Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.42K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
By Getenet Almaw
ሰበር ዜና ለባንዳዎች በሙሉ

<>

በኢትዮጵያ ላይ ሊጣል የታቀደውን #HR6600 የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለደገፉ በነውራቸው አጊጠው በድንቁርናቸው ለተኩራሩ ባንዳዎች በሙሉ መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው Von Batten-Montague-York, L.C. አዲስ ብስራት አለኝ እያለ ነው።

ይህ የፖሊሲ አማካሪ እና ጉዳይ አስፈጻሚ/ወትዋች/ ሆኖ የሚሰራ ቡድን (policy advisory and advocacy group) በውጭ የሚኖሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት የሚልኩትንገንዘብ ለመገደብ ከዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በጋራ መስራት መጀመሩን ይፋ አድርጓል!!

#HR6600 ይጽደቅ” እያለ የሚሞላፈጥ ሰው አንድ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ አገር ቤት ያለ ጅምር ቤቱን ለማስጨረስ፣ የጀመረውን ንግድ ለማስፋፋትና ለማቀላጠፉ፣ ቤተሰብቹን በተለያዩ መንገዶች ለመደገፍ (በማስተማር፣ በመጦር፣ የንግድ መነሻ ካፒታል በመስጠት፣...) ብሎም በሰው ሰራሽ አደጋና (ጦርነትን ጨምሮ) በተፈጥሮ አደጋ (ድርቅ፣ ጎርፍ፣...) ለተጎዱ ወገኖቹ የዕለት ደራሽ መለገሰ እንዳይችሉ የሚከለክል መሆኑን አያውቅም፤ ቢያውቅም ግድ አይሰጠውም — የምቀኝነት ፖለቲካ ጥግ!!

በነገራችን ላይ HR6600 የአማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ ሙሉ ለሙሉ እንዲፈርስ የሚጠይቅ መሆኑን እየመከርኩ እያወቁ በድፍረት ሳያውቁ በስህተት ይህንን ረቂቅ ሰነድ ለሚደግፉ የዋሆች ማሳሰብ እወዳለሁ!!

የአማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ ይፍረሱ የሚል እሱ ከእኛ ወገን አይደለም!!

<>

ይኸው ነው
የሕወሓትን አርማ ምልክቶችን በይፋ መጠቀም የቀረው በአማራ ፖለቲካ ውስጥ በተቃዋሚ ስም የሚንቀሳቀስ ሃይል ተፈጥሯል። ይህ በተቃዋሚ ስም የሚንቀሳቀሰው ሃይል የኋላ ደጀን በመንግስታዊ መዋቅር ከአመራርነቱ በአቅመ ቢስነቱ በወንጀሉ የተባረረ ወይም የመባረር ስጋት ያደረበት አመራር እና በደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ያለው ተመሳሳይ አካል ምርኩዝና አጀንዳ አቀባይ ሆኖ ጃስ የሚለው ነው።

በአማራ ፖለቲከኛ ራሱን እንደ አማራ ፅንፈኛ ብሔርተኛ የሚቆጥር አካል አለ። የመንግስት ተቃዋሚ ነኝ በሚል የሚንቀሳቀሰውና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በስልጣን ያኮረፈው በሕገ-ወጥ እንቅስቃሴና በሌሎች ወንጀሎች የተጠያቂነት ስጋት ያለበት ነው። የመንግስት ተቃዋሚ ነኝ በሚለው ረድፍ የሚንቀሳቀሰው ማንነቱን ደብቆ በብዕር ስም የሚጠቀመውና ወጥሮ የሚፅፈው ራሱ ወያኔ ሲሆን ሌላኛው ፅንፍ ብሔርን የፖለቲካ ማደራጃ ባደረገች ሐገር ወይም ትግል Balance of power ለመፍጠር በማሰብ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ነው። ይህ ሃይል የጠራ ማንነቱ የማይታወቅ ግለሰቦች ጭምር አክተር የሆኑበት የጋራ የጠራ አላማና የጋራ ግብ አስቀምጦ የማይታገል ይልቅስ በጥላቻ ወለድ ስሜት የወያኔን አጀንጃ ብቻ ነክሶ ይዞ 24/7 ኦሮሙማ የሚል ወይም ከሁሉም ብሔር ከክልሉ መንግስት ከፌደራሉ መንግስት ጋር መናከስን፣ መሳደብን፣ መራገምን፣ የግለሰቦችን ስም ማጥፋትን ለአማራ የሕልውና የመዳኛ መንገድ እንደሆኑ አድርጎ መለፍለፍን እንደ እስትራቴጂ የሚቆጥር ነው።

ፅንፈኛ ነኝ ብሎ መንግስትን እንደሚቃወም የሚገልጸው ሃይል በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ላኮረፈው የተጠያቂነት ስጋት ላለበት ለአፍቃሬ ወያኔው ሃይል የጎጥ ተቆርቋሪነትን ሽፋን በማድረግ ከፊት በመቅደም ቩቩዜላ ወይም ጡሩንባ ነፊ ሆኖ የሚያገለግልና የወያኔን አላማ የሚያስፈፅም ነው።

የአማራ ፖለቲካ የደፈረሰው እና ነገሮች የተወሳሰቡ የመሰሉት በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ያለው አፍቃሬ ወያኔ አቅመ-ቢስ ወንጀለኛ አመራርና በደህንነት ክንፉ ውስጥም ያለው አቅመ ቢስ የሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማራው ወንጀለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የተቆርቋሪነት ስሜት ስም የሚለቁት ወይም በሚበትኑት መረጃ መረጃ ምክንያት ነው።

አገር ለማፍረስ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ሆነው እንደ ምስጥ የሚሸረሽሩትን የወያኔ አጀንዳ አስፈፃሚዎችን ሳይረፍድበት ማፅዳት ወይም አደብ ማስያዝ ይገባዋል።

ከወያኔ በላይ ወያኔ ሆኖ የወያኔን አርማና ምልክቶችን መጠቀም የቀረው በአማራ ማልያ የሚንቀሳቀሰው አፍራሽ የጥፋት ሃይል መንጋውን በማደናገር ኢትዮጵያን በጢም ሳራዋ ለመድፋት እያሳየ ያለውን መቋመጥ፣እንቅልፍ አልባ የጥፋት እንቅስቃሴን ቸላ ማለት ተገቢ አይደለም። አላማው መቼም ቢሆን ሊሳካለት የማይችል ቢሆንም አላስፈላጊ መስዋዕትነት ላለመክፈል ግን ቅንጣት ታህል እድል ሊሰጠው አይገባም‼️

የሚሄዱበት መንገድ ልክ መስሏቸው በንፁህ ልቦናቸው የሚታገሉ የትግል ጉዟቸውን ያልመረመሩ ተደራቢ ሐቀኛ አማራዎችን አይመለከትም። የመንገዱን መዳረሻ ቆም ብሎ ማሰብ የግድ መሆኑን ግን እመክራለሁ‼️
ለእናት ኢትዮጵያ ዛሬም ድምፅ የሚሆኑ ቆራጥና የታመኑ ልጆች አሉ። ኤች አር 6600ን በመቃወም በአገረ አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን እያሰሙ ነው!

ትናንትም ሆነ ዛሬ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የሕዝብ ጥቅም የማትደራደሩ ኢትዮጵያዊያን በፀና ኢትዮጵያዊነታችሁ ባንዳነትን አሸንፋችሁታልና ምስጋና ይገባችኋል! ኩራቶችም ናችሁ‼️
እስከ ምፅዓት ድረስ ጊዜ ቢሰጣችሁ እንኳን መቼም ቢሆን ወያኔን በአማራም ሆነ በኢትዮጵያዊያን ላይ ማንገስ አትችሉም። መቼም። ሙከራው ራሱ ሰማይን በቴስታ እንደመምታት የሚታሰብ ነው።
ለኢትዮጵያ ሕልውና የእናት ጡት ነካሾቹ ወያኔና የግብር ልጆቹ ጥላቻና የተጠያቂነት ስጋት ወለድ አካኪ ዘራፍነት ሳይሆን ኢትዮጵያ ሰው በፈለገችበትና በተጣራችበት የጭንቅ ወቅት ለአንድያ ሕይወታቸው እንኳን ሳይሳሱ ከፊት ቀድመው በመሰለፍ ወያኔንና የግብር ልጆቹን ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ አላማን ያከሸፉ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ አለኝታዎች በመንግሥት መገፋት መከፋት በቁጣ ካስነሳቸው የኢትዮጵያ ሕልውና ወደአደጋ ሊያስገባ ይችላል።

ወያኔን መንገድ እየጠረገ ወደአዲስ አበባ እየመራ ሐገር ለማፍረስ በተቃዋሚ ስም ይንቀሳቀስ የነበረው ሁሉማ አሁን ላይ በምንም ጉዳይ የቱንም ያህል ቢያኮርፍና አምርሮ ቢቆጣ የትም ሊደርስ የሚችል አይደለም። ከዚህ በፊት ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ የታየ ሃይል ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን በአሸናፊው አካል መልካም ፈቃድ ብቻ የሚንቀሳቀስ በባዶው የሚጮህ የተሸነፈና የወደቀ ሃይል መሆኑ ተረጋግጦ ያደረ ሐቅ ነው።

በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር የማይደራደሩ ወያኔን አምርረው የሚጠሉና የታገሉ አሁንም ለኢትዮጵያ ስጋት የሚሆንን ሃይል ለመታገል ወደኋላ የማይሉ ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊያን የሚያነሱትን ተገቢነት ያለውን ጥያቄ መንግስት ባልሰማና ባላዬ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የሚያልፍና ይህን ሃይል የሚያስከፋና የሚያስቆጣ ከሆነ ግን በቅርቡ የምናየው የኢትዮጵያ ትንሳኤን ሳይሆን ውድቀቷን ሊሆን ይችላል። ስለሆነም መንግስት ከሐገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ለሚነሱ ተገቢ የሆኑ ጥያቄዎች ጆሮ ሊሰጥ ይገባዋል። ክብር ለሚገባውም ክብር ይስጥ።
ለሐገራቸው የቆሙና በሐገራቸው ላይ
የቆሙ አርበኛ እና ባንዳ የሚታዩበት መነፅር መስተካከል አለበት። ሐገር አፍራሽ ባንዳዎች የሚነግሱበት የወያኔ ስርዓት የሚቀጥልበትንና የሚፀናበትን እድልም ማንም ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ፈፅሞ ሊፈቅድ እንደማይችል መታወቅ ይኖርበታል።

ሰናይ ሌሊት!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቼ እንኳን ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ።

ረመዳን ከሪም!
ግፍን ማውገዛ መልካም ነገር ነው። መቼም ቢሆን የሚበረታታና የሚደገፍ ጉዳይ ነው። ኦሮሞን እንደ ሕዝብ ወይም አማራን እንደሕዝብ ለማጣጣል ወይም ወደእርስ በርስ ግጭት እንዲገቡ ለማድረግ የሚደረገው የሙከራ እንቅስቃሴ አላማው ሰብአዊነት አለመሆኑን በግልፅ ያሳያል። መልክ ወይም ቋንቋ ካልሆነ በስተቀር ግብሩ ወያኔነት ነው።
ወልቃይት እንግዶቿን እየተቀበለች ነው!

ወልቃይት ብዙ ነገራችን ነች‼️
በ yesuf Ibrahim

የወልቃይት ጉዳይ በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው አጀንዳዎች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ የሚጠቀስ ነው።
በገፊ ምክንያትነትና በቀጣይ ግብዓትነት!

ወልቃይት ማለት የሆነ የመሬት ወርድ × ቁመት ጉዳይ አይደለም! የትህነግ ስብስብ ለግማሽ ምዕተአመት ያክል ሳያቋርጥ ጥርሱን አግጥጦና አይኑን አፍጥጦ በወልቃይት ላይ የሚያማትረው ለምን እንደሆነ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል።

በዋናነት ወልቃይት ማንነቱን በግፍ የተነጥቀና የዘር ጭፍጨፋዎች ሰለባ የሆነ ሰፊ ማህበረሰብ ጉዳይ ነው። ይህ ከሁሉም በላይ የወልቃይትን ጉዳይ automatically የመላው አማራ ህዝብ አጀንዳ አድርጎታል።

"ወልቃይት" የፍትህ፣ የማንነት፣ የክብርና የታሪክ ጉዳይ ነው! የወልቃይትን ፋይዳ በደላላ ቀመር መረዳት አይቻልም። የወልቃይትን ጉዳይ "በሰሊጥ ፖለቲካ" ፈርጀው የሚያራክሱ አካላት እንደሁኔታው አስገራሚና አሳዛኝ ናቸው። ግን— የትህነግ ስብስብ ሊጥ በሚሰርቅበት ዘመን ሰሊጥስ ቢሆን እንደት ርካሽ ሊሆን ይቻላል?

ለማንኛውም—
በወልቃይት ታሪክ፣ መልክዓምድር፣ ከርሰምድርና መልከዓ-ፖለቲካ ዙሪያ ዝርዝርና ተጨባጭ ግንዛቤ ለመፍጠር— ለአማራ ተማሪዎችና ወጣቶች ሲወርድ ሲዋረድ በቀጠለው "የወልቃይት" ጉዳይ ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በሚል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

በተመሳሳይ በሌሎች የአማራ ህዝብ ነባርና መሰረታዊ ጥያቄች ዙሪያም ተገቢውን ግንዛቤ በመፍጠርና አስቻይ የትግል ስልቶችን በመንደፍ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል። የአማራ አጀንዳዎች እርስበርስ ተደጋጋፊ በመሆናቸው ለአንዱ የምንሰጠው እልባት ለቀሪዎቹ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ሊሰመርበት ይገባል!

ማስታወሻ
------
ወያኔ በግፍ ጨፈጭፎ ጅምላ መቃብሮች ውስጥ የጣላቸውን ወገኖች አፅም የማውጣትና በክብር የማሳረፉ ስራዎች ሲከናወኑ በተቻለ መጠን ታዋቂ የሆኑ የሀገር ውስጥና የዓለማቀፍ የሚዲያዎችና የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲታዘቧቸውና እንዲዘግቧቸው ማድረግ ያስፈልጋል።