Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.41K subscribers
2.98K photos
372 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ወያኔ አሁንም በፖለቲካው መድረክ አልተሸነፈም። ከፍተኛ የሆነ የፕሮፖጋንዳ ብልጫም እንደያዘ ነው።

ከሜንስትሪም ሚዲያው ይልቅ አጀንዳ ሰጭ የሆነውን የሶሻል ሚዲያን ፕላትፎርምም ለአማራ እንቆረቆራለን ለኦሮሞ ጠበቃ ነን በሚሉትና በስማቸው የተቆርቋሪነት ካባ በመደረብ፣ ሕዝባዊ አመፅ በሀይማኖት ሽፋን ጭምር በመፍጠር፣ የፀጥታ ሃይሉን ትኩረትና ስምሪት በመበታተን በቀላሉ ወደ አራት ኪሎ ሰርጎ ይገባ ዘንድ የሚያስችለውን አጀንዳ እየቀረፀ መሬት ለማስነካት የማይፈነቅለው ድንጋይ የማይወጣ ተራራ የማይወርደው ቆልቁለት አለመኖሩን እንቅስቃሴዎቹ የማይናገሩ አይደሉም። እንደ እረፍት አልባው ጥረቱ እንደ ፍላጉቱ ግን መሬት የማስያዝ አቅም መፍጠር አልተቻለውም።

ለዚህ ዋና እንቅፋቱ የመንግሥት ጠንካራ ስራ የተጠና ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን የመንግስት አለመፅናት ሐገር እንደሚያፈርስ(በአደባባይ በአዋጅ እንኳን እናፈርሳታለን እያሉት) ገና ከጅምሩ የነገሮችን አዝማሚ ተመልክቶ ውጤቱን መናገር የሚችል ስቴት ካልቸር ያለው በኢትዮጵያዊነቱ በፍጹም የማይደራደረው ሕዝብ ከፊት ቀድሞ አኩሪ ተጋድሎ በማድረጉና በነገሮች ሁሉ በፅናት መቆም በመቻሉ ነው። የወያኔ እኩይ አላማ እያከሸፈበት ያለው ራሱ ሕዝቡ ነው።

ጠላት በሐገር ቤትም ሆነ በባህርማዶ በአማራ ስም በኦሮሞ...በሌሎች ብሔሮች በተቃዋሚ ስም ለሚንቀሳቀሱት ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲሁም በሲቪክ ማህበር ስም ለሚንቀሳቀሱት አካላት አላማውን ያስፈፅሙለት ዘንድ ከዚህ በፊት ከኢትዮጵያ ሕዝዝ በተዘረፈ ሐብትና ሐገር የማፍረስ አላውን በሚጋሩ አንዳንድ አገራትና ተቋማት ከፍተኛ ዶላር ገንዘብ እየተነሰነሰላቸው፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የወንጀል ስጋት፣ በአቅም ማነስ፣ ከስልጣኔ እነሳለሁ በሚሉትና በተነሱ አኩራፊ አመራሮች በኩል በየቀኑ በሚሰጥ የልዩነት የአመፅ ቀስቃሽ አጀንዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላው ቢቀር በአማራና በኦሮሚያ ያልተቋረጠ ብጥብጥና ሁከት መፍጠር በቻለች ነበር። ሕዝቡ ቀደማቸውና የደም ነጋዴዎቹን መንገድ ዘግቶ መፈናፈኛ አሳጣቸው።

ሕዝቡ እየሆነው ባለው ነገር የተከፋና ይበልጥ እንዲከፋ የሚፈልጉ ከውስጥና ከውጭ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ ግጭት አዳዮች እናት አገሩን ሊያፈርሱበት በስስ ጎኑ ስሜቱን ኮርኩረው ወደአመፅ ለማስገባት ተደራጅተው ቢመጡበትም (በቅርቡ ይጮሁ የነበሩ አጀንዳዎችን የምናስታውሰው ነው) የተደረገለትን ተከታታይ ውጣ ደምህን ስጥ ደም አፍስስ የእርስ በርስ ግጭትን ጥሪ ባላየና ባልሰማ ከማለፉ ባሻገር ጦር-አውርዶቹን የወያኔን የግብር ልጆችን ከእቁብ የማይቆጥራቸው መሆኑን በምላሹ አረጋግጧል። ለዛም ነው በሀይማኖቱ ስም የተጠለሉትና በአማራ ሕዝብ ስም የተቃውሞ የተቆርቋሪነት ፖለቲካ እንሰራለን የሚሉት አካላት ሕዝቡን ወደመሳደብና ወደመራገም የገቡት።

ሕዝቡ ማን ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። በምንም አይነት መንገድ ቢገለፅ በየትኛውም ቀለም ቢኳኳል የጦር-አውርዶቹ የጥሪ አላማንና ግቡን ስቴት ካልቼር ያለው ሕዝብ ስለሆነ ቀድሞ ይረዳዋል። ድባቡን ያነበዋል።
የአመፀኞቹን የወያኔ የግብር ልጆችን ጥሪ ያልሰማውም መንግስትነትን ስለሚያውቅ ነው።

ስሜቱን ያልገራ የማንም አልፎ ሂያጅ አግድም አደግ የግጭት ነጋዴ ሁሉም እንደፈለገ የሚፈነጭባት መንግስት አልባ የፈረሰች አገርን በአይኑ ማየት የሚፈልግ ሕዝብ ስላልሆነ ነው የወያኔና የግብር ልጆቹን እኩይ አላማን እየቀደመ ማክሸፍ የቻለው።

ማንም ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት ለጥፋት አላማ ወደዚህ ግባ ወደዚያ ውጣ ተቀመጥ ተነሳ ስላለ አብሮ በስሜት ፈረስ የማይጋለብ በደመነብስ በመንጋ አዝማች የማይነጉድ፣ ጥሪውን የሚያስተላልፉት ሰዎች የሞራል ልዕልና የሌላቸው መሆናቸውን ሕዝባችን በሰጠው ገቢራዊ ምላሹ አረጋግጧል።

ነገር ግን አሁንም ቢሆን ወታደራዊ ድል ማስመዝገብ ያልቻለው ተሸናፊው ወያኔ በፕሮፖጋንዳ ብልጫ የፖለቲካ ድሉን ለማስጠበቅ አጀንዳ አሻሻጮቹንና ጉዳይ አስፈፃሚዎቹን በንቃት እንዲንቀሳቀሱ ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማይናወጥ ፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት የመንግስትን ስልጣን የያዘው ብልፅግና ከመቼውም ጊዜ በላይ በመንግስታዊ መዋቅሩና በውስጡ የተሰገሰጉ ብአዴንነትንና ኦህዴድነትን ለማስቀጠል የሐገርን ቁልፍ መረጃ በውጭም በውስጥም በስመ ተቃዋሚ ለተሰለፉ ነገር ግን አገር ለማፍረስ ሁሉንም ነገር አሟጠው ለተጠቀሙ የወያኔ የሕዝብ ግንኙነት ሆነው ለሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖች መረጃ የሚሸጡ የወያኔ መንገድ ጠራጊ አፍቃሬ ወያኔዎችን ከውስጡ ማጥራትና ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ተገቢ ጥያቄዎችን ሁሉ ጆሮ በመስጠት ሕዝብ መስማት የሚፈልጋቸውን ነገሮችን መናገር ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልገውን ነገር ወደመሬት አውርዶ በመስራት የመንግስትነት ኋላፊነቱን የመወጣት ታሪካዊ ግዴታ እንዳለበት ለአፍታም ሊዘነጋው አይገባም።
የአሊሚራህ ጀግኖቹ የአፋር ልጆች በጠላት ላይ ድልን እየተቀዳጁ ነው። ግፉ ወደፊት ጀግኖቹ!
ሁሉም ነገር እያለፈ ታሪክ ሆኖ እየተፃፈ የትውልድ ቅብብሎሹ ይቀጥላል። ሁሉም ነገር ባለበት ወይም አሁን ያለበትን ሁኔታ መስሎም አይቀጥልም።መንግስት የተዳከመ የመሰለበትና ሐገር የሚፈርስበት የሚመስለው(እንዲዳክምና እንዲፈርስ የሚፈልጉ ሃይሎች ጥርስ ያወጡበት ) ከባዱ የፈተና የግርግር ወቅት ያልፋል። በማያልፈው ታሪክ ውስጥ የራስን በጎ አሻራ ወይም መጥፎ ጠባሳ ጥሎ የማለፍ ምርጫው የእኛው ነው።

ማናችንም በስማ በለው በደሳለኝና በመሰለኝ በስሜት ፈረስ ጋልበን ስለአንድ ጉዳይ አቋም ከመያዛችን በፊት በቂ መረጃ ይኖረን ዘንድ በሰከነ መንገድ ነገሮችን ለመከታተልና ለመመርመር እንሞክር። መረጃ ሰብስቦ ከተነተኑ በኋላ አቋም መያዝ የሚጠበቅ ነው።ከስማ በለው ወይም ከግብታዊነት ተነስተን እንደቀልድ የምንወስነው ውሳኔ ከራሳችን አልፎ በዙሪያችን ያለን የቅርብ ሰው ጨምሮ ሊጎዳ የሚችል እንዳይሆን በማሰብ በኋላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ያስፈልገናል።

በማስተዋልና በጥበብ እንራመድ‼️
በነገራችን ላይ ለወያኔ ጉልበት ሊሆኑ የሚችሉ አጀንዳዎችን የሚያሰራጩ፣ አማራን ከሌላው ብሔር ጋር ለማጋጨት ከሁሉም አካል ጋር ለማላተም ጠላት መቀነስ ሳይሆን ማብዛት ላይ የተሰማሩ፣ የግለሰቦችን ስም በማጥፋት ካልሆነ ሌላ ምንም አይነት ሐሳብ የማይፅፉ፣ ወያኔ እንደዋና ጠላትና ስጋት እንዳይቆጠር ጠላት የሚሉትን ሰዎች በተጠና መንገድ የተለያየ ስም እየሰጡ እንደአማራ ጠላት ሊቆጥሩ የሚሞክሩ ማንነታቸውን ደብቀውም ሆነ በግልፅ በሚታወቀው ማንነታቸው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ማንነት ለማጤን እንሞክር።

ማን ከየትና ለምን አላማ እንዴት አጀንዳ እየተመጋገበ እንደሚፅፍ ለማወቅ በጥልቀት ሳይሆን የሚያጋሩትን አጀንዳ ከላይ ብቻ በመመልከት ማወቅ እንችላለን። ለሕዝብ ሳይሆን በሕዝብ ላይ የቆሙ ስለመሆናቸው ነገረ-ስራቸው ይመስክራል። ለሕዝብ የሚጠቅም አንዳችስ መልካም ነገር እንደማይፅፉ አጀንዳቸውን ማየት ብቻ በቂ ነው። ከኢትዮጵያ እሴት የተነጠለ ነውረኝነትን ጋጠ-ወጥነትን የባህሪ ገንዘባቸው ያደረጉ ዘወትር በግለሰብ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ (እስካሁን መረን በለቀቀ መንገድ የሚዘመትባቸውን ግለሰቦች ወደኋላ ተመልሳችሁ ለማጤን ሞክሩ) ምን እንዳጠፉና ብትመረምሩ ከዘመቻው ጀርባ የአጀንዳው ባለቤት ወያኔ ሆኖ ታገኙታላችሁ። በወያኔ ላይ የመረረ ጥላቻ የሌለውና ወያኔን እንደዋና ጠላትና ስጋት የማይቆጥር ሰው በዚህ ወያኔ መር ግብረ-ሃይል አይወገዝም። አይተችም። ነገሮችን ስራዬ ብለን እንከታተላቸውና ሁሉም ነገር ግልጥልጥ ብሎ ይታየናል።

የሚፅፏቸውንና የሚያጋሯቸውን አጀንዳዎች ለማንእንደሆነ ከማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ምን ለማሳካት እንደሆነ እንዲህ የሚሆኑት የሚለውን እልፍ እልፍ ብለን ነገረ-ስራቸውን ስንመረምር በቀላሉ ማወቅ እንችላለን።

ወደወያኔ ሰዎች ሚሳኤል ሁሉ እናስወነጭፋለን። በምላሹ እንዴት የቱርክ ሽጉጥ ተኮሱብን አይባልም!
የፌስቡክ የአማራ ፖለቲካ ወያኔ መር ነው። የሚመዘዙ አጀንዳዎቹን በትኩረት ተከታተሏቸው። አላማውን አጢኑት። ከወያኔ ለወያኔ የሚሆኑ ናቸው።

በአማራ ፖለቲካ ትግል ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት ከተከፈቱት የፌስቡክ አካውንቶች ውስጥ ከ90 በመቶ በላዩ የሚሆነው በተለይ በሕወሓት የውድቀት ዋዜማ አመታቶች በደህንነት ሹሙ በእነ ጌታቸው አሰፋ ከፍተኛ በጀት ተይዞለትና ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ወደፌስቡክ የተሰማራ የሕወሓት አባልና ደጋፊ ነው።

9 በመቶው የሚሆኑት ደግሞ አማራ ቢሆንም በግብራቸው ከወያኔ በፍጹም የማይለዩ ልክ እንደ ወያኔዎች ከኢትዮጵያዊነት እሴት ባፈነገጠ መንገድ ነውረኝነትን ጌጥ ያደረጉ አሳዳጊ የበደላቸው ፌስቡከሮች ናቸው። አንድ በመቶዋ ደግሞ በሐሳብ ልዕልና የሚያምኑ በምክንያት የሚፅፉ ሐሳባቸውን በተሸናፊነት ስሜት፣ በስድብና በእርግማን ለመሸጥ የማይንደፋደፉ ነገር ግን ከለውጡ በፊት በነበረው የአፈና የጥቃት ዘመን ስጋት (ፀሐፊው ቢታጣ ዘመዱ በተለያዬ መንገድ ዋጋ ይከፍል እንደነበረ ከ4አመት በፊት የነበረ ትዝታ ነው) እናም በሌሎች ምክንያቶች ራሳቸውን ሳይገልጡ የቆዩ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን አብዛኞቹ ራሳቸውን ገልጠዋል። የሐሳብ ልዕልና ላይ ትኩረት ካደረጉት መካከል የተወሰኑት ሳይገለጡ ከመድረኩ የወጡ ቢሆኑም ጥቂቶች አሁንም አሉ። እነሱም ማንነታቸው በአካል ጭምር የሚታወቁም ናቸው።
የፌስቡኩ የአማራ ፖለቲካ በራሱ በአማራው አይደለም እየተመራ ያለው። በፌክ አካውንት የሚፅፉትን የሚያስንቁ ማንነታቸው የሚታወቁ ሰዎችን ከላይ ከጠቀስናቸው ሰዎች ጋር ስንደምራቸው የሚያደርሱትን ጉዳት መገመት አይከብድም። ማንነቱን በግልፅ ገልጦ የሚፅፈው አማራ ማንነቱን ደብቆ በሚፅፉት ሰዎች ፍፁም የአጀንዳ ብልጫ ተወስዶበታል። የዚህ ዋናው ምክንያት በግልፅ የሚፅፈው አማራና የአማራ ኤሊት ማንነታቸውን ደብቀው በሚፅፉትና በነውረኝነት ባጌጡ ሰዎች ስድብ የእርግማን የዘለፋ አይነቶች ተሳቆና ስጋቱ አድሮበት ሐሳቡን ለመግለጽ ተቸግሯል። ይህን ስጋት ሰብሮ ለመውጣት የሚያስችል ልምምድም ገና አልጀመረም። ያሉት ጥቂት ናቸው።

እና ወያኔ መር የሆነው የፌስቡክ የአማራ የፖለቲካ ትግል የዘወትር አጀንዳዎችን ለምሳሌ ያህል ለማሳየት
ልዩነት መፍጠር፣ በተፈጠረ ልዩነት ላይ ተሰማርቶ ቀዳዳ ማስፋት፣ ክልሉ እንዳይረጋጋ የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል እንዲሆን አጀንዳ መስጠት፣ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ የኢኮኖሚ አይደለም የነፃነት ነው ይህ አጀንዳ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ስጋት ላይ አለመሆኑን ማሳየት የሚፈልገው የብአዴን አጀንዳ ይልና በኦሮሚያ ክልል ትራክተር ቀረበ ሰብል ተጎበኘ የሆነ ፕሮጀክት ተመረቀ ሲባል አማራ በብአዴን ተከዳ እያለ መንግስትና ሕዝብ ፍፁም በተቃርኖ እንዲተያዩ ማድረግ፣ አማራ በስርዓት እንዳይደራጅ ዘወትር ወከባ እየፈጠረ መደማመጥ እንዲጠፋ ማድረግ፣ አማራው አንድነቱን ለማጠናከር የውይይትና የስብሰባ ፕሮግራም ሲጠራና ሲቀመጥ የብአዴን ስብሰባ በማለት ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅ እንዲፈጠር የሚሰራ፣ ጃዝ ከማለት ውጭ ቀድሞ መገኘትን የማይመርጥ፣ ችግር እንዲፈጠር ማድረግና በተፈጠረው ችግር ድንኳን አስጥሎ፣ ንፍሮ አስቀቅሎ፣ ነጠላ አስዘቅዝቅ ማስለቀስ፣ በግለሰብ አስታኮ ተቋማትን ማዳከምና ማፍረስን አላማ ያደረገ አጀንዳን የሚያራምድ በሕወሓት ከፍተኛ በጀት የተመደበለት ከመቀሌ አጀንዳ እየቀረፀ የሚወረወርለት ሃይል ነው።

እንግዲህ በዚህ ወያኔ መር የአማራ ፖለቲካ ትግል ነው የአማራ የሕልውና ችግር የሚቀረፈው ሁለንተናዊ ጥቅሙ የሚረጋገጠው። ከባድ ነው።

አሳዛኙ ነገር ብዙ ሰው ጠያቂ አለመሆኑና የመንጋ ተጠቂ መሆኑ ኤሊቱ ጓዳ ገብቶ ወደውጭ አልወጣም ማለቱ አማራውን ይበልጥ ዋጋ እንዲከፍል አድርጎታል!
ከአመታት በፊት ጊዜያችሁን በከፍተኛ ንባብ ያሳለፋችሁ ምራቅ የዋጣችሁና እምቅ እውቀት ያላችሁ የተገለጠላችሁ አማራዎች እባካችሁ ወደፊት ኑና ምሩን የሚል ጥሪ ሳስተጋባ የኖርኩት ነገሩ ስላልጣመኝና ነገሮች ይበልጥ ከድጡ ወደማጡ እንዳይጓዙ በማሰብ ነበር። ሰሚ ባይገኝም ቅሉ!

አሁንም ምንም ለማድረግ አልረፈደም‼️
ቅማል
የት ልትሄጅ ነው?
መተማ
ትደርሽን ?
ልብማ።

ከወራቶች በፊት ለወያኔ ዛሬ ደግሞ ለግብር ልጆች የደገምኩት ነው፤

አቤት አየር ላይ ያለ ሰው😂
ስለ ምንም ነገር ስፅፍ እኔን/እኛን ነው? የሚሉ ሰዎች ተበራክተውብኛል።

እኔም በምላሼ "ፈስ ያለበት ዝላ አይችልም" ካልሆነ በስተቀር እኔ አንተንም ሆነ እናንተን ይመልከት አይመልከት ጉዳዬ አይደለም አንተን ወይም እናንተን አያሰብኩ አልፅፍምና። ነገር ግን የምፅፈው ነገር የሚመለከትህ ወይም የሚመለከታችሁ ከሆነ ሁለት ምርጫ ይኖርሃል ወይም ይኖራችኋል ለመታረም ወይም ለማረም መሞከር።
ከዛ ውጭ የምፅፈውን ነገር ሁሉ እኔን ወይም እኛን ነው እያላችሁ አታብግኑኝ‼️
በየግዛቶቻችሁ በፌክም ሆነ በሚታወቅ ማንነታቸው በገፆቻቸው የሚፅፉም ሆነ በእየ አስተያየት መስጫው እየገቡ በስድብም ሆነ በሐሳብ አስተያየት የሚሰጡትን አካውንቶች ማንነት ለመመርመርና አላማቸው ምን እንደሆነ? ማን ከማንስ ጋር ግንኙነት ያለው እንደሚመስል አሰላለፋቸውን በሚፅፏቸውና በሚያጋሯቸው ይዘቶች በቀላሉ ማወቅ ይቻላልና ለማጤን እንሞክር!

በጥሞና ለማንበብ ሞክሩኝ‼️

አንድን ጉዳይ እንደ ሕወሓት እየተገለባበጠ ፕሮፖጋንዳ የሚጠቀም የለም። በስምህ ይሰማራሉ። ይነግዳሉ። መልሰው ስምህን ያጠፋሉ። ሞራልም ሆነ ሕግ አያስጨንቃቸውም። ሰው ምን ይለኛል ጉዳያቸው አይደለም። የጥፋት አላማቸውን ለማሳካት የእነሱን የበላይነት ለመፍጠር አጀንዳቸውን ለመሸጥ ሁሉንም ነገር ለመመሳሰል የሚቸገሩም አይደሉም።

የአስመላሽ ተተኪው ቴዎድሮስ ፀጋዬ የአማራን ፖለቲካ ለሌሎቹ ይህን ይመስላል ለማለት የተጠቀመበትን የሚከተለውን ንግግሩን እንመልከት ""...በአማራ ብሔርተኝነት ፖለቲካ ጥርስና ጥፍር ብቻ ነው ያለው። መናከስና መቧጨር ብቻ የሚያውቅ። ማሰብ የማያውቅ፤ መደራደር የማያውቅ፤ መስከን የማያውቅ፤ ማነው ስትራቴጅክ ወዳጄና ስትራቴጅክ ጠላቴ ብሎ ማንሰላለስል የማይችል፤ የመጣን መንከስ፣ የመጣን መቦጨቅ ብቻ የሚችል ጥላቻን፣ በቀልና ቂም ብቻ የሚነዳው ፖለቲካ በአማራ ብሔርተኝነት ፖለቲካ ነግሷል።" ይላል።

የሕወሓቱ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ንግግር ወያኔ መሩን የአማራን የፌስቡክ ብሔርተኛን በትክክል የሚገልጽ ነው። የአማራ ብሔርተኛ ፖለቲከኞችን የሚገልፅ ግን አይደለም። እሱ ያወራው በአማራ ስም ስለተሰማሩት የወያኔ ምልምሎች ነው።

እነ ጌታቸው አሰፋ ከሐገር አስወጥተውና በሐገር ቤት ስልጠና ሰጥተው የበተኑት ከ30 ሺ በላይ የሚገመት ምልምል የደህንነት አባላት አሉ። 30 ሺ ቁጥሩ እንዲህ ቀላል አይደለም። ይህ በደንብ የሰለጠነ ሃይል ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ማሰብ ቀላል ነው። ብዙ ነገርም አበላሽቷል።

ሕወሓት የማይሸነፍና አዲስ አበባ ከመግባት ሊያግደው የሚችል አካል እንደሌለና ኢትዮጵያ እያበቃላት አድርጎ ሲነዛ የነበረው የተቀናጀ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ብቻ ብዙ ሰዎችን ማሳመንና ለማስደንገጥ ተሞክሮ ብዙ ነገር አሳክቷል። አንዳንዶቹን ከሕወሓት ጎን ብንቆም ይሻለናል እስኪሉ ድረስም በስነልቦና ቀድመው እንዲሸነፉ አድርጓል።

ይህን ስራ የሚሰራው በኢትዮጵያ ሕዝብ ሐብትና በኢትዮጵያ ስም የሰለነጠነውና ነገሮች የተመቻቹለት የወያኔ የደህንነት ክንፍ የሚመራው ሃይል ነው። የወያኔን ተልዕኮ ይዞ በሐገር ቤትና በባህርማዶ የተሰማራው በለውጡ ዋዜማ ነው።

በፌስቡክ በአማራ ተቆርቋሪነት ስም የሚንቀሳቀሰው ይህ ሃይል ሳይበሩን የሚመራው ብቻውን አይደለም፤ በእየ ከተሞቹ በአካል በመንቀሳቀስ በሕዝብ መዝናኛዎች፣ በአደባባዮች ተመሳስሎ መረጃ የሚሰበስብ፣ የአማራ ተቆርቋሪ መስሎ የውሸት መረጃ የሚረጭ በጥቅሉ እግረኛ አስተኳሽ (ኦፒ) ወቅቱን የጠበቀ ለአመፅ የሚሆን የሃይማኖት ወይም የፖለቲካ አጀንዳ ከሚያሰራጨው መሬት ላይ ከተበተነው ሃይል ጋር በመናበብ ነው። መሬት ላይ የተበተነው ሃይልም በአማራ ስም ፌስቡከር ነው።

በእነ ጌታቸው አሰፋ ተመልምሎ በቂ ስልጠና ወስዶ የሚንቀሳቀሰው ይህ ሃይል አንድን ነገር አጀንዳ የሚያደርገው ወይም አጀንዳውን ወደሚዲያ የሚያመጣው መሬት ላይ(አጀንዳ የሚፈጠርበት የሆነ ቦታ ወይም ከተማ አካባቢ ካለው ግብረ-መልስን) እና ፖለቲካዊ ትርፉ ከተሰላ በኋላ ነው። የሚያሰራጩት ሐሰተኛ መረጃ ወይም የሚፈጥሩት ችግር ለብዙሃኑ ሰው መሬት ላይ እነሱ በሚፈልጉት መንገድ መዳረሱ እንደተረጋገጠ(የሕዝቡ ምላሽ ምንም ይሁን ምን) እነሱ በሚፈልጉት መንገድ አጀንዳውን ፍሬም በማድረግ ወደሚዲያዎቻቸው ያሰራጯቸዋል።

እየየ ከሆነ ድንኳን ይጣላል። ፉከራ ከሆነም አማራ ተራራው ይከፈታል። ሁለቱም ግን የአማራ ጉዳዮች አይደሉም።ክፉም ሆነ ደግ የፌስቡክ ምዕመን ይሰበሰባል። የተፈጠረው ችግር ነጠላ የሚያዘቀዝቅ ከሆነ አዋጅ ይታወጃል። ወዮላችሁ እናንተ ብሔሮች መልዕክታችን ይድረሳችሁ እየመጣንባችሁ ነውና እናሳያችኋለን ይባላል። ከሳምንት በኋላ የዛሬ ሳምንት የነበረው አጀንዳ ምን ነበር ብለህ ስትጠይቅ ተረስቷል። እንኳን ችግር ተፈጠረ ወደተባለበት አካባቢ አዋጅ ያስነገረው አካል ደርሶ ጠላት የተባለው ላይ ሂሳብ ሊያወራርድ። ተረስቶ ወይም የሚረሳ ጉዳይ ስለሆነ ግን አይደለም። የአጀንዳው ባለቤት ራሱ ወያኔ በመሆኑ ነው። ችግር የሚፈጥረውም ወያኔ ነው። የተፈጠረውን ችግር ስሙልኝ ብሎ ሐገሪቱን የሚያዳርሰውም ራሱ ስለሆነ ነው። መሀል ገብቶ የሚያስጨፍረው አጀንዳ የሚያድለው ራሱ ወያኔ ስለሆነ ነው። ወያኔ ነው ማለት ትግሬ ብቻ አይደለም። የግብሩ ወራሾችና በዋናነት ተልዕኮ ተቀባይ የሆኑት ሁሉንም ያካተተ እንጅ።

መሃል ገብቶ ከእንግዲህ ሰይፍ እንጅ ሰልፍ አያስፈልገንም፣ ማንነታችንና ነፃነታችን በክንዳችን እናስከብራለን፤ እያለ ሲያስለቅስ ሲያስተክዝ የነበረው ሃይል በቀጣዩ ቀን ለስራ ወደተግባር እንግባ እንጅ ቢባል ተፈልጎ የሚገኝ አይደለም። የወያኔ አላማ አማራን አደራጅቶ እያስለቀሰ ስነ-ልቦናውን መስበር እያደራጀ ማስቆጣት እንጅ እንዲደራጅ ሆኖ ራሱን እንዲከላከል እንዲያስከብር አላማ የሰነቀ አይደለም። በወርድና በቁመቱ ልክ የፖለቲካ ውክልና እንዲኖረው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆንም ፈፅሞ አይደለም።

የወያኔም ሆነ በወያኔ ስምሪት የተሰጠው ይህ ሃይል አላማው ችግሮችን፣ግፎችን፣ ስጋቶችን በመፈፀም በማሳየት ብቻ በማጮህ፣በመንግስትና በሕዝብ መካከል የጥርጣሬ መንፈስ እየፈጠረ በማነሳሳት ሕዝብን አስቆጥቶ በመንግሥት ላይ እንዲያምጽና ወደ ሕዝባዊ አምጽ መምራት ነው።
ለዚህ የሚሆኑ ማናቸውንም ድጋፍ ከማድረግ ግን ፈፅሞ አይቆጠብም።

በፌስቡክ በአማራ ብሔርተኛ ስም የሚንቀሳቀሰው የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ ሃይል መሆኑን ተጨማሪ ማሳያ የወያኔ ሰዎች አማራን በተመለከተ ስለሚናገሩት አንዳችም ነገር ትንፍሽ አይልም። እነ ታደሰ ወረደ ጌታቸው ረዳ ከአማራ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን ሲሉ ምን ብሎ መለሰ? ምንም!! ንግግራቸውን እውን ለማድረግ ጦርነት ከፍተው በተግባር ወረራ ሲፈፅሙስ ምን ይል ነበር? ይታወቃል።
አማራው እንዲከፋፈል በተለያየ ጉራ ቆሞ በስደብ ሊሆን ይችላል በሐሳብ እንዲነታረክ አንድ እንዳይሆን ወቅቱን የማይመጥን አጀንዳ ሲመዝ ግን ነበር።

የሳይበሩ አማራ በአማራ ስም በሚንቀሳቀሱት ወያኔና የግብር ልጆቹ የተነሳ አንድም ቀን ራሱን ሳይሆን ወደራሱ ሳይመለከት ራሱ አጀንዳ ሰጭ ሳይሆን በተጣለለት አጀንዳ ብቻ ዘወትር እየተናጠሰ እዚህ አድርሰውታል። ሳይበር ላይ በአያሌው ወያኔ ከማትረፉ ባሻገር ተመልሶ ትግሬ ማለት እንዲህ ሲሆን አማራ ማለት ግን ይህ ነው ይላል።

“ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል” እንዲሉ እሱ ባሰማራቸው ተከፋዮች የበከለውን እና ያከረፋውን የአማራ ብሔርተኝነት እንደ ቴዎድሮስ ፀጋዬ አሉላ ሰለሞንና ሌሎች አፎቹ በኩል ደግሞ የአማራ ፖለቲካ አላአዋቂ በሆኑ ሰዎች የሚመራ፣ ጥላቻን የሚነግድ ለሌሎች ብሔሮች ትልቅ ስጋት እና እጅግ አውዳ*ሚ አድርጎ ያቀርባል። ራሱ በፈጠረው አማራ በመሰለው ወያኔ የተባለውንና የተሰራውን ነገር፣ የአማራን እሴት ፖለቲካዊ ስብዕና የማያንፀባርቅ ስራ ሁሉ፣ ለአማራ ለማሸከምና አማራ በዚህ እንዲሳል ለማድረግ ብዙ ታትሯል። አማራም ሆነ የትክክለኛው የአማራ ልጆች የፖለቲካ ስብዕና ግን ወያኔና የግብር ልጆቹ እንደሚሉት ፈፅሞ አይደለም!
በጥፋት አዙሪት እንዳንቀጥል ከንቀት ወጥተን ነገሮችን በጊዜ በንቃት ልንመረምር ይገባናል‼️
ቄንጠኛ የአገው ፈረሰኞች!!

እንኮን ታምፁናስ!
በአጤ ሰይፈ አርዕድ በ1313 ዓ/ም በተመሰረተችው፣ በዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ መናገሻ፣ በእቴጌ ጣይቱ ብጡል እትብት፣ በጦር መሃንዲሱ ገብርዬ መንበር፣ በአፍሪካ የኢንዱስትሪ መንደር ጀማሪ፣ በሊቀ ሊቃውንቶቹ ሀገር፣ በእልፍ ጀግኖች መፍለቂያ በሆነችው ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ደብረታቦር ተገኝተን የመካነ ኢየሱስ የመርቆርዮስ የንግስ በዓል እና የፈረስ ጉግስን ጨዋታን( ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ጥምር በዓልን) በደመቀ ሁኔታ ከወንድም እህቶቻችን ጋር አክብረናል።

ዛሬ በዓሉን በሰላም እንዲህ በደማቁ እናከብር ዘንድ ትናንት በርካታ ወገኖቻችን የማይተካ ውድ ዋጋ ከፍለውልናልና እናመሰግናቸዋለን!

የከርሞ ሰው ይበለን!
በደብረታቦር!
በደብረታቦር ከውድ ወንድሞቼ ጋር የነበረን ቆይታ እጅጉን አስደሳች ነበር።
ልዩ ምስጋና ለደብረ-ታቦር ዩኒቨርስቲ!

የከርሞ ሰው ይበለን‼️
የወልቃይት ህዝብ ከሶስት አስርት አመታት በላይ ያለማንም አጋዥ ወያኔን ብቻውን ሲቃወምና ሲታገል የኖረ ጀግና ሕዝብ ነው። በዛ የጨለማ ዘመን ማንነቱን ለማስከበር ባደረገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎም ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። በማንነቱ የተነሳ ሕልቆ-መሳፍርት ግፍም ተፈፅሞበታል። በመጨረሻም በፅናቱ ዘልቆ ሌሎች ወንድሞች ወደትግሉ ቀላቅሎ ወያኔን ማንበርከክ ችሏል።

ጥቅምት 24ም የሰሜን ዕዝ በተኛበት ሲጠቃ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ግልብጥ ብሎ በመውጣት ጠላት ድባቅ በመምታት ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ሁለንተናዊ ደጀንነቱን አሳይቷል። ከመከላከያ ቀድሞ በመውደቅ በደሙ አኩሪ ታሪክ ፅፏል።

ይህ ጀግና ሕዝብ እናት ኢትዮጵያን በሱዳን በኩል ሰርጎ በመግባት ጥቃትና ወረራ ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የነበረን ጥምር የጥፋት ሃይሎችንና ከውስጥ በኩል ደግሞ ወያኔና እሱ ያስከተላቸውን እንዲሁም ያሰማራቸውን የጥፋት ሃይሎችን እኩይ አላማን ለማክሸፍ ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም ላደረገው አስተዋጽኦ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥቶታል።
እንግዶቻችን እንኳን ወደሁለተኛው ቤታችሁ ኢትዮጵያ በሰላም መጣችሁ!

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ በደማቁ ሁኔታ እንዲካሄድ ትናንት የደምና የዲፕሎማሲ ዋጋ ተከፍሎበታል‼️