TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ጉንፋን ወይስ ኮቪድ-19? የምልክት ልዩነቶቹ
==============
በአሁኑ ሰዓት ምድራችንን አስጨንቆ የያዘው የኮቪድ-19 በሽታ ለብዙዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ታድያ ይህ ወረርሺኝ ያሳያቸዋል የሚባሉትን ምልክቶች የጤና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ሲያሳዩን ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ወረርሺኙ ብዙውን ጊዜ ከሚከሰትብን ጉንፋን ጋራ ተቀራራቢ ሊባል የሚችል የህመም ምልክት በማሳየቱ ሳብያ የምልክቶቹ መታየት ብዙ ጭንቀትን ሲያስከትልብን ይታያል፡፡ ስለዚህም በሁለቱ መካከል ያሉ የምልክት ልዩነት እና መመሳሰሎችን በተከታዩ ምስል አማካኝነት ልናሳያችሁ ወደድን፡፡
ሳምንታዊውን የቴክ ሳይንስ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ምዕራፍ ፪ ክፍል ፩ ሙሉ ዝግጅቱን በዩትዩብ ቻናላችን አማካኝነት ይከታተሉ፡፡>>>>https://www.youtube.com/watch?v=q1LPaFM0rFY
ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በ10 ሰዓት በ MOE TV ይከታተሉን
(Nilesat 12520/v/27500)
(በተጨማሪም Ethiosat ላይ እንገኛለን)
የዘመናዊ ኮምፒውተር አፈጣጠርና እድገት አጭር ታሪክ
ከ60 ዓመታት በፊት ከነበረው አንድ ቤት ከሚያክል ግዙፍና ቀርፋፋ ነገር ግን በሚሊዮን ዶላር ከሚያስወጣ የመጀመሪያው ‘ENIAC’የተሰኘ ኮምፒውተር ተነስተን ከመቶወች ዶላር ባልበለጠ ዋጋ ተገዝቶ መዳፍ ላይ ሊቀመጥ የሚችል አነስተኛ መጠንና ፈጣን ብቃት ወዳለው የኮምፒውተር ዘመን ደርሰናል፡፡ ኮምፒውተሮች ዛሬ ላሉበት የተራቀቀ እድገት ለመድረስ ብዙ ሂደቶችን አልፈዋል፡፡ ይህ ጽሁፍ የዘመናዊ ኮምፒውተር አፈጣጠርንና እድገት አጭር ታሪክ ለማስታወስ ታስቦ ከሰሎሞን ሙሉጌታ ካሳ ግርምተ ሳይ-ቴክ መጽሀፍ ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው፡፡

1950ዎቹ፡-

Ø በ “ቫኪዩም ቲዩብ“ ብቻ ይሰሩ የነበሩ ኮምፒውተሮች መጠናቸው የአንድ ቤት መጠን እስኪክል ድረስ እጅግ ግዙፍ የነበሩ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ እጅግ ቀርፋፋ ነበሩ በወቅቱ እነዚህን ኮምፒውተሮች በብቸኝነት ይጠቀምባቸው የነበረው የአሜሪካ ሚሊቴሪ ተቋም ሲሆን ዋጋቸውም ከፍተና ነበር፡፡

1960ዎቹ፡-

Ø ከትራነዚሰተሮች መፈጠር የተነሳ ቀርፋፋውን የ “ቫኪዩም ቲዩብ“ አሰራርን በመቀየር የኮምፒውተሮቹን የአካል መጠን መቀነስ ሲቻል ብቃታቸውንም ማሻሻል ተቻለ፡፡ በዚህ ወቅት ነበር ሜይንፍሬም (mainframe) የተባሉ ፈጣን ውድ ኮምፒውተሮች ተፈጥረው ከሚሊቴሪናየመንግስት ተቋም አልፎ ለግል ድርጅቶች ጥቅም ላይ መዋል የጀመሩት፡፡

1970ዎቹ፡-

Ø በመቶዎች የሚቆጠሩ ትራንዚሰተሮችን ያካተተ ኢንተግሬትድ ሰርኪዩት (integrated circuit) አንድ ክፍል ሊሞላ የሚችል መጠን ያለውን የሜይ ፍሬም ኮመፒውተር አሳንሶ በጠረዛ ላይ የሚቀመጥ ኮምፒውተር (desktop) እንዲፈጠር አስቻለ::

1980ዎቹ፡-

Ø በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተራንዚስተሮች እጅግ በታም ትንሽ በጠን ባለው የኮምፒውተር ቺፕ ውስጥ ህያው መሆን የኮምፒውተር መጠን በታም አንሶ በአንዲት ቦርሳ ውስጥ የሚገባና ከድርጅት አልፎ ለግል ጥቀም መዋል የሚችልበት “personal computer” (PC) ዘመን ተወለደ፡፡ ኮምፒውተሮች ጠረጴዛ ላይ ከመቀመጥ አልፈው ጭን ላይ የሚቀመጡበትን መጠን ይዘው “laptop” በሚል ስያሜ ብቅ አሉ፡፡





1990ዎቹ፡-

Ø የኢንተርኔት መወለድ ኮምፒውተሮች እርስበርሳቸውና በሌላ ቦታ ከሚገኝ ከፍተኛ አቅምና መረጃ ብዛት ለው የኮምፒውተር ስብስብ ‘datacenter’ ጋር ተገናኝተው ከዚህ ቀደም በራሳቸው አቅም ብቻ ከሚሰጡት አገልግሎት እጅግ የላቀ ጥቅምን በፍጥነት መስጠት እንዲችሉ አደረገ፡፡

2000ዎቹ፡-

Ø በእጃችን መዳፍ እንኳን የማይሞሉ ነገር ግን በብቃታቸው ከአንድ መጠኑ ከፍ ካለና ምርጥ ከሚባል ኮምፒውተር ያልተናነሰ ተግባር ማከናወን የሚችሉ እንደ ረቀቀ ስልክ (smart phone) ያሉ ተንቀሳቃሽ ቁሶች በስራ ላይ ዋሉ፡፡ ከስልኮችም አልፎ ታብሌቶቻችን፣ ሰዓቶቻችን፣ የቤት ቁሶቻችን፣ መኪናወቻችንና ልብሶቻችን ሳይቀር የኮምፒውቲንግ ብቃት እተካተተባቸው ይገኛል፡፡

Ø ከዚህም በተጨማሪ ይህ ዘመን አብሮን ባለ በአንድ ኮምፒውተር ብቻ ከመደገፍ ይልቅ እንደ ክላውድ ኮምፒውቲንግ (cloud computing) እና የመሳሰሉ የተራራቁ በኢንተርኔት ተገናንተው መስራት የሚችሉና ከእና ርቀው በተለያየ የኣለም ክፍሎች ተበታትነው በሚገኙ እጅግ ፈታን ኮምፒውተሮች አማካኝነት እጅግ በርካታ ተግባር ማከናወን ተቻለ፡፡

(ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ፣ ግርምተ ሳይ-ቴክ፣ገጽ299-301)
ስልጠና፤ለዲዛይነሮች
============
ውድ ተከታታዮቻችን “BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” በሚል ርዕስ በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና ዳግም በአዲስ መልክ በኢንስቲትዩቱ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ( https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg ) እንድትከታተሉ ባሳለፍነው ሳምንት መጋበዛችን ይታወሳል፡፡
በመሆኑም ስልጠናውን ከሰኞ ጀምሮ በዩትዩብ ቻናላችን መከታተል የምትችሉ ሲሆን ስልጠናውን አስመልክቶ የሚቀርቡላችሁን የመለማመጃ ጥያቄዎች ሞልታችሁ በኢሜይል አድራሻችን (stic.ethiopia@gmail.com) የምታደርሱን ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡ ስልጠናውን ለመከታተል ምንም አይነት ምዝገባ የማያስፈልገው መሆኑን መግለፅ እንወዳለን፡፡
ቀለም እና ብሔራዊ ማንነት
==============
ቀለሞችን አይተን በውስጣችን የሚከሰቱት የደስታ፣ ሀዘን፣ ፍቅር፣ ኩራት እና ሌሎች ስሜቶች በሀገራዊ ማንነታችን ላይ የተመሰረቱ እንደሆነ የሚያሳይ ጥናት በቅርብ ይፋ ሆኖ ነበር፡፡ በዚህም አጥኚዎች አንድ ሰው ከየትኞቹ ቀለሞች ጋራ የስሜት ትስስር እንዳለው በመመልከት ብቻ ሰውየው የየት ሀገር ሰው እንደሆነ መገመት ችለዋል፤ ከግምቶቻቸው ውስጥም 80 በመቶ ያህሉ ትክክል ሆነው ተገኝተዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ከቻይና፣ ጀርመን፣ ግሪክ እና ብሪታንያ የተውጣጡ 711 ሰወዎችን በናሙናነት አካተው ነበር ጥናታቸውን ያከናወኑት፡፡ በጥናቱ ላይ በጎ ፍቃደኝነታቸውን አሳይተው የተገኙት የጥናቱ ተሳታፊዎች እንደ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ-አረንጓዴ የመሳሰሉ የቀለማት ስያሜዎችን እንዲያነቡ ተደርገዋል፡፡ በዚህም አማካኝነት ከተቀመጡት 20 የስሜት አይነቶች ውስጥ አዕምሮአቸው ለየትኛው ቀለም ምን አይነት ስሜት እንደሚያሳይ እና ቀለሞቹ ከስሜቶቹ ጋራ ያላቸው የስሜት ትስስር ጥንካሬ ተለክቶበታል፡፡
ከተሳታፊዎቹ መካከል የብዙዎቹን ስሜት በመቀስቀስ ረገድ ቀይ፣ ጥቁር እና ሮዝ ቀለሞች ቀዳሚዎች ነበሩ፡፡ በተቃራኒው ቡናማ እና ሀምራዊ አነስተኛ የስሜት መነሳሳትን ሲከስቱ ታይተዋል፡፡ በሌላ መልኩ ጥቁር ቀለም ከሁሉም ሀገራት በመጡት ተሳታፊዎች ዘንድ የሀዘን ስሜትን ገላጭ ሆኖ ሲገኝ ቀይ በበኩሉ እንደ ፍቅር እና ደስታ ያሉ አውንታዊ ስሜቶችን ንዴት እና ጥላቻን ከመሳሰሉት አሉታዊ ስሜቶች አጣምሮ መያዙን በሮያል ሶሳይቲ ኦፕን ሳይንስ ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣው ይህ ጥናት አመላክቷል፡፡
ሆኖም እንደየ ዜግነታቸው የተወሰኑ ልዩነቶች ተስተውለዋል፡፡ ለምሳሉ ከጀርመን የመጡት ተሳታፊዎች ከየትኛውም ሀገር በላቀ ቡናማ ቀለም ከአስጸያፊነት ጋራ ሲያስተሳስሩት፤ ከግሪክ የመጡቱ በበኩላቸው ሀምራዊን በዋናነት ከሀዘን ጋራ በማስተሳሰር ብቸኞቹ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በከቻይና የመጡት ተሳታፊዎች ደግሞ ነጭ ቀለም በበለጠ አሉታዊ ስሜትን ሲጭርባቸው (በቻይናዊያን ባህል ቀብር ላይ ነጭ መለበሱን ልብ ይሏል)፤ ቢጫ ቀለም ደግሞ ከግሪኮች በተቀረ በሁሉም ሀገራት ላይ አውንታዊ ስሜትን አጭሯል፡፡
የተሰበሰበን ጥሬ ሀቅ (Data) ወስዶ አንድ ፕሮግራም የሰው ልጆች ወዲያው ሊያስተውሏቸው የማይችሉ ግምት እና ትስስሮችን እንዲያሳይ አድርጎ የሚያሰለጥነውን ማሽን ለርኒንግ የተባለ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) አይነት በመጠቀም ነው ተመራማሪዎቹ የትኛው የጥናቱ ተሳታፊ ከየት ሀገር እንደሆነ ለመለየት የቻሉት፡፡ እንደ ቡድኑ ከሆነ ጥናቱ መሰል ቴክኖሎጂ ለወትሮው ጥሬ ሀቆች ውስብስብ፣ ብዙም ግልፅ ያልሆኑና ለመለየት የሚዳግቱ የሚሆኑበትን የስሜት ጥናት (Emotion Research) ዘርፍን ለመረዳት እንደሚያስችል ጥቁምታን የሰጠ ነው፡፡
ምንጭ፡ Science
ኮቪድ-19ኝን ተከትሎ የበዛው ፅንስ ውስጥ ሞተው የሚወለዱ ህፃናት ምጣኔ
==============
የተለያዩ ጥናቶች እያመላከቱ እንዳሉት በዓለም ዙርያ በማህፀን ውስጥ ሞተው የሚወለዱ ህፃናት ምጣኔ በአሳሳቢ ፍጥነት እያደገ ነው፡፡ እንደ አጥኚዎች ከሆነ በአንዳንድ ሀገራት ነፍሰ ጡር ሴቶች ኮቪድ 19ኝን ተከትለው በመጡ ገደቦች ምክንያት ለወትሮው ሊያገኙት ይገባ የነበረው የጤና ባለሙያ ክትትል ተነፍጓቸዋል፡፡ በዚህ መንስኤነትም ህፃናት ሞተው እንዲወለዱ የሚያደርጉ የጤና እክሎች ተገቢውን ክትትል አላገኙም፡፡ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በስነ ወሊድ ስፔሻሊስት እንደሆኑት ጄን ዋርላንድ አነጋገር “ነፍሰ ጡር ሴቶችን ከኮቪድ 19 ለመከላከል በምናደርገው ጥረት ባልታሰበ ሁኔታ በማህፀን ሞተው የሚወለዱ ህጻናትን ቁጥር አሳድገናል”፡፡
በጉዳዩ ላይ ከተሰሩት ጥናቶች በስፋት የሚልቀውና በኔፓል ውስጥ በሚገኙ ዘጠኝ ሆስፒታሎች ልጅ የወለዱ 20 ሺህ ሴቶችን አካሎ የወጣው ጥናት ከሁለት ሳምንት በፊት በላንሴት ግሎባል ኸልዝ ላይ ታትሞ ወጥቶ ነበር፡፡ ጥናቱ ይፋ ባደረገው ውጤት መሰረት በማህጸን ሞተው የሚወለዱ ህጻናት ቀድሞ ከነበረበት ከ1000 ውልጃዎች 14ቱ በማህጸን ሞቶ መወለድ ምጣኔ የወረርሺኙን ስርጭት ለመገደብ የተጫኑ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን ተከትሎ ቁጥሩ በግማሽ በመጨመር ከሚወለዱ 1000 ህፃናት ውስጥ 21ዱ በማህጸን ሞተው እንደሚወለዱ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ከዚህ የህፃናት በማህፀን ውስጥ ሞቶ የመገኘት ምጣኔ ዕድገት በስፋት የተስተዋለው የእንቅስቃሴ ዕገዳው በተጣለባቸው የመጀመሪያዎቹ አራት ሳምንታት ውስጥ ነበረ፡፡ በዚህ ወቅት ሰዎች ምግብ ለመግዛት ካልሆነና ጥብቅ የጤና ጉዳይ ካላጋጠማቸው በቀር ከቤት ለመውጣት አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡
በስዊድን ባለሙያዎች የሚመራው ጥናት እንዳመለከተው ምንም እንኳን በማህጸን ውስጥ ሞተው የሚወለዱ ህፃናት ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ ቢያሻቅብም አጠቃላይ ቁጥሩ ላይ ግን ለውጦች አልታዩም፡፡ ይህ ግን በተለይ በሆስታል የሚከናወኑ ውልጃዎች ቀድሞ በሳምንት ከነበሩበት የአማካኝ 1261 ውልጃ በግማሽ በማሽቆልቆል ወደ 651 ዝቅ ከማለቱ ጋራ የተያያዘ ነው፡፡ በወቅቱ ሆስፒታል ውስጥ ሲደረጉ ከነበሩት ውልጃዎች መካከልም ሰፊውን እጅ የያዙት ውስብስብ የሆኑ ውልጃዎች ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት ከሆስፒታል ውጭ የወለዱ እናቶችም ሆነ ልጆቻቸው ምን እንዳጋጠማቸው መረዳት ባለመቻላቸው ሳብያ ከአጠቃላዩ የነፍሰጡሮች ቁጥር ውስጥ ምን በማህፀን ውስጥ የሞቱ ህፃናትን እንደወለዱም ሆነ አጠቃላይ ምጣኔው ስለመጨመሩ በእርግጠኝነት እንዳይናገሩ አድርጓቸዋል፡፡
በሆስፒታል ውስጥ ከተደረጉ ውልጃዎች መካከል በማህፀን ውስጥ የሞቱ ህፃናት ውልጃዎች የተከሰቱት ወረርሺኙ እናቶች ላይ በቀጥታ ባመጣባቸው የጤና ጉዳቶች ሳይሆን የጤና ስርአቱን ከማቃወሱ ጋራ በተገናኘ ሊሆን መቻሉን ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡ ምናልባትም የመጓጓዣ ስርኣቱ መስተጓሉን ተከትሎ ነፍሰ ጡር እናቶች የፅንሱን ሁኔታ ለመከታተል ወደ ሆስፒታል መሄድ አለመቻላቸውን አልያም ቀጠሮአቸው መሰረዙን፤ ሌሎች ደግሞ ወረርሺኙን ሽሽት ወደ ሆስፒታሎች ከማቅናት መቆጠባቸውንና ክትትል ካደረጉምነ በይነ መረብ እና የስልክ ግንኙነትን በመጠቀም ብቻ መሆኑን ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡
ከኔፓል ባለፈ ሌሎች የአለም ሀገራትም ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ እራሳቸውን አግኝተዋል፡፡ በሀገረ እንግሊዝ ለንደን ወስጥ ባለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ሆስፒታል የተደረገ ሌላ ጥናት እንዳመላከተው በሆስፒታሉ በሚደረጉ ውልጃዎች ላይ በወርሀ ጥር የነበረው ከ1000 ውልጃዎች 2.38ቱ ሞቶ የመወለድ ምጣኔ ከየካቲት እስከ ሰኔ ባሉት ወራት ውስጥ ወደ 9.31 ማደጉን አመላክቷል፡፡ ይህም እንደ ባለሙያዎቹ ከሆነ እናቶች በወረርሺኙ አመጣሽ ምክንያቶች አማካኝነት ወደ በሆስፒታል መጥተው የህክምና ክትትል ባለማድረጋቸው ወይም የጤና እክሎች ሲባባሱ ብቻ ወደ ሆስፒታል በማቅናታቸው መነሻነት ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ በህንድ እና ስኮትላንድም ይህ ሁኔታ ታይቷል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት እናት እና ልጁን ከጉዳት ይጠብቅ ዘንድ ነፍሰ ጡር ሴቶች በእርግዝና ወራቶቻቸው ውስጥ ቢያንስ ለስምንት ጊዜ ክትትል እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡ አብዛኛዎቹ በፅንስ ውስጥ ሞተው የመወለድ ችግሮችንም በእርግዝና ወቅት በጎን በመተኛት፣ ማጨስ በማቆም እንዲሁም ለጤና ባለሙያዎች ፅንሱ እንቅስቃሴውን እንደቀነሰ በማሳወቅ መከላከል ይቻላል፡፡ በተለይ በመጨረሻዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ በአግባቡ ክትትል ማድረግ እጅግ ጠቃሚ ሲሆን በሌሎቹ ወራት ቢሆንም ግን ሰፍሰ ጡር እናቶቹ እንደ ደም ግፊት እና የልጁን ዕድገት በጤና ባለሙያዎች ይመረመራሉ፡፡
ምንጭ፡ Nature
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” ክፍል 1
===================
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” በሚል ርዕስ በዲዛይኒንግ ዙርያ ያዘጋጀነውን ስልጠኛ ከዛሬ ሰኞ መስከረም 18 ጀምሮ በዩትዩብ ቻናላችን ማስተላለፍ እንደምንጀምር ቃል በገባነው መሰረት የመጀመሪያውን ክፍል በዩትዩብ ቻናላችን ስላስቀመጥነው በዚህ ( https://www.youtube.com/watch?v=dt34qHT9jJc ) ሊንክ አማካኝነት ገብታችሁ መመልከት ትችላላችሁ፡፡
ቻናላችንን ሱብስክራይብ በማድረግ ቋሚ ወዳጃችን ይሁኑ!!!
ለስራዎ ምቹ የሆነ ላፕቶፕ እንዴት ይገዛሉ?
=======
በአሁኑ ወቅት ላፕቶፕ ለመግዛት ሲታሰብ ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ ያሉት ላፕቶፖች በሙሉ የራሳቸው የሆነ ጥሩና መጥፎ መገለጫ ቢኖራቸውም ላፕቶፕ ሲገዙ ቢንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መገለጫዎችመመልከት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
1ኛ. የስክሪን ስፋት እና
የላፕቶፕ ክብደት (Screen size and weight)
የላፕቶፕ
ስክሪን በአብዛኛው ከ9-17 ኢንች (ከ23-43 ሳንቲ ሜትር) ድረስ ይሆናል፡፡ የስክሪን ስፋቱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የላፕቶፑም ክብደት ይጨምራል፡፡ እዚህ ላይ ላፕቶፑን ለምን እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ የላፕቶፑ መጠን እየጨመረ በሔደ ቁጥር ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ከባድ ላፕቶፖችን አዘውትሮ መሸከም በሰውነታችን ቅርጽ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ልዩ ልዩ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ ስለዚህ ስራችን ብዙ እንቅስቃሴ ያለበት ከሆነ ክብደታቸው አነስተኛ የሆኑና በቀላሉ ልናንቀሳቅሳቸው የምንችላቸውን መርጦ መግዛት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰፊ ስክሪን ያላቸው ላፕቶፖች የባትሪ ቆይታ ጊዜያቸው አነስተኛ ነው፡፡
2ኛ. CPU (የላፕቶፑ አእምሮ)
በአለማችን
ሁለት የታወቁ የCPU አምራች ኩባንያዎች አሉ፡፡ እነዚህም Intel እና AMD ናቸው፡፡ Intel ገበያውን የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በጨመር ሲቆጣጠረው፤ AMD ደግሞ ተወዳዳሪ የሆኑ ሞዴሎችን በአነስተኛ ዋጋ ያቀርባል፡፡ እዚህም ላይ ኮምፒውተሩን ለምን ስራ እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ የግራፊክስ ባለሙያ ከሆኑ ኤዲተር ከሆኑ ጥንድ ኮር (Dual-core CPU) ቢጠቀሙ የተሸለ የመፈጸም ብቃት አለው፡፡ ከዚህ ውጭ ለመሰረታዊ የኮምፒውተር አገልግሎት የሚፈልጉት ከሆነ ነጠላ ኮር (single-core CPU) ያለውን ላፕቶፕ ቢገዙ ከዋጋም አንጻር ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
3ኛ. RAM
ኮምፒውተርን
ለመደበኛ አገልግሎት ማለትም ለቤትከሆነ ውስጥ እና ለቢሮ ወይም ለጉዞ የሚጠቀሙት ከሆነ ከ 2-4 GB ያላቸውን መጦ መግዛት የተሻለ ነው፡፡ የግራፊክ አርቲስት ከሆኑ ወይም ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮዎች የሚያዘጋጁ ከ4 GB እስከ 8 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መርጦ መግዛት ውጤታማ ያደርጋል፡፡ ተማሪዎች የቤት ስራቸውን ለመስራት፣ ለኢሜይል ወይም የጠለያዩ ድረ ገፆችን መጎብኘት የመሳሰሉ ተግባራትን ለመከወን ግን 1 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መግዛትም ይቻላል፡፡
ምንጭ፡ www.howstuffworks
ህጻናት በአንጻራዊነት ኮሮናን እንዴት መቋቋም ቻሉ
******************************************
የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ ከመድሀኒቱን ፍለጋ ባልተናነሰ ለቫረሱ ተጋላጭ የሆነው የእድሜ ክልል የቱ ነው የሚለውም ሀሳብ ተደጋግሞ ሲነሳ ተሰምቷል፡፡ ባለፉት አምስትና ስድስት ወራት በቫይረሱ የተጠቁ ህጻናት ቁጥር ከጎልማሶችና ከእድሜ ባለጠጎች አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ ነው፡፡ የተያዙትም ቢሆን የማገገም እድላቸው ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
እንደ ተመራማሪዎች ከሆነ መጀመሪያ በተደረገ ጥናት በህጻናትና በጎልማሶች መካከል ያለውን በሽታ የመከላከል ብቃት ለመፈተሸ ተሞክሯል፡፡ በዚህም ህጻናት በሰውነታቸው ውስጥ የተሸለ በሽታ የመከላከል አቅም አላቸው፡፡ ይኸውም በህጻናት ያለው በሽታ ተከላካይ ክፍል ወደ ሰውነታቸው የገባውን የኮሮና ቫይረስ ሰውነታቸውን ማጥቃት ከመጀመሩ በፊት በፍጥነት ስለሚያጠፋው ነው፡፡
ጥናቱን የመራው የAlbert Einstein College of Medicine፣ ዶክተር የሆነችው ቤስቲ ሄሮልድ እናዳለችው የህጻናት ሰውነት ለቫይረሱ የሚሰጠው ምላሽ ፈጣን መሆኑ ህጻናቱን ከከፋ አደጋ ጠብቋቸዋል፡፡ በጎልማሶች ያለው በሽታ ተከላካይ ክፍል ለቫይረሱ ምላሽ የሚሰጠው በጣም በተንቀራፈፈ መልኩ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ቫይረሱ ታማሚውን ለማጥቃት ምቹ ጊዜ ያገኛል፡፡
ጥናቱ እንዳመለከተው ህጻናት ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል ብቃታቸው (innate immune system) ያልደከመ ሲሆን በጎልማሶች ያለው ግን የመድከም እና የማርጀት ጠባይ ያታይበታል፡፡
ምንጭ :- The New York Times
የሰሃራ በረሃን በዛፍ መሸፈን ይቻል ይሆን?
=================
ከ5 እስከ 11ሺህ ዓመታት በፊት ባለው ጊዜ ውስጥ ልክ የመጨረሻው የበረዶ ዘመን (ice age) እንደተቋጨ የሰሃራ በረሃ ፍፁም ተለወጠ፡፡ በአሸዋ ጉብታዎቹ ላይ ዕፅዋት መብቀል ጀመሩ፤ በመጠኑ እየጨመረ የመጣው ዝናብም የበረሃ ዋሻዎቹን ወደ ሀይቅነት አሻገራቸው፡፡ ከኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት በስምንት ዕጥፍ የሚልቅ 9 ሚሊዮን ካሬ ኪ.ሜ የሰሜናዊ አፍሪካ ክፍል ወደ አረንጓዴነት ተለውጦ ሳር እና ቁጥቋጦውን የሚመገቡ እንደ ጉማሬ፣ ዝሆን እና አንድ ሌላ የዱር ቀንድ ከብት ዝርያን እስከመሳብ ደርሰ፡፡ ሆኖም ይህ ልምላሜ እንደ ጉም በኗል፤ አፍሪካም ልክ እንደራሰ በራ ሰው የሰሃራ በረሃን በጭንቅላቷ አኑራ ትገኛለች፡፡ ታድያ ዘመነ ልምላሜዋ መመለስ ይችል ይሆን?http://techin.gov.et/post/298/
5 የተሳሳቱ የኮሮናቫይረስ አመለካከቶች እና ሳይንሳዊ ማብራሪያቸው
=============================
በፈረንጆቹ 2020 ስለኮሮናቫይስ ወረርሽኝ መስማት ስንጀምር የብዙዎች ጥያቄ ያተኮረው ስለበሽታው ምንነት፣ እንዴት ሰዎችን እንደሚያጠቃ እና ራሳችንን ከበሽታው ለመከላከል ምን አይነት መንገዶች መከተል እንደሚኖርበን የሚያጠይቅ ነበር፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ቀን በገፋ ቁጥር ይበልጥ እየታወቁና በተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምሮች እየተረጋገጡ ቢሄዱም በሌላ መልኩ ደግሞ የሚያወዛግቡ እና ብዙ የተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳባቸው ጉዳዮችም ነበሩ፡፡
http://www.techin.gov.et/post/299/
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” online training፡- Part 3
Simple Drawing Exercises
===================
In this tutorial we will be going over the basic sketching technique, drawing free lines, arcs, circles and ellipses in doing so we will work on basic shape. https://www.youtube.com/watch?v=jdQFPAFOJaE
For more science and technology information’s, please subscribe to our cannel.