Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.42K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
By Yesuf Ibrahim

የትህነግና የኦነግ ምግባር በግልፅ ይታወቃል። ጨካኝነት ነባር ማደሪያና መተዳደሪያቸው ነው። ሰዎችን በግፍ እየገደሉ ይፎክራሉ፣ ይሞጋገሳሉ፣ ይሸላለማሉ፣ ድርጊቱን በድምፅና ቪዲዬ ቀርፀው ያሰራጩታል።

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እድሜልክ የሰለጠኑበት ግፍና ጭካኔ አሸናፊ እንደማያደርጋቸው በመገንዘብ አማራውን በተለይም ፋኖን ተመሳሳይ ገፅታ ለማላበስ ሲረባረቡ ይስተዋላል።

የነሱን ገፅታ ለአማራው የማላበስ ስልት ለመከተል ወስነው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። የጨካኞቹ ጥምረት የጋራ መግባቢያ ቋንቋ "አማርኛ" መሆኑ እንዲዘነጋ ይፈልጋሉ።

ፋኖዎች የማረኳቸውን የጠላት ተዋጊዎች ሰብስበውና መጠለያ ሰጥተው እንደሚቀልቡ እናውቃለን። ዋናው ጉዳይ ኢሰብዓዊነትን መፀየፍና ማውገዝ መሆን ሊሆን ይገባል። የተሻለ የህግና የፖለቲካ ባህል መገንባት ብቸኛው መውጫ መንገድ ነው!
መንጋ አዝማቹና መንጋው ያለ ቡጢ እንዲሁ በቀላሉ ተዘርሯል‼️

ከዚህ በኋላ ሕልውና እና ሁለንተናዊ ጥቅሙን አሳልፎ ለመስጠት መናጆ የማይሆን ሕዝብን በፀና ትግል እንፈጥራለን። የሚቃረነውን በቋንቋው አናግረን በድል ሰገነት ላይ በመቆም በውስጣዊ ደስታ እንጨፍራለን።
ኢትዮ 360 (አንዳንዶች Egypt 360 ይሉታል🤣) ከወያኔ ጓዳ ወጥቶ የአማራ ካምፕን ምሽግ በማድረግ በተቆርቋሪ ስም አማራን ወደ አዘቅት እንዲወርድ ተግተው ከሚሰሩ መንጋ አስጨፋሪዎች ውስጥ ቀዳሚው የፀረ-አማራ ሃይሎች ( በዋናነት የወያኔና የኦነግ ) ጉዳይ አስፈፃሚ የዩትዩብ ሚዲያ ነው። የፀረ-አማራ ሃይሎች ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው ይህ የዩትዩብ ሚዲያ ከወያኔ በላይ ወያኔ በመሆንም አማራ ላይ ሂሳብ ይወራረድ፣ ኢትዮጵያም ትፈርስ ዘንድ በሕልውና ዘመቻው ብቻ ያሳየውን አቋም መውሰድ ከበቂ በላይ ነው። የወያኔን አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት የማይናቅ አሻራውን ያሳረፈ የወያኔ የግብር ልጆች ስብስብ ኢትዮጵያ በአሸዋ ላይ የተገነባች አገር ስላልሆነች ነው እንጅ እንደጥፋት ተባባሪነቱ እንደምኞቱ ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ከግብር አባቱ ወያኔ ጋር አሮጌ ከበሮ ሊደልቅ ቋምጦ የነበረ የጥፋት ሃይል ነበር። የወያኔም ሆነ የግብር ልጆቹ ምኞትና ሕልም ግን በጀግኖቹ የቁርጥ ቀን ኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ተመክቶ በመልሶ ማንከት ከንቱ መሆን ችሏል።

እንደ ባንዳዎቹ እና እንደ ባዳዎቹ እረፍት የለሽ የሐሰተኛ የፖሮፖጋንዳ የሽብር ዘመቻ እንደ ልቡሳነ-ስጋዎቹ የጥፋት አላማ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያንም ማስቀጠል እኛም ዛሬን በነፃነት ማየት ባልቻልን ነበር።

ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ልክ እንደጥንቱ የቱንም ያህል ውስጣዊ ልዩነቶች ቢኖርባቸው እንኳን በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር ግን መቼም ቢሆን ተደራድረው እንደማያውቁ የታሪክ ድርሳናት የሰጡትን ምስክርነት ዛሬም(የእኛ ትውልድ) የአባቶቹን አንፀባራቂ ገድል ዳግም በገቢር በማረጋገጥ ለአለም ማሳየት ችሏል።

"ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ይህንም ለማሳካት ሲኦልም ድረስ መውረድ ካለብኝ እወርዳለሁ" የሚል ሐገር የማፍረስ ዘመቻ በአዋጅ ነግሮ እሱንም ሊያጠፉት ኢትዮጵያንም ሊያፈርሱበት መጣንብህ እያሉት ይቅርና ለስልጣን ቢሆን እንኳን ነቀርሳ ሃይል መሆኑን እሰራላችኋለሁ ብሎ የሰራባቸውን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ የሚረዱት ነበርና ለተቀናጀው የሐሰተኛ የሽብር ዘመቻ ጀሮ የሰጠ አልነበረም።

በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ የተደቆሰውን ወያኔን በጦርነት ያላሳካውን አላማ በአማራ ካምፕ ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ተሰባስበናል የሚሉት አካላት ከወያኔ በላይ ለሕልውናው ስጋት ሆነው ወያኔን እያስናቁ ነው። ወያኔ በአማራ ኤሊት ላይ ሂሳብ የማወራረድ ሕልሙን በአማራ ተቆርቋሪነት ጥላ ስር የተሰባሰቡ የግብር ልጆቹ ሕልሙን ሊያሳኩለት በአያሌው ቀን ተሌት ሲደክሙ ባጅተዋል።
ኢትዮ-360 የተባለ የወያኔ አጀንዳ አስፈፃሚ የዩትዩብ ሚዲያ በአማራ በኩል ጠንካራና ተገዳዳሪ ሃይል እንዳይፈጠር፣ አማራ በሐገራዊ ጉዳዮች ወሳኝ ድርሻ እንዳይኖረው በሌሎች የኢትዮጵያ ወንድምና እህቶች ዘንድ የተናቀና ለአጋርነት የማይፈለግ ሃይል ይሆን ዘንድ በአማራ ብልፅግና ውስጥ ዘው ብሎ በመግባት ወያኔ የሚጠላውን እየጠላ ወያኔ የሚወደውን እየወደደ ከወያኔ ጋር በመቀናጀት ያደረገው የስም ማጥፋት ዘመቻ ከሞላ ጎደል አልተሳካለትም ማለት አይቻልም። እነዚህ በአማራ ማልያ እየተጫወቱ በአማራው ላይ ከፍተኛ ነጥብ እንዲቆጠርበት የሚያደርጉ የኢትዮ-360 መንጋ አዝማቾች እንዲሁም በአማራ ፖለቲካና አክቲቪዝም የሚሳተፉ ተጨማሪ መንጋ አዝማቾች በአይን ጥቅሻ አጀንዳ እየተመጋገቡ ያደረጉት የስም ማጥፋት አማራውን የመከፋፈል የጥፋት ዘመቻ አሁን ላይ አማራው ሁነኛ ልበ ሙሉ ተወካይ እንዳይኖረውና ተሸማቃቂ ተወካይ እንዲፈጥር የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።
መንጋ አዝማቾቹና መንጋው ኦነግን የተቃወመ በመምሰል(ሕወሓት ስልጣን ላይ የለም በሚል ሲስተማቲካሊ ያልፉታል) የአማራ ብልፅግናን እየተሳደበ የኦነግ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች በኦህዴድ በኩል እንዲነግሱ ለማድረግ ያላለው ነገር የለም ።

የአማራ ብልፅግናን ብአዴን ስለሆነ ይው*ደም እያሉ ከአመት እስከ አመት ከሚሸልለው መንጋ ጋር ሲመጋገቡ ከርመው የብልፅግና ጠቅላላ ጉባኤ ሲደርስ ከአማራ ብልፅግና ውስጥ ቆንጆ መረጣ በመግባት (ያው ግም ለግም አብረህ አዝግም እንዲሉ ቢጤያቸውን(በግብር) )) ለሚመስላቸው አካል የገፅታ ግንባታ ለመስራት ሲሞክሩ ወያኔን አምርረው የተቃወሙትንና የታገሉትን ደግሞ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት በአጭር አነጋገር በአማራ ብልፅግና ውስጥ ያሉ ልዩነቶቹን ወደ አደባባይ በማውጣትና ልዩነቶች ላይ በመረባረብ ተጨማሪ ስንጥቆችን በመፍጠር የእርስ በርስ ሽኩቻው እንዲጧጧፍና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ አማራው መሳቂያና መሳለቂያ ሆኖ ሁነኛ አጋር እንዳይኖረው እነኚህ በአማራው ዲያስፖራ መዋጮ ሕልውናቸው የተመሰረተ ሰዎች በአዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓችነትና መንጋ አዝማችነታቸው አማራውን ለከፍተኛ ፖለቲካዊ ኪሳራ ዳርገውታል። ወደፊም ይህ የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ የዩቲዩብ ሚዲያ ጆሮ ካገኘ የማይቀበጣጥረው የማይሸረሽረው የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ አንድነት አይኖርም። የዚህ በአማራ ማሊያ የሚጫወተው እና በአማራ ዲያስፖራ ላይ ሕልውናውን የመሰረተው የጥፋት ቡድን ኦነግና ወያኔ ሕይወት ዘርተው እንዲነሱና እንዲነግሱ በአማራ በኩል ያሉ የፖለቲካ አካላት ደግሞ እንዲኮስሱና እንዳይነግሱ የስም ማጥፋት የዘመቻ ማዕከሉን አማራ ላይ አድርጎ ይቀጥላል። ምክንያቱም የወያኔ የግብር ልጆች ስብስብ የኦነግ አጋር ነውና።

ይህ የጥፋት ሚዲያ ዓመታዊ ገቢው 349,000 ዶላር እንዳሁም ወርሃዊ ገቢው 30,000 ዶላር እንደሆነ የዩቲዩብ መረጃው ያሳያል።
ይህ በአማራ ህዝብ ደም በተለይ በመነገድ የተገኘ ገንዘብ አልበቃ ብሏቸው የዋሁን አገር ወዳድ ድያስፖራ በየጊዜው ለፋቶ በላቡ ያገኘውን ገንዘብ በጎ ፈንድሚ ይቀፍሉታል።
ይህን ሁሉ ገንዘብ እያገኙ ሰሞኑን ለኤርሚያስ ለገሰ ብለው እየለመኑ ነው።
ይህ ሁሉ ገንዘብ ከዲያስፖራው (በተለይም ከአማራው) ተሰብስቦ የገንዘብ ምንጩ እየደረቀበት ያለውን ወያኔን ለማዳን ይውላል። ይህንን ያገጠጠ እውነታ ማጣራት የሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ ግዴታ ነው።
ኢንጂነር ጌታቸው ገነት ይባላል። የሚኖረው በአሜሪካ ነበር። የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ባዳዎች በቅንጅት ኢትዮጵያን ለማፍረስ በቅንጅት ሁለንተናዊ ጦርነት ሲከፍቱ የአሜሪካ ኑሮውን በመተው ወደኢትዮጵያ በመምጣት የሐገር መከላከያ ሰራዊት ለመቀላቀል ወደማሰልጠኛ ገባ። ዛሬ ስልጠናውን ጨርሶ በሁርሶ ማሰልጠኛ ተመርቋል። የኢትዮጵያን ነፃነትና ክብር ለመጠበቅ ልክ እንደትናንቱ ዛሬም ከፊት የሚቀድሙ ቆራጥ እልፍ ጀግኖች አሉ።
በዚህ አጋጣሚ የነገ ኮ/ል ጀኔራል ለመሆን እድሉ ያላችሁ ወጣቶች መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀል ይገባናል‼️
ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!

የአማራ አርበኝነት ተጋድሎ (ፋኖነት) አንዳንድ የታሪክ ድርሳናት በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት የተጀመረ፣ ለሀገሩ ለህዝቡ ነፃነትና ሉአላዊነት በራሱ ወኔና ፍፁም ፍላጎት ትጥቁንና ስንቁን አሟልቶ በነፃ ቤዛ ለመሆን የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ጀግኖች መጠሪያ “አርበኛ-ፋኖ” ይሰኛል፡፡ የፋኖ አርበኝነት በሀገራችን ኢትዩጵያ የውጭና የውስጥ ወራሪና ግፈኛ ቅኝ ገዥዎችን እና የሀገር ጠላቶችን የእብሪት ክንድ አልፈስፍሶ በማጥፋት የሀገርንና ህዝብን ክብርና ነፃነት የሚጠብቅ ስለመሆኑ የሀገራችን ታሪክ ያረጋግጣል፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን በሀይል መቆጣጠር የቻለው ግፈኛውና ጨቋኝ አድሏዊ የአፓርታይድ አገዛዝ ህዝባችን ላይ የጫነው ትህነግ እያረደሰ ያለውን ከፍተኛ ግፍና በደል ለመቀልበስ የፋኖ የአርበኝነት ተጋድሎና የወጣቶች የመብት ጥያቄ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው እሙን ነው፡፡ በቅርብ ወራትም ከማዕከላዊ መንግስት ፈላጭ ቆራጭ ስልጣን በህዝብ ትግል ገሸሽ የተደረገው ግፈኛው ትህነግ ሀገር ለማፍረስ፣ ለመዝረፍ፣ እናቶችን ለመድፈር፣ ዜጎችን ለመግደል፣ለማፈናቀልና የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት ለማድረስ ራሱን አደራጅቶ ወደ መሃል ሀገር ወረራ በፈፀመበት ጊዜ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች በሁሉም ጦር ግንባሮች ተሰልፈው ከጠላት ጋር በመፋለም ከሌሎች የመንግስት ጥምር የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን እጅግ አኩሪ ድል በመጎናፀፍ ሀገርን ከመበተን ህዝቦቿንም ከስቃይና ውርደት መታደግ መቻሉ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ በዚህም ከህዝብ አብራክ የወጣው የፋኖ አርበኝነት የመንፈስና የስነ-ልቦና ውቅር ከዘመን ወደ ዘመን ከትውልድም ወደ ትውልድ እሴቱንና ታሪኩን ጠብቆ እያስተላለፈ ለሚገኘው ለመላው ህዝባችን በተለይም ለአማራ ህዝብ ምስጋና ያቀርባል፡፡ሆኖም የፋኖ አርበኝነት ትግል በተበጣጠሰ ሁኔታ በየአካባቢው በጎበዘ አለቃ የሚመራና ያልተማከለ መሆኑ ለሀገርና ህዝብ መስጠት የሚገባውን ሁሉ ለመወጣት ተግዳሮት ሁኖ እንደቆየም ይታወቃል፡፡ ተበትኖ የቆየው የአማራ ፋኖ አንድነትን ለማምጣትና የሰራዊቱንና የደጋፊውን እንዲሁም ግልፅ የአላማ አንድነት ለማፅናት በርካት ተግባራት እየተካሔደ ያለበት ወቅት ላይ ስንሆን በጎንደር የሚገኙ 5/አምስት/ ዞን አስተዳደር ስር እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር ስር መቀመጫቸውን ያደረጉ ፋኖዎችና መሪዎቻቸውን ውህደት በመፈፀም ከዛሬ ጀምሮ “የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር” የተሰኘ አንድነት ላይ መድረሳችንን እያበሰርን ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ መላው የፋኖ ዓባላትና የትግሉ ቤተሰቦች በቀጣይ እንደ አማራ ወጥ የሆነ አንድነት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተረድተን እጅግ በርካታ አባላት ያለው የጎንደር ቀጠና ፋኖ በአንድነት ተዋቅሮ መቅረቡን ተገንዝባችሁ ሁሉም ወገን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እንዲደግፍና በዓባልነት ተመዝግቦ መታገል እንደሚችን እናሳውቃለን፡፡

ፋኖ የውስጥ የአላማና የአደረጃጀት አንድነቱን በማረጋገጥ የጠላትን ወረራ ለማምከንና በጠላት ወረራ ስር የሚገኙ ህዝባችንና አካባቢዎች ነፃ ለማውጣት የሚረዳ መሆኑን ስለታመነበትና ህዝባችን ፋኖ አንድ ይሁንልን ሲል በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ለወራት የውስጥ የውይይት ሂደቶችን በማለፍ ሙሉ መግባባት ላይ በመደረስ ወጥ በሆነ ተቋማዊ የፋኖ አንድነት ውህደት ላይ በመድረሱ መላው የአማራ ህዝብና የሀገራችን ልጆች፣ ዓባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ/ እንኳን ደስ አለን/ እያልን በቀጣይ በአባላት የስነ-ምግባርና የሙያ ጥራት ላይ ትኩረት አድርገን ህዝባችንና ወዳጆቻችን እንዲሁም ሀገራችን በሚፈልጉት ትክክለኛ ቁመና ላይ ለመድረስ አበክረን እንደምንሰራ ቃል እየገባን የወገናችን ሙሉ ድጋፍ እንዳይለየን አደራ እንላለን፡፡

የአማራ ፋኖ በሚያደረገው የህልውና ጦርነት ትግል እስከ ዛሬ አብረውን ተሰልፈው በጀግንነት ለህዝብና ሀገራቸው እየታገሉ ለቆዩና እየታገሉ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻ፣ ፖሊስና ህብረተሰቡ፣ ለአፋር ልዩ ሀይልና ለታጋዩ ህብረተሰብ በሙሉ ጀግኖችና አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር በጦርነቱ ላበረከቱ አባላት ሁሉ፣ ለፌደራል ሙህራን፣ መሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ የማህበረሰቡ አንቂዎች፣ አርሶ አደሩና ተማሪው፣ ወጣቶች ዲያስፖራዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና ለመላው ታጋይ የህብረተሰብ ክፍል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ምስጋና እያቀረብን በቀጣይ አብረን ለመስራት የበለጠ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡

በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ዘርና ማንነትን መሰረት ያደረገ የንፁሀን አማራና ሌላው ወገናችን ማንኛውንም ጥቃትና ጭፍጨፋ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ የማንነት ተጠቂ ወገኖቻችን ደህንነት ለማስከበር ማንኛውንም መስዋትነት በመክፈል ለማረጋገጥ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ እናረጋግጣለን፡፡

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ለህዝብና ለሀገር ሉዑላዊነትና ደህንነት፣ ፍታዊነት፣ ለሀገርና ህዝብ ጥቅም መከበርና የማንነትና ርዕስት መብት መከበር በቅንነት ከሚሰራ ማንኛውም አካል ጋር በአጋርነት ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ በጠላት ወረራና ተላላኪ ተቀፅላ አሸባሪ ሃይሎች አረመኔያዊ ተግባር ህይወታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ አካላቸውን ላጡና የስነልቦና ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ልባዊ ሀዘኑን እየገለፀ አሁንም በጠላት ግፈኛ አሸባሪ ቡድን የግፍ ግዞት ስር ለምትገኙ ወገኖቻችን ለፀሀይ በታች ማንኛውንም ትግል በማድረግ ነፃ ለማውጣት እንደምንታገል እናረጋግጣለን፡፡

ጠላት ዝግጅት በማድረግ ለተጨማሪ ወረራ እየተዘጋጀ መሆኑን ተገንዝበን የሀገራችን ህዝቦችና መንግስት የጠላትን አስኳል ለመጨረሻ ጊዜ ለማምከን እንዲዘጋጅና የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በተሸላ ቁመና አብሮ እንደሚሰለፍ እናሳውቃለን፡፡

1ኛ- ሀገርና (ህዝቦቿ) ከህልውና ስጋት ፈፅሞ ያልወጣ መሆኑን ተገንዝበን የወገንን ውሳጣዊ አንድነትና ትብብር በመቻቻልና በሆደሰፊነት አንድነቱን እንድናፀና ጥሪ እናደርጋለን።

2ኛ- የአማራ የማንነትና ወሰን ጥያቄና ጠላት በወረራ በግፍ የያዛቸው አካባቢዎች ከጠላት ወረራ ነፃ እንዲወጡና አፋጣኝ ህጋዊ ውሳኔ እንዲሰጣቸው

3ኛ- በወረራ የተፈናቀሉ፣ ሰብአዊና ቁሳዊ እንዲሁም ስነ-ልቦናዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖቻችን አስፈላጊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው

4ኛ. የአማራ ፋኖ በመምሰል የሚደረጉ የህዝብ ሞራል የማይፈቅዳቸው ኢ ሞራላዊ ስርአት አልበኝነቶችና ሃላፊነት የጎደለው የተናጠል እኩይ ድርጊቶችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አጥብቆ ያወግዛል፡፡ ህዝባችን የማይፈልጋቸውን ድርጊቶች የሚፈፅሙ አባሎችን ካገኘ በመተ.ደንባችን መሰረት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እየገፅን በተከበረው የአማራ ፋኖ ጭምብል ከአላማ የወጣ እኩይ ተግባር የሚፈፅሙ የተቋማችን አባል ያልሆኑ አካሎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መላው ህዝባችንና የመንግስት የፀጥታ መዋቅር ትብብር እንዲያደርግልን ጥሪ እናቀርባለን።

5ኛ. በህዝባዊና ሃገራዊ ትግል የህይወትና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው፣ ለጠፉ በህይወት የሚገኙ ጠንካራ ተጋዮችና ከማሃበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ለተነጠሉ የአማራ ፋኖ አባሎች መንግስትና ህዝባችን አስፈላጊውን ድጋፍና እውቅና እንዲያደርጉ እናሳስባለን ፡፡
6ኛ- በጥቃቅን ጉዳዮች ለእስር የተዳረጉ ለቀጣይ የህልውና ትግል አስፈላጊ የሆኑ ታጋዮች ይቅርታና ምህረት በማድረግ ትግሉ እንዲቀላቀሉ እንዲደረግ

7ኛ- መላው የአማራ ፋኖ አባል ለቆመለት ህዝባዊ አላማ አደራ እንዲገዛና ከአላማ ውጭ በማያገባን ጉዳይ ሁሉ ጣልቃ እንዳንገባና የአላማ ስነ ምግባር እንድንጠብቅ እያሳሰብን የመንግስት የፀጥታ ሃይልም አጋር መሆናችንን ተገንዝቦ በሚከሰቱ ጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ያልተፈለገ ግጭትና ትርምስ እንዳይፈጠር ሃላፊነት ተሰምቶን በማስተዋልና በአንድነት መንፈስ የሚያጋጥሙ ጥቃቅን ክስተቶችን እድንፈታ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

8ኛ. ጠላት በማንኛውም ጊዜ ሊወረን እንደሚችል ተገንዝበን ሳንዘናጋ ማንኛውንም ዝግጅት እድናደርግ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

9ኛ- በአፈሰስነው ደማችን፤ በከሰከስነው አጥንታችን ወደ መንበረ ስልጣን የመጣው መንግስት ሀ) በኦሮሚያ ክልል በግፍ የተፈናቀሉና የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመባቸው ላሉ አማራዎች ወገኖቻችን ሊታደግ ይገባልለ) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአማራዎች ላይ የተፈፀመው ነውረኛና ዘግናኝ ግድያ እናወግዛለን የዚህ እኩይ ድርጊት ባለቤት የሆኑ አካላት በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ እንጠይቃለን፡፡

10ኛ- አሁናዊ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ስናይ ትውልድ እንደማምከን የሚቆጠር እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም ትምህርት ሚኒስተር የማሻሻያ መፍትሔ እንዲያቀርብ በአፅኖት እንጠይቃለን፡፡

11ኛ- እኛ የአማራ ፋኖዎች ሀገርና ህዝብ አደጋ ላይ በሆኑበት ወቅት ጦረኛ : በሠላም ጊዜ የልማት አርበኛ መሆናችን ይታወቃል። ስለሆነም የሀገርን ዳር ድንበር እየጠበቅ ማልማት የምንችልበትን የልማት አማራጮች እንዲመቻችልን ስንል እንጠይቃለን።

12ኛ- የአማራ ፋኖ የከፈለውን ዋጋ በመካድ በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በፋኖ አባላት ላይ የሚደረግ ወከባ : ማሳደድ እና የግድያ ዘመቻ ሊቆም ይገባል።

13ኛ- በቀጣይ የመላው የአማራ ፋኖ አንድነት ተቋማዊ ውህደት እውን እንዲሆን ትብብርና ድጋፍ እንዳይለየን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

"ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታቶች !!

መጋቢት 11/2014 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ አንድነት
በጎንደር ኢትዮጵያ !
አብን ከውስጥና ከውጭ በስመ አማራ ተቆርቋሪነት የተሰለፉ የአፍራሾቹን አላማ አክሽፎ ጉባኤውን በድልና በሰላም አጠናቋል። በጣም ደስም ይላል። በተሸናፊዎች ጩኸት መደንቆራችን ግን ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ክብሯን ሊያዋርዱ ቀን ተሌት እንቅልፍ አጥተው የሚደክሙ የእናት ጡት ነካሽ እንዳለ ሁሉ ስሟን በአለም አደባባይ የሚያነግሱ ብርቅዬ ልጆች አሏት።

የቤልግሬድ የ2022 የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ አንደኛ ሆና አጠናቃለች። እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮ 360 እና ኢትዮ ፎረም በመቀሌ

የትግሬ ወራሪ ቡድን ስር ከሚገኙት ሚዲያዎች ውጭ መቀሌ ላይ ህዝብ እንዲሰማቸው የተከፈቱለት ሚዲያዎች አሉ። የሚሆነው እንዲህ ነው። ከዩቱዩብ አውርደው በስፒከር ለሕዝብ እንዲሰማ ያደርጉታል።

ያው ትህነግን ያህል ሚዲያ አፋኝ የለም። በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አንደኛውና ትልቁ የተጠቀመበት ሚዲያን እንዴት ማፈንና ማሰራጨት እንዳለበት ነው። ስለሆነም ማን ለሕዝብ መድረስ ማን መታፈን እንዳለበት ያውቃል። ለጊዜው በአማራጭነት ሁለቱን ሚዲያዎች መርጦለታል። አንደኛው ኢትዮ ፎረም ነው። ይህ ሚዲያ ከትህነግ በቀጥታ የተከፈለው ነው። ከወራት በፊት አቻምየለህ ታምሩ ከአቃቤ ሕግ ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ እነ ደብረፅዮን ለዚህ ሚዲያ እንዴት ሲከፍሉት እንደነበር ጠቅሷል።

ይህ ሚዲያ ላይ አሁን የሚሰራው ጋዜጠኛ በአንድ ወቅት በመተማ አሳፎ ቤንሻንጉል የሚደርሰውን የታላቋ ትግራይ የሚሏትን የሀሰብ አገር ካርታ ስህተት አስመስሎ በኢቲቪ የለቀቀው ጋዜጠኛ ነው። አሁን ደግሞ አማራን ሲሰድብ፣ ትህነግን ሰበብ ፈልጎ ሲደግፍ የሚውል ነው። ከዚህ ሚዲያ ባሻገር ሕዝብ እንዲሰማው በአደባባይ ማን ፈቃድ አገኘ! ኢትዮ 360! ለምን ይመስልሃል? ትግርኛ ሙዚቃ ስለሚለቅ ነው? በትግርኛ ፕሮግራም ስላለው ነው? ትህነግ የሀሰብ ነፃነትን ስለሚፈቅድ ነው? አይደለም!

ምንም እንኳን ከስር ባለው ፅሁፍ ሁለቱም ፀረ ትግሬ ናቸው ያለችው ሆን ብላ ነው። የውጭ ሰላም አስከባሪ ካልገባ የሚሉትን የሚያቀርበው 360 ነው፣ አዲስ አበባ ድረስ ሰተት ብለው ይግቡ ልቀቁላቸው የተባለው 360 ላይ ነው፣ ሲመቱም ምንም ሳይሆኑ ሰተት ብለው ይውጡ እባካችሁ ተብሎ የተለመነላቸው 360 ላይ ነው፣ በሁመራ በኩል ኮሪደር ይለቅላቸው የተባለው 360 ላይ ነው፣ ድርድር ይቀመጡ የተባለው 360 ላይ ነው፣ በቅርቤ የቤንሻልጉሉ ጉዳይ የመጀመርያ ፍንጭ ወጥቶ ደብረፅዮን ቃል በቃል የተናገረው አጀንዳ የተጀመረው 360 ላይ ነው። ኧረ ስንቱ?

ትህነግ አይደለም ትግራይ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ሚዲያ አፍኗል። አሁን ከኢንተርኔት አውርዶ ሕዝብን ሊያስደምጣቸው የሚችለው ይጠቅሙኛል የሚላቸውን ሚዲያዎች ነው። ለማንኛው ትግራይ ላይ የተፈቀዱ ሚዲያዎች ዝርዝር

1) ድምፀ ወያነ

2) TMH

3)ትግራይ ቲቪ

4) ኢትዮ ፎረም

5) ኢትዮ 360

ማሳሰቢያ:_ ያለ ትህነግ ፈቃድና እቅድ ምንም አይነት ሚዲያ በነፃነት ይሰማል ብለው እንዳይሸወዱ። ትግራይ ነው።

ሌላ ማሳሰቢያ:_ ትህነግ ሁለቱን ሚዲያዎች መርጦ ሕዝብ እንዲሰማቸው ያደረገው ከፊታቸው "ኢትዮ" የሚል ስላላቸው እንዳይመስልዎት። አጀንዳቸውን ፈልጎት ነው። በምንም እሱን የሚጠቅሙ እንጅ የማይጎዱ እንደሆኑ ስለሚያውቅ ነው። አንደኛውን እንደከፈለው ዐቃቤ ሕግ አረጋግጧል። ሌላኛውን በአጀንዳው መገመት ነው።
****
ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እንደፃፈው