Telwin Creative Space
1.21K subscribers
134 photos
14 videos
56 links
The creative space to learn graphic design in Amharic. Follow our easy, beginner-friendly tutorials and start creating professional designs.
Download Telegram
አዳዲስ ክህሎቶችን በመማር ሂደት ላይ ያስተዋልኩት አንድ ነገር ቢኖር ፤ ክህሎቱን ሳልማረው በፊት በሩቁ ለዘርፉ የነበረኝ እይታ እና ተምሬ እራሴን ዘርፉ ውስጥ ሆኜ ሳየው ያለኝ እይታ እጅግ የተለያዩ መሆናቸውን ነው።ነገር ግን በዚህ መሃል ለሁለት ዓይነት ሰዎች ያለኝ ተቃራኒ የሆነ ስሜት መቼም ከውስጤ አይጠፋም።ነገሩን ምንም ሳላውቀው በፊት ማወቅ እንደምችል እና ቀላል እንደሆነ እንዲሰማኝ ላደረገኝ ሰው ያለኝ ውዴታ እና ፤ ከባድ እና የማይቻል እንደሆነ እንዲሰማኝ ላደረገኝ ሰው ያለኝ ጥላቻ!

Feb 25/2025

🌐 @TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💯12👎21
ዓላማ እና ፍላጎት

ስለ ግራፊክ ዲዛይንና መሰል የcreative ዘርፎች በየሶሻል ሚዲያው የሚወራውን ተፈላጊነትና ጥሩ የገቢ ምንጭነት በመስማት ብዙዎቻችን "ግራፊክ ዲዛይን መማር እፈልጋለው" ቪዲዮ ኤዲቲንግ መማር እፈልጋለው" ... ስንል ይሰማል። በዚህ ደረጃ ብዙ ሰው ወደ creative ዘርፉ ለመግባት መፈለጉ የ creative communityውን ከማሳደግ  ፣ ልምድ ለመለዋወጥ የተሻለ እድሎችን ከመፍጠር  እንዲሁም ለአገርኛ የcreative ስራዎች የሚሆኑ ማቴሪያሎችን በስፋት ለማዘጋጀት እድል ከመፍጠሩ አንፃር ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም ፤ ምን ያህሎቻችን ነገሩን ከተራ ፍላጎት በዘለለ በዓላማ ደረጃ ይዘነዋል የሚለው እንደኔ ወሳኝ ጥያቄ ነው።

ብዙዎቻችን "ይህን መማር እፈልጋለው" የምንለው ፤ ተሰርቶ ያለቀውን ውብ ስራ አይተንና የሚያስገኘውን ገቢ ሰምተን እንጂ ያየነውን ውብ የcreative ስራ ለመስራት የሚያስችለውን ክህሎት ለመጨበጥ ምን አይነት ጥረት እንደሚፈልግ ፣ በምንሰራቸው ስራዎች የሰማነውን አይነት ገቢ ለማግኘት ምን አይነት ስራ ከእኛ እንደሚጠበቅ አውቀንና ለዚያ ራሳችንን ዝግጁ አድርገን አይደለም።

በዚህ የተነሳ ዛሬ graphic design ፣ ከሳምንት በኋላ video editing ፣ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ web እሱንም እንተውና ደግሞ crypto ፣ እሱም አልጨበጥ ሲለን digital marketing ...

የዚህ ሁሉ ሰበብ እንደኔ ተራ ፍላጎትንና ዓላማን አለመለየት ነው።በፍላጎት ደረጃ ጥሩ ገቢ ቢኖረው ፣ የዘመኑ ተፈላጊ ሙያዎች ባለቤት ቢሆን ማን ይጠላል? ማንም። ማንም አይጠላም! ስንት ምንመኘው ነገር አለ ግን ፈለግን ወይም ተመኘን ማለት ዓላማን ሰነቅን ፣ ለዓላማውም የሚያስፈልገውን መስዋትነትን ለመክፈል ዝግጁ ሆንን ማለት አይደለም።

እናማ ዓላማ እና ልባችን ላይ ውል ብሎ የሚያልፍን ተራ ፍላጎት ከለየን ፤ ጊዜያችን ሳይባክን የትኛው ዘርፍ ላይ ማተኮር እንዳለበን ለመወሰን አንቸገርም ባይ ነኝ። አይመስላችሁም?

🌐 @TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍274
😄 Photoshop Course Exercise 5

⭐️ 🔠🔠🅰️🔠🔠
........................................................

NEBAT
SARAH
ABU AFNAN
MAME

አራታችሁም ጥያቄው በሚያዘው መሰረት layerኦችን arrange ከማድረግ ባለፈ realistic composition ለመፍጠር ያደረጋችሁትን ጥረት አደንቃለሁ። በርቱ በዚሁ ቀጥሉ!

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏122🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎨Color mode

ከዚህ በተቃራኒው በ RGB መሰራት ያለበትን በCMYK በ CMYK መሰራት ያለበትን ደግሞ በ RGB ብንሰራ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?

🌐 @TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6🤔2
የፊታችን ቅዳሜ ላይቭ ይኖረናል። ርዕሰ ጉዳያችን የትኛው ይሁን?
Final Results
28%
How to Think Like a Designer?🤔
31%
Skills Every Designer Should Have💡
40%
The Design Journey From Idea to Final Output🎇
Telwin Creative Space
🎨Color mode ከዚህ በተቃራኒው በ RGB መሰራት ያለበትን በCMYK በ CMYK መሰራት ያለበትን ደግሞ በ RGB ብንሰራ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? 🌐 @TelwinCreative
Color Mode ቢቀያየር ምን ይፈጠራል?

ለምሳሌ በ RGB mode መሰራት የነበረበትን የሶሻል ሚዲያ ዲዛይን በ CMYK mode ብንሰራው ወይም በ CMYK መሰራት የነበረበትን ባነር በ RGB Mode ብንሰራው ምን ይሆናል?

የሶሻል ሚዲያ ዲዛይኑ በ CMYK በመሰራቱ ምንም ላይሆን ይችላል ግን ዲዛይን ላይ መጠቀም የምንችላቸውን ከለሮች ለህትመት በሚሆኑ ከለሮች ብቻ ይገድብብናል።

በተቃራኒው ግን ባነሩን በ RGB ከሰራነው ከታተመ በኋላ የምናያቸው አንዳንድ ከለሮች ዲዛይን ላይ ከሰራንባቸው ከለሮች የተለዩ ሊሆኑ ይችላሉ።

🤔እንዴት?

🖨 ፕሪንተሮች የሚጠቀሙት CMYK ከለርን ነው ዲዛይኑን የተሰራው ደግሞበ RGB mode ነው ፤ በዚህ መሀል ምናልባት ፕሪንተሮች በሚጠቀሙት CMYK ከለር ሊታተም የማይችል ከለር ተጠቅመን ሊሆን ይችላል። ይሄኔ ፕሪንተሩ ምን ያደርጋል? ያን ከለር ማተም ስለማይችል ወደሚችለው ተቀራራቢ ከለር ቀይሮ ያትመዋል። ሰለዚህ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይፈጠር የምንሰራውን ዲዛይን በትክክለኛው Color Mode ላይ አድርገን መስራት ይኖርብናል።

ግን RGB, CMYK ምን ማለት ነው?

🌐 @TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍122
📄 Photoshop Course Exercise 6

🔗 https://forms.gle/DLyvqQBiAH4xASPE6

⚠️ ይህ Exercise ክፍት ሆኖ የሚቆየው እስከ ነገ ዕሮብ ምሽት 5፡00 ነው! ከዚያ በኋላ ይዘጋና የደፈኑ ተማሪዎች ስም ዝርዝር ወጥቶ ሲያበቃ ይከፈታል።

🌟 የደፈኑ ተማሪዎች Exercise STARS List ላይ የሚኖራቸው ቅደም ተከተል ጨርሰው ባስገቡበት የጊዜ ቅደም ተከተል መሰረት ነው።

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6
🏬 ህንጻዎች ላይ ያሉ ባነሮችን ለማየት ማንጋጠጥ ከጀመርክ ፤ እወቅ! ግራፊክ ዲዛይነር እየሆንክ ነው።
ካልጀመርክ ግን መጀመር አለብህ 😁

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁23👍4
"በፍጹም ልትወድቅ የማይገባበት ብቸኛው ጊዜ ፣ የመጨረሻ ሙከራህን የምታደርግበት ጊዜ ነው።"

ፊሊፕ ናይት

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
10👍7
😄 Photoshop Beginner Course | 07 | Selection tools #2

🔖 Lasso tools


🖥 https://youtu.be/wtDzHAXsTVQ

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍41
Live stream scheduled for
🔴 Live session 

➡️ The DESIGN JOURNEY - From Idea to Final Output

አንድ የዲዛይን ስራን ከclient ከመቀበል አንስቶ ሙሉ ለሙሉ አልቆ እስከማስረከብ ድረስ ያለውን ሂደት እንቃኛለን።

🟣ከ client ጋር እንዴት እንደምንግባባ ፣
🟣የ Design idea እንዴት እንደምናፈልቅ ፣
🟣የDesign process ምን እንደሚመስል
🟣ለDesign የምንጠቀማቸውን መሰረታዊ እና ተጓዳኝ tools & materials እነማን እንደሆኑ ከሌሎች ተያያዥ ነጥቦች ጋር እንዳስሳለን።

መጨረሻ ላይ ያሏችሁን ጥያቄዎች አቅርባችሁ ምላሻቸውን እናያለን።

🗓 ነገ ቅዳሜ መስከረም 17/2018

🕝 ምሽት 2፡30

🌐 በTelwin የቴልግራም ቻናል

🔗  የላይቩ ሊንክ https://t.me/TelwinCreative?livestream=0ad94250c073140cfc

➡️ Share

🌐 @TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍72
😄 Photoshop Course Exercise 6

⭐️ 🔠🔠🅰️🔠🔠


🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5
Exercise 6ን በተሰጠው የጊዜ ገደብ የሰሩት 12 ተሳታፊዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ሁሉንም ጥያቄ በተለይ practical ጥያቄዎችን በትዕዛዙ መሰረት የሰሩት 4ቱ ብቻ ናቸው።

የመጀመሪያውን Exercise በተሰጠው ጊዜ የሰሩት ግን ከ40 በላይ ነበሩ።

ሁሌም የምናየው ነገር ነው። ስንጀምር ብዙ ሆነን እንጀምራልን ፤ የምንጨርሰው ግን በትክክለኛ እና እውነተኛ ዓላማ የጀመርነው ብቻ ሆነን እንገኛለን።

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2😢2
አንድ የዲዛይን ስራ ከጀምር አንስቶ እስከመጨረሻው ድረስ የሚያልፍባቸው ሂደቶች ምንድን ናቸው?

ቀድሞ የመለሰ ጎበዝ ነው🏆

የባለፍውን live የተሳተፋችሁ አሁን ትታያላችሁ 🔍

🌐@TelwinCreative
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁163
ይሄን meme አስታወሳችሁት?
😁14
Telwin Creative Space
ይሄን meme አስታወሳችሁት?
አሁን ላይ እየኖርኩት ነው 🙈

ልዩነቱ የኔ ጉንፋን ነው
😁105🏆1
👍172