Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.41K subscribers
2.98K photos
371 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
በእኔና የቁርጥ ቀን ወዳጆቼ እምነት ወያኔ የአማራና የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካ ቀንደኛ ጠላት ነው። በግጭት ተጠንስሶ በግጭት ያደገ፤ ግጭትን የህልውናው ማስቀጠያ ያደረገ ቀውስ ጠማቂ ድርጅት ነው። ሰምሮለት ቀላል ግምት የማይሰጠው የግብር ልጆች አፍርቷል። ሲያሻቸው ግጭትን መጦሪያቸው የሚያደርጉ፣ አልያም ደግሞ በገዛ ወገናቸው ደም ቁማር ሰርተው ለግብር አባታቸው መንገድ የሚጠርጉ አሉ።

በወያኔ እብደት በተለኮሰው ጦርነት ጥቅምት 24 በጀመረው ሕግ የማስከበር ዘመቻም ሆነ በሰኔ/2013 የወያኔ የጦር ወረራ (war of aggression) ዝንተ-ንቡር የሆነውን ጠላታችን ጨርሶ ወደመቃብር ለማውረድ ጊዜው አሁን ነው በሚል የአሸናፊነት መንፈስ ተነሳስተን እኔና ወንድሞቼ የምንችለውን አድርገናል። ያለማጋነን የወያኔ መጥ*ፋት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ኮንጎ ድረስ የዘለቀ የሰላም ትርጉም ይኖረዋል ብለን እናምናለን። በዚህ እምነት ነበር የዘመትነው። እዚህ ላይ የኔንም ሆነ የወዳጆቼን ገድል ለመዘርዘር አይደለም። ተፈጥሮዬ እንደዛም አይደለም። በሂደቱ ያስተዋልኳቸው፣ ያየኋቸው አስደንጋጭ ነገሮች እንደአስፈላጊነታቸው ለሕዝብ በተለይም ለወጣቱ መማሪያ ይሆን ዘንድ መነገር ባለበት ልክ መነገር ግን ይኖርበታል። "ያየነውን እንመሰክራለን የሰማነውን እንናገራለን" እንዲል መፅሐፍ ወደፊት ስለነበረው ስለምናውቀው ነገር ሁሉ በመፅሐፍ መልክ የምንከትበውም ይሆናል።

በአማራ ስም ምለው ሲገዘቱ ውለው የሚያድሩ በተግባር ግን የአማራ ጥንተ-ጠላት የሆነው ወያኔን መርዛማ አስተሳሰብ የተሸከሙ የወያኔ የግብር ልጆች ራቁታቸውን ማስጣት ይገባል። ይህን ማድረግ መቻል የሕልውና ስጋት አለበት ብለን ለምናምነው አማራ ትልቅ የመፍትሔ እርምጃ ይሆናልና።

ወያኔ በሕዝባችን ላይ የጦር ወረራ መፈፀም ከጀመረ በኋላ በተለይም በወሎ በኩል ገፍቶ ሲመጣ ወደ ደሴ እንዳንሄድና ከሄድነም በኋላ "በተቆርቋሪነት" ስሜት ስልክ እየደወሉ በሰው በኩልም :-

"ለዚህ ሁሉ ያበቃን አብይ አህመድ ነውና ወያኔ ሲፈልግ እንኳን ደሴ ለምን አዲስ አበባ አይገባም?"

"እናንተን እንፈልጋችኋለን፤ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳትከፍሉ። አርፋችሁ ተቀመጡ፤ አትድከሙ።"

ከማለት አልፈው ደሴ ላይ ብቻ ሳይሆን በጎንደር ማይጠብሪ ግንባርም እኛን ለማስ*ገደል ሞክረው ያልተሳካላቸው በሚኒስትርና በክልል ቢሮ ኋላፊ ደረጃ ያሉ የወያኔ መንገድ ጠራጊ ምንጣፍ ጎታቾች ነበሩ።

እነዚህ የአማራ ቡግንጆች በቅርቡ በወያኔ አጀንዳ አስፈፃሚው በEthio-360 በሚባለው የዩቲዩብ ሚዲያና የወያኔ አጀንዳ በሚያሻሽጡት የፌስቡክ ጦረኞች በኩል በይፋ መወድስ ቀርቦ አልመለከትም ብዬ እርግጠኛ ለመሆን ግን አልደፍርም። ኢትዮጵያን ሊያፈርስ፣ አማራን ሊያጠ*ፋ፣ የመጣን ዝንተ-ጠላት የሆነው ወያኔ አሸናፊ እንዲሆን ስትራቴጂያዊ ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩ፣ በአመራር ድጋፍ ስም የሚያገኙትን መረጃ ለሦስተኛ ወገን አሳልፈው በመስጠት በገዛ ሕዝባቸው ደም ከጠላት ጋር ያበሩ፣ ሰራዊቱን ለመበተን ያሴሩ፣ጉግማንጉጎች ለአይናችን እድሜ ይስጠን እንጅ የሕዝብ ልጅ ተደርገው ሊቀርቡ ይችላሉ። የወያኔና የአሰተሳሰቡ ተሸካሚዎች ፍላጎት አማራን ማሳነስ በገዳዮቹ እንዲወከል ማድረግ ነው። እድሉን ካልተነፈጉ በስተቀር የበርባን ጠበቃዎች ገና ብዙ ጉድ አያሰሙንም ብሎ መተማመን ፈፅሞ አይቻልም።

በዚህ ሁሉ የታሪክ ቅሌት ውስጥ አንድ ወሳኝ እውነታ መኖሩን ግን ሁሉም ሰው ያስምርበት። የእኛን ወደወሎ ግንባር መዝመት አይናቸውን ያቀላው፣ ባለመሰዋታችን የተነሳ ብቻ ጥርሳቸውን ያፋጩ፣ ከንፈራቸውን የነከሱና አሉባልታ ያናፈሱ የወያኔ መንገድ ጠራጊ አመራሮችና በእነሱ ስር ስምሪት የተሰጣቸው አክቲቪስቶች የመኖራቸውን ያህል፣ በሕልውና ጦርነቱ ከያዝነው አቋም ከምንሰራው የሥነ-ልቦና ግንባታና ከእኛ ለሚጠበቀው መሬት የነካ ያልተቆጠበ ጥረትና እንቅስቃሴ በወቅቱ ስልክ ደውለው ያመሰገኑን ያልጠበኳቸው ከሚኒስተር ጀምሮ የሌሎች ክልሎች ባለስልጣናት ጭምር አሉና ከራሳቸውን አልፈው ስለሀገር ለሚጨነቁ ሰዎች ስንል ነገሮችን ለማስከን ሞክረናል እንጅ የእያንዳንዱን ገመና የሀገር ክህደት እንደብቅል ማስጣት፣ አመድ አቡናኞችን በግልጽ ማራገፍ የማያስችል ቁመና አስፈላጊ መረጃ ስለሌን አይደለም።

ያልተሰነድ ነገር የለም‼️
ታሪክ ይፍረደን ብለን አንተወውም፣ ፍርድ እናውቃለንና‼️
"ወያኔ የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ዋና ጠላትና ስጋት ነው" ስል አንተ ብልፅግና የአብይ አህመድ ውታፍ ነቃይ የሚሉኝን አማርኛ ተናጋሪ ሰዎችን ከትግርኛ ተናጋሪ የሕወሓት ሰዎች በምን ልለያቸው? ተደናጊረ😂
ከቋንቋ በስተቀር እኮ ፍፁም የግብር ልዩነት የላቸውም። ወያኔ የሚወደውን የሚወዱ የሚጠላውን የሚጠሉ ናቸው።
በሱዳን ውስጥ ራሳቸውን እንደነፃ አውጭ እንዲቆጥሩ ተደርገው በወያኔ መልማይነትና ስምሪት ሰጭነት በእነ ግብፅና የሱዳን መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ ስልጠናቸውን የጨረሱና እየጨረሱ የሚገኙ ሃይሎች ከውስጥ በኩል ካለው የእናት ጡት ነካሹ ወያኔና የግብር ልጆቹ ጋር በማቀናጀት በሱዳን ጦር መሪነት በተለያዩ ግንባሮች ሰፊ የማጥቃትና የወረራ ዘመቻዎችን ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ስለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ስለሆነም በወገን በኩል ለእነዚህ የጥፋት ሃይሎች የተቀናጀ የወረራ ዘመቻን በብቃት ለመመከት በሚያስችል ቁመና ላይ ስለመገኘታችን ራሳችንን ልንፈትሽና ከበቂ በላይ የሆነ ሁለንተናዊ ከፍተኛ ዝግጅት ከወዲሁ ልናደርግ ይገገባል። የደረጀና የተደራጀ በአንድ ዕዝ ስር የሚመራ፣ ዲስፕሊንድ የሆነ፣ ኮዝ ያለው አንድ ጠንካራ ሃይል የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ መገንባት ያስፈልጋል። በሐገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በዝርው የሚልከሰከሰውንና የሚንቀሳቀሰውን የተበጣጠሰ ታጣቂንም ወደአንድ ዕዝ በመሰባሰብ በስርዓት እንዲመራ በማድረግ አቅምን ማጎልበት ይገባል።

የወያኔ ሕልውና እስካለ ድረስ የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እረፍት ያገኛል ተብሎ አይታሰብም። የሚያስብ ሰው ካለ አንድም የወያኔ የአላማው ተጋሪ የሆነ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የወያኔን ተፈጥሯዊ ስሪት፣ ከጀርባ የተሰለፉትን የውጭ ሃይሎችን አላማንና ከፊት የሚያሰማራቸውን የግብር ልጆቹን ነገረ-እንቅስቃሴ በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ነው። ሰይጣን ራሱን ብርሃናዊ መላእክት አስመስሎ ማቅረብ ይችላል እንጅ ብርሃን መሆን እንደማይችልም ሊታወቅ ይገባል። ወያኔ በግጭት ተወልዶ በግጭት ያደገና ያለግጭት ሕልውና የሌለው ፀረ-አማራ ወይም ፀረ-ኢትዮጵያ ሳይሆን ፀረ-ሰውነት የሆነ አሸባሪ ሃይል ነው።

ይህ ዘላለማዊ ደመኛ የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ቀንደኛ ጠላት የካቲት 11 የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ከውጭ በኩል ካለው የጥፋት ሃይሎች ጋር በመቀናጀት የተለያዬ ስያሜዎችን ሰጥቶ በተለያዩ ግንባሮች በአዲስ መንገድ ከፍተኛ የወረራ ዘመቻ ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ ነው።
በዚህ የካቲት 11 የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ሊፈፅማቸው ላሰባቸው የወረራ ዘመቻዎች ጉልበት ይሆኑት ዘንድ አስቀድሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ትኩረት ለማስቀየርና ሕዝቡን ወደምሬት ይቀይርልኛል ያላቸውን ቁጣ ቀስቃሽ ጥፋቶችን በተለያዩ አካባቢዎች ቀድሞ ባደራጃቸውና ባቋቋማቸው አሁንም ያለማቋረጥ ድጋፍ በሚያደርግላቸው ጉዳይ ፈፃሚ የሳተላይት ድርጅቶችና ግለሰቦች በኩል ከፍተኛ ግፎችን በማስፈፀም ላይ ነው።

የምንሰማቸውን ሕዝባዊ ቁጣ ቀስቃሽ አጀንዳዎችን የጥቅምት 24 የሰሜን ዕዝ ጥቃት ከመፈፀሙ በፊት እና በተመሳሳይ የዛሬ አመት በዚህ ወቅት በምዕራባዊያኑ በረቀቁ የቴክኖሎጅ ውጤት በሆኑ መሳሪያዎች ፣በዲፕሎማሲና በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ በሚደረግለት ድጋፍና በሕዝባዊ ማዕበል ከቆላ ተንቤን ለመውጣት ከፍተኛ የሆነ የተቀናጀ እንቅስቃሴ በጀመረበት ወቅት እናያቸው የነበሩ ጉልበት ሰጭ የአመፃ ምልክቶችን ናቸው።
ጊዜዎቹንና ሕዝባዊ አመፅ ሊቀሰቅሱ የሚችሉ አጀንዳዎቹን ወደኋላ ተመልሶ ማየትና ነገሮችን ለመመርመር እንሞክር። ወያኔ ምን ያህል በተጠና በታቀደና በተናበበ መንገድ ከሚያደርገው የትጥቅ ትግል ጋር የሚመጋገብ ጉልበት ሰጭ የጥፋት አላማውን ለማስፈፀም እንደሚሰራ ማየት እንችላለን።

ከጥቅምት 24 በፊት የነበረውን አልፈን ባለፈው አመት በያዝናቸው ወራቶች ይፈፀሙና ይራገቡ የነበሩ ወደሕዝባዊ አመፅ የሚወስዱ አጀንዳዎችን ብቻ ተመልሰን ማየት ብቻውን ብዙ ነገሮችን ይገልጥልናል። የዛሬውንም ሁኔታ ለመረዳት ያግዘናል። በወቅቱ በትግራይ ክልል በተለያዩ የዘመቻ ስያሜዎች በከፍተኛ ሁኔታ ወያኔ ከተንቤን ለመውጣት መንቀሳቀስ የጀመረበት ጊዜ ነበር። በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት በመፍጠር ግፍ እንዲፈፀም በማድረግ ሕዝባዊ አመፅ አስነስቶ፣ የሐገሪቱ የፀጥታ ሃይል ትኩረት ለመበታተን ልክ እንደሰሞኑ አይነት የትኩረት ማስቀየሻ፣ ሕዝባዊ አመፅ መቀስቀሻ እኩይ አጀንዳዎችን በመቅረፅ በሳተላይት ድርጅቶችና ግለሰቦች በኩል አላማውን ለማስፈፀም ያላደረገውና ያልሆነውን ነገር መርምሮ ማግኘት ይከብዳል። በሚያስፈፅመው ግፍ በሚያስነሳው ግጭት ሕዝባዊ አመፅ ማስነሳት የሐገሪቱን የፀጥታ ሃይሎችን ትኩረት መበታተን እንኳን ባይችል ትኩረቱን ከእሱ እንዲነሳ አድርጎ በኢትዮጵያዊያን መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር በማድረግ አንድነታቸውን ለማዳከም ወደጦሩም አዝልቆ የቀዘቀዘ የመዋጋት ሞራል እንዲኖረው ወደማድረግና ዋና ጠላትነቱን ወደሌላ አካል እንዲዞር የማድረግ ተፅዕኖ አይኖረውም ብሎ የሚናቅ ጉዳይ ግን አይሆንም።
ስለሆነም የወረራ ዘመቻ ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ላለው ወያኔ ጉልበት ሊሆኑ የሚችሉ አጀንዳዎችን ከማሰራጨት ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል። ትኩረታችንን ከዋና ጠላታችን ላይ ለአፍታም ቢሆን ልናነሳ አይገባም‼️

አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅትም ቀድመን ልናደርግ ይገባል‼️
በፍንጃል ሲጠነቁሉበት ሳይሆን ቡና ሲጠጡበት እርካታን ይፈጥራል!

ሰናይ ቅዳሜ!
ከፍተኛ ጥንቃቄና ዝግጅት እናድርግ። ጠላት የካቲት 11 የምስረታ በዓሉን ከፍተኛ የወረራ ዘመቻ በማድረግ ራያና ወልቃይት ላይ አከብራለሁ ብሎ አሮጌ ከበሮውን እየደለቀ ይገኛል። ወደግንባሮቹ ተጨማሪ ሃይል እያስጠጋም ነው።
በወገን በኩል የትም እንደማይደርስ አስበን ጠላትነቱን ከማሳነስ ይልቅ ከውጭ እየመራ አስከትሏቸው ለሚመጣው ሃይል ጭምር ትልቅ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ የሚባለውን ሁሉ ሁለንተናዊ ዝግጅት አላስፈላጊ መስዋዕትነት ላለመክፈል ቀድመን ልናደርግ ይገባል። ታሪክ እስካልሆነ ድረስም ረፍት ሊሰጥ የማይችል ሕልውናውን በግጭት ላይ የመሰረተ ሃይል መሆኑን አለመርሳትም ተገቢ ነው።
የብልፅግና ጠቅላላ ጉባኤ የሚካሄድበት ተጨማሪ ቀን ካለው በብልፅግና ውስጥ ብአዴንነታችሁን ያስቀጠላችሁ ወያኔን መንገድ እየጠረጋችሁና እየመራችሁ አዲስ አበባ ለማስገባት ባለ በሌለ አቅማችሁ የሰራችሁ ያልበለፀጋችሁ አፍቃሬ-ወያኔዎች፣ በአቅም ማነስ ከስልጣን እንነሳለን፣ በወንጀል እንጠየቃለን ብላችሁ ትልቅ ስጋት አድሮባችሁ ከሆነ በመንጋ የጀግንነት ካባ ሽልማት የሚሰጥበት ጊዜው አሁን ነውና ሳያልፍባችሁ ትጠቀሙበት ዘንድ እንመክራለን።

ከስልጣን ስለተነሳ፣ አቅም ስለሌለህ፣ በወንጀል የተጠያቂነት ስጋት ስላለብህ፣ ወያኔን መንገድ እየጠረግህ መንገድ እየመራህ ስለመቆየትህ፣ እስከዛሬስ ግፎች ሲፈፀሙ ወይም ሕግ-ሲጣስ የት እንደነበርክ፣ ዛሬ እንድትናገር ያደረገህ ምን እንደሆነና ምንስ እንደተናገርክ ጠይቆ የሚቃወምህ ሰው ከንፍሮ ጥሬ ስለሆነ ሳይረፍድባችሁ ወቅቱን ለመጠቀም መሯሯጥ ይገባችኋል።

ኑ እናንተ የተጠያቂነት ስጋት ያለባችሁ ብአዴንነታችሁን ያስቀጠላችሁ በብልፅግና ውስጥ ያላችሁ ያልበለፀጋችሁ አፍቃሬ ወያኔዎች፣ ከያላችሁበት ውጡና መድረኩን በእዬዬ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ሞክሩ። በዚህ ጩኸት በበረከተበትና ግርግር በበዛበት አንድ ብቻ አይደለም ሺ ጀግና በመንጋ ጩኸት መፍጠር በሚቻልበት ወሳኝ የታሪክ መታጠፊያ ወቅት ወደፊት መጥቶ እድሉን አለመጠቀም ሞኝነት ነውና እንደምንም ብላችሁ ተጠቀሙበት። የጀግንነት ካባውን ለጊዜው ለመደረብ ሞክሩ እንጅ ጀግንነቱ ስለመፅናቱ ደግሞ ቀጣዩ የታሪክ ምዕራፍ የሚናገረው ይሆናል።

በመጨረሻም በብልፅግና ውስጥ ስላለው ብአዴንነቱን ስላስቀጠለው አፍቃሬ ወያኔ ይህን ካልኩ በኋላ ቅን ለሆኑ ወገኖችን ግን
እናንተ ለሕዝብ ተቆርቋሪ የሆናችሁ ወገኖች ሆይ! አንድን ጉዳይ ወይም አጀንዳ ከመጋራታችን በፊት ስለጉዳዩ ነገሮችን ከተለያዬ አቅጣጫዎች ለመመርመር መሞከርና በቂ መረጃና ማስረጃ መሰብሰብ አልፎም ተንትኖ አቋም መያዝ ነገ ላይ ቀድመው የተነሱት ጉዳዮች ምንነት ሲገላለጥ ባደረግነው ነገር እንዳናፍርና አላስፈላጊ መስዋዕትነትም እንዳንከፍል ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።
በተመለደው የስማ በለው በስሜት ፈረስ እየጋለቡ የስድብ፣ የእርግማን ናዳ ማውረድ ቀላል ነገርም ይሆናል ነገ ላይ ግን ራሳችንን ለትዝብት ከመጣልና አላስፈላጊ ዋጋ ነገ ላይ ከማስከፈል ውጭ አንዳችስ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደማንችል ግን ሊሰመርበት ይገባል።
በሕዝብ ተቆርቋሪነት ጭምብል ብልፅግናን ሲራገሙና ሲሳደቡ ውለው የሚያድሩ ሰዎችን ነገረ-ስራ ብንመረምር አብዛኞቹ የብልፅግና ተቃዋሚ የሚመስሉት በብልፅግና ውስጥ በብአዴንነቱ ከቀጠለው አፍቃሬ ወያኔው(ወንጀለኛ፣ አቅመ-ቢስ፣ ከስልጣን ከተነሳውና የመነሳት ስጋት ካለበቱ፣ ከወያኔ መንገድ ጠራጊና ምንጣፍ ጎታቹ) ሃይል ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሲሰሩና ሲላላኩ የምናገኛቸው በነውር ያጌጡ ሰዎች ሆነው እናገኛቸዋለን።

ለሕዝብ ጥቅም በሕዝብ ስም ሲጯጯሁ ወይም እንታገላለን ሲሉ ሊሰማ ይችላል እንጅ አላማቸው ብአዴንነትን ለማስቀጠል ያለእረፍት በወያኔ ግብር የደመቁና የሞራልን ዋጋን የማያዉቁ ሰዎች ናቸው። ከበስተቀሮች ውጭ!
"ቁጥቋጦዎች እንዲነግሱ የግድ ዋርካዎች ይገንደሱ" የሚሉ የእንባጮ ስር ተሰብሳቢ መካሪዎችን ወሬ መቼም ቢሆን ተግባራዊ እንዲሆን እድል አንሰጠውም‼️
ማንነቱን ደብቆ ከሚጠቀም የፌስቡክ ተጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ በአቋማቸው ባልስማማም እንኳን ሁለት ሰዎችን ብቻ አልነቅፍም። አጀንዳቸው ፍፁም ግለሰብ ተኮርና ነውረኝነት የሚንፀባረቅበት አይደለም። ከዚህ ውጭ ጓደኛዬ የሆነ የፌስቡክ ፌክ አካውንት ተጠቃሚ ጓደኛዬ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ግለሰብን ከመስደብና ከመራገም ያለፈ ቁምነገር ያለው አይደለምና ብሎክ እያከናነብኩት እገኛለሁ። በነገራችን ላይ በዚህ አጋጣሚ ማንነቱን ደብቆ ከሚፅፍ ፌስቡከር ውስጥ ፍፁም ትህትና ያለው አጀንዳው ከግለሰብ ወጥቶ ስለሕዝብ ሕልውናና ጥቅም የሚቆረቆር ካለ በዚህ አጋጣሚ እንድትጠቁሙኝ እፈልጋለሁ። እስካሁን ማንነቱን ደብቆ(በአካል በፍፁም የማይታወቅ አልፎም ዘሩ የማይታወቅ) ከምታውቁት የፌስቡክ ተጠቃሚ ውስጥ አጀንዳው ሕዝባዊና ለችግሮች መፍትሔ በማቅረብ የምታውቁት ሰው ካለ ጠቁሙኝ። በፍጹም የማውቀው አንድስ እንኳን ሰው ስለሌለ ነው። በእርግጥ የሚታወቅ ማንነት ኖሯቸው ማንነቱ ከማይታወቀው ከተደበቀው አፍቃሬ ወያኔን የሚያስንቁ ሰዎች የሉም እያልኩ አይደለም።
በነገራችን ላይ በአማራ የብሔርተኝነት ፖለቲካ ውስጥ ማንነታቸውን ደብቀው የሚፅፉ ሰዎች ማንነታቸውን ገልፀው በሚፅፉ ሰዎች ላይ አንተ ባንዳ ብልፅግና የአብይ ውታፍ ነቃይ ምናምን እያሉ እንደሚፅፉ ሰዎች ሞራል ያለው ማንነታቸውን የገለጡ የተጣራ መረጃ ያላቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን?
ማንነታቸውን ደብቀው እንደሚፅፉ ሰዎች ማንነታቸውን ገልጠው የሚፅፉ ሰዎችን ነፃነት ለመቀማት የሚሰራ የለም። ማንነታቸውን ደብቀው የሚፅፉ ሰዎችን መንጋው የሚያውቃቸው ብቻ ሳይሆን የማያውቀውን ንግግርና ፅሑፍ የማመን ባሕል እንዳለው ከዚህ በፊት ስለተረዳ አፍቃሬ ወያኔ መድረኩን እንደፈለገ እንዲፈነጭበት እድል ሰጥቶታል።ይህ ሁሌም ያበሳጨኛል።እረፍትም ይነሳኛል።
በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥም ሆነ በተቃዋሚው ጎራ ተሰልፈው ወያኔን ከአራት ኪሎ ወደመቀሌ እንዲመሽግ ካደረጉትና ከለውጡ በኋላም ወያኔ ወደመሀል ፖለቲካው እንዳይመለስ በሀሳብና በተግባር የታገሉ ድንቅ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አሉ።

ምንም እንኳን ወያኔን ወደመቀሌ እንዲመሽግ ማድረግ የተቻለ ቢሆንም ለኢትዮጵያ አሁናዊና ዘላለማዊ የደረጀና የተደራጀ እንደ ወያኔ ያለ ዋና ጠላትና ስጋት የለም ያሉና በፀና አቋማቸው በቻሉት ልክ ወጥረው ሲታገሉ ከነበሩ ጠንካራ የአማራ ልጆች አልፎም 'ኢትዮጵያኒስት' ከሆኑ ከሌሎች ብሔሮች መካከል እንደሕዝብ ጠላት እንደከሃዲ ወይም እንደ ብልፅግና "ተከፋይ" ወይም "የአብይ ውታፍ ነቃይ" እየተፈረጀና እየተቆጠረ (በተቃራኒው የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ፣ የአስተሳሰቡ ተሸካሚ የ Stockholm syndrome ተጠቂ ዋና ካድሬዎቹ መወድስ እየቀረበላቸው) ፀረ-ወያኔ የሆኑ የቁርጥ ቀን ልጆች ግንየተለያዩ ታፔላዎች እየተለጠፈባቸው ስማቸው በመንጋ የጩኸት ዘመቻ እንዲጠፋ ያልተደረገ የምታውቁት ሰው ካለ ብትጠቁሙኝ ደስ ይለኛል።

በሆነ ምክንያትና ሰበብ ግለሰብ ተኮር የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ባልተጠና እና ባልተደራጀ መንገድ እንዲሁ የሚደረጉ ይመስላችሁኋልስ? በፍጹም አይደለም! ታስቦና ተጠንቶ ነው የስም ማጥፋት ዘመቻው የሚከፈተው።

ለወያኔ ጠላትና ስጋት የማይሆኑ ሰዎችን እንደ ሕዝብ ተቆርቋሪና ጀግና ሲቆጠሩ ግን አይተናል። የቱንም ያህል ግዘፍ-የሚነሳ ስህተት ቢሰራና በሕዝብ ጥቅም ቢደራደር ባላየና ባልተሰማ ይታለፋል እንጂ በተቀናጀ መንገድ ቀርቶ ከአዝማቾቹ ውስጥ አንድ ሰው ስሙን በክፉ አያነሳውም። ምክንያቱም ያ ሰው የወያኔና አጋሮቹ ስጋት አይደለማ! ያ ሰው ለወያኔ ናፋቂዎች አይጎረብጥማ!!

ቆም ብለን ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫ ለመመርመር እንሞክር‼️

በሁሉም አቅጣጫ ወያኔን የማትረፍ፣ አስተሳሰቡን የመመለስ፣ አጋርነትን የማሳየት አደገኛ የክህደት አሰላለፍ ጎልቶ ወጥቷል‼️

እነዚህ ከሃዲያን በቃ ሊባሉ እንጅ ምርኩዝ ልንሆንላቸው የሚገባ አይደለም‼️
ሺ ቢንጫጫ
በአንድ ሙቀጫ።

እንኳን ብአዴንነቱን ያስቀጠለው ብአዴን የሚለው አፍቃሬ ወያኔ ብአዴን ዋናውን ወያኔን አንበርክከነዋል። ለወያኔ መንገድ እየጠረገ ምንጣፍ የጎተተው የማደጎ ልጅ ሁሉ እንኳን የእኛን እጣፈንታ የራሱንም የመወሰን እድል አይኖረውም፤በምህረት አይናችን ካላየነው በስተቀር። አማራን አንገት ለማስደፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከመስራት የበለጠ የክህደት ወንጀል የሚልቅ ፈፅሞ የለምና‼️

ለማንኛውም የወያኔን ምንጣፍ ጎታቾችን ግብር ያወገዝነው(የገጠምነው) ካሸነፍን በኋላ እንጅ ገና ገጥመን ለማሸነፍ አይደለም‼️
እመኑኝ በአማራ ፖለቲካ ውስጥ በጭንብል ፈትፋች ከነበሩት ውስጥ በቅርቡ ራሳቸውን ገልጠው ቴዎድሮስ ፀጋዬን የሚያስንቁ ይሆናሉ። ጎጠኞችን አደራጅተው የእድሩን ጡሩንባ ሲያስነፉ የምናውቃቸው ሰዎች በግላጭ መጥተው ቀንና ሌት የእዬዬውን ጥሩንባ ይነፋሉ። እንዳትረሱት‼️
የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ አህመድ ላይ ማን ምን እንዳደረገና እንዲደረግ እንደሚፈልግ በዝርዝር እመጣበታለሁ። ለጊዜው በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንና በፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም በክልሉ ልዩሃይል የተቀናጀ አስደማሚ ስራ የታቀደው ሴራ ከሽፏል። በዚህ እኩይ ሴራ የተሳተፉና ለመሳተፍ የተንፈራገጡ በሶማሌ ክልል ያሉ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎችም በኩል ጃዝ ያሉ የወያኔ የግብር ልጆች ዋጋቸውን እንደሚያገኙ ለአፍታም ቢሆን በፍፁም አልጠራጠርም። እንደ አቧራ ይራገፋሉ። ይሰመርበት‼️

ከታላቁ የሶማሌ ሕዝብና መንግስት ጎን ነን‼️
በወያኔ አጀንዳ አቧራ ልታስነሳ ትችላለህ እንጅ የወያኔን አላማ ለመፈጸም የሚስችል የማድረግ አቅም የለህም። በጠላት ወያኔ በታቀደ መንገድ የተደረጉ የጥፋት ሙከራዎች ሁሉም እየከሸፉ ነው፣ ወደፊት ሊደረጉ የሚችሉት የጥፋት እቅዶችም ይከሽፋሉ። የወያኔ አጀንዳ አሻሻጮች በከፍተኛ ደረጃ ወደራሳቸው እየተኮሱ ነው። ውጤቱ ምን ይሆናል አብረን የምናየው ነው።
የእናት ጡት ነካሹ የባንዳ ቡድኑና የግብር ልጆቹ እናት ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሉ የሚባሉ ሁሉንም አማራጮች ለመጠቀም የቻሉትን ሁሉ እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጠላት ሁለንተናዊ ጦርነት ነው የከፈተው። ግንባር ላይ የነፍጥ ውጊያ ብቻ አይደለም እያደረገ ያለው። በተለያዩ አካባቢዎች በሳተላይት ድርጅቶቹና ግለሰቦቹ በኩል ተልዕኮ ሰጥቶ በሪሞት ግፎች እንዲፈፀሙ የልዩነት ስንጠቃዎች እንዲከናወኑ ሁሉንም ሙከራ አጠናክሮ ቀጥሏል።

እኩይ ምኞቱ በግብር ልጆቹ ተሳትፎ እስከምን ድረስ መጓዝ ይችላል የሚለውን ወደፊት አብረን የምናየው ሆኖ፤ሕልሙ ግን ከቀን ቅዥት እንደማያልፍ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

ጠላት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከውስጥና ከውጭ ተቀናጅቶ በከፈተው ሁለንተናዊ ጦርነት ላይ በሂደቱ ለጠላት አብረው ከጎኑ የተሰለፉ ሰዎች ሁሉ ታሪካቸውን በጥቁር መዝገብ ላይ ከማስፈር ያለፈ የማድረግ አቅም የላቸውምና ነገ ላይ ራሳቸውን ለትዝብት ይጥላሉ ብቻ ሳይሆን አወዳደቃቸውንም የከፋ ያደርጋሉ። በዘርህ አያድርስ በሚያሰኝ የታሪክ ቅሌት ውስጥ መሳተፍን መርጠዋልና‼️
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተከታይ እህቶቻችን በሚለብሱት አለባበስና ሥርዓት መንገድ ለብሳ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝታለች።

ይህን ያደረገችው ለቤተክርስቲያኗ ክብር ለመስጠት ካልሆነ እንደ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቷ ብቻ ሳይሆን የመንግስት ፕሮቶኮል አንፃር ካየነው ነጠላ ሳትለብስ የመገኘት መብቷ የተጠበቀ ነው። በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ ስለተነሳው ጉዳይ እንጅ ስለአለባበሷም የኦርቶዶክስ ተከታይ ትዕዛዝ የመስጠት የሞራልም ሆነ የሕግ ግዴታ የለባትም። የሕዝብን ጥያቄ የመመለስ ግዴታዋ እንደተጠበቀ ሆኖ።

በርግጥ በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ወያኔ መሩ ኃይል ነጠላ ለብሳ ብትመጣም ትናንት ካለው በተቃራኒ ዛሬ መልሶ ደግሞ ያንኑ አጀንዳ አንስቶ 'ነጠላውን ለማርከስ' ወይም 'ነጠላ በመልበስ አንታለልም' የታሰበማ ሴራ ቢኖር ነው ከማለት ወደኋላ የማይል ከራሱ ጋር የተጣላ ኃይል ነው።

በነገራችን ላይ አዳነች ላይ በኃይማኖት ሽፋን በነበረው ዘመቻ ከኦርቶዶክስ ኃይማኖት ውጭ ያሉ (በግብር ኦርቶዶክስ ያልሆኑ አላልኩም) ጭምር ናቸው አጀንዳውን ቀንና ሌሊት እየተቀባበሉ ሲያጮሁት የነበረው። የራሳቸውን ቤተክህነት ለማቋቋም ካሰቡት ጀምረው የወያኔ የሳይበር ሰራዊትም በሙሉ ባልተቀደሰ ጋብቻ ቁርኝት ፈጥሮ ለጥፋት ዘምቷል።

ይህ የሆነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተደረገው ጦርነት አዳነች አበቤ በጓዳም ሆነ በአደባባይ የጠራና ወጥ የሆነ የፀና አቋም ያሳየች የወያኔ የራስ ምታት የእግር እሳት መሆኗን በተግባር ስላረጋገጠች ነው። አዳነች በጦርነቱ ባሳየችው ትግል ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከታዩ ሴት ፖለቲከኞች ተስተካካይ የሌላት ያደርጋታል። ሀቁን መዋጥ ያስፈልጋል፣ የአማራ ፖለቲካ እንደእርሷ ብቃት ያለው ሴት አመራር የሚያወጣበት ጊዜ እጅግ ይናፍቀኛል፣ አዳነች አማራ ስላልሆነች አቅምና ችሎታዋን ለማድነቅ የምቸገር ሰው አይደለሁም ከወንድም የኦሮሞ ሕዝብ የተገኘች ፀረ-ወያኔ ምርጥ ኢትዮጵያዊት ነች።

በጦርነቱ ባሳየችው እጅግ አስደማሚ አቋምና እረፍት አልባ ትግል ወያኔ መሩ መንጋ በኃይማኖት ሽፋን በስሜት ቀስቅሶ በስማ በለውና በተዛባ መረጃ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተው የተበቀለ ስለመሰለውና ላልተጠናቀቀው ጦርነት ሕዝቡን በብሶት አጀንዳ ለማሳመጽ ካለው የፀና እምነት የተነሳ ነው። በደመነብስ ያለምንም መረጃ እንዲሁ መቃወም ስለተቻለ ብቻ ደግሞ እንደፈለገ 'አካኪ ዘራፍ' ያለው ሰው እልፍ ነው።

አሉ የሚባሉ ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙት በውይይት በሕግና ሥርዓት እንጂ በጩኸት ወለድ ግርግር ሀገር እንዲፈርስ በሚያደርግ የትርምስ መንገድ አይደለም። በዚህ መንገድ ከወያኔ በስተቀር የሚያተርፍበት አካል የለምና‼️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሀገር የገነባች በአፍሪካ ረዥም ዕድሜ ያላት ጥንታዊ ተቋም ነች። ዛሬ ፈተናዎች በዝተውባት ወያኔ መሩ ሊጠቀምባት ቢሞክርም ርግጠኛ መሆን የሚቻለው ቤተክርስቲያኗ ፈተናዎቿን በእውነተኛ ልጆቿ እና የኢትዮጵያን አንድነት በሚፈልጉ የመንግሥት አመራሮች ቀናነት በውይይት ሁሉም ይስተካከላል። በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትሪያሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ የሰጡት መግለጫ የጠላትን ድብቅ ሴራ የሚያከሽፍ ነው።

የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተባበሩ የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎችና የግብር ልጆቹ እኩይ ሴራ ሁሉ ይበጣጠሳል፤ በቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ከኢትዮጵያ ላይ የተጣበቁ መዥገሮች ሁሉ ተተልትለው ይራገፋሉ።