነትም እንገኝ ዘንድ፣ በተወደደ ልጅህ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእሱ ያለ ክብር፣ ጽንዕ፣ ለአንተ ይገባል። ከእሱ ጋራ ፣ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ምስጋና፣ ግዛት፣ ጌትነት ያለህ ዛሬም፣ ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።

(ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ማታ ከተጸለየው የተወሰደ)

👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
👉🏻👉🏻 #አባትህን_ስማ_ልጄ !?!
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
🛑 የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያቹ እነሆ የአባቶቻችን ምክር ብንሰማ ሐጢያት ፤ ሞት ፤ በሽታ ያየን ነበርን ሁላችንም በልቦናችን ይህንን ይዘን አባታችን ደሞ እንዲህ ይሉናል
#በብፁዕ_አቡነ_ናትናኤል
👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
🕯 #ዜና_እረፍት 🕯
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌📌 ለ40 ዓመት የላሊባላን አብያተ መቃድስ የአገለገሉት የቤተማርያሙ ሊቀገበዝ መለሰ አረፉ ።
📌📌 ሊቀገበዝ መለሰ በቅዱስ ላሊበላ ገዳም እንግዳ በመቀበልና የቅዱስ ላሊበላን ቅርስ በታመኝነት በመጠበቅ የታወቁ ታላቅ አባት ነበሩ። ለቤተሰቦቻቸው እና ለገዳሙ መጽናናትን ያድልልን።
👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
---------------------

📌 ግንቦት 18-ጌታችን መልአኩን ልኮ ‹‹ ተጋድሎህ በመጠን ይሁን ›› በማለት ተጋደሎውን እንዲቀንስ ያዘዘው አባ ገዐርጊ ዕረፍቱ ነው፡፡

👉 ዳግመኛም ይኽች ዕለት ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከባት ዕለት ናት፡፡ ይኸውም የክብር ባለቤት ጌታችን ካረገ በኋላ በ10ኛ ከትንሣኤውም በ50ኛ ቀን ለደቀ መዛሙርቱ ‹‹ከአብ የሚሠርጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ›› ብሎ ተስፋ እንደሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ፡፡

📌 ሰማዕቱ ቅዱስ ሲኖዳ መታሰቢያው ነው፡፡

👉 #አባ_ገዐርጊ፡- የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ደጋግ ጻድቃን ናቸው፡፡ በአደገም ጊዜ የወላጆቹን በጎች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ፡፡ ነገር ግን እርሱ የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር፡፡ 14 ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሳሳችውና በጎቹን ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሄደ፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል›› እንዳለ (2ኛ ቆሮ 11፡14) አባ ገዐርጊ ወደ ገዳሙ እየተጓዘ ሳለ በሽማግሌ አምሳል ከይሲ ሰይጣን ተገለጠለትና ከዓላማው ሊያደናቅፈው ፈተነው፡፡ እንዲህም አለው ‹‹ልጄ ሆይ ስለ አንተ አባትህ ልብሱን ቀዶ አየሁት፣ የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎት አባትህ ያዝናል፣ ያለቅሳል፡፡ ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልታጽናና ይገባሃል›› አለው፡፡ አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ሳይንቀሳቀስ ቆመመ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ ‹‹ከእኔ ይልቅ አባት እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም›› ብሏል ብሎ አሰበ፡፡ ማቴ 10፡37፡፡ ይህንንም ባሰበ ጊዜ ሰይጣን እንደጢስ ሆኖ ተበትኖ ጠፋ፡፡

👉 አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደሆነ ዐወቀ፡፡ በዚያን ጊዜም አስቀድሞም ተገልጦለት የነበረው የብርሃን ምሰሶ ተገለጠለት፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኩሴ አምሳል ተገለጠለትና አብሮት ተጓዘ፡፡ መልአኩም አባ ገዐርጊን አባ አርዮን ገዳም አደረሰው፡፡ አባ ገዐርጊም ጽኑ ተጋድሎውን ጀመረ፡፡ በገዳሙ 14 ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር እህል አይቀምስም ውኃም አይጠጣም ነበር፡፡ ለ14 ዓመትም ከመቀመጥ በቀር ምንም አልተኛም፡፡ ከዚህም በላይ ተጋድሎውን በጨመረ ጊዜ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ‹‹በመጠን ተጋደል›› ብሎታል፡፡ መልአኩም ተገልጦለት ‹‹‹ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ተጋደል› ብሎሃል ጌታ›› ካለው በኋላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት፡፡ ሁልጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም፣ ትንሽም እንጀራን እንዲበላ፣ ከእራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስኪነጋ ተግቶ እንዲጸልይ ሥርዓት ሠራለት፡፡

👉 መልአኩ በሠራለት በዚህ ሥርዓት መሠረት አባ ገዐርጊ ብዙ ዘመን ሲጋደል ከኖረ በኋላ በበረሃ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ተቀመጠ፡፡ ነገር ግን ጌታችን ተገልጦለት ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው፡፡ ደብሩም ከከበሩ መክሲሞስ ዱማትዮስ ገዳም አጠገብ ነበር፡፡ ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ አብርሃም ከተባለ ደገኛው ጋር ተገናኙና ሁለቱም በጋራ ለመኖር ተስማምተው ወደ አስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ ሄዱ፡፡ እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጧ በተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ ያችም ቦታ እስከዛሬ ታውቃ ትኖራለች፡፡ ስሟም በግቢግ ትባላለች፡፡ እርሷም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጣሪያዋን ሰንጥቆ ወደ እነዚህ ሁለቱ ቅዱሳን የወረደባት ቅድስት ቦታ ናት፡፡ እነርሱም በክብር ሰገዱለት፡፡ ጌታችንም ባርኳቸውና አጽናንቷቸው ዐረገ፡፡ በዚያችም ጌታችን በወረደባት መስኮት ብርሃን ተመለከቱ፡፡ እስከዛሬም ድረስ የተከፈተች ሆና ትታያለች፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን ለመኮሳት የሚሆኑ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሱ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ አብርሃም ጥር 2 ቀን ዐረፈ፡፡ ከእርሱም በኋላ አባ ገዐርጊ በ72 ዓመቱ ግንቦት 18 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ሰማዕቱ አቡነ ሲኖዳ፡- ሀገራቸው ግብፅ ብሕንሳ ነው፡፡ መጽሐፍ ሰማዕትም ጻድቅም ይላቸዋል፡፡ ሽኖዳ እየተባሉም የሚጠሩ ሲሆን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአክስት ልጅ ናቸው፡፡ ሙሉ ዕድሜያቸውን በገዳም ነው የኖሩት፡፡ በማርቆስ መንበር ላይ ተሹመው በፓትርያርክነት እያገለገሉ እያለ በዘመናቸው ከሃዲው ንጉሥ መክስምያኖስ ነግሦ ስለነበር ክርስቶስን በማመናቸው እጅግ ብዙ አሠቃይቷቸዋል፡፡

👉 ከሃዲው ንጉሥ መክስምያኖስ ወደ እርሱ እንዲመጡ ካደረገ በኋላ በእርሱ ጣዖት እንዲያምኑ ጠየቃቸው፡፡ አቡነ ሲኖዳም በክርስቶስ እንደሚያምኑ ሲነግሩት በምድር ላይ ደማቸው እንደ ውኃ እስኪፈስ ድረስ ጽኑ ግርፋትን አስገረፋቸው፣ ዐይናቸውም ሊወጣ ደረሰ፡፡ በእሥር ቤትም ከጣሏቸው በኋላ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ከቁስላቸው ፈውሶ አበረታቸውና ገና እንደሚጋደሉ ነገራቸው፡፡ ንጉሡም ‹‹ሞቶ እንደሆን እዩት›› ብሎ ወታደሮቹን ቢልክም ፍጹም ጤነኛ መሆናቸውን ነገሩት፡፡ ልብሳቸውንም አስወልቆ አይቶ ካረጋገጠ በኋላ ‹‹ታላቅ ሥራይ ነው›› በማለት ዘቅዝቀው እንዲሰቅሏቸውና ከሥር እሳት እንዲያነዱባቸው አዘዘ፡፡ ይህንንም በአባታችን ላይ አደረጉባቸው፡፡ አሁንም ምንም ዓይነት ሥቃይ እንዳልገደላቸው ባየ ጊዜ በብዙ ካሠቃያቸው በኋላ መጋቢት 14 ቀን አንገታቸውን በሰይፍ አስቆርጦታል፡፡

👉 ይኽችም ዕለት መታሰቢያ በዓላቸው ናት፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን::

👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
🛑 ከአንድ ወር ብሄራዊ የጸሎት መርኃግብር በኋላ ቀጥሎ የቆየው የየቤተ እምነቱ የጸሎት መርኃግብር መቋረጡን የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሀፊ ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ ገለፁ !!!

📌 ለተከታታይ 30 ቀናት በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት ሲከናወን የቆየው ብሄራዊ የጸሎትና ምህላ መርኃግብር መቋጫውን ማግኘቱን ተከትሎ ፀሎቱ እና ምህላው እንዲቀጥል በተቀመጠው አቅጣጫ ድረስ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ የቆየ ቢሆንም የአንዳንድ ተቋማት ከስታንዳርዱ (ይዘቱ) ውጭ በመውጣት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መርህ በጣሰ መልኩ እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙ በመሆናቸው ከግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፀሎት መርኃግብሩ የማይተላለፍ መሆኑ ተገልጿል።

📌 መርኃግብሩ በ EBC,Fana Tv,Addis TV,Walta Tv ሲተላለፉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ ከዚህ በኋላ በተጠቀሱት የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት እንደማይቀጥሉ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
📌📌 እግዚአብሔርን እንጠብቅ ወይስ እኛ እንጀምር ⁉️
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
🟢 ብዙዎቻችን እግዚአብሔር ጠባቂያችን እንጂ ሊያስጠብቀን እንደሚችል አንረዳም፡፡ ይሰጣል ግን ሊያስጠብቅህ ይችላል አብርሐም ይስሀቅ ልጁን ለማግኘት 99 ዓመት መጠበቅ ነበረበት፡፡ ድንግል ማርያምን ለማግኘት ሀና በአብሮ አደጎቿ ሴቶች መዘለፍ ሆኖባት ነበር፡፡ ማኑሔ እና ሚስቱም ሶምሶንን ለማግኘት በጣም ብዙ ጠብቀው ነበር፡፡ ካህኑ ሕልቃና እና ሚስቱ ሐናም ሳሙኤልን ለማግኘት ጠባቂያቸውን ጠብቀው ነበር፡፡ የሐናን ሀዘን ብዙ ሴቶች ሳያዝኑት አይቀርም ተንሰቅስቃ አልቅሳ ነበር በካህኑ ዔሊ ፊት << ሰካራም >> እስከትመስል ድረስ ከአዕምሮዋ ተለይታ ትለፈልፍ ነበር፡፡ ለምን ቢሉ ፈጣሪ ማህጸኗን ስለዘጋው፡፡ ለምን? ሐናን የመሰለ ምስኪን ሴት ደም እንባ ብታለቅስ ለእግዚአብሔር ምን ይረባዋል? ወይስ አስጠብቆ ስለሚሰጣት የተባረከ ፍሬ ሐና ደስታዋ እንዲበዛላት አስቦ ይሆን? ወይንስ ውድ ነገር እንዲሁ በተፈጥሮ ስጦታ ብቻ ስለማይገኝ ይሆን?

🟡 አጠፍነውም ዘረጋነውም እግዚአብሔር ያስጠብቃል አንዳድ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ስናነብ ደግሞ ግራ እንጋባለን፡፡ ግን ለምን ይህን ያህል እግዚአብሔር ያስጠብቀናል? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡ መልሱ ቀላል ነው እሱ እግዚአብሔር ነው የሚያደርገውን ያውቃል ሲሰጠን ያስጠበቀንን የዘመን ክብደት እና ሐዘን አናስታውስም ሲመጣ የጠበቅነውን መጠበቅ ፍጹም እንረሳለን፡፡ እመቤታችንን ያገኘች ሐና ስለ መገለሏ ትዝም ቅርም አይላትም፣ ሳሙኤልንም ያገኘችው ሐና ማልቀስ ምን እንደሆነ ከነ መፈጠሩም ረስታዋለች ያለቀሰው አይኗ በልጇ ፍቅር ተጠምዶ ማልቀሱን ክዷል፡፡ ሌሎቹም እንደዛው፡፡

🔴 ወዳጄ፡- አንድ ነገር ጠይቀህ ጌታ ሲያስጠብቅህ፣ ሲያቆይብህ በደስታ ዝለል ምክንያቱም ያ የቆየብህ የመቅደሱም ደጃፍ አስደግፎ ያስጠበቀህ ሲመጣልህ ደስታውን አትችለውም ተዓምር ነው የሚሆንብህ ከቀደሙህ ፊት ትሰለፋለህ ጓደኞችህ ልጅ ሲደጋግሙ አይተህ "ምነው የኔ ጌታ ለኔ አንድ አጣህ?" እንዳላልከው ሁሉ ሲያንበሻብሽህ እነሱ በ4 ልጅ ሲጨነቁ አንተ እንደ አብርሐም በአንዱ ብቻ ትስቃለህ እነሱ ልጅ ጠይቀው ልጁ ሲያገኙ አንተ ልጅ ጠይቀህ አቆይቶ ሲሰጥህ እንደ ሶምሶን ህዝቡን ነጻ የሚያወጣ እንደ ሳሙኤል ማታ ማታ እግዚአብሔር የሚያጫውተውን ትታቀፋለህ እንደ እያቄም እና ሐና የስለት ልጅ ጠይቀህ ለብዙዎች መልካም ዜና ያላት ቆንጅዬ መልዐክ የመሰለች ልጅ ትስማለህ... እና የሚያስጠብቅህን ጌታ አታማር የሚቆይብህን ጌታ ኢ-ፍትሐዊ አታድርገው ቀረ ብለህ በራስህ ጉዞህን አትጀምረው፡፡ ሲመሽ ይመጣል፣ እጅ ሲያጥርህ ይመጣል፣ እንድሜዬ ገፋ ስትል ይመጣል፣ ከዚህ በኋላ "ለምኔ" ስትል ከአንድ ዙሩን ያስጀምርኻል፣ "ኧ...ህ" ብለህ ስታበቃ "ኦ...ህ" ብሎ ያስደንቅኻል ቢዘገይም ይመጣል ሲቀርም ይመጣል፡፡
አሜን፡፡

👉🏻 ደሜ ነህ
👉🏻 መልዕቱ ለሚያስፈልጋቸው ሼር አድርጉት፡፡

👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
መነኩሴ የነበረ አሁን ግን ለማጭበርበር ሲሆን ልብሱን ለብሶ ብቅ የሚል ምውት
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌📌 ድራማ በሚሠራ ሰው አትበሳጭ። ይኼ እኮ በራሱም በሰዎችም ላይ ድራማ የሚሠራ ሰው ነው። ዛሬ ቆብ አድርጎ ታየ። በሌላ ፎቶ ላይ ራቁቱን ይታያል። ይኼ በጣም የሚያሳዝን ሰው ነው። ከቁምነገር አትቁጠረው። ሰይጣን የሚጫወትበት ሰው ስለሆነ ያሳዝናል። ውሸት የሰይጣን ነው። ልብሱም ትምህርቱም ውሸት ከሆነ ሰው ጽድቅ አይገኝም። « ልብሱንና ትምህርቱን ጠልቼአለሁ » ስላለው እምነት እንደገና ላስተምር ብሎ ብቅ ማለት የሰይጣን ግልገልነት ነው። የሥጋ ፍላጎታቸው አሸንፏቸው ለወደቁ ሰዎች ማዘን እንጂ መናደድ አይገባም። ምናልባት ዕድሜ ለንስሐ ሰጥቶት አንድ ቀን ይጸጽተው ይሆናል። በጥምቀት ያገኘው የልጅነት ፀጋ ከእግዚአብሔር ነውና አይጠፋም። አንድ ቀን ይህ የጉርምስና ዕድሜው ሲያልፍ እና ዝሙትና የምግብ ፍቅሩ አንድም በበሽታ አንድም በመከራ ልክ ሲገባ ይመለሳል። እስከዛው ግን እንደሞተ ሰው ነው የምቆጥረው። ጌታ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15 በጠፋው ልጅ አንጻር እንዳስተማረን አሁን ለቤተ ክርስቲያን ይህ ሰው «የሞተ ልጇ» ነው። ነፍስ ይማር።

🛑 ... ወደ ቀጣዩ ገጽ ይሻገራል።

📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📌📌 በነገራችን ላይ ለምንኩስና ተጠርተው የምንኩስና ሕይወት ሲከብዳቸው ምንኩስናቸውን የተዉ ሰዎች ብዙ ናቸው። ነገር ግን ምንኩስናቸውን ቢተዉትም እምነታቸውን አጥብቀው እስከ ዕለተ ሞታቸው ይዘልቃሉ እንጂ እንደነዚህ ሰዎች አያብዱም። መናፍቅ ለመባልም ያልበቁ ሰዎች በሙሉ «መናፍቅ» እያልን ማጀገን አይገባም። እነዚህ ዱርዬዎች ናቸው። መናፍቅ የሚባለው እንደ አርዮስ እንደ መቅዶንዮስ ያለ እንጂ የሰፈር ዱርዬ ሁሉ « መናፍቅ አይባልም » የተወናበደ፣ የተታለለ፣ « የተሸወደ » ነው።
-
📌📌 ሁላችንንም በቤቱ ያጽናን፤ እንዲህ በሰይጣን ከመዋረድ ይሠውረን። በዚህ አይሳቅም። ያሳዝናል። እዘኑለት እንጂ አትሳቁበት አትሳለቁበት፣ አልቅሱለት። ሰይጣን ቢያታልለው ነው። ይሰውረን።

👉🏻 Kesis Ephrem

🟢 ሼር
🟡 ሼር
🔴 ሼር
👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ በአንድነት እንዲቆም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠየቀ።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌 የጉባዔው የበላይ ጠባቂዎችና አባላት የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር ፣ በቀለም ፣ በኃይማኖት ፣ በብሔርና በፖለቲካ አቋም ሳይለያይ ግንባታውን ለማጠናቀቅ በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

📌 መንግሥትም ከተፋሱስ ሀገራት ጋር የሚያደርገውን ድርድር በሰላማዊ መንገድ በመቀጠል ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም የጉባዔው የበላይ ጠባቂዎች አሳስበዋል። የሃይማኖት አባቶቹ ግድቡ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የልማትና የዕድገት ተስፋ መሆኑን አስታውሰው መንግሥት የሚያደርገውን ድርድር አጠናክሮ መቀጠል አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
” ጠይቀህ ሞክረህ በምታጣው ነገር አትዘን እራስህን በጭንቀት አትጉዳ ሁሉ ቢፈቀድልህም ሁሉም ግን አይጠቅምህምና ስላጣህውም ነገር ቢሆን አመስግን። እኔ የቅርብህ ነኝና አትፍራ።የሚያስፈልግህን ነገር በዕንባ ከጸሎት ጋር ወደ እኔ አሳውቅ እንጅ አትጨነክ። ”

🟢🟡🔴 ፊልጵስዩስ 4÷6 🟢🟡🔴

🛑 💥 J🅾️IN 💥 . 💥f🅾️ll🅾️w 💥 ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
“ ከታላላቆቹ #መላእክት አንዱ #ገብርኤል_ሊረዳኝ መጣ ”
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
👉🏻👉🏻 “ እግዚአብሔር የፈጠራቸው መላእክትና ሠለስቱ ደቂቅ ሌሎችም እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ እርሱ የተመሰገነ ነው፤ ለዘለዓለሙ ከፍ ከፍ ያለ ነው። እግዚአብሔር ከሞትና ከሲኦል እጅ፣ ከመቃብር አፍ አድኖናልና፣ ከሚነደውም ከምድጃው እሳት ታድጎናል፤ ከነበልባሉም መካከል አውጥቶናል፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ስሙንም አመስግኑ፤ ቸር ነውና”(ዳን.፫፣፷፯) ይላሉ ሠለስቱ ደቂቅ አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል። ይህ ጸሎት ሠለስቱ ደቂቅ በሚነደው እቶነ እሳት ጉድጓድ ውስት ሆነው በእግዚአብሔር ቸርነት ፣በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የተደረገላቸውን ተአምር በማየት አንድ ሆነው በኅብረት ለፈጣሪያቸው የዘመሩት፣ የጸለዩት፣ ያቀረቡት ምስጋና ነው።

👉🏻👉🏻 “ እግዚአብሔርን አምነው፣ ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው፣ ፈርተው፣ ተንቀጥቅጠው፣ አክብረው፣ አምልኮቱን በሕግ በሥርዓት በሚፈጽሙት መላእክተ እግዚአብሔር በዙሪያቸው ተገኝተው ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃቸዋል ”(መዝ.፴፣፯-፰)። ቅዱሳን መንፈሳውያን፣ ክቡራን ብርሃናውያን፣ ልዑላን ሰማያውያን፣ ኃያላን፣ ጽኑዓን የሰው ጠባይና አካል የሌላቸው የቅዱሳን መላእክት የሊቃነ መላእክት ተፈጥሮ ሰማይና ምድር በተፈጠረበት በዕለተ እሑድ ነው።

🛑 ... ወደ ቀጣዩ ገጽ ይሻገራል።

📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
👉🏻👉🏻 ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት” እርሱ አለ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ ተፈጠሩም “(መዝ.፻፵፰፣፭) ብሏል። ከዚህም ጋር እግዚአብሔር አምላክ በመጀመሪያው ዕለተ እሑድ ሰማይንና ምድርን እንደ ፈጠረ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገር ሲሆን መላእክትንም በዚሁ ዕለት መፍጠሩን ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል። ቅዱሳን መላእክት፣ ሊቃነ መላእክት ምእመናን ምእመናት የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ለመርዳት ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው። እነዚህ ረቂቃን ፍትረታት መላእክት፣ ሊቃነ መላእክት ዓለም ከተፈጠረ፣ ዘመን ከተቈጠረ ጀምሮ በዘመነ አበው፣ በዘመነ መሳፍንት፣ በዘመነ ነገሥት፣ በዘመነ ካህናት፣ በዘመነ ሥጋዌ ሰውን ከመርዳት የቦዘኑበት ጊዜ አልነበረም።

👉🏻👉🏻 እስከዛሬ ፣ ከዚያም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከአበው ቅዱሳን ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃንና ሰማዕታት ጋር እግዚአብሔርን ከማመስገን፣ ሰውን ከመርዳት የዘገዩበት ጊዜ አልነበረም፤ የለም አይኖርምም። መላእክት በሥነ ፍጥረት መነሻ፣ በዕለተ እሑድ የተፈጠሩ ረቂቃን፣ መንፈሳውያን፣ ኃያላን ስለሆኑ ሲገለጡ ግርማቸው፣ ሲናገሩ ድምፃቸው ያስፈራል፤ ያስደነግጣል፤ የእግዚአብሔር ክብር መገለጫዎች ናቸውና።

👉🏻👉🏻 የሥጋውያን ፍጥረታት ጠባይ መብላት፣ መጠጣት፣ መልበስ፣ ማጌጥ፣ መድከም፣ ማንቀላፋት ሲሆን የቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮ ንጹሕ፣ ቅዱስ የሆነውን እግዚአብሔርን ሲቀድሱ መኖር ነው።

( ከብፁዕ አቡነ ገሪማ ትምህርት የተወሰደ )

👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
..........
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🛑 " #i_can't #breathe‼️ "
🛑 " #መተንፈስ_አልቻልኩም‼️ "
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌 በአፍሪካውያን ( #በጥቁሮች ) ላይ እየተደረገ ያለው የዘቀጠ ዘረኝነት የሚያስከትለው ዋጋ ከሚያስቡት በላይ ነው‼️

📌 በአሜሪካ ሚንያፖሊስ የተፈፀመው የአውሬነት ተግባር ያሳዝናል ዳግማዊ ምንሊክ የጣልያን ምርኮኛ ይዘው የዓለም አቀፍ ሕግ ሳይጠቅሱ ምርኮኛ መብቱ መከበር አለበት ብለው ተንከባክበው ይዘው በሰላም ወደ ሀገራቸው ሸኝተዋል ነበር። ከመቶ ዓመት በፊት የነበሩት አባቶቻችን በሃይማኖትም በሰዋዊነትም ስልጡኖች ነበሩ። ከመቶ ዓመት በኋላ የተፈጠረ ዘረኛ ግን እጁን የፊጥኝ አስሮም አንገቱ ላይ ቆሞ ልተንፍስበት እያለ እያቃሰተ ገደለው።

📌 ዛሬ የታላላቅ ሚዲያዎች መነጋገሪያ የሆነው ቪዲዮ ልብ የሚነካ የዘረኝነትን ጥግ የሚያሳይ ነው። ይህ ዘረኛ ነጭ የአሜሪካ(ሚኒያፖሊስ) -ፖሊስ በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ይህን አፍሪካዊ አሜሪካዊ አንገቱ ላይ ለ9 ደቂቃ በጉልበቱ አንቆ መተንፈስ አልቻልኩም እባክህ እያለው ባደባባይ ገደለው። አብረውት ከነበሩት አራት ፖሊሶች ጋር ወዲያው ከሥራቸው የተባረሩ ሲሆን፣ FBI ወንጀሉን እየመረመረው ነው። ሟቹ ጆርጅ ፍሎይድ ፦" ኧረ መተንፈስ አልቻልኩም ኧረ አየር አጣሁ ፤ እባክህ አትግደለኝ " እያለ በጣር ቢጮኽም ገዳዩ ፖሊስ ሊራራለት ግብረ አበሮቹም ሊያስጥሉት አልቻሉም።

📌 እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥
የሐዋርያት ሥራ 17:26

👉🏻 J🅾️IN #እና f🅾️ll🅾️w #ያድርጉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos
🛑 #ዘረኝነት‼️ 🛑
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌 በአፍሪካውያን ( በጥቁሮች ) ላይ እየተደረገ ያለው የዘቀጠ ዘረኝነት የሚያስከትለው ዋጋ ከሚያስቡት በላይ ነው‼️

👉🏻 #የተለያዩ_ዘሮች_ሊኖሩ_የቻሉት_እንዴት_ነው⁉️
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌 “ አዳምም የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ሚስቱን ሔዋን ብሎ ጠራት። ” ዘፍጥረት 3:20

👉🏻 #መጽሐፍ_ቅዱስ_ምን_ይላል⁉️
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌 አምላክ አዳምና ሔዋን የተባሉትን ሁለት ሰዎች ከፈጠረ በኋላ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም” አላቸው። (ዘፍጥረት 1:28) በመሆኑም አዳምና ሔዋን ለመላው የሰው ዘር አባትና እናት ሆኑ። በኋላ ላይ የጥፋት ውኃ መጥቶ የምድርን ነዋሪዎች በሙሉ ባጠፋ ጊዜ አራት ጥንዶች ማለትም ኖኅና ሚስቱ ከሦስት ልጆቻቸውና ከልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ተረፉ። መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም የኖኅ ልጆች ዝርያ እንደሆንን ይናገራል።—ዘፍጥረት 9:18, 19

👉🏻 #ባለሙያዎች_ምን_ይላሉ⁉️
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
📌 የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) “ሁሉም የሰው ልጆች ዝርያቸው አንድ ሲሆን ሁሉም ከአንድ የዘር ግንድ የመጡ ናቸው” ብሏል። የዘርና የዘር ጥላቻ አዋጅ፣ 1978

🛑 ... ወደ ቀጣዩ ገጽ ይሻገራል።

📩 ( #facbook ) https://www.fb.me/terbinos
📩 ( #telegram ) https://t.me/Terbinos