TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ህዋ እንዴት ቀዝቃዛ ሆነ ?
********************
ፀሐይ የውስጠኛው ክፍሏ እስከ 27 ሚሊዮን ዲግሪ ፋራናይት የሚደርስ ሙቀት ሲኖረው የውጨኛው ክፍሏ ደግሞ እስከ 10 ሺ ዲግሪ ይሞቃል፡፡ ከመሬት ርቀን ወደ ህዋ ስንወጣ ግን - 455 F የሚደርስ ቅዝቃዜ የገጥመናል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ሙቀት በህዋ ውስጥ እንደ ጨረር፣ ኤሌክትሮ-መግነጢሳዊ ሞገድ (infrared wave) ከሞቃት አካል (ከፀሐይ) ወደ ቀዝቃዛ አካላት ይጓዛል፡፡ ይህ ሞገድ የሚያገኛቸውን ሞሎኪዩሎች(የጋዝ ቅንጣቶች) በሙሉ ሙቀት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህም መንገድ ሙቀት ከፀሀይ ወደ ምድር ይጓዛል፡፡ ይህ ሲሆን በጨረሩ ጉዞ ውስጥ የሚገኙ ሞሎኪዩሎች ብቻ ሲሞቁ ከዚህ መንገድ ውጭ ያሉት ግን እንደ ቀዘቀዙ ይቀራሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ NASA መረጃ ሜርኩሪ የምትባለው ፕላኔት በምሽት ሰዓት ያላት ሙቀት ለፀሐይ ጨረር ከምትጋለጥበት ከቀን በ1000 ዲግሪ ያነሰ ሙቀት ይኖራታል፡፡
በምድራችን ግን በማንኛውም ሰዓት ሙቅ አየር እናገኛለን፡፡ ይህም የሆነው ሙቀት በምድር ላይ እንደ ሌሎቹ በአንድ መንገድ ሳይሆን በሶስት መንገዶች የሚጓዝ በመሆኑ ነው፡፡ ይኸውም ኮንዳክሽን፣ ኮንቬክሽን እና ራዲየሽን በሚባሉ መንገዶች ነው፡፡ ከፀሐይ የሚፈነጥቀው ጨረር ሞሎኪዩሎችን ሲያሞቃቸው የሞቁት ሞሎኪዩሎች በዙሪያቸው ካሉ ሌሎች ሞሎኪዩሎች ጋር በመነካካት ሙቀትን ያስፋፋሉ፡፡
በህዋ የሉት የጋዝ ሞሎኪዩሎች (ቅንጣቶች) ግን በጣም ጥቂትና ተራራቁ በመሆናቸው በንክኪ (conduction) ሙቀትን ማስተላለፍ አይችሉም፡፡ በዚህ የተነሳ ምንም እንኳን የፀሐይ ጨረር በአካባቢው ቢያልፍም ቅዝቃዜው እንዳለ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ ኮንቬክሽን የመሬት ስበትን የሚፈልግ የሙቀት መተላለፊያ መንገድ በመሆኑ የስበተ መጠናቸው ዜሮ በሆኑ አካባቢዎች ሙቀት ሳይተላለፍ ይቀራል፡፡
ምንጭ Popular Science
እሳት አደጋን የሚከላከሉ ቁሶች ምንድናቸው
===============
በእሳት ንብረት ላይ የሚደርስ ውድመትን ስለመቀነስ ሲነሳ ያማይቃጠሉ ናቸው ስለተባሉ ቁሶች ሰምተው ያውቁ ይሆናል፡፡ እዚህ ጋር ግን ማስተዋል የሚገባው የማይቃጠል ወይም Fireproof የሚለው ቃል የተሳሳተ መሆኑን ነው፤ ምክንያቱም ከሞላ ጎደል ካርቦንን በውስጡ የተያዘ ማንኛውም ቁስ በቂ ሙቀት ካገኘ በእሳት ሊቀጣጠል ይችላልና፡፡ ከዚህ ይልቅ እሳትን የሚቋቋም ወይም እሳትን የሚያስቆሙ/የሚያቀዘቅዙ የሚለው ስያሜ ተስማሚ ነው፡፡
ለአብነት አንድ ፕላስቲክ ብዙ ካርበን እና ሃይድሮጅን በውስጡ በመያዙ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀጣጠል ባህርይ አለው፡፡ ጋዝም እንዲሁ ካርበን እና ሀይድሮጅን በውስጡ ይዟል፤ በተጨማሪም በቀላሉ የመትነን እና በጣም በላቀ መልኩ ሊቀጣጠል ይችላል፡፡ በአንፃሩ እሳትን የሚቋቋሙ ቁሶች በቀላሉ የማይቃጠሉት ናቸው፡፡ ለምሳሌ በዘመናዊ ማዕድ ቤቶች ምግብ ማብሰያ ጠረጴዛ ላይ የሚገኘው ሰው ሰረታሽ ድንጋይ ይጠቀሳል፡፡ ይህ ቁስ በእሳት ከማይቃጠለው የረጠበ የአልሙኒየም ኦክሳይድ ውህድ በተሰሩ ድንጋዮችን የተሞላ ሲሆን፤ እነዚህ ድንጋዮች በቁሱ ውስጥ ያለውን የነዳጅ መጠን (ሊቀጣጠል የሚችል ካርበን) በመቀነስ እሳትን ይበልጥ የሚቋቋም ያደርጉታል፡፡>>>>>http://techin.gov.et/post/311/
የፆታ ልዩነት እና የእድሜ ጣሪያ መለዋወጥ
=======================
ድርጅቱ በሪፖርቱ እንደሚያነሳው በእያንዳንዱ ማህበረሰብ የሚፈጠሩት ፆታዊ የስራ መደቦች እና አጠቃላይ አመለካከቶች በወንዶችና ሴቶች መካከል ያለውን የእድሜ ጣሪያ በቀጥታ የመወሰን አቅም ቢኖራቸውም ተፈጥሮአዊ የፆታ ልዩነት እና ባዮሎጂካዊ እውነታዎችም ሌላ ምከንያት ተደርገው ይቀመጣሉ፡፡
ዝርዝሩን ለማንበብ http://www.techin.gov.et/post/312/
ሙቀትን በድምጽ ሞገድ የሚለካው ቴርሞ ሜትር
********************************
የአንድን ነገር ሙቀት ለመለካት ሙቀቱ ከሚለካው አካል ጋር ንክኪ የሚያደርጉ ክሊኒካል እና ላበራቶሪካል የሚባሉ የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን አብዛኛዎቻችን እናውቅ ይሆናል፡፡ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በወጣ ዘገባ ሙቀትን በድምጽ መለካት መቻሉን ሰምተን ልናካፍላችሁ ወደድን፡፡
ሙቀት ያላቸው እቃዎች መጋል ብቻ ሳይሆን ሙቀት በተሰማው እቃ ያሉ ቅንጣቶች (particles) በሚርመሰመሱ ጊዜ መጠነኛ የሆነ ለስላሳ ድምጽ ያሰማሉ፡፡ የሰዎች ጀሮ እነዚህን ድምጾች ለማዳመጥ ንቁ ቢሆን እንደ ሬዲዮ እሽታ አይነት ድምጽ አላቸው፡፡ እቃው በጣም እየሞቀ ሲሄድ የድምጹ መጠንም በዚያው ልክ ይጨምራል ሲል የተናገረው በፒተርስበርግ ዩኒቨርሲቲ የሚሰራው ቶም ፐርዲ ነው፡፡
ቶም ፐርዲ እና የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲው ሮቢንጂት በጋራ በመሆን አንድን የጋለ ነገር በግለቱ ምክንያት የሚፈጠርን ድምጽ በማዳመጥ ያለውን መጠነ ሙቀት መለካት የሚችል መሳሪያን ፈጥረዋል፡፡ ይህም መሳሪያ የድምጽ ሞገድን ከአየር በተሸለ ማስተላለፍ የሚችል ሲልከን ናይትራይድ የተገጠመለት ነው፡፡ ለወደፊት በመጠነኛ ሙቀት ከፍተኛ ተግባራትን ለሚያከናውኑ ኮምፒውተሮች (quantum computing devices) ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል ሲሉ የፊዚክስ ምሁራኑ መግለጻቸውን የዘገበው Science News Magazine ነው
በበራሪ ነብሳት ለተማረረ
**********************
በአለማችን ህይዎት ካላቸው ነገሮች መካከል ብዙ የሚሆኑት ትንንሽ ነብሳት ናቸው፡፡ ይኸውም በአጠቃላጥ ካሉት ህይዎት ካላቸው ነገሮች ማካከል 80% የሚሆነውን ይሸፍናሉ፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ነብሳት ለልዩ ልዩ ሳይንሳዊ ትቶች በጣም አስፈላጊ ቢሆኑም በተለይ ትንኞችና ዝንቦች በቤታችን ውስጥ አሉታዊ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ በተለይ በሞቃታማ አካባቢዎች የሚያደርሱት ተጽእኖ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በእነዚህ ነብሳት ምክንያት የሚመጣውን መረበሽ ለማቆም የተለያዩ መፍትሔዎችን እንጠቀማለን፡፡
እነዚህን ነብሳት አካባቢን በማይረብሽ መልኩ (eco-friendly) በቤታችን አጥምዶ የሚያደርሱትን ረብሻ ማትፋት የሚችል መሳሪ ቀርቧል፡፡ መሳሪያውም ነብሳቱን መሳብ የሚችል ብርሀን ፈንጣቂ (ultraviolet lamp) የተገጠመለት ሲሆን በዚህ ብርሀን ተስበው የሚመጡትን ነብሳትም በአንድላይ ማከማቸት የሚችል ማጠራቀሚያም ተገጥሞለታል፡፡ በማጠራቀሚው ውስጥም በኤሌክትሪክ የሚሰራ ነብሳቱን ሊገድል የሚችል መረብ ተዘጋጅቶለታል፡፡
መሳሪውን ካስቀመጥንበት 80sqm ያሉ በራሪ ነብሳትን ሁሉ ጠራርጎ መሰብሰብ ይችላል፡፡ ሌላው የዚህ መሳሪያ አስደናቂ ነገር የብርሀን አጠቃቀሙ ነው፡፡ በአካባቢው ያለው ብርሀን ሲቀንስ የመሳሪያው ብርሀን ይጨምራል፡፡
በአጠቃላይ ይህ መሳሪያ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ ከመሆኑ በተጨማሪ ትናንሽ በራሪ ነብሳትን ለማጥፋት የሚደረግን የኬሚካል ርጭት ማስቀረት የሚችል ነው፡፡ አምራቾቹ መሳሪያውን Wizap ብለው ሰይመውታል፡፡
ምንጭ፡ Popular science
ወረርሽኞችን እንዴት ማስቆም ይቻላል
*************************************
አለማችን በልዩ ልዩ ወረርሽኞች ተጠቅታለች፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ተስፋችንን በክትባቶች ላይ ብንጥልም እውነቱ ግን አብዘኞቹ ወረርሽኞች እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁ መሆኑ ነው፡፡ የጥንት ሰዎች ልክ እንዳሁኑ በተለያዩ ወረርሽኞች ተጠቅተዋል፡፡
ለምሳሌ The Black Death እየተባለ የሚጠራው ከ1346-1353 የተከሰተው ከሁሉም በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተከሰተው በልዩ ልዩ ጥናቶች እንደተመለከተው ለ2000 ዓመታት ያክል ወረርሽኝ ሆኖ የተከሰተው ምንጩ ባክቴሪያ የሆነው yersinia pestis ሌላው በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እዚህ ላይ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የወረርሽኞች የመስፋፋትና የገዳይነት አቅምም እየጨመረ መምጣቱን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
የሆንግ ኮንግ ጉንፋን እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት እስከ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ቢሆንም አሁንም ግን ስርጭቱ አላቆመም፡፡ እንዲሁም ከጥቂት አስርት አመታት በፊት የተከሰተው ኤች አይ ቪ ቫይረስ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ስርጭቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ እንደ WHO የቁጥር መረጃ ከሆነ በ2019 ብቻ በአለም ዙሪያ 690 ሺህ ሰዎች በዚሁ በሽታ ህይዎታቸው አልፏል፡፡
ሌላም ሳርስ የተባለ ከ2002-2003 ብቻ 800 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን የቀጠፈ በሽታ በአለማችን መከሰቱ የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ የሞት መጠኑ ያልታዎቀ በግማሽ አመት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ኮቪድ 19 ተከሰተ፡፡
በአጠቃላይ በአለማችን የተከሰቱ ልዩ ልዩ ወረርሽኞችን ስንመለከት በቁጥጥር ስር ለመዋል ረጅም አመታትና ብዙ ትውልዶች ስፈልጓቸዋል፡፡ በመሆኑም ስለ ወረርሽኞች ያለን እውቀት መዳበር፣ የማህበረሰብ አጠቃላይ ጤና መሻሻል፣ አዳዲስ ክትባቶች መገኘታቸው የየራሳቸው የሆነ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚያግዝ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመግታት ዘርፈ ብዙ ጥናቶች የተደረጉ ቢሆንም እንዲሁም ስልጣኔ እየጨመረ ሲሄድ የክትባት ፍለጋው እየተሳካ ቢመጣም የውሸባን (ቀሳ) (quarantine) ያክል ግን ውጤታማ የሆነ መፍትሔ አልተገኘም፡፡ አሁን እያለፍንበት ያለውም ወረርሽኝ ማብቂያ ሊገኝ የሚችለው ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሔዎች በጥምረት በተግባር ሲውሉ ብቻ ነው፡፡ ምንጭ BBC news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
CDC ኮሮናቫይረስ በህፃናት እና በአዋቂዎች ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው ከባድ የጤና ቀውስ እያስጠነቀቀ ነው
=====================
የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ መዕከል (CDC) ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ ህፃናት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያየ የበሽታ ምልክቶች ወይም (syndromes) በአዋቂዎች ላይም የመከሰት እድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ በዚህ ሲንድረም ዙሪያ የሚወጡ መረጃዎች በሚገባ እንዲጤኑ እና በትኩረት እንዲታዩ ጥሪ አስተላልፏል፡፡http://www.techin.gov.et/post/318/
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” online training፡- Part 6
Basic Geometry / Basic forms
====================
In this tutorial we will be going over Basic forms for complex drawing.
https://www.youtube.com/watch?v=kw7TdZ7jkXQ
For more science and technology information’s, please subscribe to our cannel.
የእይታ ችግር ላለባቸው ትልቅ መላ
**********************************
ቺይኮ አሳካዋ ትባላለች፡፡ አይነ ስውር ናት፡፡ የኮምፒውተር ሳይንቲስት ስትሆን በስራ ምክንያት በየወሩ ከአሜሪካ ጃፓን ከጃፓን አሜሪካ የአውሮፕላን ጉዞ ታደርጋለች፡፡ በረራ ያደረገችው ብቻዋን ከሆነ ከአየር መንገዱ ሰራተኞች አንዱ ወደምትፈልገው ቦታ ያደርሳታል፡፡ ካልሆነም የምትፈልገውን ሰው እስክታገኝ ለረጅም ሰዓት ትጠብቃለች፡፡
ችግር ብልሀትን ይወልዳል እንዲባል በዚህ ነገር የተማረረችው ቺይኮ ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ሻንጣን ሰርታ አቅርባለች፡፡ ይህም ፈጠራዋ ከአውሮፕላን ከወረደች በኋላ በፍጥነትና ደህንነቷ እንደተጠበቀ ወደ መዳረሻዋ የሚመራት ነው፡፡ ሻንጣው የጉዞ ሻንጣ ሲሆን ካሜራና ሴንሰር የተገጠመለት ነው፡፡ ካሜራና ሴንሰሩ በአብዛኞቹ ራስ ነድ መኪኖች (autonomous car) እንደተገጠሙት ያለ ነው፡፡ ሻንጠው አካባቢውን እንዲያውቅ ሰው ሰራሽ ክህሎትን (artificial intelligence) ይጠቀማል፡፡ ሻንጣውን ለማዘዝ የሞባይል መተግበሪያ እንዲጠቀም ተደርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሻንጣው የሰው ፊት መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል፡፡ ይህም ተጠቃሚውንና በቅርብ ያለ ሰውን እንዲለይ ያስችለዋል፡፡
ይህች ድንቅ እንስት ሌሎች ብዙ ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ለአለም ያስተዋወቀች ሲሆን ከእነዚህም መካከል "aDesigner," ለዲዛይነሮች የሚያግዝና ዌብሳቶችን ለተጠቃሚዎች ቀላል የሚያደርግ ቴክኖሎጂ፣ በድምጽ ኢንተርኔት መክፈት የሚያስችል በተለይ ለአይነ ስውራን ምቹ የሆነ ፈጠራ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ባለድንቅ ቴክኖሎጂውን ሻንጣ ለመስራት ያነሳሳትን ነገር ስትናገር " ብቻየን ስራመድ ምንም ምቾት አይሰማኝም፡፡ ሁልጊዜ በጉዞ ብቸኝነቴን ሊቀርፍልኝ የሚችል ቴክኖሎጂ ምን ሊሆን ይችላል እያልኩ አስባለሁ፡፡ እንዲሁም ስጓዝ የደህንነት ስሜት እንዲሰማኝና በፍጥነት እንዲሆን እፈልጋለሁ ይህም ነው ይህን ሻንጣ እንድሰራ መነሻ የሆነኝ" ትላለች፡፡ ሻንጣው ሌሎች አይነ ስውራንን ሊያግዙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለታል፡፡
ምንጫ CNN Travel
በህክምና ዘርፍ የዚህ ዓመት ኖቬል ሽልማት አሸናፊዎች
===================
በዓለም ዙርያ ለብዙ የሄፒታይተስ እና ጉበት በሽታዎች መነሻ የሆነውን የሄፒታይተስ ሲ ቫይረስን ያገኙትና መረጃዎችን የገለጡት ሦስት የስነ ቫይረስ (Virology) ተራማሪዎች የዚህ ዓመት የህክምና ዘርፍ የኖቬል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ አሸናፊዎቹ ሃርቪ አልተር በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካን ብሄራዊ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያ ሲሆኑ፤ ማይክል ሆውተን እና ቻርልስ ሪይስ ደግሞ የካናዳው የአልበርታ ዩኒቨርሲቲ እና አሜሪካን የሚገኘው የሮክፌለር ዩኒቨርሲቲ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ሦስቱ ተመራማሪዎች በሄፒታይተስ ሲ ላይ የሰሩት ስራ በአሁኑ ሰዓት በበሽታው ላይ ለሚደረገው ስኬታማ ህክምና መንገዱን የጠረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የእነዚህ ተመራማሪዎች ጥናት ጅማሮ ከአራት አስርት ዓመታት በፊት አንስቶ ነው፤ እ.አ.አ ከ1970ዎቹ ሃርቪ አልተር ደም በመስጠት በሚደረገው ህክምና አማካኝነት የሚከሰት የጉበት ህመም መተላለፍን ሲያጠና ቆይቷል፡፡ ቀደም ያለ ስራ ሄፒታይተስ ኤ እና ቢ ቫይረሶችን ቢያገኝም ሃርቪ አልተር ሶስተኛና የደም ውስጥ በሽታ አምጪ ተህዋሲ የሆነው ቫይረስ በሽታውን ወደ ቺምፓንዚዎች ሊያስተላልፍ እንደሚችል አሳየ፡፡ ከዚህ በመቀጠል ማይክል ሆውተን ከስራ አጋሮቹ ጋራ በመሆን በበሽታው ከተጠቁ ቺንፓንዚዎች በተወሰደ ዘረ መል አማካኝነት ቫይረሱን መበየን ችለዋል፡፡ ይህም ከፋቫቪራዴ ቤተሰብ የሚመደብ አዲስ የRNA ቫይረስ አይነት መሆኑን ማሳየት የቻለ ውጤት ነበር፤ ስሙንም ሄፒታይተስ ሲ ብለው ጠሩት፡፡ ቻርለስ ሪይስ በሚመራው የጥናት ቡድን አማካኝነት የተደረገ ምርምር ደግሞ የዘረ-መል ምህንድስና ስልቶችን በመጠቀም ቫይረሱ ያጠቃቸው ህዋሶች ላይ ለሚደረገው የቫይረሱ መባዛት ምክንያት የሆነውን የሄፒታይተስ ሲ ክፍል መለየትና በጉበት በሽታ ውስጥ ያለውን ድርሻ ማሳየት ችሏል፡፡
በአለም የጤና ድርጅት መረጃ መሰረት 71 ሚሊዮን ሰዎች በየዓመቱ በሄፒታይተስ ሲ ሲጠቁ 400 ሺህ ያህሉ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ ሰፊውን ድርሻ የሚወስዱት የሲሮሲስ እና ጉበት ካንሰር በሽታዎች ናቸው፡፡ የኖቬል ሽልማቱ አሸናፊ ተመራማሪዎቹ ስራ ከሌሎች ባለሙያዎች አበርክቶት ጋራ በመሆን በሄፒታይተስ ምርመራ እና ህክምና ላይ ትልቅ መሻሻል እንዲመጣ መንስኤ ሆኗል፡፡ ቀድሞ በበሽታው ላይ ይተገበሩ የነበሩት ከባድ ግን ብዙም ውጤታማ ያልሆኑ የህክምና ስልቶች ምስጋና ለተመራማሪዎቹ ጥረት ይሁንና ቫይረሱን በቀጥታ ወደሚገቱ መድሃኒቶች ዞረዋል፡፡ መድሃኒቶቹ አብዛኛውን የሄፒታይተስ ሲ አመጣሽ በሽታዎችን ማከመም የሚችሉ ሆነው ሳለ ግን ዋጋቸው ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ለሚኖሩ ዜጎች የሚቀመስ አለመሆኑ ተደራሽነታቸውን ቀንሶታል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት ከ10 ዓመት በኋላ ሄፒታይተስ ሲን ጨርሶ ከምድራችን ለማስወገድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ እንደ ዘርፉ ባለሙያዎች ከሆነ ግን ይህን ማድረግ ክትባትን ያሻል፡፡ ይህ ግን በተለይም ለበሽታው ክትባት ለማግኘት ካለው መዘናጋት እና ዝቅተኛ ርብርብ አንፃር አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ከዚህም ባሻገር ምንም እንኳን አሁን የደረስንበት ቴክኖሎጂ ደረጃ ሊፈታው የሚችለው ቢመስልም ቫይረሱ ከሌሎች የቫይረስ አይነቶችም አንፃር ያለው የላቀ ውስብስብነት ሌላው ፈተና ነው፡፡ ታድያ የኖቤል ሽልማቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ትልቁን እርምጃ ለተራመዱት ተመራማሪዎች መበርከቱ በሽታው የሚገባውን ትኩረት ለመሳብ ሊረዳው ይችል ይሆን የሚል ተስፋን ፈጥሯል፡፡
ምንጭ፡ Nature
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” online training፡- Part 7 (final)
Simple Drawing Exercises on Basic geometry
In this tutorial we will be going over exercise on basic forms, the seven element of art, Which are building block for Artist and designer.
https://www.youtube.com/watch?v=tUK2By1ig_I&t=71s
Answer the questions in Plain paper (A4/A3) and get participation certificate. Email us your captured answer with your full name.
Check out our email and PDF file in the description.
Thank you.
ውድ ተከታታዮቻችን “BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” በሚል ርዕስ በኢንስቲትዩቱ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ሲተላለፍ የቆየውን ስልጠና አስመልክቶ የሚቀርቡላችሁን የመለማመጃ ጥያቄዎች በመወረቀት ላይ (A4 ወይም A3) ሞልታችሁ ከነስማችሁ በኢሜይል አድራሻችን (stic.ethiopia@gmail.com) የምታደርሱን ይሆናል፡፡
//ስልጠናውን በአግባቡ ለተከታተሉና የሚቀርቡትን የመለማመጃ ጥያቄዎች ሞልተው ከላይ በተጠቀሰው የኢሜል አድራሻችን ለሚልኩልን ሰልጣኞች ሰርተፊኬት አዘጋጅተን የምናደርስ መሆኑን በድጋሚ እንገልፃለን፡፡//
የመለማመጃ ጥያቄዎችን በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://drive.google.com/file/d/1uVzucK89r8dvHm3jyMOTTsxh4eNykbhk/view
የአፍንጫ መድማትን ለማቆም የሚያስችል መንገድ
********************************
ምንም እንኳን የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር አስደንጋጭ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የተለመደ ነው፡፡ በአሜሪካ በተደረገ ጥናት ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የአፍንጫ መድማት ይታይባቸዋል፡፡ በተለይ ከ2-10 ዕድሜ ክልል ያሉ ህፃናትና ከ50-80 ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ከፍተኛውን የቁጥር ድርሻ ይወስዳሉ፡፡
አፍንጫችን የምንስበውን አየር የሚያረጥቡ ብዙ የደም ስሮች አሉት፡፡ በአፍንጫችን በኩል የሚገባው አየርም ወደ አፍንጫችን ግድግዳ ተጠግቶ በሚያልፍበት ወቅት ለዚህ የመድማት ችግር ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው ከፍተኛ ግፊት ያለው ነፋስ ሲኖርና በእጃች አላስፈላጊ መነካካት ስናዘወትር ነው፡፡ እዚህ አካባቢ የሚከሰት መድማት anterior nosebleeds በመባል ይታወቃል፡፡
ብዙ ጊዜ ያልተለመደውና የከፋ ጉዳት ሊያደርስ የሚችለው ከውስጠኛው የአፍንጫ ስር የሚመነጨው posterior nosebleeds የሚባለው ነው፡፡ ልዩ ህክምናም የሚስፈልገው የአፍንጫ መድማትም ይህኛው ነው፡፡ የዚህ አይነቱ የአፍንጫ መድማት በአደጋ የአፍንጫ መሰበር ሲያጋጥም፣ የቅርብ ጊዜ የአፍንጫ ቀዶ ህክምና ሲኖር፣ ደምን ሊያቀጥኑ የሚችሉ መድሀኒቶችን ስንጠቀም፣ የደም ስሮችን የሚጎዳ ተፈጥሯዊ ችግር ሲኖርና የሉኪሚያ ተጠቂ ስንሆን የሚከሰት ነው፡፡
ይሁንና የአፍንጫ መድማትን በቀላሉ በቤት ውስጥ ማሰቆም ይቻላል፡፡ ችግሩን ለማስቆም ብዙ መንገዶች ቢኖሩም በአሜሪካ የሚገኘው Yale Medicine ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅደም ተከተሎች መከተል ተገቢ ነው ይላል፡፡
ተስተካክሎ በመቀመጥ የአፍንጫን ለስላሳውን ክፍል በለስላሳ ጨርቅ ወይም በሶፍት ለ10 ደቂቃ ያክል መያዝ
እጅን ፊት ለፊት አድርጎ አፍንጫን መያዝና በአፍ ብቻ መተንፈስ
በጨርቅ የተጠቀለለ በረዶ ከግንባራችን ስር በማድረግ የአፍንቻችን የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ ማድረግ
መተኛት ወይም መንጋለል ልባችንን ወደ አፍንጫችን ስለሚያቀርበው በተቻለ መጠን ተስተካክሎ መቀመጥ
ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች በአግባቡ ከተገበርን መድማቱ የመቆም እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም መሔድ የሚጠበቅብን ጊዜ ሊኖር እንደሚችል ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ Revere Health የተባለ የምርምር ተቋም ወደ ህክምና ሊያስኬዱን የሚችሉ ምልክቶችን እንዲህ ሲል ዘርዝሯል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን መንገዶች ተጠቅመን የአፍንጫ መድማቱ ካልቆመ
የአፍንጫ መድማቱ የተከሰተው በአደጋ ከሆነ
አፍንጫችን የደማው የደም ማቅጠኛ መድሐኒቶችን ከወሰድን በኋላ ከሆነ
ምንጭ:- www.howstuffworks.com