Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.41K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
"ቁጥቋጦዎች እንዲነግሱ የግድ ዋርካዎች ይገንደሱ" የሚሉ የእንባጮ ስር ተሰብሳቢ መካሪዎችን ወሬ መቼም ቢሆን ተግባራዊ እንዲሆን እድል አንሰጠውም‼️
ማንነቱን ደብቆ ከሚጠቀም የፌስቡክ ተጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ በአቋማቸው ባልስማማም እንኳን ሁለት ሰዎችን ብቻ አልነቅፍም። አጀንዳቸው ፍፁም ግለሰብ ተኮርና ነውረኝነት የሚንፀባረቅበት አይደለም። ከዚህ ውጭ ጓደኛዬ የሆነ የፌስቡክ ፌክ አካውንት ተጠቃሚ ጓደኛዬ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ግለሰብን ከመስደብና ከመራገም ያለፈ ቁምነገር ያለው አይደለምና ብሎክ እያከናነብኩት እገኛለሁ። በነገራችን ላይ በዚህ አጋጣሚ ማንነቱን ደብቆ ከሚፅፍ ፌስቡከር ውስጥ ፍፁም ትህትና ያለው አጀንዳው ከግለሰብ ወጥቶ ስለሕዝብ ሕልውናና ጥቅም የሚቆረቆር ካለ በዚህ አጋጣሚ እንድትጠቁሙኝ እፈልጋለሁ። እስካሁን ማንነቱን ደብቆ(በአካል በፍፁም የማይታወቅ አልፎም ዘሩ የማይታወቅ) ከምታውቁት የፌስቡክ ተጠቃሚ ውስጥ አጀንዳው ሕዝባዊና ለችግሮች መፍትሔ በማቅረብ የምታውቁት ሰው ካለ ጠቁሙኝ። በፍጹም የማውቀው አንድስ እንኳን ሰው ስለሌለ ነው። በእርግጥ የሚታወቅ ማንነት ኖሯቸው ማንነቱ ከማይታወቀው ከተደበቀው አፍቃሬ ወያኔን የሚያስንቁ ሰዎች የሉም እያልኩ አይደለም።
በነገራችን ላይ በአማራ የብሔርተኝነት ፖለቲካ ውስጥ ማንነታቸውን ደብቀው የሚፅፉ ሰዎች ማንነታቸውን ገልፀው በሚፅፉ ሰዎች ላይ አንተ ባንዳ ብልፅግና የአብይ ውታፍ ነቃይ ምናምን እያሉ እንደሚፅፉ ሰዎች ሞራል ያለው ማንነታቸውን የገለጡ የተጣራ መረጃ ያላቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን?
ማንነታቸውን ደብቀው እንደሚፅፉ ሰዎች ማንነታቸውን ገልጠው የሚፅፉ ሰዎችን ነፃነት ለመቀማት የሚሰራ የለም። ማንነታቸውን ደብቀው የሚፅፉ ሰዎችን መንጋው የሚያውቃቸው ብቻ ሳይሆን የማያውቀውን ንግግርና ፅሑፍ የማመን ባሕል እንዳለው ከዚህ በፊት ስለተረዳ አፍቃሬ ወያኔ መድረኩን እንደፈለገ እንዲፈነጭበት እድል ሰጥቶታል።ይህ ሁሌም ያበሳጨኛል።እረፍትም ይነሳኛል።
በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥም ሆነ በተቃዋሚው ጎራ ተሰልፈው ወያኔን ከአራት ኪሎ ወደመቀሌ እንዲመሽግ ካደረጉትና ከለውጡ በኋላም ወያኔ ወደመሀል ፖለቲካው እንዳይመለስ በሀሳብና በተግባር የታገሉ ድንቅ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አሉ።

ምንም እንኳን ወያኔን ወደመቀሌ እንዲመሽግ ማድረግ የተቻለ ቢሆንም ለኢትዮጵያ አሁናዊና ዘላለማዊ የደረጀና የተደራጀ እንደ ወያኔ ያለ ዋና ጠላትና ስጋት የለም ያሉና በፀና አቋማቸው በቻሉት ልክ ወጥረው ሲታገሉ ከነበሩ ጠንካራ የአማራ ልጆች አልፎም 'ኢትዮጵያኒስት' ከሆኑ ከሌሎች ብሔሮች መካከል እንደሕዝብ ጠላት እንደከሃዲ ወይም እንደ ብልፅግና "ተከፋይ" ወይም "የአብይ ውታፍ ነቃይ" እየተፈረጀና እየተቆጠረ (በተቃራኒው የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ፣ የአስተሳሰቡ ተሸካሚ የ Stockholm syndrome ተጠቂ ዋና ካድሬዎቹ መወድስ እየቀረበላቸው) ፀረ-ወያኔ የሆኑ የቁርጥ ቀን ልጆች ግንየተለያዩ ታፔላዎች እየተለጠፈባቸው ስማቸው በመንጋ የጩኸት ዘመቻ እንዲጠፋ ያልተደረገ የምታውቁት ሰው ካለ ብትጠቁሙኝ ደስ ይለኛል።

በሆነ ምክንያትና ሰበብ ግለሰብ ተኮር የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ባልተጠና እና ባልተደራጀ መንገድ እንዲሁ የሚደረጉ ይመስላችሁኋልስ? በፍጹም አይደለም! ታስቦና ተጠንቶ ነው የስም ማጥፋት ዘመቻው የሚከፈተው።

ለወያኔ ጠላትና ስጋት የማይሆኑ ሰዎችን እንደ ሕዝብ ተቆርቋሪና ጀግና ሲቆጠሩ ግን አይተናል። የቱንም ያህል ግዘፍ-የሚነሳ ስህተት ቢሰራና በሕዝብ ጥቅም ቢደራደር ባላየና ባልተሰማ ይታለፋል እንጂ በተቀናጀ መንገድ ቀርቶ ከአዝማቾቹ ውስጥ አንድ ሰው ስሙን በክፉ አያነሳውም። ምክንያቱም ያ ሰው የወያኔና አጋሮቹ ስጋት አይደለማ! ያ ሰው ለወያኔ ናፋቂዎች አይጎረብጥማ!!

ቆም ብለን ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫ ለመመርመር እንሞክር‼️

በሁሉም አቅጣጫ ወያኔን የማትረፍ፣ አስተሳሰቡን የመመለስ፣ አጋርነትን የማሳየት አደገኛ የክህደት አሰላለፍ ጎልቶ ወጥቷል‼️

እነዚህ ከሃዲያን በቃ ሊባሉ እንጅ ምርኩዝ ልንሆንላቸው የሚገባ አይደለም‼️
ሺ ቢንጫጫ
በአንድ ሙቀጫ።

እንኳን ብአዴንነቱን ያስቀጠለው ብአዴን የሚለው አፍቃሬ ወያኔ ብአዴን ዋናውን ወያኔን አንበርክከነዋል። ለወያኔ መንገድ እየጠረገ ምንጣፍ የጎተተው የማደጎ ልጅ ሁሉ እንኳን የእኛን እጣፈንታ የራሱንም የመወሰን እድል አይኖረውም፤በምህረት አይናችን ካላየነው በስተቀር። አማራን አንገት ለማስደፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከመስራት የበለጠ የክህደት ወንጀል የሚልቅ ፈፅሞ የለምና‼️

ለማንኛውም የወያኔን ምንጣፍ ጎታቾችን ግብር ያወገዝነው(የገጠምነው) ካሸነፍን በኋላ እንጅ ገና ገጥመን ለማሸነፍ አይደለም‼️
እመኑኝ በአማራ ፖለቲካ ውስጥ በጭንብል ፈትፋች ከነበሩት ውስጥ በቅርቡ ራሳቸውን ገልጠው ቴዎድሮስ ፀጋዬን የሚያስንቁ ይሆናሉ። ጎጠኞችን አደራጅተው የእድሩን ጡሩንባ ሲያስነፉ የምናውቃቸው ሰዎች በግላጭ መጥተው ቀንና ሌት የእዬዬውን ጥሩንባ ይነፋሉ። እንዳትረሱት‼️
የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ አህመድ ላይ ማን ምን እንዳደረገና እንዲደረግ እንደሚፈልግ በዝርዝር እመጣበታለሁ። ለጊዜው በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንና በፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም በክልሉ ልዩሃይል የተቀናጀ አስደማሚ ስራ የታቀደው ሴራ ከሽፏል። በዚህ እኩይ ሴራ የተሳተፉና ለመሳተፍ የተንፈራገጡ በሶማሌ ክልል ያሉ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎችም በኩል ጃዝ ያሉ የወያኔ የግብር ልጆች ዋጋቸውን እንደሚያገኙ ለአፍታም ቢሆን በፍፁም አልጠራጠርም። እንደ አቧራ ይራገፋሉ። ይሰመርበት‼️

ከታላቁ የሶማሌ ሕዝብና መንግስት ጎን ነን‼️
በወያኔ አጀንዳ አቧራ ልታስነሳ ትችላለህ እንጅ የወያኔን አላማ ለመፈጸም የሚስችል የማድረግ አቅም የለህም። በጠላት ወያኔ በታቀደ መንገድ የተደረጉ የጥፋት ሙከራዎች ሁሉም እየከሸፉ ነው፣ ወደፊት ሊደረጉ የሚችሉት የጥፋት እቅዶችም ይከሽፋሉ። የወያኔ አጀንዳ አሻሻጮች በከፍተኛ ደረጃ ወደራሳቸው እየተኮሱ ነው። ውጤቱ ምን ይሆናል አብረን የምናየው ነው።
የእናት ጡት ነካሹ የባንዳ ቡድኑና የግብር ልጆቹ እናት ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሉ የሚባሉ ሁሉንም አማራጮች ለመጠቀም የቻሉትን ሁሉ እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጠላት ሁለንተናዊ ጦርነት ነው የከፈተው። ግንባር ላይ የነፍጥ ውጊያ ብቻ አይደለም እያደረገ ያለው። በተለያዩ አካባቢዎች በሳተላይት ድርጅቶቹና ግለሰቦቹ በኩል ተልዕኮ ሰጥቶ በሪሞት ግፎች እንዲፈፀሙ የልዩነት ስንጠቃዎች እንዲከናወኑ ሁሉንም ሙከራ አጠናክሮ ቀጥሏል።

እኩይ ምኞቱ በግብር ልጆቹ ተሳትፎ እስከምን ድረስ መጓዝ ይችላል የሚለውን ወደፊት አብረን የምናየው ሆኖ፤ሕልሙ ግን ከቀን ቅዥት እንደማያልፍ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

ጠላት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከውስጥና ከውጭ ተቀናጅቶ በከፈተው ሁለንተናዊ ጦርነት ላይ በሂደቱ ለጠላት አብረው ከጎኑ የተሰለፉ ሰዎች ሁሉ ታሪካቸውን በጥቁር መዝገብ ላይ ከማስፈር ያለፈ የማድረግ አቅም የላቸውምና ነገ ላይ ራሳቸውን ለትዝብት ይጥላሉ ብቻ ሳይሆን አወዳደቃቸውንም የከፋ ያደርጋሉ። በዘርህ አያድርስ በሚያሰኝ የታሪክ ቅሌት ውስጥ መሳተፍን መርጠዋልና‼️
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተከታይ እህቶቻችን በሚለብሱት አለባበስና ሥርዓት መንገድ ለብሳ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝታለች።

ይህን ያደረገችው ለቤተክርስቲያኗ ክብር ለመስጠት ካልሆነ እንደ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቷ ብቻ ሳይሆን የመንግስት ፕሮቶኮል አንፃር ካየነው ነጠላ ሳትለብስ የመገኘት መብቷ የተጠበቀ ነው። በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ ስለተነሳው ጉዳይ እንጅ ስለአለባበሷም የኦርቶዶክስ ተከታይ ትዕዛዝ የመስጠት የሞራልም ሆነ የሕግ ግዴታ የለባትም። የሕዝብን ጥያቄ የመመለስ ግዴታዋ እንደተጠበቀ ሆኖ።

በርግጥ በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ወያኔ መሩ ኃይል ነጠላ ለብሳ ብትመጣም ትናንት ካለው በተቃራኒ ዛሬ መልሶ ደግሞ ያንኑ አጀንዳ አንስቶ 'ነጠላውን ለማርከስ' ወይም 'ነጠላ በመልበስ አንታለልም' የታሰበማ ሴራ ቢኖር ነው ከማለት ወደኋላ የማይል ከራሱ ጋር የተጣላ ኃይል ነው።

በነገራችን ላይ አዳነች ላይ በኃይማኖት ሽፋን በነበረው ዘመቻ ከኦርቶዶክስ ኃይማኖት ውጭ ያሉ (በግብር ኦርቶዶክስ ያልሆኑ አላልኩም) ጭምር ናቸው አጀንዳውን ቀንና ሌሊት እየተቀባበሉ ሲያጮሁት የነበረው። የራሳቸውን ቤተክህነት ለማቋቋም ካሰቡት ጀምረው የወያኔ የሳይበር ሰራዊትም በሙሉ ባልተቀደሰ ጋብቻ ቁርኝት ፈጥሮ ለጥፋት ዘምቷል።

ይህ የሆነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተደረገው ጦርነት አዳነች አበቤ በጓዳም ሆነ በአደባባይ የጠራና ወጥ የሆነ የፀና አቋም ያሳየች የወያኔ የራስ ምታት የእግር እሳት መሆኗን በተግባር ስላረጋገጠች ነው። አዳነች በጦርነቱ ባሳየችው ትግል ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከታዩ ሴት ፖለቲከኞች ተስተካካይ የሌላት ያደርጋታል። ሀቁን መዋጥ ያስፈልጋል፣ የአማራ ፖለቲካ እንደእርሷ ብቃት ያለው ሴት አመራር የሚያወጣበት ጊዜ እጅግ ይናፍቀኛል፣ አዳነች አማራ ስላልሆነች አቅምና ችሎታዋን ለማድነቅ የምቸገር ሰው አይደለሁም ከወንድም የኦሮሞ ሕዝብ የተገኘች ፀረ-ወያኔ ምርጥ ኢትዮጵያዊት ነች።

በጦርነቱ ባሳየችው እጅግ አስደማሚ አቋምና እረፍት አልባ ትግል ወያኔ መሩ መንጋ በኃይማኖት ሽፋን በስሜት ቀስቅሶ በስማ በለውና በተዛባ መረጃ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተው የተበቀለ ስለመሰለውና ላልተጠናቀቀው ጦርነት ሕዝቡን በብሶት አጀንዳ ለማሳመጽ ካለው የፀና እምነት የተነሳ ነው። በደመነብስ ያለምንም መረጃ እንዲሁ መቃወም ስለተቻለ ብቻ ደግሞ እንደፈለገ 'አካኪ ዘራፍ' ያለው ሰው እልፍ ነው።

አሉ የሚባሉ ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙት በውይይት በሕግና ሥርዓት እንጂ በጩኸት ወለድ ግርግር ሀገር እንዲፈርስ በሚያደርግ የትርምስ መንገድ አይደለም። በዚህ መንገድ ከወያኔ በስተቀር የሚያተርፍበት አካል የለምና‼️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሀገር የገነባች በአፍሪካ ረዥም ዕድሜ ያላት ጥንታዊ ተቋም ነች። ዛሬ ፈተናዎች በዝተውባት ወያኔ መሩ ሊጠቀምባት ቢሞክርም ርግጠኛ መሆን የሚቻለው ቤተክርስቲያኗ ፈተናዎቿን በእውነተኛ ልጆቿ እና የኢትዮጵያን አንድነት በሚፈልጉ የመንግሥት አመራሮች ቀናነት በውይይት ሁሉም ይስተካከላል። በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትሪያሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የሰጡት መግለጫ የጠላትን ድብቅ ሴራ የሚያከሽፍ ነው።

የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተባበሩ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎችና የግብር ልጆቹ እኩይ ሴራ ሁሉ ይበጣጠሳል፤ በቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ከኢትዮጵያ ላይ የተጣበቁ መዥገሮች ሁሉ ተተልትለው ይራገፋሉ።
ነፍጣችንን አንስተናል‼️

ክብርና ምስጋና አማራ አንገት እንዳይደፋና ቀና ብሎ ይሄድ ዘንድ መስዋዕትነት ለከፈሉ በሙሉ ይሁን‼️
አንደኛው ክንፍ ይቀራል። እውነት ለመናገር በአንድ ቀን ልዩነት ውስጥ መሆኑ የብለን ነበር ፖለቲካውን ትንሽ አደብዝዞብኛል😂

የጩልሌዎቹን የመጫዎቻ ካርድ አስጨርሰን እኛ የከዘነውን ቴራ ባይት መረጃ ገና ሳንጠቀምበት ራሳቸውን ቀድመው በመግለጣቸው ከዚህ ቀደም እንዳልኩት የፎርፌ አሸናፊ ሊያደርጉን ነው። ምንም ማድረግ አይቻልም። አረፋ ማስደፈቁ ጭንብል ማስገለጡ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በመጨረሻም እንደ ስራቸው ፈታኝነት ታይቶ ካርዳችንን ልንጠቀምበት እንችላለን። እንጅ ቀድመን የነውረኝነት ካፒቴን ለመሆን አንሯሯጥም‼️
ትኩረታችንን ወያኔ ላይ እናድርግ። ወያኔ ላይ ትኩረታችንን እናድርግ ማለት ግን ነፍጥ ያነሳውን ትግረኛ ተናጋሪን ብቻ ማለት ሳይሆን የግብር ወራሾቹም ላይ ጭምር ማለታችን ነው። የነቃ የተደራጀና ታጥቆ የፀና ሐይል ያሸንፋል‼️
የአሸናፊነትና የከፍታ ምልክት‼️

እንኳን ደስ አለን!
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአሸናፊነትና የከፍታ ምልክታችን ነው‼️
ደቂቀ ወያኔዎች ወደእኛ የመሮጫ መም ከመግባት አልፈው ድንገት በውድድሩ መካከል ከተደበቁበት የተሳዳቢዎች መቀመጫ ነውር ትሪቡን ዘለው ገብተው ዙሩን አክርረውታል። አንዳንዶቹ ወደትክክለኛው የውድድሩ ሜዳ መግባታቸው የሚያስደስት ቢሆንም (የስውን ውድቀት ስለማንመኝ) ድንገት ገብተው የወርቅ ሜዳሊያውን መንገድ ዘግተው በማደናገር እንዳይወስዱት ቆመን መጠበቅ የለብንምና ፍጥነታችንን ጨምረን መሮጥ ይጠበቅብናል። ለማንኛውም የውድድሩን ሕግ ጠብቆ ያልሮጠ ሜዳሊያውን ስለማያጠልቅ በቀጣይ ጊዜ ህግ እና ስርዓቱን አክብራችሁ ተመዝግባችሁ ሩጫውን ከመነሻው እንድትጀምሩ እናሳስባለን። መልካም ውድድር😂