Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.43K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
እሱን ባሳማራቸው የራሱ ሰዎችና ቅጥረኞች በኩል በመቆጣጠር (disinformation, misinformation )የሆኑ መረጃዎችን በማሰራጨት ወጣቱን በጥላቻ እንዲሞላና እንዲቆጣ ለማድረግ ሞክሯል።

ለአማራ ሕዝብ ሕልውና እና ሁለንተናዊ ጥቅም የሚታገሉ የሚመስሉ ነገር ግን በወያኔ ሰዎች የሚመራ በርካታ የዩትዩብ ሚዲያዎችን ከፍቷል። ቅጥረኛ አማራዎችን ደግሞ በተለያዬ መንገድ የ ዩትዮብ ሚዲያ እንዲኖራቸው ወይም እንዲከፍቱ አድርጎ አጀንዳውን ለመሸጥ የሞከረና አሁንም እየሰራበት የሚገኝ ሲሆነ በአማራ ስሞች ደግሞ ለምሳሌ እንደ ጀግና በሚቆጠሩ ወይም በሚታዩ ሰዎች ስምና ፎቶዎች፣ በታሪካዊ ቦታዎች ስምና ፎቶዎች፣ በከተሞች ስምና ፎቶዎች፣ እልፍ ዘ-ጊዮኖችን እንዲሁም ሌሎች ስሞችን በመጠቀም በሺ የሚቆጠሩ ፔጆችን እና ፌክ አካውንቶችን ከፍቶ የሶሻል ሚዲያውን በመቆጣጠር አማራው የሚጠፋበትን ከሌላው ብሔር የሚነጠልበትን "አማራነትን" እንዲያቀነቅን በተቀናጀ መንገድ ትልቅ የጥፋት ስራ ተሰርቶበታል።

አማራ ነኝ የሚለው ሃይል እንዲል የሚፈለገው ወደስልጣን የወጣውን አብይ አህመድን የኦሮሞን ተረኛ ሃይል ስለመሆኑ የሚያሳዩ ወይም የሚመስሉ ነገሮችን ብቻ ነጋ ጠባ ነቅሶ በማውጣትና ያንኑ ጉዳይ ደጋግሞ በማጉላት ኦሮሞ አማራን ሊውጠው ስለመሆኑ ስጋት መፍጠር የዘወትርና ብቸኛው አጀንዳው ማድረግ ነው። በዚህ በኩል የጠላት ጥረት በተወሰነ መልኩ አልተሳካም ማለት አይቻልም። ይህ ሃይል ከመጀመሪያው ጀምሮ ወያኔን ስትራቴጂክ አጋር በማድረጎ የተነሳ ሲሆን(ሞተሩ ወያኔ ስለሆነ) አንዴ ኦሮሙማን ሌላ ጊዜ አብይ አህመድን ሌላ ጊዜ ደግሞ ብልፅግናን ለአማራ ሕዝብ እንደዋና ጠላት የሚቆጥርና ሌሎች ብሔሮችንም ሊባሉ የማይገባቸውን ነውረኛ ነገሮችን እላፊ ሄዶ የሚናገርና አማራው ከማንም ብሔር ጋር በወዳጅነት እንዳይቀጥል በተጠናና በታቀደ መንገድ ሲሰራ የቆዬ ራሱንም ልክ እንደ የአማራ ፅንፈኛ ቁጠሩኝ የሚል የአማራ እዳ ነው።

አማርኛ ተናጋሪው ወያኔና የግብር ልጆቹ የሳይበር ሰራዊት ኦሮ-ማራን ለማፍረስ የተረኝነትና የኦሮሞን 'ዋጭና ሰልቃጭነትን' ለማሳየት ያነጣጠሩት አዲስ አበባን ከዲሞግራፊ የለውጥ ጉዳዮች፣ ከስራ ቅጥር ከበዓላት አከባበር ጋር በማገናኘት፤ ወለጋን፣ከሚሴን፣አጣዬን፣ቤንሻንጉልን መሬት ላይ ተልዕኮ በተሰጣቸው በሳተላይት ድርጅቶቹ በኩል በንፁሃን ላይ የተጠና ኦፕሬሽን በማድረግ የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ በማካሄድ መጭውን ጊዜ አጨልሞ ለማሳየትና እየመጣ ያለውን የአደጋ አስፈሪነት እወቁልኝ ለማለት ሞክሯል። ይህ ሃይል ከመርዶ ነጋሪነት ጥሩንባ ይዞ የእልቂት ጥሪ ከመንፋት ወይም ሐዘን ከማወጅ ያለፈ በሰነድም ሆነ መሬት ወርዶ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ ለማስቆም በመፍትሄው ዙሪያ የሕይወት መንገድ ለመቀየስ ጥሪ ቢደረግለት የውሃ ሽታ ሆኖ የሚቀር ነው። የጠላት ዋና ግቡ አማራው የማይድንበትን ወያኔያዊ "አማራነትን" ተፈጥሮ ማየት ነው። በአጭሩ አማራ ነኝ እያለ ከሌሎች ብሔሮች የሚነጥለውን ግብር እንዲዋረስ የሚያደርገውን አማራነትን ማስቀንቀን ነው። ሶሻል ሚዲያው ላይ 'አማራ ነኝ' እንደሚለው ሃይል ለአማራ መከፋፈል የእርስ በርስ ሽኩቻ ተጠያቂ የሚሆን አካል በፍፁም አልነበረም: ሊኖር እንደማይችል ሊታወቅም ይገባል። የተዳከመ እንጅ ጠንካራ ተቋም እንዲገነባ የማይፈቀድለት እንዲሁ ሁሌም የሚብሰከሰክ፣ የሚቆዝም፣ የሚያለቃቅስ፣ እርስ በራሱ የማይደማመጥ፣ የማይከባበር ለወያኔ ስጋት የማይሆን ሁሉንም እንደጠላት መቁጠርንና ወዳጅ ማጣትን እንደ ስትራቴጅ የሚቆጥር ጥርስ የሌለው የተቅበዘበዘ አማራን ተፈጥሮ ማየት ታሳቢ ያደረገ የጠላት አላማ ነው።

ሌላው ደግሞ አማራው "አማራ ነኝ" እንዲል በራሱ በወያኔ እንደ አንደኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ መብት በማይሰጣቸውና መዋቅራዊ ግፍ እንዲፈፀምባቸው በሚያደርጋቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ አማራዎች "የአማራነት ስሜት እንዳለባቸው ስለሚታሰብ አማርኛ ተናጋሪ ትግሬዎችን የአማራነት ሰርተፍኬት ሰጭና ነሽ የግፎች መስካሪ ሆነው ወደፊት እንዲመጡና የአማራ ፅንፈኝነትን እንዲያቀነቅኑ በአያሌው ተሰርቷል። በኦርቶዶክስ ሐይማኖት በመምህርነት :በዲያቆንነት: በቀሲስነት ለአማራ የሚቆረቆሩ መስለው የሚንቀሳቀሱ ሰባኪያነ-ወያኔዎች በፍፁም ነውረኝነት ጭምር ተላብሰው የአማራውን ፖለቲካ ለመዘወር ጥረት አድርገዋል። እያደረጉም ነው። በሌሎች ክልሎች ተወለድን የሚሉ እነዚህ ሚዲያ ላይ በአማራዎች ላይ ተፈፀሙ በሚባሉ ጥቃቶች ላይ የሚያስተላልፉት መልዕክትና የሚይዙት አቋም የጥቃቱ ፈፃሚዎች ከሚባሉት ቢብስ እንጅ ያነሰ አይደለም። አንድ ለአማራ ተቆርቋሪ ነኝ ሊል የሚችል የእዛ አካባቢ ተወላጅ ችግሩን እንደሰማ ተጨማሪ እልቂት እንዲደርስ የሚያደርገው ጥሪ ስሜቱን መቆጣጠር ስላልቻለ ነው ብለን እንለፈው ቢባል እንኳን ' ከ ዓመት እስከ ዓመት በየጊዜው በእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍን (ወገኖቹን በእሳት መሃል አስቀምጦ) እንዴት እንደተቆርቋሪነት ሊቆጥር ይችላል?!' የሚል ጥያቄ የሚጭር ነው። ደግሞ በጎ ተሳትፎ አለማሳየታቸው ብቻ አይደለም እኮ የሰዎቹን አማርኛ ተናጋሪ ትግሬዎች ናቸው የሚያስብለኝ። እንስከን :ለአማራ ጠላት የሚያበዛ ወዳጅ የሚያሳጣ አላስፈላጊ ንግግር አናድርግ የሚሉትን አርቆ-አሳቢ ትክክለኛ ተቆርቋሪ ወገኖችን በብአዴንነት ለመክሰስ ወይም እንደ አድርባይ ለመቁጠር ሞራል የሌላቸው የጃስ በለው አቀንቃኝ መሆናቸውም ጭምር ነው። በወያኔ ተልዕኮ ከተሰጠው ሰው በስተቀር እንደአማራ ምንም አይነት መሬት የነካ ዝግጅት በሌለበት ሁኔታ፤ መናገር ወይም መፃፍ ስለተቻለ ብቻ ቤተሰቦቹ በቀጣዩ ቀን ቀድሞ በተደራጀና በተዘጋጀ የጥፋት ሃይል ያልቁ ዘንድ ቅስቀሳ ሊያደርግ የሚያስችል የሞራል ልዕልና ሊኖረው የሚችል ተቆርቋሪ አለ ብዬ አላስብም።
ከንፍሮ ጥሬ ግፍ ያንገበገባቸው አማራዎች የተሳሳተው መስመር ስለመከተላቸው ያልገመገሙ ስለመኖራቸው መስካሪ አያሻም። የሚታወቁና ልካቸውም የተለየ ነው።
አማራውን በሁሉም ነገር ድንኳን አስጥሎ ንፍሮ አስቀቅሎ ነጠላ አስዘቅዝቆ የሚያስለቅሰው ወያኔና የግብር ልጆቹ እንጅ ለአማራው የሚቆረቆሩ ትክክለኛ የአማራ ልጆች ድምፅ አለመሆኑ ሊቲወቅ ይገባል። ድምፁ የአገር አፍራሾቹ ወያኔና የግብር ልጆቹ ነው‼️

የፅሑፉ አላማ ችግሮች የሉም ከሚል ወያኔያዊ ትርጉም አሰጣጥ ፈፅሞ የራቀ ነው‼️
ፎቶው ከ ወደ ቻይና ወይስ ከ ወደራሽያ አካባቢ የተገኘ ነው ነው በሚል ለማመን ተቸግሬ ዙም እያደረግኩ ሁሉ ነው አገላብጭ ያየሁት😂

ደብረታቦር ዩኒቨርስቲን አለማድነቅ ንፉግነት ነው!

ደብረታቦር የመጀመሪያ የአፍሪካ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደር የተጀመረባት መንደር ነች!

ዛሬ ደግሞ ሮኬት በማስወንጨፍ ቀዳሚዋ ሆናለች!

ዩኒቨርስቲዎች ለማህበረሰብ ነውጥ ሳይሆን ለውጥ የሚሰሩ ችግር ፈችዎች መሆን ሲጀምሩ የሐገሪቱን ሁኔታ የመቀየር እድል ይኖረዋል።

የደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ጅምር የሚደነቅና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም አርአያውን ሊከተሉ ይገባል‼️
ከአይሁድ ጫጫታ ይልቅ፣ ጲላጦስን ሰላም የነሳው የክርስቶስ ዝምታ ነው።
የባቢሎን ዘመንን ከሻቱ አካላት ጋር ፈፅሞ ሕብረት አይኖረንም‼️
እናት አገር ኢትዮጵያን በመክዳት ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተሰልፎ የባንዳ ባንዳ ይዞታን ይዞ በያለበት እየዳከረ ያለ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕልውና አሁናዊ ስጋት አይደለም። የባንዳ ባንዳው ከታሪካዊ ጠላት ጋር ተሰልፎ፣ አንዳንዴም ከጠላት በላይ ሰይጦ፣ ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ፣ ብሔራዊ አገር አልቦ ሊያስቀረን ያደረገው "የውርንጫ ድካም" የሆነ ሙከራ ትላንት በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን የተባበረ ክንድ ተሸንፏል።

ዛሬ ላይ ለኢትዮጵያ ሕልውና አደጋና ስጋት የሚጋርጠው እንደ ጃንሆይ ዘመን ባንዳዎች በአርበኞች ላይ የበላይነት ይዞታ ይዘው አሁናዊ አገር ወዳድ አርበኞች በስርዓቱ የሚገባቸውን እውቅና እና ክብር ሳያገኙ በምትኩ በአገር መክዳት ወንጀል ሊጠየቅ የሚገባው የባንዳ ባንዳው እና የድል አጥቢያ አርበኛው የመንገስ እድል ከተሰጠው ይሆናል።

የአብይ አህመድ መንግስት ከታሪክ ይማራል የሚል እምነት አለኝ‼️
የኢትዮጵያ አለኝታዎች!

እንደሐገር ነፃነታችንንና ሉዓላዊነታችንን አስከብረን የቆምነው በጀግኖች ያልተቋረጠ ዓመት ሙሉ ከባድ መስዋዕትነት ነው‼️

ማህፀነ ለምለሟ እናት ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በደምና በአጥንታቸው የሐገራቸዉን ዳር ደንበር የሚያስከብሩን ጀግኖች ልጆች አፍርታለች‼️
በነገራችን ላይ ወያኔ በሰላም ለመኖር ቀርቶ ስለሰላም ለማውራት ተፈጥራዊ ስሪቱ አይፈቅድለትም። በግጭት ተፀንሶ በግጭት ያደገ የሕልውና መሰረቱ ግጭት የሆነ ለኢትዮጵያ ዘላለማዊ ጠላት ነው።

ወያኔ በአሁን ሰዓት ስለሰላም እያወራ ለጦርነት በከፍተኛ ደረጃ እየተዘጋጀ ነው። ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እየተመራ መደበኛ የጦር ግንባሮችን ከመክፈቱ በፊት በሐገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በግብር ልጆቹ በኩል የተለያዩ ጥቃቶችን በመክፈት ሕዝቡን በምሬት ለማስነሳት እየሞከረ ሲሆን ጀግናው የኢትጵያን ሰራዊት ደግሞ ትኩረቱንና ስምሪቱ እንዲበታተን አልሞ እየሰራ ነው። ጠላት አላማው ስለሆነ የሚያገኘውን ቀዳዳ ሁሉ ተጠቅሞ ጥፋት ለማድረስ የተዘጋጀ ነው። ለጠላት አላማ ተባባሪ አለመሆን ከሐገር ወዳድ ዜጎች የሚጠበቅ ምላሽ ነው።

በአማራ እና በኦሮሞ ማልያ ወያኔ የሳይበሩን ዓለም በከፍተኛ ደረጃ መቆጣጠሩ የሚታወቅ ሲሆን የሁለቱን ብሔር ተወላጆችን ለአላማው መሳካት ምርኩዝ ቱቦ ይሆናሉ ያላቸውን ሰዎችና ድርጅቶችን የገፅታ ግንባታ እንዲሰራላቸው በማድረግ ወደፊት በማምጣት በጥሩንባ ነፊነት አሰማርቶ ሕዝቡን ሰላም ለመንሳትና ወደጥፋት መጠቃቃት እልቂት ለመክተት ከፍተኛ ሙከራ አድርጓል። አሁንም ያልቆመ ተጠናክሮ የቀጠለ እንቅስቃሴ ነው።

የጠላት ትልቁ ጉልበቱ ፍፁም የፕሮፓጋንዳ ብልጫ በመንግስት ላይ መውሰድ መቻሉ ነው። ስቴት ማሽነሪዎቹን ሽባ አድርጓቸዋል። በወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ያልሆነ በሚነዛው የፈጠራ የውሸት መረጃ ያልተደነባበረ በጥፋቱ ሐሳቡ ቁጥጥር ስር ያልዋለና እጅ ያልሰጠ የወያኔ ተቃዋሚ በባትሪ ቢፈለግ ሊገኝ የሚችለው ነፃ አዕምሮ ጥቂት ነው።
የወያኔን አላማና አጀንዳ ያለ-ወያኔ ስፖንሰርነት የሚያስተጋቡ በአማራም ሆነ በኦሮሞ ወይም በሌሎች ብሔሮች በኩል እልፍ የግብሩ ወራሾች እንዲፈጠሩ ማድረጉ ለወያኔ ትልቅ ስኬት ነው።

ለማንኛውም

ወያኔ ስለሰላም ሳይሆን ስለጦርነት ያለውን ዝግጁነት ነው ሰሞኑን በተለያዬ መንገድ እየነገረን ያለው። ከባህሪው ውጭ የሚያስተላልፋቸው መልዕክቶች ማዘናጊያዎች ናቸው። ወያኔ በአዲስ መልክ ራሱን በማደራጀት በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ድጋፍ ሰጨነትና አጋዥነት ጦርነት ከመክፈት ውጭ የተሻለ አማራጭ እንደሌለው የሚያምን የጥፋት ሃይል ነው። በጦርነት ማሸነፍ እንደማይችል የሚረዳ ቢሆንም ይዞ የመሞት የእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አስተሳተብ ተጠቂ ነው። ይህ ሐይል ለኢትዮጵያ የጥፋት መልዕክተኛ ነው። ሕልውና እስካለው ድረስ መቼም ቢሆን በሰላም የሚተኛ ሃይል አይደለምና ሁለንተናዊ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል።

በምንም ነገር መቼም ቢሆን ልንዘናጋ አይገባም‼️
በዛሬው ዕለት በሁመራ የጎዳና ላይ ኢፍጣር/አፍጥር ፕሮግራም ተካሂዷል። የአፍጥር ፕሮግራሙ በጎንደር-ወልቃይት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ነው።

በመርሃግብሩ ከጎንደር ዑለማዎችና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተው ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተገኝቷል።
የማናሸንፈዉን አካል እንኳን በአደባባይ በጓዳም ደፍረን ለሐሜት እንኳን እንቸገራለን፤ ስለጠላቶቻችን በአደባባይ ደረታችንን ነፍተን የገጠምነው ከእኛ በላይ ስላልሆኑ ነው‼️
ዛሬን በነፃነት ደረታችን ነፍተን ቀና ብለን እንሄድ ዘንድ፣ ትንሳኤያችንን ከቤተሰቦቻችን ጋር ሆነን በሰላም በድምቀት እናክብር ዘንድ፣ ትናንት በየሸጡ፣ በየጉድጓዱ፣ በየሜዳው፣ በየጋራ ሸንተረሩ፣ እና በዱር በገደሉ አፈር እስክትመስሉ በርሃብና በውሃ ጥም እየተሰቃያችሁ እኛ የሰላም አየር እንተነፍስ ከውዷ ሐገራችሁ በፊት እኛ እንፍረስ ብላችሁ ደማችሁን ያፈሰሳችሁ አጥንታችሁን የከሰከሳችሁ የእናት ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ክብር ይገባችኋል።


የተከፈለልንን የደም ዋጋ በምንም የማይተካ ነውና ሁሌም እናስታውሳችኋለን። መቼም አንረሳችሁም! ይህን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን፣ ለማጣጣልና ስማችሁን ለማጥፋት በክፋት ብንነሳ ደማችሁና አጥንታችሁ ይፍረደን!

እናንተ የኢትዮጵያ ሕልውና የመጨረሻ ምሽጎች፤ የሰላማችን የነፃነትና የክብራችን ዋስትና ናችሁና በማንምና በምንም የማንቀይራችሁ ጀግኖቻችን ስለሆናችሁ በነገሮች ሁሉ እስከመጨረሻው ድረስ ከጎናችሁ አብረን እንቆማለን‼️

ውድ ኢትዮጵያዊያን ስለምትወዷት እናት ኢትዮጵያ ስለሰላማችንና ስለክብራችን በዚህ ሰዓት ከቤተሰብ ተለይተው መዋያና ማደሪያቸውን ምሽግ ስላደረጉ የጀግናው መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩሃይል ሚሊሻ እና ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ላላቸው ዋና ጠላታቸውን ለይተው ለሚያውቁ ወያኔ ካልከሰመ እረፍት ለሌላቸው ለሕዝብ ጥቅም ለቆሙ በእየ አውደ ውጊያው በእሳት ለተፈተኑና ለተለበለቡ ጀግና የአማራ ፋኖ አባላት ጎረቤት የሆኑና የምናውቃቸውን ቤተሰቦቻቸውን በሙሉ እንኳን ለበዓለ ትንሳኤው አደረሳችሁ ብሎ በተለያዬ ነገር በተለይ ከታይታ በወጣ ለሕሊና ሰላም ስንል መጠየቅ ያስፈልጋል።

ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ነገን መስራትም ነው‼️


መልካም የትንሣኤ በዓል ለውድ ጀግኖቻችንና ለጀግኖች ቤተሰቦች በሙሉ‼️

ኢትዮጵያ ዛሬም እንደ ትናንቱ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ከውጭ ባዳዎች እና ከውስጥ ባንዳዎች የሚቃጣባትን ትንኮሳዎችን በማክሸፍ ነፃነቷንና ክብሯን አስከብራ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች‼️