በጥፋት አዙሪት እንዳንቀጥል ከንቀት ወጥተን ነገሮችን በጊዜ በንቃት ልንመረምር ይገባናል‼️
በአጤ ሰይፈ አርዕድ በ1313 ዓ/ም በተመሰረተችው፣ በዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ መናገሻ፣ በእቴጌ ጣይቱ ብጡል እትብት፣ በጦር መሃንዲሱ ገብርዬ መንበር፣ በአፍሪካ የኢንዱስትሪ መንደር ጀማሪ፣ በሊቀ ሊቃውንቶቹ ሀገር፣ በእልፍ ጀግኖች መፍለቂያ በሆነችው ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ደብረታቦር ተገኝተን የመካነ ኢየሱስ የመርቆርዮስ የንግስ በዓል እና የፈረስ ጉግስን ጨዋታን( ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ጥምር በዓልን) በደመቀ ሁኔታ ከወንድም እህቶቻችን ጋር አክብረናል።
ዛሬ በዓሉን በሰላም እንዲህ በደማቁ እናከብር ዘንድ ትናንት በርካታ ወገኖቻችን የማይተካ ውድ ዋጋ ከፍለውልናልና እናመሰግናቸዋለን!
የከርሞ ሰው ይበለን!

በደብረታቦር ከውድ ወንድሞቼ ጋር የነበረን ቆይታ እጅጉን አስደሳች ነበር።
ልዩ ምስጋና ለደብረ-ታቦር ዩኒቨርስቲ!
የከርሞ ሰው ይበለን‼️
ልዩ ምስጋና ለደብረ-ታቦር ዩኒቨርስቲ!
የከርሞ ሰው ይበለን‼️
የወልቃይት ህዝብ ከሶስት አስርት አመታት በላይ ያለማንም አጋዥ ወያኔን ብቻውን ሲቃወምና ሲታገል የኖረ ጀግና ሕዝብ ነው። በዛ የጨለማ ዘመን ማንነቱን ለማስከበር ባደረገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎም ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። በማንነቱ የተነሳ ሕልቆ-መሳፍርት ግፍም ተፈፅሞበታል። በመጨረሻም በፅናቱ ዘልቆ ሌሎች ወንድሞች ወደትግሉ ቀላቅሎ ወያኔን ማንበርከክ ችሏል።
ጥቅምት 24ም የሰሜን ዕዝ በተኛበት ሲጠቃ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ግልብጥ ብሎ በመውጣት ጠላት ድባቅ በመምታት ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ሁለንተናዊ ደጀንነቱን አሳይቷል። ከመከላከያ ቀድሞ በመውደቅ በደሙ አኩሪ ታሪክ ፅፏል።
ይህ ጀግና ሕዝብ እናት ኢትዮጵያን በሱዳን በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃትና ወረራ ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የነበረን ጥምር የጥፋት ሃይሎችንና ከውስጥ በኩል ደግሞ ወያኔና እሱ ያስከተላቸውን እንዲሁም ያሰማራቸውን የጥፋት ሃይሎችን እኩይ አላማን ለማክሸፍ ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም ላደረገው አስተዋጽኦ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥቶታል።

እንግዶቻችን እንኳን ወደሁለተኛው ቤታችሁ ኢትዮጵያ በሰላም መጣችሁ!
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ በደማቁ ሁኔታ እንዲካሄድ ትናንት የደምና የዲፕሎማሲ ዋጋ ተከፍሎበታል‼️

ከዓመት እስከ ዓመት በተቆርቋሪነት ስም ግለሰቦችንና ተቋማትን ስም ለማጠልሸት የሚሞክሩ ማንነታቸው የሚታወቅና ማንነታቸውን ደብቀው የሚፅፉ ሰዎችን ማንነት ለመለየት እንሞክር። እነማን ናቸው? እነማንስ ላይ ነው የስም ማጥፋት ዘመቻስ የሚከፈተው? ምን ያህሉ መስሎት ባለማወቅ ምን ያህሉስ በተጠና መንገድ ነው ዘመቻውን የሚያራግበው? መንግስትን እቃወማለሁ፤ ብአዴንን አከስማለሁ ከሚለው ሃይል ውስጥ ግለሰቦችንም ሆነ ከተቋማት ውስጥ ከመሬት ተነስቶ ያለስራ አንዱን መርጦ በማንገስ ሌላውን የማኳሰስ ስራ መስራት ከራስ ጋርስ አያጋጭም? ወይስ አጀንዳ ሰጩ ወያዬ ስለሆነ ? ስማቸው ተመርጦ እንዲጠፋ የሚደረጉት ግለሰቦች ምን ቀይ መስመር ሳቱ ተብለው ነው? ግለሰቦችን ስም ጥላሸት መቀባት ተፈጥሯዊ ስሪታቸው ስለሆነ ወይስ ከወያኔ ተልዕኮ ስለተሰጣቸው? እንዲህ የሚያደርጉት ለሚሉት ጥያቄዎች መልሱን ከራሳቸው ነገረ-እንቅስቃሴ ማግኘት እንችላለን።
በበኩሌም ማንነታቸው ደብቀው ከሚፅፉ ሰዎች ውስጥ (ለአማራ ሕልውና ሁለንተናዊ ጥቅም ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መከበር ላይ ብቻ አነጣጥረው ሐሳባቸውን የሚያካፍሉ ) ሁለት ገፆችን ብቻ አውቃለሁ። ከእነዚህ ውጭ ያሉ ማንነታቸው በአካል የማይታወቁ አካውንቶች በሙሉ አጀንዳቸው ግለሰብና ተቋማትን በተቆርቋሪነት ማልያ ነጋ ጠባ ስም ማጠልሸት ነው።
የሰዎቹን አላማና ባሕሪይ ብዙም ጥናት ማድረግ ሳይጠበቅብን የሚያሰራጩትን አጀንዳ በማየት ማወቅ እንችላለን። ማንነታቸውን ደብቀው ከሚፅፉት ሰዎች ባልተናነሰ ሳይሆን በላቀ መንገድም ዘወትር የግለሰቦችን ስም ከማጠልሸት ከሌሎች ስራ ተነስቶ አቃቂር ከማውጣት ያለፈ መልካም ነገር የሌላቸው ከአማራ እሴት ያፈነገጡ አሳዳጊ የበደላቸው ማንነታቸው የሚታወቁ አግድም አደግ ሰዎች የሉም ማለት አይደለም።
አማራ ነኝ ከማለት አልፎ የአማራነት ሰርተፍኬት እሰጣለሁ የሚሉ የአማራ ሕዝብ ስጋቶች ራሳቸውን ደብቀው መፃፍ ለምን አስፈለጋቸው? ለስድብ ለመከፋፈል ለመራገም ለመረጃ መሰብሰቢያና ለወያኔ ጉልበት ለመፍጠር በተጠና መንገድ የተከፈቱ ስለሆኑ ነው ወይስ ...?!
በነገራችን ላይ ብአዴንን ከሚረግሙት በላይ ብአዴንነቱን ባስቀጠለ ከወያኔ ጋር ልዩ ትዝታ ባለው ባልበለፀገው ብልፅግና ውስጥ እግር ስር ተወሽቆ እየተጠቀመ ያለ አንዳችስ አካል የለም። ሁሉም ሰው እንደነሱ ያለሳንቲም የማይሰራ ጆተኒ ስለሚመስላቸው ነው ዘወትር ሐሳባቸው በሙሉ ስለክፍያ ስለሆድ የሆነው።
በየትኛውም መንገድ ወያኔ እንዲያንሰራራ ወይም አላማው እንዲሳካ ሊያደርግ የሚችልን ማንኛውንም መንገድ ቀድመን ለመዝጋት አናመነታም‼️

ወያኔና ግብረ-አበሮቹ አዲስ አበባ ለመግባት ሐገር ለማፍረስ ያለ የሌለ ሃይላቸውን ተጠቀመው ያደረጉት የጥፋት አላማ በቁርጥ ቀን ኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ከሸፎ ዛሬ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባን በደማቅ ሁኔታ እያከበርን ይገኛል። ይህ ይሆን ዘንድ ብዙዎች ከባድ የደምና የዲፕሎማሲ ዋጋ ከፍለውበታል። በዚህ ጉዳይ ወያኔና የግብር ልጆቹ ብስጭታቸውን ቢገልፁ የማይጠበቅ አይደለም። ከወሬ የዘለለ የማድረግ አቅም ጠፍቶ እንጅ ፕሮግራሙን ለማደብዘዝም ያልተቋረጠ ጥረት መኖሩ ግልጽ ነው።
በየትኛውም መንገድ ወያኔ እንዲያንሰራራ ወይም አላማውን እንዲያሳካ ዕድል የሚሰጠውን መንገድ ቀድመን ለመዝጋት አንዳችስ እንኳን አናመነታም‼️
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ብርቱ ክንድ ነፃነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!