Telwin Creative Space
1.21K subscribers
134 photos
14 videos
56 links
The creative space to learn graphic design in Amharic. Follow our easy, beginner-friendly tutorials and start creating professional designs.
Download Telegram
Telwin Creative Space
@TelwinCreative
በፈረንጆቹ 2021 March ወር መጨረሻ ላይ በዲዛይነሮች ኮሚኒቲ መካከል መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተ አንድ ዜና ነበር። ይህም የቻይናው የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩብንያው Xiaomi (ሻውሚ) ይፋ ያዳረገው አዲሱ የድርጅቱ ሎጎ ነበር።

ሎጎው በጃፓን ቶክዮ በሚገኘው Musashino Art University የዲዛይን ፕሮፌሰር በሆነው ጃፓናዊው ስመ ጥር ግራፊክ ዲዛይነር Kenya Hara የተነደፈ ነው።

አዲሱ ሎጎ ከቀድሞው የኩባንያው ሎጎ ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ሲሆን በጉልህ የሚታየው ብቸኛው አዲስ ነገር sharp የነበሩት ጠርዞች rounded መሆናቸው ብቻ ነው ፤ ይህም ብዙዎች ዘንድ አግራሞትን ከመጫሩ ባለፈ የተደረገው ማሻሻያ አንዳንዶች ዘንድ መሳለቂያ እንዲሆን አድርጓል።

ነገር ግን ዲዛይነሮችን ይበልጥ ያነጋገረው እና ያስገረመው ጉዳይ ይህ አልነበረም ፤ ይልቁኑ XiaomiKenya Hara ለዚህ ስራው የከፈለው የገንዘብ መጠን ነበር።

Xiaomi ለብዙዎች ላልተዋጠላቸው አዲስ ተብሎ የበፊቱን ሎጎ በጥቂት ማሻሻያ ብቻ ላቀረበው ዲዛይነር Kenya Hara የከፈለችው ገንዘብ $300,000 ነበር።በዚህም የተነሳ ብዙዎች በተለይ ከተሰራው ስራ አንጻር  እጅግ በጣም የተጋነነ ክፍያ እንደሆነ በማውሳት ክስተቱን ሲቀባበሉት ተስተውሏል።

Kenya Hara በበኩሉ ለ Xiaomi ያቀርባቸው የነበሩ የሎጎ ዲዛይን አማራጮች ለረዥም ጊዜ ውድቅ ሲደረጉ መቆየታቸውን እና በስተመጨረሻም ተቀባይነት ያገኘው ዲዛይን ይህ እንደሆነ በማስረዳት ያደረገው ማሻሻያ ተራ rounded ቅርፅ ሳይሆን ሂሳባዊ ስሌት ላይ የተመረኮዘ ረቂቅ ስራ እንደሆነ ገልጿል።"ቢሆንም እንኳ ሎጎው ከዚህ በላይ የተሻለ መሆን ይችል ነበር ክፍያውም የተጋነነ ነው" የሚለው የብዙዎች አስተያተት ነው።

ነገር ግን በዚህ መሐል Xiaomi የብዙዎችን ትኩረት መሳብ መቻሉና መነገጋሪያ ሆኖ መሰንበቱ ማንም የማይክደው ክስተት ሆኖ አልፏል።😉

አላህ ለኛም እንዲህ አይነቱን Client ጀባ ይበለን!

@TelwinCreative
👍12
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🖥 የግራፊክ ዲዛይን ሶፍትዌሮች Popular Graphic Design Software)

🖌 CorelDraw

🟢 ከላይቭ የተወሰደ !

@TelwinCreative
👍3🙏1
😕🙄😁

@TelwinCreative
😁18
Who is known as the father of modern graphic design?

@TelwinCreative
የዛሬ 3ዓመት አከባቢ ስለ ሎጎ እና ዓይነቶቹ የጻፍኩትን አጭር ፅሁፍ ላጋራችሁ በደንብ አንብቡት እና እጠይቃቸኋለው።

===============
💡 #ስለሎጎ_Logo ምን ያህል ያውቃሉ?
ሎጎ (አርማ) ማለት በአጭሩ አንድን ድርጅት ወይም ተቋም ወይም ምርት ወይም አገልግሎት የሚገልጽ እና የሚወክል #ምልክት ነው።ይህ ምልክት ጽሁፍ ወይም ምስል ወይም ቅርጽ ሊሆን ይችላል።አሊያም እነዚህን ይዘቶች በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ መለያ ሊሆን ይችላል።ለተለያዩ ድርጅቶች እና ተቋማት መለያነት ተነድፈው ጥቅም ላይ የዋሉ የተለያዩ የሎጎ ዓይነቶች አሉ።ዝርዝራቸውን እንሆ :-

1️⃣.Word mark (Logo type)
ይህ የሎጎ ዓይነት የድርጅቱን ስያሜ በጽሁፍ በማስቀመጥ ብቻ የሚነደፍ ሲሆን ፤ የፊደላቱ ቅርጽ በእጅ ጽሁፍ አጻጻፍ ወይም ለዚሁ ተብሎ በተነደፈ Font (የፊደላት ቅርጽ/ስታይል) አሊያም በሌላ ለየት ባለ የአጻጻፍ ስልት የተጻፈ ሊሆን ይችላል።ለዚህ ምሳሌ ከሚሆኑ ዝነኛ ሎጎዎች መካከል የ ኮካ ኮላ (Coca Cola) ፣ የሶኒ (SONY) ፣ የካነን (Canon) እንዲሁም የጉግል (Google) ሎጎዎች ተጠቃሽ ናቸው።

2️⃣.Letter mark
ይህ የሎጎ ዓይነት የድርጅቱን ስያሜ የመጀመሪያ ፊደላት ብቻ በመጠቀም የሚነደፍ የሎጎ ዓይነት ሲሆን ፤ ከመጀመሪያው Word mark ሎጎ የሚለየው ሎጎው የሚያካትተው ሙሉ የድርጅቱን ስያሜ ሳይሆን የስያሜውን የመጀመሪያ ፊደላት ብቻ መሆኑ ነው።ለዚህ ታዋቂ ምሳሌ መሆን ከሚችሉ ሎጎዎች መካከል የ ናሽናል ኤሮናቲክስ ኤንድ ስፔስ አድሚኒስትሬሽን /ናሳ/ - እ.ኤ.አ 1975 - 1992 ጥቅም ላይ የዋለው ሎጎ (The National Aeronautics and Space Administration /NASA/ from 1975 until 1992) ፣ እና የ ኬብል ኒውስ ኔትዎርክ /ሲኤንኤን/ (Cable News Network /CNN/) ሎጎ ተጠቃሽ ናቸው።ይህ ዓይነቱ ሎጎ ስማቸውን መጥራት (ምላስ ላይ) ለሚከብዱ አሊያም ስያሜያቸው ረዥም ለሆኑ ድርጅቶች ዓይነተኛ ምርጫ ነው።

3️⃣.Pictorial mark (Brand mark)
ይህ የሎጎ ዓይነት ድርጅቱን በሚገልጹ ምስሎች ወይም ምልክቶች የሚነደፍ ሲሆን ምንም ዓይነት ጽሁፋዊ ይዘት የለውም።ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ከሚሆኑ ሎጎዎች መካከል የ አፕል (Apple) ፣ የትዊተር (twitter) እና የ ኢንስታግራም (Instagram) ሎጎዎች ተጠቃሽ ናቸው።

4️⃣.Abstract logo mark
ይህ የሎጎ ዓይነት የ Pictorial mark (ከዚህ በፊት ሶስተኛ ላይ የጠቀስነው የሎጎ ዓይነት) አንድ አካል ሲሆን ከ Pictorial mark የሚለየው ይህኛው የሎጎ ዓይነት የሚነደፈው እንደ Pictorial mark በግልጽ ምንነታቸው በታወቁ ምስሎች እና ምልክቶች ሳይሆን በአንጻሩ ረቂቅ በሆኑ የጂኦሜትሪክ ቅርጾች ነው።ለዚህ እንደ ምሳሌ የ ፔፕሲን (pepsi) ሎጎ መጥቀስ ይቻላል።

5️⃣.Mascots
ይህ ዓይነቱ ሎጎ ስዕላዊ ገጸ ባህሪያትን በመጠቀም የሚነደፍ ሲሆን ለዚህ ሚስተር ፒናትን (Mr. Peanut) እንደምሳሌ መውሰድ እንችላለን።

6️⃣.Combination mark
ይህ የሎጎ ዓይነት ከላይ የጠቀስናቸውን የሎጎ ዓይነቶች ( ስያሜ እና ምልክትን ወይም ስያሜ እና ቅርጽን ወይም ስያሜ እና ምስልን) በማጣመር የሚነደፍ የሎጎ ዓይነት ሲሆን በርከት ያሉ ሎጎዎችን በዚህ መልኩ እናገኛለን ለምሳሌ ያህል የአዶቤ (Adobe.inc) የ አዲዳስ (adidas) ፣ የማይክሮ ሶፍት (Micro soft) እና የህዋዌ (HUAWEI) ሎጎዎችን መጥቀስ ይቻላል።

7️⃣.Emblem
ይህ የሎጎ ዓይነት ልክ እንደ Combination mark (ከዚህ በፊት ስድስተኛ ላይ የጠቀስነው የሎጎ ዓይነት) ስያሜ እና ቅርጽን ወይም ምስልን ... በማጣመር የሚነደፍ የሎጎ ዓይነት ሲሆን ከ Combination mark የሚለየው የድርጅቱ ስያሜ እና የተነደፈው ቅርጽ ወይም ምስል ለየብቻ የሚቀመጡ ሳይሆኑ ስያሜው በሎጎው ቅርጽ ውስጥ ታቅፎ የሚቀመጥ መሆኑ ነው ።ለዚህ እንደምሳሌ የ ናሳ (NASA) ፣ የ ቢኤም ደብልዩ (BMW) እና የ ፎርድ (Ford) ሎጎዎችን መጥቀስ ይቻላል።

By Esmael Kemal
Jul 24 2022

@TelwinCreative
7👍3
እነዚህ ሎጎዎች ከየትኛው የሎጎ አይነት የሚመደቡ ናቸው?
👍1
Who is excited to start the course?
🔥22🤝8👍7
ሀገራችን ላይ ባለው የኮርስ አሰጣጥ (በተለይ ግራፊክ ዲዛይን ላይ) ላይ የምታይዋቸው እና ቢስተካከሉ የምትሏቸው ክፍተቶችን ምንድን ናቸው?

በእኛም ኮርስ ላይ እንዳንግማቸው ሀሳባችሁን አጋሩኝ።
👍2
የት ጠፋህ?!
አሰላም አለይኩም ወረህመቱላህ
ያጀመዓ እንዴት ሰነብታችሁ? በያላችሁበት አላህ ሰላማችሁን ያብዛላችሁ።ከአሁን አሁን ኮርሱን ጀመርን ብላችሁ እየጠበቃችሁ ባላችሁበት ድንገት ጥፍት ብያለው ፤ ለዚህ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለው። ከአቅሜ በላይ በሆኑ ድንገተኛ እና ተከታታይ ሃጃዎች ተጠምጄ ነበር።ከዚህ በፊት ስክሪን ሹት አድርጌ አንዳጋርኋችሁ የፎቶሾፕን ኮርስ ሪከርድ ማድረግ ልጀምር ጫፍ እንደደረስኩ ጠቆም አድርጊያችሁ ነበር።ሆኖም አላህ ያሻው ሆኗል ለኸይር ነው።

ኮርሱን እንዲሁ ብድግ ብሎ ከማቅረብ ይልቅ በጥንቃቄ ጀማሪን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እያንዳንዱ ነጥቦች ቅደም ተከተላቸው ፣ ገለጻቸው ፣ ምሳሌያቸው ቀድመው ሊዘጋጁ ይገባል የሚል እምነት አለኝ። ያ ባይሆን ምናልባት በፊቱኑ ጀምረን ወይም እስካሁንም ጨርሰን ሊሆን ይችል ነበር ፤ ግን ከየት ጀምሬ ወደ የት እንደምሄድ ፣ እንዴት እንደማስረዳችሁ በምን እንደማስረዳችሁ እዛው እያስተማርኩ ከሆነ የማስበው እና የማዘጋጀው ፣ የእናንተን ጊዜ ከማባከኑ በዘለለ የምትጨብጡትም ትምህርት የተበታተነና የተግበሰበሰ ነው የሚሆነው።

በአላህ ፈቃድ የኮርሱን 2 ክፍሎች ሪከርድ አድርጌ እንደጨረስኩ ቀጣይ ክፍሎችን ሳንጠብቅ እንጀምራለን። እነዚያን እየተማርን ቀጣዮቹ ክፍሎች ይቀዳሉ ኢንሻአላህ።

እስካሁን ለጠፋሁት በምን ልካሳችሁ?👀

@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌224👍1
እ.ኤ.አ በ1987 በ አሜሪካ ውስጥ በሚገኘው ሚሽገን ዩኒቨርሲቲ በ Computer vision ዘርፍ የዶክትሬት ተማሪ የነበረው ቶማስ ኖል Display የተሰኘን በ ማክንቶሽ ኮምፒዩተር ምስሎችን በ Black & White የሚያሳይ ቀለል ያለ ሶፍትዌር ኮምፒዩተሩ ላይ ሰራ ።በጊዜው Industrial Light & Magic በተሰኘ ካምፓኒ በ ቪዥዋል ኢፌክት ሱፐርቫይዘርነት ይሰራ የነበረው ወንድሙ ጆን ኖል ሶፍትዌሩን በተመለከተ ጊዜ ነገርየው ወደ ፊት ትልቅ ተስፋ ሊኖረው እንደሚችል አሰበ።ሁለቱ ወንድማማቾች በጋራ በመሆን የሶፍትዌሩን አቅም ይበልጥ አሳድገው የተሟላ የ ምስል ማቀናበሪያ አደረጉት ስሙንም Image pro ብለው ጠሩት።

ወንድማማቾቹ ቶማስ እና ጆን ሶፍትዌሩን እንደ አፕል እና አዶቤ ላሉ ስመ ጥር የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አቀረቡ።ነገር ግን ሀሳቡ ያሳመነው በጊዜው የ አዶቤ አርት ዳይሬክተር የነበረው ራስል ብራውን ነበር። በ1998 ወንድማማቾቹ ከአዶቤ ጋር አዶቤ ብቸኛ የሶፍትዌሩ አቅራቢ እና ሻጭ ሆኖ ሶፍትዌሩን ለገበያ እንዲያቀርብ ውል ተፈራረሙ።

1990 አዶቤ በማክንቶሽ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚሰራ የሶፍትዌሩን የመጀመሪያ ቨርዥን ይፋ አደረገ።በጊዜ ሂደት አዶቤ የሶፍትዌሩን ሙሉ ባለቤትነት በመጥቅለል እንዲሁም በየጊዜው በአዳዲስ ማሻሻያዎች በማዘመን ሶፍትዌሩ በምስል ቅንብር ዘርፍ ዝነኛ እና ግንባር ቀደም እንዲሆን አደረገው።

ይህ ሶፍትዌር የፎቶ ቅንብር ንጉሱ Photoshop ነው!

@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍61
ግራፊክ ዲዛይነር ለመሆን ያሰባችሁ ይህንንም የዲዛይነርነት ህይወት ክፍል እያሰባችሁ!🤨

ሁሉን ወዶ አይሆንም 😁

@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰7👍4😴2