በማርስ የተገኙት ሐይቆች
***********************
በ2018 በፕላኔቶች ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉ ተመራማሪዎች በማርስ ደቡባዊ ዋልታ ከበረዶ ስር ትልቅ የጨዋማ ውሃ ሀይቅ አግኝተናል ብለው ነበር፡፡ አሁን ያ አለ የተባለው ሐይቅ ማረጋገጫ ያገኘ ሲሆን ሌሎች ሶስት ሐይቆችም ተገኝተዋል፡፡
ከቀናት በፊት ከኔቸር አስትሮኖሚ 1 የወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በአውሮፓ የህዋ ምርምር በማርስ ዙሪያ የሚሰራው ማርስ ኤክስፕረስ የራዳር መረጃን በመጠቀም ግኝቱን አረጋግጧል፡፡ ይህም በቀይዋ ፕላኔት ህይወት ላላቸው ነገሮች መኖሪያ የሚሆን የመጀመሪያው የውሀ አካል ያደርገዋል፡፡
የውሀ አካሉን ህልውና ለማረጋገጥ ተመራማሪዎች ከ2012 እስከ 2019 ድረስ 134 ምልከታዎችን አድርገዋል፡፡ የተገኙት የውሀ ክፍሎችም ባጠቃላይ እስከ 75000 ስኩየር ኪሎ ሜትር ይሸፍናሉ፡፡
ፕላኔቷ ከፀሐይ በ4ኛ ደረጃ ርቃ የምትገኝ በመሆኗ ከመሬት እጅግ ትቀዘቅዛለች፡፡ በአማካኝም 227,936,640 km ያክል ከፀሐይ ትርቃለች፡፡ እንደ ናሳ መረጃ ከሆነ የማርስ ከባቢ አየር በ 95.32% ካረቦንዳይ ኦክሰይድ፣ 2.7% ናይትሮጅን፣ 1.6% አርገን፣ 0.13% ኦክስጅንና በ0.08% ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ የተሸፈነ ነው፡፡
ምንጭ Cnn international, SPACE .COM

ባለ 3200 ሜጋ ፒክስሉ መፃኢ ካሜራ የመጀመሪያውን ፎቶ ግራፍ አንስቷል
በካሊፎርኒያ መቀመጫውን ያደረገው SLAC ናሽናል አክስለሬተር ላብራቶሪ የመጀመሪያ የተባለውን ይህን ግዙፍ ካሜራ የሰራው Vera C. Rubin ለተሰኘው ኦብዘርቫቶሪ ሲሆን ይህም የወደፊቱ LSST ካሜራ በመሆን ጥልቅ ምልከታዎችን እና ሰፋፊ የምርምር ውጤቶችን ለማሳለጥ የሚረዳ ባለ 3200 ሜጋ ፒክስል ካሜራ ነው፡፡
ይህ ካሜራ የዓለማችን የመጀመሪያው ትልቁ ዲጂታል ካሜራ ሲሆን በርሱ የተነሳው ፎቶ ደግሞ በዚህ ትልቅ የዲጂታል ካሜራ የተነሳ የመጀመሪያው እና ትልቁ ታሪካዊ ፎቶ እንዲሰኝ አድርጎታል፡፡
ባለሞያዎቹ እንደተናገሩት ከሆነ ይህንን ፎቶ በሙሉ ቁመናው ለመመልከት 378 4k UHD ያህል ጥራት ያለው ቴሌቪዢን የሚያስፈልግ ሲሆን፤ ይህም ማለት የጥራቱ ጥልቀት አንዲትን የጎልፍ መጫወቻ ኳስ ከ 25 ኪሎሜትር ርቀት በጥራት ማሳየት ያስችለዋል እንደማለት ነው፡፡
ምንም እንኳ ፎቶው የጎልፍ ኳስን ባይሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳው፤ በቅርበት የተነሳውን የአበባ ጎመን እጅግ በሚገርም ርቀት እና በውስጡ ያለውን ክፍል ረቂቅ በሆነ መልኩ ማሳየት ችሏል፡፡
ካሜራው ወደ 9ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ሲሆን 3ሚሊዮን ዶላር ገደማ ወጪ አድረጓል ሲሉ የ SLAC ናሽናል አክስለሬተር ላብራቶሪ ተመራማሪዎች ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- Live Science

“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” online training፡- Part 4
Perspective (1, 2 & 3 Point Perspectives)
In this tutorial we will be going over linear perspective in which we will cover one point, two point and three point perspectives.
https://www.youtube.com/watch?v=YH53yFLeQ-0
For more science and technology information’s, please subscribe to our cannel.

YouTube

Book References
Thomas Valcke, Basic Sketching Technique for the industrial Designer, Version 1
Koos Eissen and Roselien Steur…

የእጽዋት ዝርያዎች በአደጋ ውስጥ
*********************
በአለማችን ከሚገኙ እጽዋት መካከል 40% የሚሆኑት የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ሲል ሪፖርት ያደረገው ሮያል ቦታኒክ ጋርደን የተባለ አለማቀፍ ድርጅት ነው፡፡ ከዚህ በፊት በ2016 በተሰራ ጥናት 20% የሚሆኑ የእጽዋት ዝርያዎች አደጋ ውስጥ ናቸው ተብሎ ነበረ፡፡
"State of the World's Plants and Fungi 2020" ከቀናት በፊት ከ42 ሀገራት በተውጣጡ 210 ተመራማሪዎች በተሻለ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ዘዴ የችግሩን ጥልቀት አጥንተዋል፡፡ በምእራብ ለንደን የሚገኝ አንድ RBG Kew የተባለ በእጽዋት ላይ የሚሰራ ድርጅት እንዳወጣው መረጃ የደን ጭፍጨፋ፣ የበካይ ጋዝ ልቀት፣ በእጽዋት ላይ የሚደረግ ህገወጥ ንግድና ሀገር በቀል ያልሆኑ እጽዋት መስፋፋት ለችግሩ እንደ ምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡
አጥኝዎች እንደሚሉት በእጽዋት ዙሪያ ያለው እውቀት አነስተኛ መሆኑ የእጽዋት ጥበቃውን ስራ ደካማ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በRBG Kew የሳይንስ ዳይሬክተሩ አሌክሳንደር አንቶኔሊ ለ CNN እንደተናገረው አንዳንድ ዝርያዎችን በማይታመን ፍጥነት እያጣናቸው ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህ 40% የሚሆኑ እጽዋት የሌሉበት ዓለም ለወደፊት አሁን የምናውቀው ዓለም ሊሆን አይችልም፡፡ ዳይሬክተሩ አክሎም ሁሉም ነገር የተያያዘ በመሆኑ የሚመጣው ጉዳት ከፍተኛ ነው ብሏል፡፡
በጥናቱ ውስጥ ከተካተቱ 5411 የመድሐኒት እጽዋት መካከል 723 የሚሆኑት አደጋ ውስጥ ናቸው፡፡ ከዚህ በተቃራኒው የእነዚህ የመድሀኒት እጽዋት ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል፡፡ እነዚህ እጽዋት ያሉበት ደረጃ ተባብሶ extinct ከመሆናቸው በፊት ከፍተኛ በጀት ተበጅቶ ስራ መሰራት አለበት ሲል ሪፖርቱ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ ይህንንም ከማድረግ በተጨማሪ ይላል ሪፖርቱ በአሁኑ ወቅት 90% የሚሆነውን ምግብ የምናገኘው ከ15 እጽዋት በመሆኑ ይህን ማሻሻል ይገባል፡፡ ተመራማሪዎች ሌሎች 7039 የሚሆኑ የእጽዋት ዝርያዎች ለምግብነት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል ጠቁመዋል፡፡ ለሐይል ምንጭነት ደግሞ 2500 የሚሆኑ እጽዋት ያሉ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውሉት ከ10 ያነሱ ናቸው፡፡
ይህን ችግር ለመፍታት ከበጀት በተጨማሪ አለማቀፍ ትብብር አስፈላጊ ነው፡፡ ሪፖርቱ በተጨማሪ የእጽዋቱ ተጠቃሚዎች ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ሲኖርባቸው መንግስታት ደግሞ በፖሊሲ የተደገፈ ስራ መስራት አለባቸው ብሏል፡፡
በመረጃ ምንጭነት CNNን ተጠቅመናል፡፡

የበረሀ አንበጦች ወረራ
=============
የበረሃ አንበጣዎች ከፍተኛ ቁጥር ባለው መንጋ የሚንቀሳቀሱና በአንድ ጊዜ ሰፊ ቦታ መሸፈን የሚችሉ ሶስት አጽቄዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ነብሳት በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት በሰብል ላይ የሚያደርሱ ሲሆን የአፈጣጠር ባህሪያቸውም ከፌንጣ ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ http://www.techin.gov.et/post/309/

www.techin.gov.et
Technology Innovation Inistitute
The Federal Democratic Republic of Ethiopia’s Office of the Prime Minister is currently restructuring under the premiership of Prime Minister Abiy Ahmed. Under the new structure the Office comprises eleven structures.
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” online training፡- Part 5
Exercises on perspective
===================
In this tutorial we will be going over exercises on linear perspective in which we will cover one- point, two -point and three - point perspectives.
https://www.youtube.com/watch?v=-83hfA6NPaM&t=94s
For more science and technology information’s, please subscribe to our cannel.
Exercises on perspective
===================
In this tutorial we will be going over exercises on linear perspective in which we will cover one- point, two -point and three - point perspectives.
https://www.youtube.com/watch?v=-83hfA6NPaM&t=94s
For more science and technology information’s, please subscribe to our cannel.
YouTube
Exercises on perspective
In this tutorial we will be going over exercises on linear perspective in which we will cover one- point, two -point and three - point perspectives.
Book References
Thomas Valcke, Basic Sketching Technique for the industrial Designer, Version 1
Koos Eissen…

ህዋ እንዴት ቀዝቃዛ ሆነ ?
********************
ፀሐይ የውስጠኛው ክፍሏ እስከ 27 ሚሊዮን ዲግሪ ፋራናይት የሚደርስ ሙቀት ሲኖረው የውጨኛው ክፍሏ ደግሞ እስከ 10 ሺ ዲግሪ ይሞቃል፡፡ ከመሬት ርቀን ወደ ህዋ ስንወጣ ግን - 455 F የሚደርስ ቅዝቃዜ የገጥመናል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ሙቀት በህዋ ውስጥ እንደ ጨረር፣ ኤሌክትሮ-መግነጢሳዊ ሞገድ (infrared wave) ከሞቃት አካል (ከፀሐይ) ወደ ቀዝቃዛ አካላት ይጓዛል፡፡ ይህ ሞገድ የሚያገኛቸውን ሞሎኪዩሎች(የጋዝ ቅንጣቶች) በሙሉ ሙቀት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህም መንገድ ሙቀት ከፀሀይ ወደ ምድር ይጓዛል፡፡ ይህ ሲሆን በጨረሩ ጉዞ ውስጥ የሚገኙ ሞሎኪዩሎች ብቻ ሲሞቁ ከዚህ መንገድ ውጭ ያሉት ግን እንደ ቀዘቀዙ ይቀራሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ NASA መረጃ ሜርኩሪ የምትባለው ፕላኔት በምሽት ሰዓት ያላት ሙቀት ለፀሐይ ጨረር ከምትጋለጥበት ከቀን በ1000 ዲግሪ ያነሰ ሙቀት ይኖራታል፡፡
በምድራችን ግን በማንኛውም ሰዓት ሙቅ አየር እናገኛለን፡፡ ይህም የሆነው ሙቀት በምድር ላይ እንደ ሌሎቹ በአንድ መንገድ ሳይሆን በሶስት መንገዶች የሚጓዝ በመሆኑ ነው፡፡ ይኸውም ኮንዳክሽን፣ ኮንቬክሽን እና ራዲየሽን በሚባሉ መንገዶች ነው፡፡ ከፀሐይ የሚፈነጥቀው ጨረር ሞሎኪዩሎችን ሲያሞቃቸው የሞቁት ሞሎኪዩሎች በዙሪያቸው ካሉ ሌሎች ሞሎኪዩሎች ጋር በመነካካት ሙቀትን ያስፋፋሉ፡፡
በህዋ የሉት የጋዝ ሞሎኪዩሎች (ቅንጣቶች) ግን በጣም ጥቂትና ተራራቁ በመሆናቸው በንክኪ (conduction) ሙቀትን ማስተላለፍ አይችሉም፡፡ በዚህ የተነሳ ምንም እንኳን የፀሐይ ጨረር በአካባቢው ቢያልፍም ቅዝቃዜው እንዳለ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ ኮንቬክሽን የመሬት ስበትን የሚፈልግ የሙቀት መተላለፊያ መንገድ በመሆኑ የስበተ መጠናቸው ዜሮ በሆኑ አካባቢዎች ሙቀት ሳይተላለፍ ይቀራል፡፡
ምንጭ Popular Science

እሳት አደጋን የሚከላከሉ ቁሶች ምንድናቸው
===============
በእሳት ንብረት ላይ የሚደርስ ውድመትን ስለመቀነስ ሲነሳ ያማይቃጠሉ ናቸው ስለተባሉ ቁሶች ሰምተው ያውቁ ይሆናል፡፡ እዚህ ጋር ግን ማስተዋል የሚገባው የማይቃጠል ወይም Fireproof የሚለው ቃል የተሳሳተ መሆኑን ነው፤ ምክንያቱም ከሞላ ጎደል ካርቦንን በውስጡ የተያዘ ማንኛውም ቁስ በቂ ሙቀት ካገኘ በእሳት ሊቀጣጠል ይችላልና፡፡ ከዚህ ይልቅ እሳትን የሚቋቋም ወይም እሳትን የሚያስቆሙ/የሚያቀዘቅዙ የሚለው ስያሜ ተስማሚ ነው፡፡
ለአብነት አንድ ፕላስቲክ ብዙ ካርበን እና ሃይድሮጅን በውስጡ በመያዙ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀጣጠል ባህርይ አለው፡፡ ጋዝም እንዲሁ ካርበን እና ሀይድሮጅን በውስጡ ይዟል፤ በተጨማሪም በቀላሉ የመትነን እና በጣም በላቀ መልኩ ሊቀጣጠል ይችላል፡፡ በአንፃሩ እሳትን የሚቋቋሙ ቁሶች በቀላሉ የማይቃጠሉት ናቸው፡፡ ለምሳሌ በዘመናዊ ማዕድ ቤቶች ምግብ ማብሰያ ጠረጴዛ ላይ የሚገኘው ሰው ሰረታሽ ድንጋይ ይጠቀሳል፡፡ ይህ ቁስ በእሳት ከማይቃጠለው የረጠበ የአልሙኒየም ኦክሳይድ ውህድ በተሰሩ ድንጋዮችን የተሞላ ሲሆን፤ እነዚህ ድንጋዮች በቁሱ ውስጥ ያለውን የነዳጅ መጠን (ሊቀጣጠል የሚችል ካርበን) በመቀነስ እሳትን ይበልጥ የሚቋቋም ያደርጉታል፡፡>>>>>http://techin.gov.et/post/311/

techin.gov.et
Technology Innovation Inistitute
The Federal Democratic Republic of Ethiopia’s Office of the Prime Minister is currently restructuring under the premiership of Prime Minister Abiy Ahmed. Under the new structure the Office comprises eleven structures.
የፆታ ልዩነት እና የእድሜ ጣሪያ መለዋወጥ
=======================
ድርጅቱ በሪፖርቱ እንደሚያነሳው በእያንዳንዱ ማህበረሰብ የሚፈጠሩት ፆታዊ የስራ መደቦች እና አጠቃላይ አመለካከቶች በወንዶችና ሴቶች መካከል ያለውን የእድሜ ጣሪያ በቀጥታ የመወሰን አቅም ቢኖራቸውም ተፈጥሮአዊ የፆታ ልዩነት እና ባዮሎጂካዊ እውነታዎችም ሌላ ምከንያት ተደርገው ይቀመጣሉ፡፡
ዝርዝሩን ለማንበብ http://www.techin.gov.et/post/312/

ሙቀትን በድምጽ ሞገድ የሚለካው ቴርሞ ሜትር
********************************
የአንድን ነገር ሙቀት ለመለካት ሙቀቱ ከሚለካው አካል ጋር ንክኪ የሚያደርጉ ክሊኒካል እና ላበራቶሪካል የሚባሉ የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን አብዛኛዎቻችን እናውቅ ይሆናል፡፡ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በወጣ ዘገባ ሙቀትን በድምጽ መለካት መቻሉን ሰምተን ልናካፍላችሁ ወደድን፡፡
ሙቀት ያላቸው እቃዎች መጋል ብቻ ሳይሆን ሙቀት በተሰማው እቃ ያሉ ቅንጣቶች (particles) በሚርመሰመሱ ጊዜ መጠነኛ የሆነ ለስላሳ ድምጽ ያሰማሉ፡፡ የሰዎች ጀሮ እነዚህን ድምጾች ለማዳመጥ ንቁ ቢሆን እንደ ሬዲዮ እሽታ አይነት ድምጽ አላቸው፡፡ እቃው በጣም እየሞቀ ሲሄድ የድምጹ መጠንም በዚያው ልክ ይጨምራል ሲል የተናገረው በፒተርስበርግ ዩኒቨርሲቲ የሚሰራው ቶም ፐርዲ ነው፡፡
ቶም ፐርዲ እና የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲው ሮቢንጂት በጋራ በመሆን አንድን የጋለ ነገር በግለቱ ምክንያት የሚፈጠርን ድምጽ በማዳመጥ ያለውን መጠነ ሙቀት መለካት የሚችል መሳሪያን ፈጥረዋል፡፡ ይህም መሳሪያ የድምጽ ሞገድን ከአየር በተሸለ ማስተላለፍ የሚችል ሲልከን ናይትራይድ የተገጠመለት ነው፡፡ ለወደፊት በመጠነኛ ሙቀት ከፍተኛ ተግባራትን ለሚያከናውኑ ኮምፒውተሮች (quantum computing devices) ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል ሲሉ የፊዚክስ ምሁራኑ መግለጻቸውን የዘገበው Science News Magazine ነው

በበራሪ ነብሳት ለተማረረ
**********************
በአለማችን ህይዎት ካላቸው ነገሮች መካከል ብዙ የሚሆኑት ትንንሽ ነብሳት ናቸው፡፡ ይኸውም በአጠቃላጥ ካሉት ህይዎት ካላቸው ነገሮች ማካከል 80% የሚሆነውን ይሸፍናሉ፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ነብሳት ለልዩ ልዩ ሳይንሳዊ ትቶች በጣም አስፈላጊ ቢሆኑም በተለይ ትንኞችና ዝንቦች በቤታችን ውስጥ አሉታዊ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ በተለይ በሞቃታማ አካባቢዎች የሚያደርሱት ተጽእኖ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በእነዚህ ነብሳት ምክንያት የሚመጣውን መረበሽ ለማቆም የተለያዩ መፍትሔዎችን እንጠቀማለን፡፡
እነዚህን ነብሳት አካባቢን በማይረብሽ መልኩ (eco-friendly) በቤታችን አጥምዶ የሚያደርሱትን ረብሻ ማትፋት የሚችል መሳሪ ቀርቧል፡፡ መሳሪያውም ነብሳቱን መሳብ የሚችል ብርሀን ፈንጣቂ (ultraviolet lamp) የተገጠመለት ሲሆን በዚህ ብርሀን ተስበው የሚመጡትን ነብሳትም በአንድላይ ማከማቸት የሚችል ማጠራቀሚያም ተገጥሞለታል፡፡ በማጠራቀሚው ውስጥም በኤሌክትሪክ የሚሰራ ነብሳቱን ሊገድል የሚችል መረብ ተዘጋጅቶለታል፡፡
መሳሪውን ካስቀመጥንበት 80sqm ያሉ በራሪ ነብሳትን ሁሉ ጠራርጎ መሰብሰብ ይችላል፡፡ ሌላው የዚህ መሳሪያ አስደናቂ ነገር የብርሀን አጠቃቀሙ ነው፡፡ በአካባቢው ያለው ብርሀን ሲቀንስ የመሳሪያው ብርሀን ይጨምራል፡፡
በአጠቃላይ ይህ መሳሪያ ከአካባቢ ጋር ተስማሚ ከመሆኑ በተጨማሪ ትናንሽ በራሪ ነብሳትን ለማጥፋት የሚደረግን የኬሚካል ርጭት ማስቀረት የሚችል ነው፡፡ አምራቾቹ መሳሪያውን Wizap ብለው ሰይመውታል፡፡
ምንጭ፡ Popular science

ወረርሽኞችን እንዴት ማስቆም ይቻላል
*************************************
አለማችን በልዩ ልዩ ወረርሽኞች ተጠቅታለች፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ተስፋችንን በክትባቶች ላይ ብንጥልም እውነቱ ግን አብዘኞቹ ወረርሽኞች እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁ መሆኑ ነው፡፡ የጥንት ሰዎች ልክ እንዳሁኑ በተለያዩ ወረርሽኞች ተጠቅተዋል፡፡
ለምሳሌ The Black Death እየተባለ የሚጠራው ከ1346-1353 የተከሰተው ከሁሉም በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተከሰተው በልዩ ልዩ ጥናቶች እንደተመለከተው ለ2000 ዓመታት ያክል ወረርሽኝ ሆኖ የተከሰተው ምንጩ ባክቴሪያ የሆነው yersinia pestis ሌላው በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እዚህ ላይ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የወረርሽኞች የመስፋፋትና የገዳይነት አቅምም እየጨመረ መምጣቱን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
የሆንግ ኮንግ ጉንፋን እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት እስከ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ቢሆንም አሁንም ግን ስርጭቱ አላቆመም፡፡ እንዲሁም ከጥቂት አስርት አመታት በፊት የተከሰተው ኤች አይ ቪ ቫይረስ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ስርጭቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ እንደ WHO የቁጥር መረጃ ከሆነ በ2019 ብቻ በአለም ዙሪያ 690 ሺህ ሰዎች በዚሁ በሽታ ህይዎታቸው አልፏል፡፡
ሌላም ሳርስ የተባለ ከ2002-2003 ብቻ 800 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን የቀጠፈ በሽታ በአለማችን መከሰቱ የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ የሞት መጠኑ ያልታዎቀ በግማሽ አመት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ኮቪድ 19 ተከሰተ፡፡
በአጠቃላይ በአለማችን የተከሰቱ ልዩ ልዩ ወረርሽኞችን ስንመለከት በቁጥጥር ስር ለመዋል ረጅም አመታትና ብዙ ትውልዶች ስፈልጓቸዋል፡፡ በመሆኑም ስለ ወረርሽኞች ያለን እውቀት መዳበር፣ የማህበረሰብ አጠቃላይ ጤና መሻሻል፣ አዳዲስ ክትባቶች መገኘታቸው የየራሳቸው የሆነ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚያግዝ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመግታት ዘርፈ ብዙ ጥናቶች የተደረጉ ቢሆንም እንዲሁም ስልጣኔ እየጨመረ ሲሄድ የክትባት ፍለጋው እየተሳካ ቢመጣም የውሸባን (ቀሳ) (quarantine) ያክል ግን ውጤታማ የሆነ መፍትሔ አልተገኘም፡፡ አሁን እያለፍንበት ያለውም ወረርሽኝ ማብቂያ ሊገኝ የሚችለው ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሔዎች በጥምረት በተግባር ሲውሉ ብቻ ነው፡፡ ምንጭ BBC news