Telwin Creative Space
1.22K subscribers
135 photos
14 videos
57 links
The creative space to learn graphic design in Amharic. Follow our easy, beginner-friendly tutorials and start creating professional designs.
Download Telegram
ማነኛውም ማሳካት የምንፈልገውን ነገር ከዳር ለማድረስ ዓላማ መኖሩ የግድ ይላል። ፍላጎትና ወኔ ለመጀመር ይጠቅሙን ይሆናል ፤ ለመዝለቅና ረጅም ለመጓዝ ግን አያዋጡም። የሰው ልጅ እንደመሆናችን በዚህች ዓለም ውስጥ በተለያዩ ክስተቶች ውስጥ እናልፋለን ፤ ደስታ ፣ ሐዘን ፣ ንዴት ፣ ብስጭት ... እነዚህ ነገራቶች በፍላጎትና ወኔያችን ላይ የራሳቸውን አሻራ ጥለው ያልፋሉ። ፍላጎት መቼ እንደሚርቀን ወኔ መቼ እንደሚከዳን አናውቅም። ህልማችንን ለማሳካት በምናደርገው ጉዞ ፍላጎትና ወኔን እንደመጓጓዣ መጠቀም ድንገት ተበጥሶ አውላላ ሜዳ ላይ ሊያስቀረን በሚችል የባቡር ፉርጎ ላይ እንደመንጠልጠል ነው። የምር ህልምህን ማሳካት ከፈግክ ጉዞህን በፍላጎትና ጊዜያዊ ወኔ ሳይሆን ግልፅ በሆነ ዓላማና ግብ ጀምረው!

#TelwinArticles

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11🤝2
የቅዳሜ ላይቫችን በምን ርዕስ ላይ ይሁን?
Telwin Creative Space
ማነኛውም ማሳካት የምንፈልገውን ነገር ከዳር ለማድረስ ዓላማ መኖሩ የግድ ይላል። ፍላጎትና ወኔ ለመጀመር ይጠቅሙን ይሆናል ፤ ለመዝለቅና ረጅም ለመጓዝ ግን አያዋጡም። የሰው ልጅ እንደመሆናችን በዚህች ዓለም ውስጥ በተለያዩ ክስተቶች ውስጥ እናልፋለን ፤ ደስታ ፣ ሐዘን ፣ ንዴት ፣ ብስጭት ... እነዚህ ነገራቶች በፍላጎትና ወኔያችን ላይ የራሳቸውን አሻራ ጥለው ያልፋሉ። ፍላጎት መቼ እንደሚርቀን ወኔ መቼ…
ዓላማ እና ፍላጎት

ስለ ግራፊክ ዲዛይንና መሰል የcreative ዘርፎች በየሶሻል ሚዲያው የሚወራውን ተፈላጊነትና ጥሩ የገቢ ምንጭነት በመስማት ብዙዎቻችን "ግራፊክ ዲዛይን መማር እፈልጋለው" ቪዲዮ ኤዲቲንግ መማር እፈልጋለው" ... ስንል ይሰማል። በዚህ ደረጃ ብዙ ሰው ወደ creative ዘርፉ ለመግባት መፈለጉ የ creative communityውን ከማሳደግ  ፣ ልምድ ለመለዋወጥ የተሻለ እድሎችን ከመፍጠር  እንዲሁም ለአገርኛ የcreative ስራዎች የሚሆኑ ማቴሪያሎችን በስፋት ለማዘጋጀት እድል ከመፍጠሩ አንፃር ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም ፤ ምን ያህሎቻችን ነገሩን ከተራ ፍላጎት በዘለለ በዓላማ ደረጃ ይዘነዋል የሚለው እንደኔ ወሳኝ ጥያቄ ነው።

ብዙዎቻችን "ይህን መማር እፈልጋለው" የምንለው ፤ ተሰርቶ ያለቀውን ውብ ስራ አይተንና የሚያስገኘውን ገቢ ሰምተን እንጂ ያየነውን ውብ የcreative ስራ ለመስራት የሚያስችለውን ክህሎት ለመጨበጥ ምን አይነት ጥረት እንደሚፈልግ ፣ በምንሰራቸው ስራዎች የሰማነውን አይነት ገቢ ለማግኘት ምን አይነት ስራ ከእኛ እንደሚጠበቅ አውቀንና ለዚያ ራሳችንን ዝግጁ አድርገን አይደለም።

በዚህ የተነሳ ዛሬ graphic design ፣ ከሳምንት በኋላ video editing ፣ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ web እሱንም እንተውና ደግሞ crypto ፣ እሱም አልጨበጥ ሲለን digital marketing ...

የዚህ ሁሉ ሰበብ እንደኔ ተራ ፍላጎትንና ዓላማን አለመለየት ነው።በፍላጎት ደረጃ ጥሩ ገቢ ቢኖረው ፣ የዘመኑ ተፈላጊ ሙያዎች ባለቤት ቢሆን ማን ይጠላል? ማንም። ማንም አይጠላም! ስንት ምንመኘው ነገር አለ ግን ፈለግን ወይም ተመኘን ማለት ዓላማን ሰነቅን ፣ ለዓላማውም የሚያስፈልገውን መስዋትነትን ለመክፈል ዝግጁ ሆንን ማለት አይደለም።

እናማ ዓላማ እና ልባችን ላይ ውል ብሎ የሚያልፍን ተራ ፍላጎት ከለየን ፤ ጊዜያችን ሳይባክን የትኛው ዘርፍ ላይ ማተኮር እንዳለበን ለመወሰን አንቸገርም ባይ ነኝ። አይመስላችሁም?

From the archive -  Sept 21/2025

#TelwinArticles

🌐 @TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12🔥1
Live stream scheduled for
🔴 Live session 

➡️ Ask Me About Graphic Design

🟣በግሉ የተማረ ዲዛይነርና በinstitute የሰለጠነ ዲዛይነር ልዩነታቸውና የሚያገኙት ጥሩና መጥፎ ጎን ምንድን ነው?
🟣Ai ዲዛይነሮችን ሊተካ ይችላል?
🟣የዲዛይን Psychology ፣ በሰው አእምሮ ላይ የ colors & fonts ተፅእኖ ምን ይመስላል?

ሌሎችንም ያሏችሁን ጥያቄዎች አቅርባችሁ ምላሻቸውን እናያለን።

🕝 ዛሬ ምሽት 3፡00

🌐 በTelwin የቴልግራም ቻናል

🔗  የላይቩ ሊንክ https://t.me/TelwinCreative?livestream=04566fdbfd50dac28b
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6🔥1
Which software is mainly used for vector design?
Anonymous Quiz
31%
😄
8%
😂
43%
😆
18%
😍
2
Pomodoro

Productivity ላይ እንቅፋት ከሚሆኑብን ነገሮች መካከል አንዱ የ ሙድ ማጣት ነው። ብዙዎቻችን ጋር "ዛሬ የስራ ሙዴ አልመጣም ፣ ዛሬ የመማር ሙዴ አልመጣም ፣ ዛሬ የማንበብ ሙዴ አልመጣም ..." ማለት የተለመደ ነው። አዎ የሰው ልጅ እንደመሆናችን ዘውትር መስራት ፣ ሁሌም መማር ፣ ያለማቋረጥ ማንበብ ... አታካች ነው። ኃይላችንን ለማደስ የእረፍት ጊዜ ማስፈለጉ አያጠያይቅም ። "ሆኖም ሙዴ ካልመጣ አልሰራም ፣ አልማርም ፣ አላነብም ... " ማለት ግን ፤ የጀመርነውን ፕሮጀክት ከማራዘም ውጭ ምንም ጥቅም የሌለው የሰነፍ ምክንያት ነው። ሙድ ይመጣል ይሄዳል ፤ እኛ ግን ሙድ ኖረም አልኖረም በፕሮግራማችን መሰረት ስራችን ላይ ፣ ትምህርታችን ላይ ፣ ንባባችን ላይ ... ወዘተ መገኘት የግድ ነው። ባይሆን ሙድ ሳይኖረን መስራት የምንችልበትን አንድ trick አለ እሱም Pomodoro ነው። ideaው ለ 25 ደቂቃ focus አድርጎ መስራት ከዚያ 5 ደቂቃ break መውሰድ ከዚያ ተመልሶ ለ 25 ደቂቃ መስራት መልሶ 5 ደቂቃ break ማድረግ ... ይህንን 4 ጊዜ ከደጋገሙ በኋላ ረዘም ያለ break መውሰድ ነው። ይህ technique "just 25 ደቂቃ ነች ሰራ ሰራ አድርጌ break አደርጋለው" ብለን ራሳችንን እየሸወደን ረዥም መስራት ያስችለናል። ብዙ ጊዜ ስራውን ከጀመርን በኋላ ሙዳችን ስለሚመጣ break ማድረጉን ራሱ ልንረሳው ወይም አውቀን ልንተወው እንችላለን። ለዚህ ተብለው የተዘጋጁ appኦች አሉ pomodoro ብላችሁ search ስታደርጉ ታገኛላችሁ። አውራዳችሁ ሞክሯቸው ይጠቅሟችኋል።


#TelwinArticles

🌐 @TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍10🔥2

በቀን ውስጥ መስራት የምፈልጋቸውን ነገሮች በቅደም ተከተል list ለማድረግና ተፈፃሚነታቸውን ለመከታተል የምጠቀመው tool Microsoft  to Do ነው።ያለምንም ውጣ ውረድ taskኦችን በቀላሉ manage ለማድረግ ስለሚቀል በጣም ይመቸኛል።

ለPcም ለስልክም የተዘጋጀ App ስላለው እንደየሁኔታው በሁለቱም እጠቀመዋለው። እዚህጋ በጣም ደስ የሚል feature አለው ፤ እሱም የPcው እና የስልኩ App ላይ በተመሳሳይ Microsoft Account ከገባን  በየትኛውም device plan ያደረግናቸውን ታስኮች ማግኘትና manage ማድረግ እንችላለን።

ብዙ Advanced የሆኑ features ያላቸው ሌሎች tools አሉ።ግን plan ማድረግና ማስተካከል ላይ ብዙ ጊዜ ከመፍጀት ይልቅ ቶሎ taskኦችን list አድርጎ ወደ ስራ መግባትን ስለምመርጥ Microsoft to Do ይመቸኛል።

እስካሁን እንደዚህ አይነት toolኦችን የመጠቀም ልምድ ያላችሁ አጠናቅራችሁ ቀጥሉ ፤ የሌላችሁ ደግሞ መጠቀም ጀምሩ።

በቀን ውስጥ መስራት ያለብንን ነገር እንደዚህ አይነት tool ላይ ማስቀመጥና በጭንቅላት ብቻ መያዝ ለውጡ ጎልቶ ላይታየን ይችላል። ግን በተግባር ስንሞክረው ሰፊ ለውጥ እንዳለው መታዘብ እንችላለን።

የሆነን ስራ ጨርሰን ቀጥሎ ምን መስራትና የቱን ማስቀደም እንዳለብን ለመወሰን ስንቴ ተወዛግበናል? ፣ ብዙ የሚሰሩ ነገሮች እንዳሉ ህሊናችን እየነገረን ግን የሚሰራው ምን እንደሆነ ለማስታወስ ስንቴ ጊዜ ወስደን አስበናል? ፣ ጠዋት ላይ ስለ ቀናችን ስናስብ ዛሬ እንሰራዋለን እንጨርሰዋለን ብለን ያሰብነውን ነገር ረስተነው ሳንሰራው ስንት ጊዜ አዘግይተነዋል።

Microsoft to Do ከዚህ ሁሉ ይታደገናል። አንዱን ስራ ጨርሰህ taskኡን mark ስታደረግው ይሄ ያለቀው task ወደ complete section  ይሄድና ቀጥሎ ላለው task ቦታውን ይለቃል። so አንዱን ስራ በጨረስክ ቁጥር ቀጥሎ ምን መስራት እንዳለብህ ማሰብ እንኳን አይጠበቅብህም። እና ደግሞ taskኦችን ጨርሰህ mark ስታደርግ Appኡ የሚያወጣው ድምፅ👌 የሆነ የአሸናፊነት ስሜት ይሰጥሃል። ለምን እንደሆነ አላውቅም ብቻ እሱን ለመስማት ስራዎችን ሁላ ቶሎ ቶሎ ልትጨርስ ትችላለህ😅

እና ... Microsoft to Do ያልሞከራችሁት ሞክሩት ትወዱታላችሁ።

From the archive -  Oct 11/2025

#TelwinArticles

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
18👌2
Inspiration vs Comparison
👍62
😄 Photoshop Beginner Course |19

🔖Pen Tool

🔗https://youtu.be/QZSzIPXOj_s

@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍81
💻 Photoshop Beginner Course |20

🔖Type Tools

🔗https://youtu.be/Q3jEtiR552U

@TelwinCreative
👍42
💻 Photoshop Beginner Course |21

🔖Shape Tools

🔗https://youtu.be/yXmeYQoiFmY

@TelwinCreative
👍21
💻 Photoshop Beginner Course |22

🔖Fill Layers, Masking & Smart Object

🔗https://youtu.be/wS1YXxBwd98

@TelwinCreative
👍411
💻 Photoshop Beginner Course |23

🔖Adjustment Layers

🔗https://youtu.be/sF1B9fk9dj4

@TelwinCreative
👍31
💻 Photoshop Beginner Course |24

🔖 Layer Styles

🔗https://youtu.be/VRyrfnEQY8o

@TelwinCreative
1
Live stream scheduled for
🎉 Photoshop Course Closing Session

💻 ላለፉት ተከታታይ ወራት ሲሰጥ የነበረው የ Photoshop Beginner Course መጠናቀቁን በማስመልከት የተዘጋጀ!

🟣 ኮርሱን ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ ምን ነበር?
🟣 ኮርሱን የማዘጋጀትና የማቅረቡ ሂደት ምን ይመስል ነበር?
🟣 ሰዎች ጋር የነበረው አቀባበልና አስተያየት ምን ነበር?
🟣ከዚህስ በኋላ ምን ይቀጥላል?
🟣 በቀጣይ Telwin ላይ ምን እንጠብቅ?

🎙 እነዚህንና መሰል ነጥቦችን እናንተን ባሳተፈ መልኩ እንዳስሳለን

🗓 ነገ እሁድ ግንቦት 16/2018

🕔 ምሽት 3፡00

📍 በTelwin የቴልግራም ቻናል እንገናኝ

🔗  የላይቩ ሊንክ https://t.me/TelwinCreative?livestream=7bbfc257d3252b249d
🔥13👏5🎉1
Started!
💻 Photoshop Beginner Course |25

🔖 Practice | Modern Furniture Social Media Poster

🔗https://youtu.be/NpTUVa78R6s

🎉 Final Photoshop Beginner Course Video 🎉
👍82