Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.42K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ከሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች የተውጣጡ ወንድሞቻችን የአማራ የዕዳ ደብዳቤ በተቀበረባትና በተቀደደባት ወልቃይት አዲረመጥ ከፍተኛ የሆነ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል። ውድ ወንድሞቻችን ቆይታችሁ ያማረ እንዲሆን እንመኛለን!

ወልቃይት ከነዓናችን ነች‼️
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ
****

ፍትሕ በሐሰት ትርክትና የጥላቻ ስሜት የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን!

አሸባሪውና ዘረኛው ትሕነግ የሽምቅ ተዋጊ በነበረበት ጊዜ ጀምሮ ወልቃይትና ጠገዴ አካባቢ ያለውን ስትራቴጅያዊ ጠቀሜታና ሀብት በመገንዘብ አካባቢውን ለመቆጣጠር ወጣ ገባ ማለት ከጀመረበት 1972 ዓ.ም ጀምሮ በተለይም አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ በወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ግድያ፣ ማፈናቀልና አፈና ሲፈፅም ቆይቷል:: በዚህም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ማንነታቸው ወንጀል ሆኖባቸው እንደወጡ ቀርተዋል፡፡ በጥቅሉ፣ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጀሮ የነፈገው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፡

ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም አሸባሪውና ዘረኛው ትሕነግ በሰሜን ዕዝ ልዩ ልዩ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ማድረሱን እና በሁለት አቅጣጫ ደግሞ አማራ ክልል ላይ የጦር ወረራ መፈፀሙን ተከትሎ በሕግ ማስከበር ዘመቻው በደረሰበት የመልስ ምት፣ ቡድኑ አካባቢውን ለቆ እንዲሄድ የተደረገ ሲሆን፤ በሚያፈገፍግበት ወቅት ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም. በማይካድራ ከተማ በሺህ የሚቆጠሩ አማሮችን፤ በተመሳሳይ ሕዳር 03/ 2013 ከሁመራ ከተማ አርባ ኪሎ ሜትር በምትርቀው ‹እድሪስ› የተባለች የገጠር ቀበሌ/ከተማ ላይ የተመረጡ የአማራ ባለሀብቶችን ጨፍጭፎ መሄዱ የሁሉንም ልብ የሰበረ ክስተት እንደነበር ይታወሳል፡፡

አሸባሪው ቡድን ከወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ አካባቢ ተመትቶ መልቀቁን ተከትሎ የሁመራ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ሲውል በዙሪያው የጅምላ መቃብሮች የተገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ቀጠና በተለያየ ጊዜ የተለያየ ቦታ ላይም በርካታ የጀምላ መቃብሮች ተገኝተዋል:: ከሰሞኑ በወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አካባቢ ለአስራ ስድስት ወራት ጥናት ሲሰራ የቆየው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን የአካባቢው ማኅበረሰብ "ገሃነም" እያለ በሚጠራው የትሕነግ ድብቅ የማሳቃያ፣ መግደያና ማሰሪያ ቦታ እጅግ አስደንጋጭ የሆነ የጅምላ መቃብር ተገኝቷል:: ትህነግ በሐሰት ትርክት ከቆመበት ተፈጥሯዊ የጭካኔ ባህሪውና በአካባቢው ሲፈጽማቸው ከኖሩ ዓለማቀፍ ወንጀሎች አኳያ ተጨማሪ ምርመራ ቢደረግ አያሌ የጅምላ መቃብሮች እንደሚገኙ አያጠራጥርም::

ስለሆነም:-

፩. የፌደራል መንግሥቱ በተለይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የአማራ ክልል መንግሥት ጥናቱን ቀድመ ብሎ ከጀመረው የጎንደር ዩኒቨርሲቲና መሰል የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ይኸን መዋቅራዊ ሆኖ ለሦስት አስርት ዓመታት የዘለቀ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጣራ እንዲያደርጉ፣ ይህን ዓለማቀፍ ወንጀል የፈፀሙ የትህነግ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ሁሉን አቀፍ (ሙያዊና ተቋማዊ) ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አብን አጥብቆ ይጠይቃል::

፪. የአማራ ሕዝብ አሁንም በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ (ወለጋና አካባቢው) የጅምላ ፍጅት ሰለባ ሆኖ የቀጠለ ስለሆነ መንግሥት የጅምላ ፍጅቱን እንዲያስቆም እየጠየቅን፣ የወንጀሉ ተባባሪና አቀናባሪ የሆኑ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ኃላፊዎችን ጨምሮ ወንጀል ፈፃሚዎችን ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ለሕግ እንዲያቀርብ በጥብቅ እንጠይቃለን:: የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ በዜጎች የሰብዓዊ መብት ዙሪያ የሚሰሩ ሀገር በቀልና የውጭ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች የተፈፀሙ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋዎችን እንዲያጣሩና ተጠያቂነትም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ እንጠይቃለን::

ፍትሕ በሐሰት ትርክትና የጥላቻ ስሜት የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን!

መጋቢት 26/ 2014

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አለን‼️

HR6600 እና S3199 ባሉበት እንዲቆሙ መወሰኑ ለእናት አገር ኢትዮጵያ ድምፅ ለሆናችሁ የምንጊዜም አለኝታ ኢትዮጵያዊያን ትልቅ ብስራት ለባንዳዎች ደግሞ የመርዶ ዜና ነው።

ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ የቱንም ያህል በፈተናዎች ብትከበብም በድል መሻገሯ ለአፍታም የሚያጠራጥር አይሆንም!

ቀሪውን ፈተና በድል ለመወጣት በተለመደው ቁርጠኝነት መቀጠል ያስፈልጋል!

አላስፈላጊ መስዋዕትነት ለመቀነስ እንጅ በአንድነት በፀና አላማ ቆመን የማናሸንፈዉ ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል አለመኖሩን የመጣንባቸው ወይም የተጓዝንባቸው ምዕራፎች ሕያው ምስክር ናቸው‼️
ወንድም ተስፋዬ ወርቁ በተወለደበት ተንታ ወረዳ አጅባር ከተማ ስለአማራ ህዝብ ትግል ሲጨነቅ በጉልህ የሚታወቅ ጀግና ወንድም ነው። ተስፋዬ የአብን አባል ሲሆን ባለፈው ሰኔ በተደረገው ምርጫ ድርጅቱን ወክሎ ተንታ ላይ ከተወዳደሩት እጩዎች አንዱ ነበር። ከምርጫው መጠናቀቅ ብዙም ሳይቆይ ህወሓት የአማራን ግዛቶች ወርሮ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲገስግስ የአማራ ክልል መንግሥት ያደረገውን የክተት ጥሪ በጀግንነት ተቀብለው በሁለት ሳምንት ስልጠና ብቻ ጠላትን ለመፋለም ጦር ግንባር ከገቡት በታሪክ ሲወደሱ ከሚኖሩ ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን መካከል አማራውን በኩራት ከሚወክሉት ጥቂት ቆራጦች የሚጠቀስ ነው። ጀግናው ተስፋዬ ወርቁ ግዳጁን በድል አጠናቆ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ክላሽ ተሸልሞ በክብር ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ለአሳየው አኩሪ ተጋድሎም በተንታ ከተማ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ወጣት ነው።
ዛሬ የተስፋዬን ጉዳይ ያነሳሁት ተንታ ወረዳን ወክሎ ወደ "አማራዊቷን ከንዓን" ወልቃይትን ለመጎብኘት ከተጓዙት ወጣቶች መካከል እንዳለ በማየቴ ነው። አማራነትን በቃል ሳይሆን በተግባር የኖረ እንደ ተስፋዬ ወርቁ ያለ ለብዙዎች አርአያ የሚሆንን ወጣት ማክበር ስለሚገባ እንኳን ለኢትዮጵያ ህልውና ተስፋ ወደሆነችው ወልቃይት "ከንዓን" በሰላም መጣህ ማለት እፈልጋለሁ።

የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ለተስፋዬ ወርቁ እና ከእርሱ ጋር ዘምተው በድል የተመለሱ ጀግኖች ካሉ ልዩ እንክብካቤ እንድታደርጉላቸው በትህትና እጠይቃለሁ።
መያዣና መጨበጫ የሌለው፤ ከተራ ጩኸትና መፎክር የማያልፍ፤ግልጽ የሆነ ራዕይና ግብ ባለቤት ያልሆነ፤ የተዘበራረቀና የተምታታበት የ herd mentality ተጠቂ አይደለም ሰፊውን ሕዝብ ለአንድ ዓላማ ሊያሰልፍ፣ ሊያሳምንና አግባብቶም ከጎኑ ሊያስከትል ይቅርና እስከ ምፅዓት ድረስ ጊዜ ቢሰጠው እንኳን እርስ በርስ ሊስማማና ሊደማመጥ ፈፅሞ አይችልም።

በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ ጊዜያዊ ኃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጥያቄዎችንና አለመግባባቶችን በተረትና ምሳሌ ወይም በእንካ ስላንትያ ሊፈታ የሚችል አይደለም። ችግሩን በመናቅ ለማዳፈን ወይም በችግሩ ላይ ቤንዚል በማርከፍከፍ ሐገር በማቃጠል ሊፈታ የሚችል የሕዝብ ጥያቄ የለም። አሉ የሚባሉ ችግሮቻችን የሚቀረፉት በሰከነ መንገድ በሚደረጉ ውይይቶች እና በጥበብ መራመድ ስንችል እንጅ እግርና እጅ በሌለው ስሜት ወለድ የጃስ በለው ፖለቲካ በማቀንቀን አይደለም። ከምንም በላይ ሕዝቡን የማይወክሉ ብቻ ሳይሆን ጠላት በሆኑ ሰዎች ጭምር ጥያቄው ሲዘወር ሌላ ጥያቄ ከመፍጠር ውጭ መፍትሄው ይርቃል።
በተጨማሪም የምድጃ ዳር ወሬ ለሚቃርሙ አሉባልተኞች እና የሕልውና መሰረታቸውን ግጭት ላይ ላደረጉ ለአቀሳሳሪ የደም ነጋዴዎች ጆሮ ከመስጠት ካልተሻገርን የሕዝብ ጥያቄ መልኩን ቀይሮ ነገረ-ስራችንም ወደራስ መተኮስ ብቻ የመሆን እድሉን ያሰፋዋል።

አንድን ጉዳይ ውጤቱን ሳያሰሉ አጀንዳ አድርጎ መታገል ደመ-ነብሳዊነት ነው‼️
በብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል አዲስ የኮማንዶ ሰልጣኞች የመክፈቻ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው። ከውስጥ በባንዳዎች እና ከውጭ በባዳዎች በኢትዮጵያ ላይ ሊቃጣ ለሚችል ጥቃት አስተማማኝ ሃይል የመገንባት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉ የሚደገፍ ነው‼️

ኢትዮጵያ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ነፃነቷንና ክብሯን አስጠብቃ ታፍራና ተከብራ ትኖርና ለቀጣዩ ትውልድ ትሻገር ዘንድ ታሪካዊ ኋላፊነታችንን ለመወጣት መስራት ከሐገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ይጠበቃል።
በየሸጡ፣ በየጉድጓዱ፣ በየሜዳው፣ በየጋራ ሸንተረሩ፣ እና በዱር በገደሉ አፈር እስክትመስሉ በርሃብና በውሃ ጥም እየተሰቃያችሁ እኛ የሰላም አየር እንተነፍስ ህልውናችን ይቀጥል ነፃነታችን ይከበር ዘንድ እየከፈላችሁት የሚገኘው በምንም የማይተካ የደም ዋጋን መቼም አንረሳም። ይህን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን፣ ለማጣጣልና ስማችሁን ለማጥፋት በክፋት ብንነሳ ደማችሁና አጥንታችሁ ይፍረደን! እንኳን አጥንታችሁን ከስክሳችሁልን ደማችሁን አፍስሳችሁልን ይቅርና ለሚጠሉን በጠላትነት ሊፈርጁን ለሚሞክሩን ለሚቆጥሩን አካላትን ወዳጅ ለማድረግ አንደበታችን ለማመስገን አልተዘጋም! እናንተ የኢትዮጵያ ሕልውና የመጨረሻ ምሽጎች ናችሁና እስከመጨረሻው ድረስ ከጎናችሁ አብረን እንቆማለን‼️

ኢትዮጵያ ዛሬም እንደ ትናንቱ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ከውጭ ባዳዎች እና ከውስጥ ባንዳዎች የሚቃጣባትን ትንኮሳዎችን በማክሸፍ ነፃነቷንና ክብሯን አስከብራ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች‼️
በአማራ ፖለቲካ አንድን ግለሰብ ከስራውና ከስነ-ልቦናው ይልቅ ዋና መስፈርቱን የደም ጥራት ያደረጉ ብሔርተኞች "እንትና በአባቱ ኦሮሞ ነው፤ እንትና በአያቱ ትግሬ ነው፤... ከማለት አልፈው ጭራሽ እንትና ወይም እሱ እኮ በሚስቱ እንዲህ ነው" የሚሉ ሰዎች ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራን የአማራ ሕዝብ ዋና ተቆርቋሪ እና የቅርብ ተጠሪ አድርገው ለማቅረብ የሚሞክሩት ናቸው። ኤርሚያስ ለገሰ እኮ አማራን ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ በተለይም ከኦሮም ህዝብ ጋር ለማጋጨት ብቻ ሳይሆን ራሱ አማራው አንድ እንዳይሆን ለተጨማሪ ጥቃትና መከራ እንዲጋለጥ ቤንዚል በማርከፍከፍ የወያኔ አጀንዳን ከሚያስፈፅሙ የአማራ ጠላቶች ቀዳሚው ነው።
የአማራ ፖለቲካም በአማራ ተቆርቋሪዎች ይቅርና አማራ ባልሆኑ ጠላቶች ከመዘወር አሁንም የሚወጣ አይመስልም። Ethio-360 ኢትዮጵያን ለማፍረስ ወያኔን ከሚጋልቡ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አጀንዳ ተቀብሎ የሚሰራ ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላትና እዳ የሆነ ሚዲያ ነው።

ሐገር ለማፍረስ ከመስራት በላይ የሐገር ክህደት ግን ምን አለ? ትናንት ወያኔ አልፎ ሂያጁን ሁሉ የአይንህ ቀለም አላማረኝም እያለ በግፍና በገፍ እያፈሰ በሐገር ክህደት ወንጀል ይከስ ነበር። የዶ/ር አብይ መንግስት ደግሞ በአዋጅ ሐገር እናፈርሳለን ከሚሉ ጠላቶች ጋር የተሰለፉትን የጥፋት ሃይሎችን ባላየና ባልሰማ ለማለፍ ልምምድ እያደረገ ነው። ይህ አካሄድ ኢትዮጵያን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። ባንዳነት እንዲነግስ አርበኝነት እንዲኮስስ መንግስት ስፖንሰር እየሆነ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ሐገር ለማፍረስ የሚሰሩ ባንዳዎች የሚከበሩበት ሁኔታ እየተመቻቸ ሐገር ለማዳን የሰሩና የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች በስራቸው የሚንኳሰሱና የሚገፉ ከሆነ ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ክብር እና ጥቅም መከበር እሰራለሁ ማለት በራሱ ቀልድ ነው። ይህ ድርጊት ከቀጠለ የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ወይም እንድትፈርስ ከማንም በላይ ፍላጎት እንዳለው የሚያስቆጥር ነው።
ወያኔን ከአራት ኪሎ ወደመቀሌ እንዲመሽግ ወይም እንዲያፈገፍግ ልንለው እንችላለን የኦሮ-ማራ ጥምረት የአንበሳውን ድርሻ ስለመውሰዱ ለጥያቄ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ለአመታት የተከማቸው የጥያቄዎች ሁሉ ድምር ጥያቄ እና የግፍ ፅዋው ሞልቶ መፍሰሱን ተከትሎ ወያኔን ለማውረድ በአይን ጥቅሻ የተፈጠረው መግባባት፥ የተቀጣጠለው የሕዝብ አመፅ እንዳይቀለበስ ግለቱን ጠብቆ ይሄድ ዘንድ፥ የኦሮ-ማራ ቅንጅት ግሩም ነበር።
በአማራ ክልል "የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው" በሚል ጎንደር ላይ የተሰማው ዘመን ተሻጋሪ በፍም እሳት መሃል የወጣ ድምፅ እንዲሁም የኦሮሞ ወጣቶች የጣናን የእንቦጭ አረም ለመንቀል ያሳዩት ዘመቻ፤ በታሪክ ድርሳናት በቀጣዩ ትውልድ ባለብዙ መልክ ትርጉም የሚሰጠው ነው።

ለአመታት በወያኔ የተዘራው የጥላቻና የመከፋፈል ፍሬ ያፈራል ሲባል የአንድነት የወንድማማችነት የመተባበር መንፈስ መሬት ነክቶ እንዲታይ የሆነበት ወቅት ነበር።
ለዛም ነበር የሕወሓት ሰዎች አይናቸው ደም ለብሶ በቁጣ እየተንተከተኩ ኦሮ-ማራን አንዴ "ያልተቀደሰ ጋብቻ ሌላ ጊዜ ደግሞ "እሳትና ጭድ" ሆነው ሳለ እንዴት በአንድነት ቆመው ልናያቸው እንችላለን በሚል መረን በለቀቀ የጥላቻ ንግግር በአደባባይ መናገራቸው ክፉ ሕልማቸው ምን ድረስ እንደነበረና አደጋ ላይ እንደወደቀ ምልክት የሰጡበት ነበር።

እንደሕዝብ አማራ እና ኦሮሞ እርስ በርሳቸው በሰይፍ ለማጫረስ የተደከመበት የአመታት መንግስታዊ ስፖንሰርነትን የሁለቱ ኤሊቶች እጅ ለእጅ ተያይዘው አንድ ነን ከሚል አፋዊ ንግግር ባለፈ ገቢራዊ ምላሽ ማሳየታቸው የወያኔን ወሽመጥ የቆረጠ ነው። የኦሮ-ማራ ጥምረት ለወያኔ የራስ ምታት የእግር እሳት ነው። በስልጣን ለመቆየትም ሆነ ወደስልጣን ለመመለስ ወይም ሐገር ለማፍረስ ኦሮሞ እና አማራን ማጋጨት የወያኔ የሕልውናው መሰረት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ወያኔም ወደመቀሌ ከመሸገ ወይም ከአፈገፈገ በኋላ ትኩረት ሰጥቶ የሰራው ስራ ይኼን ነው።

የኦሮ-ማራ ጥምረት ወያኔን ከአራት ኪሎ ለመንቀል ያስቻለ ሕዝባዊ ተሳትፎ የተደረገበት አስደናቂ ስኬታማ ድል የተመዘገበበት ኦፕሬሽን ነው።

የኦሮ-ማራን ጥምረት የሕወሓትን ተፈጥሯዊ ስሪት ካለመረዳት ለኢትዮጵያ ፖለቲካ እንግዳ ከመሆን ወይም ከወያኔ ጋር ጥቅም-ነክ ግንኙነት የነበራቸው በተልዕኮ የተሰማሩ ሰዎች እንቅስቃሴው እንዳያድግ በጊዜ ይቋረጥ ዘንድ መንቀሳቀሳቸው ለወያኔ የፈጠሩት ጉልበት የሚናቅ አይደለም።


የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለወያኔ በሚያደርጉት ድጋፍ ወይም በወያኔ በኩል ለኦነግ በሚደረግ ድጋፍ ብቻ የሚሳካ አለመሆኑ የተሸፈነ አይደለም። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ደግሞ ቅድሚያ የኦሮ-ማራን ጥምረት ማፍረስ ከዛም አማራው "አማራ ነኝ" ኦሮሞውም "ኦሮሞ ነኝ" ብሎ ጫፍና ጫፍ ይዞ እንዲቆም ማድረግ መቻል አለበት።

ታዲያ የኦሮ-ማራ ጥምረት ለማፍረስ አንደኛውን ወገን "በስልጣን ሽኩቻ ወይም በተረኝነት ስም" ሌላኛውን ወገን ደግሞ "የነፍጠኛው የአሃዳዊው ስርዓት እየተመለሰ ነው" በሚል ጎራ እንዲፈጠር በማድረግ፤ በሂደት ደግሞ ሁሉም ወገኖች(ማለትም የአማራም ሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ) ትግላቸው እንደተጠለፈ እና የአብይ አስተዳደር ለነገ ጭምር ተስፋ ያላዘለ በማስመሰል በሕዝባዊ አመፅ ተደግፎ ወያኔ በነፍጥ በተመራ ጦርነት አገር ለማፍረስ በተጠና መንገድ በሐሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በከፍተኛ በጀት በተመረጡ ሰዎች ቀደም ተብሎ ጀምሮ ስራዎችን ለመስራት ተሞክሯል።

ወያኔ ለ27 ዓመት ያህል ፈላጭ ቆራጭ መንግስት ሆኖ መቆየቱ ከለውጡ በኋላም ሐገር የማተራመስ እድሎችን አልዘጋበትም። በኢትዮጵያ የለውጥ ታሪክ የወያኔን ለየት የሚያደርገው እስከሙሉ ቁመናና አቅሙ ከማዕከል ወደዳር መገፋቱ ነው። በዚህም እስከ ቀበሌ ድረስ የነበረውን ኔትወርክ በመጠቀም በሚያገኘው መረጃ መሰረት( በተለይ በአማራ በኩል ትግሬ አለመሆኑ እንጅ ከወያኔ በላይ "አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት" በሚለው አስተሳሰብና ተያያዥ የወያኔ ስልጠናዎችን በየጊዜው ሲንቆረቆርባቸው የነበሩና አዕምሯቸው ከዚህ ውጭ መመልከት እንዳይችል ተደፍኖባቸው የቀሩት ሰዎች ባለመቀየራቸው) መቀሌ ተቀምጦም በቀላሉ አጀንዳውን በእነሱ በኩልም ለማስፈፀም ነገሮችን በሙሉ አልጋ በአልጋ አድርጎለታል።

ከአማራውም ከኦሮሞውም እንደፈለኩ manipulate ለማድረግ ይቀሉኛል ያላቸውን አቅም የሌላቸውን፤ 'መረጃ ይዤባቸዋለሁ' የሚላቸውንና 'የፌደራሊስት ሃይሎች' የሚላቸውን፤ እንዲሁም ቅጥረኞችን በማሰማራት ወደ በኋላ ደግሞ ከለውጡ ጋር የመቀጠል እድል የሌላቸውን፤ የተጠያቂነት ስጋት ያለባቸውን ሰዎች ወደፊት እንዲመጡና በተለያዬ መንገድ በገፅታ ግንባታ ስማቸውን በመሸጥ የጥፋት አጀንዳውን በእነሱ በኩል ወደሕዝብ ለማስረፅ ተሞክሯል። አሁንም የቆመ አይደለም። ከእነዚህ ማንነታቸው ከሚታወቁ አማራና ኦሮሞ ውስጥ ከተመረጡት (አውቀውትም ሳያውቁትም) ከሆኑ ሰዎች ጋር አጀንዳ የሚመጋገቡ ማንነታቸውን ደብቀው በጭንብል ያልሆኑትን ማንነት ሆነው የሚያስጨፍሩ በቀድሞው የደህንነት ሹም ጌታቸው አሰፋ የተበተኑ በሺ የሚቆጠሩ ሰልጣኞችም ይገኙበታል።

የኦሮ-ማራን ጥምረት ለማፈራረስ ከአክሱም ዩኒቨርስቲ ብቻ ኦሮሞኛ ቋንቋ ሰልጥነው የወጡ ከ2000 በላይ የሚሆኑ ወያኔዎች በኦሮሞ በኩል ስምሪት በመውሰድ ለውጡን ወይም የአብይን አስተዳደር "የአሃዳዊ የነፍጠኛ ስርዓት እንደሆነና እሱን ለማፅናት እየሰራ ስለመሆኑ" የዘወትር አጀንዳቸው አድርገው የኦሮሞን ሕዝብ ከአብይ አህመድ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአማራው ጋር እንዲጋጭ በስፋት ቀስቅሰውበታል። የኦሮሞን ሕዝብ ቋንቋን መሰረት አድርጎ በተከለለው ክልል ያገኘውን ጥቅም ጭምር አብይ አህመድ ሊነጥቀው የመጣ የጥፋት መሲህ ነውና ኦሮሞ ሆይ ተነስ እያሉ የእልቂት ጥሪ አቅርበውለታል። ይህን አጀንዳ የሕወሓት ስራ አስፈፃሚዎች ሳይቀር ወደአደባባይ ወጥተው ውግንናቸው ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ስለመሆኑና ለኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ጭምር እንደሚታገሉ በDW በ TMH ሚዲያዎቹ በኩል ለማስመሰልና የኦሮሞ ሕዝብ ለአመፅ እንዲነሳሳ ቅስቀሳ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያን ለማፍረስ አማራው ቅድሚያ አማራ ነኝ ብሎ መቆም እንዳለበት በወያኔ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚታመንበት ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩት በደቡብ ክልል የሚገኙት ብሔሮችና በሌሎችም ክልሎች ያሉ ሕዝቦች በአማራ ላይ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው። እነዚህ ኢትዮጵያኒስት ኤሊቶች በአማራው ላይ ተስፋ መቁረጥ የሚችሉት አማራው አማራ ነኝ ብሎ በሁሉም ዘንድ እንደጠላት እንዲታይ የሚያደርግና በራሱ አንድ ሆኖ መቆም የማይችል የተዳከመ ሐይል ሆኖ የሚያሳየውን 'ወያኔያዊ አማራነትን' ማቀንቀን ከተቻለ ብቻ ነው።

ወያኔያዊ አማራነትን አማራ "አማራ ነኝ" ብሎ እንዲያቀነቅን ደግሞ ወያኔ በ27 አመት የመንግስትነት ቆይታው በየቦታው የቀበራቸውን timing bombs ለመጠቀም ተሞክሯል። በግፍና በብሶት አማራው "አማራ ነኝ" ምርጫውና ብቸኛ የመዳኛ መንገድ መስሎ እንዲታየው በአንፃሩ የኢትዮጵያዊነትን ማዕቀፍን የመጠቃቱ ምንጭ አድርጎ እንዲቆጥረው ለማሳየት ተሞክሯል። ታዲያ አማራው ከግፍ ብዛት በብሶት አማራ ነኝ ብሎ እንዲቆም ግፎችንና መከራዎችን ወደሕዝቡ ለማድረስና ለማስረፅ ለአማራ የሚታገሉ የሚመስሉ የሚዲያ ብልጫን መውሰድ ግድ ይለው ስለነበር ለዚህ ደግሞ ተመራጩና ቀላሉ ማህበራዊ ሚዲያ ነውና