Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.41K subscribers
2.98K photos
372 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
በግጭት ላይ ሕልውናው የተመሰረተው ወያኔ በኢትዮጵያዊነቱ በማይደራደረው የአፋር ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል። የጥምና ጊዜ እንዳይኖር ሕወሓት ጦርነት በመክፈት የማደናገር ስራ ካልሰራ በስተቀር ከትግራይ ሕዝብ የሚነሳበትን ጥያቄ መመለስና ማስተዳደር የሚያስችል የመንግስትነት ቁመና የለውም። በሕዝቡ በኩል የሚነሳበትን ቅሬታና ጥያቄዎችን ለማዘናጋት እንዲሁም በወታደራዊ ክንፉና በፖለቲካ ክንፉ መካከል ያለውን ልዩነት የማቀራረቢያ ጊዜ መግዛት ይፈልጋል። በራያዎቹ በእነ ጀኔራል ፃድቃን ገብረተንሳይ የሚመራው ቡድን እና በአድዋዎቹ በእነ ጀኔራል ታደሰ ወረደ በሚመራው ቡድን መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደለየለት ጠላትነት እንዳይሻገር ይፈልጋሉ። ለዚህም የሰብዓዊ ድጋፍ በሚጓጓዝበት አፋር በኩል ጦርነት ከፍተው አለማቀፉ ማህበረሰብ በሰብአዊ የእርዳታ ስም የወልቃይት ኮሪዶርን እንዲያከፍትለት በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲያደርግ አልሟል። በሌላ በኩል በወልቃይት እና ሁመራ በኩል ላሰበው ወረራ መጠነሰፊ ዝግጅት እያደረገ የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረት ወደ አፋር እንዲዞርና የተከዜ ግንባር ቀለል እንዲልለት አስቦም ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም ህወሓት በአፋርም ጦርነት ከፈተ በወልቃይት አሊያም በመሀል ዋግና ራያ የሚጠብቀው ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ልዩሃይላችን ሚሊሻና ፋኖ እንዲሁም ደጀኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታ ትንታጎቹ የአፋር ልጆች ከሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ ጠላትን በሚገባው ቋንቋ እያናገሩት ይገኛሉ።

በአስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ከአፋር ሕዝብ ጎን ቆመን ድጋፋችንን እያሳየን በራያ በአበርገሌም ሆነ በወልቃይት ሱዳን በኩል ያለውን ሁኔታ ሳንዘናጋ በንቃት መከታተልና አስፈላጊ የሚባለውን ሁሉ ዝግጅት ከወዲሁ ማድረግ ይጠበቅብናል።

የነቃ የተደራጀ የታጠቀና የፀና ሕዝብ ያሸንፋል‼️
በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ጀግናው የአፋር ሕዝብ ከጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም ጦርነት የከፈተበትን ጠላት አፈር እያስቃመ ታሪክ በመስራት ወደፊት መገስገሱን ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ አጠናክሮ ቀጥሏል‼️

በተባበረ ክንድ በድል አድራጊነት ወደፊት እንወነጨፋለን!
ወያኔ አሁን በአፋር ከከፈተው ጦርነት ጋር ሊቀጣጠልና ጉልበት ሊሰጠው የሚችለውን ወደመሐል ሐገሪ ሊፈጥረው አቅዶት የነበረውን የጥፋት አላማውን ተናበንና ተቀናጅተን ማክሸፍ በመቻላችን ደስታና ኩራት ይሰማኛል። ወያኔ የግብር ልጆቹ እና እኛ በዚህ ዙሪያ በደንብ ተግባብተናል ጥርስ እየተነካከስን ነው አይደል? ምንም ማድረግ አይቻልም፤ አትቀደም😂
ብለን ነበርን አሁናዊ ጠቀሜታ ካለው‼️
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ከማይደራደረው ጦርነት ከተከፈተበት ከአፋር ሕዝብ ጎን ሊቆም ይገባዋል!

የአፋር ሕዝብ በጀግንነት ከጠላት ጋር እየተፋለመ ይገኛል!

በሌላ በኩል በሱዳን መሬት በግብፅና በምዕራባዊያኑ በከፍተኛ በጀት ሲሰለጥኑ የቆዩ በነፃ አውጭነት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በሱዳን ጦር መሪነት ለከፍተኛ ጦርነት እንቅስቃሴ ላይ ሲሆኑ በውስጥ በኩል ደግሞ ወያኔ በከፍተኛ ሕዝባዊ ማዕበል ወደ ወልቃይት ወረራ ለመፈጸም ሙሉ ዝግጅቱን እንደጨረሰ መረጃዎች ያመለክታሉና በወገን በኩል ለዚህ የሚመጥን ከፍተኛ ዝግጅት ከወዲሁ ልናደርግ ይገባናል‼️

እሳት ከተቀጣጠለ በኋላ እኔን ውሰድና ማግደህ እሳቱ ይጥፋ አዘኔታ በኋላ ፈፅሞ የማይጠቅም አዛኝነት ነው!

በምንችለው በሚጠበቅብን ነገር ሁሉ የወገንን ጦር እንደግፍ ከጎኑ እንቁም። በተለይ ለወያኔና ለግብረ አበሮቹ ጉልበት ሊሆኑ ከሚችሉ አጀንዳዎች እራሳችንን እንጠብቅ!

በነገሮች ሁሉ እንበርታ። እንፅና‼️

ድል ለታላቋ ኢትዮጵያ‼️
በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰርቶ የማይታወቅ ታሪክ በጀግኖች #የአፋር ወጣቶች እየተሰራ ይገኛል 👌ከነሱም ውስጥ አንድ ጀግና ላስተዋውቃችሁ የትምህርት ቢሮ ሺፈር የሆነው ጀግና ታጋይ አሸባሪው ጁንታው በዞን ሁለት በከፈተው ጦርነት የጀግናው የአፋር ለዩ ሃይል ቁስሎኞች ከፍተኛ ጦርነት ካለበት አከባቢ 12 ቁስለኛ ይዞ ከመጋሌ ከተማ 26 ብሬን በጁንታው ቢተኮስበትም ቁስሎኞቹን ይዞ ከመውጣት ያገደው ነገር አልነበረም ይህ ጀግና ከፊትም ከኋላም እየተተኮሰበት ቁስለኞቹ ጎማ አልቆበት በቸርኬ ዱቡቲ ሆስፒታል አድርሰዋል ይህ ጀግና ክብር ይገበዋል ። ዘመን ተሻጋሪው
እኛ ከአፍንጫችን ስር ካለ ባህር ወይም ኩሬ ዳር አልፈን የቀይ ባህር ፖለቲካ የሚያሳስበን የኢየሩሳሌም እጮኛዎች ነን‼️
ሐገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገ*ለሽ በላ ።

የሚለውን ሕዝባዊ ግጥም ዘንድሮ የገ*ሉ ሰዎች ወይም ባንዳዎች ማቀንቀናቸው የጨዋታውን ድባብ የኢትዮጵያን ሁኔታ መቀየር ችለዋል😂

ባንዳ ሆኖ አድማጭ ማግኘት መቻል ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የመጀመሪያው ፈተና ነው‼️
በነገራችን ላይ ምንም ነገር ብትፅፍ ከስር መጥተው የስድብ ናዳ የሚያወርዱ የምድጃ ዳር ወሬ ሀሜት የሚያሰራጩ ከኢትዮጵያዊ እሴት የተፋቱ በነውር አጊጠው ነውረኛ ነገር ዘወትር የሚያስተጋቡ የወያኔ የግብር ልጆች እነማን ናቸው የሚለውን እንኳን ከዚህ በፊት እርሾ ኖሯችሁ ይቅርና በአዲስ መልክ ገና ከዚህ በኋላ ስራቸውን ተከታትላችሁ ማወቅ ትችላላችሁ። ስራቸውን አይታችሁ ስለእነሱ እጁም ታዝናላችሁ። ፍፁም በራሳቸው ስራ የማይተማመኑና የማይቆሙ ሌሎችን ካልዘለፉ ሜዳው ዳገት የማይሆንባቸው ሌቱ የማይነጋላቸው እንደ ቀትር እባብ የሚቅበዘበዙ ሰዎች ናቸው።
አገር ያስቀጠለ የጀግና እረፍት
------------=---------

በቅርበት የሚያውቁት "የእኛ ኢትዮጵያ ተደፍራ አታውቅም" በሚለው ወርቃማ ንግግሩ ያውቁታል። ያ የዋግ ምድር ጥንትም እነ አርበኛ ጀነራል ኃይሉ ከበደን ለእናት አገር ያበረከተ የጀግኖች ምድር ነው። ዛሬም የእኛ ኢትዮጵያ ተደፍራ አታውቅም" እያሉ ለእናት ሀገር ብለው ራሳቸውን መስዋት የሚያደርጉ እንደ ኮሎኔል አማረ ሞላ አይነት ጀግኖች በቅለውበታል።

ጀግናው የአውደ ውጊያ የላቀ ጀግና ሜዳሊያ አንደኛ ደረጃ ተሸላሚው ኮሎኔል አማረ ሞላ አገርን ለመታደግ ከአሸባሪው ጋር ሲተናነቅ ያረፈ ጀግናችን ነው። በኮሎኔሉ መስዋትነት ኢትዮጵያ ቀጥላለች። ሀገር ያስቀጠለ የጀግና አረፍት ታሪክ ሁኖ ቀጥሏል። የኮሎኔሉ አስከሬን በዛሬው ቀን ባደገበት ቦታ ሰቆጣ እንዲያርፍ ይደረጋል።

ስለተደረገልን ሁሉ ስንዘክርህ እንኖራለን!
በተግባር የወያኔን ግብር ባለመልበስ የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ድረስ በፅናት ቆመን መከፈል ያለበትን ሁሉ መስዋዕትነት በመክፈል ኢትዮጵያን በመታደግ አስመስከረናል‼️
የወያኔ አጀንዳ ወይም ጉዳይ አስፈፃሚ ካልሆንክ በስተቀር በዚህ ፖስት እንዴት ልትናደድ ወይም ልትቃጠል ትችላለህ?!

ወይ ነውርን ጌጥ የማድረግ አባዜ‼️
ወያኔ አሁንም በፖለቲካው መድረክ አልተሸነፈም። ከፍተኛ የሆነ የፕሮፖጋንዳ ብልጫም እንደያዘ ነው።

ከሜንስትሪም ሚዲያው ይልቅ አጀንዳ ሰጭ የሆነውን የሶሻል ሚዲያን ፕላትፎርምም ለአማራ እንቆረቆራለን ለኦሮሞ ጠበቃ ነን በሚሉትና በስማቸው የተቆርቋሪነት ካባ በመደረብ፣ ሕዝባዊ አመፅ በሀይማኖት ሽፋን ጭምር በመፍጠር፣ የፀጥታ ሃይሉን ትኩረትና ስምሪት በመበታተን በቀላሉ ወደ አራት ኪሎ ሰርጎ ይገባ ዘንድ የሚያስችለውን አጀንዳ እየቀረፀ መሬት ለማስነካት የማይፈነቅለው ድንጋይ የማይወጣ ተራራ የማይወርደው ቆልቁለት አለመኖሩን እንቅስቃሴዎቹ የማይናገሩ አይደሉም። እንደ እረፍት አልባው ጥረቱ እንደ ፍላጉቱ ግን መሬት የማስያዝ አቅም መፍጠር አልተቻለውም።

ለዚህ ዋና እንቅፋቱ የመንግሥት ጠንካራ ስራ የተጠና ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን የመንግስት አለመፅናት ሐገር እንደሚያፈርስ(በአደባባይ በአዋጅ እንኳን እናፈርሳታለን እያሉት) ገና ከጅምሩ የነገሮችን አዝማሚ ተመልክቶ ውጤቱን መናገር የሚችል ስቴት ካልቸር ያለው በኢትዮጵያዊነቱ በፍጹም የማይደራደረው ሕዝብ ከፊት ቀድሞ አኩሪ ተጋድሎ በማድረጉና በነገሮች ሁሉ በፅናት መቆም በመቻሉ ነው። የወያኔ እኩይ አላማ እያከሸፈበት ያለው ራሱ ሕዝቡ ነው።

ጠላት በሐገር ቤትም ሆነ በባህርማዶ በአማራ ስም በኦሮሞ...በሌሎች ብሔሮች በተቃዋሚ ስም ለሚንቀሳቀሱት ግለሰቦችና ቡድኖች እንዲሁም በሲቪክ ማህበር ስም ለሚንቀሳቀሱት አካላት አላማውን ያስፈፅሙለት ዘንድ ከዚህ በፊት ከኢትዮጵያ ሕዝዝ በተዘረፈ ሐብትና ሐገር የማፍረስ አላውን በሚጋሩ አንዳንድ አገራትና ተቋማት ከፍተኛ ዶላር ገንዘብ እየተነሰነሰላቸው፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የወንጀል ስጋት፣ በአቅም ማነስ፣ ከስልጣኔ እነሳለሁ በሚሉትና በተነሱ አኩራፊ አመራሮች በኩል በየቀኑ በሚሰጥ የልዩነት የአመፅ ቀስቃሽ አጀንዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላው ቢቀር በአማራና በኦሮሚያ ያልተቋረጠ ብጥብጥና ሁከት መፍጠር በቻለች ነበር። ሕዝቡ ቀደማቸውና የደም ነጋዴዎቹን መንገድ ዘግቶ መፈናፈኛ አሳጣቸው።

ሕዝቡ እየሆነው ባለው ነገር የተከፋና ይበልጥ እንዲከፋ የሚፈልጉ ከውስጥና ከውጭ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ ግጭት አዳዮች እናት አገሩን ሊያፈርሱበት በስስ ጎኑ ስሜቱን ኮርኩረው ወደአመፅ ለማስገባት ተደራጅተው ቢመጡበትም (በቅርቡ ይጮሁ የነበሩ አጀንዳዎችን የምናስታውሰው ነው) የተደረገለትን ተከታታይ ውጣ ደምህን ስጥ ደም አፍስስ የእርስ በርስ ግጭትን ጥሪ ባላየና ባልሰማ ከማለፉ ባሻገር ጦር-አውርዶቹን የወያኔን የግብር ልጆችን ከእቁብ የማይቆጥራቸው መሆኑን በምላሹ አረጋግጧል። ለዛም ነው በሀይማኖቱ ስም የተጠለሉትና በአማራ ሕዝብ ስም የተቃውሞ የተቆርቋሪነት ፖለቲካ እንሰራለን የሚሉት አካላት ሕዝቡን ወደመሳደብና ወደመራገም የገቡት።

ሕዝቡ ማን ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። በምንም አይነት መንገድ ቢገለፅ በየትኛውም ቀለም ቢኳኳል የጦር-አውርዶቹ የጥሪ አላማንና ግቡን ስቴት ካልቼር ያለው ሕዝብ ስለሆነ ቀድሞ ይረዳዋል። ድባቡን ያነበዋል።
የአመፀኞቹን የወያኔ የግብር ልጆችን ጥሪ ያልሰማውም መንግስትነትን ስለሚያውቅ ነው።

ስሜቱን ያልገራ የማንም አልፎ ሂያጅ አግድም አደግ የግጭት ነጋዴ ሁሉም እንደፈለገ የሚፈነጭባት መንግስት አልባ የፈረሰች አገርን በአይኑ ማየት የሚፈልግ ሕዝብ ስላልሆነ ነው የወያኔና የግብር ልጆቹን እኩይ አላማን እየቀደመ ማክሸፍ የቻለው።

ማንም ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት ለጥፋት አላማ ወደዚህ ግባ ወደዚያ ውጣ ተቀመጥ ተነሳ ስላለ አብሮ በስሜት ፈረስ የማይጋለብ በደመነብስ በመንጋ አዝማች የማይነጉድ፣ ጥሪውን የሚያስተላልፉት ሰዎች የሞራል ልዕልና የሌላቸው መሆናቸውን ሕዝባችን በሰጠው ገቢራዊ ምላሹ አረጋግጧል።

ነገር ግን አሁንም ቢሆን ወታደራዊ ድል ማስመዝገብ ያልቻለው ተሸናፊው ወያኔ በፕሮፖጋንዳ ብልጫ የፖለቲካ ድሉን ለማስጠበቅ አጀንዳ አሻሻጮቹንና ጉዳይ አስፈፃሚዎቹን በንቃት እንዲንቀሳቀሱ ከፍተኛ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማይናወጥ ፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት የመንግስትን ስልጣን የያዘው ብልፅግና ከመቼውም ጊዜ በላይ በመንግስታዊ መዋቅሩና በውስጡ የተሰገሰጉ ብአዴንነትንና ኦህዴድነትን ለማስቀጠል የሐገርን ቁልፍ መረጃ በውጭም በውስጥም በስመ ተቃዋሚ ለተሰለፉ ነገር ግን አገር ለማፍረስ ሁሉንም ነገር አሟጠው ለተጠቀሙ የወያኔ የሕዝብ ግንኙነት ሆነው ለሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖች መረጃ የሚሸጡ የወያኔ መንገድ ጠራጊ አፍቃሬ ወያኔዎችን ከውስጡ ማጥራትና ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ተገቢ ጥያቄዎችን ሁሉ ጆሮ በመስጠት ሕዝብ መስማት የሚፈልጋቸውን ነገሮችን መናገር ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልገውን ነገር ወደመሬት አውርዶ በመስራት የመንግስትነት ኋላፊነቱን የመወጣት ታሪካዊ ግዴታ እንዳለበት ለአፍታም ሊዘነጋው አይገባም።
የአሊሚራህ ጀግኖቹ የአፋር ልጆች በጠላት ላይ ድልን እየተቀዳጁ ነው። ግፉ ወደፊት ጀግኖቹ!
ሁሉም ነገር እያለፈ ታሪክ ሆኖ እየተፃፈ የትውልድ ቅብብሎሹ ይቀጥላል። ሁሉም ነገር ባለበት ወይም አሁን ያለበትን ሁኔታ መስሎም አይቀጥልም።መንግስት የተዳከመ የመሰለበትና ሐገር የሚፈርስበት የሚመስለው(እንዲዳክምና እንዲፈርስ የሚፈልጉ ሃይሎች ጥርስ ያወጡበት ) ከባዱ የፈተና የግርግር ወቅት ያልፋል። በማያልፈው ታሪክ ውስጥ የራስን በጎ አሻራ ወይም መጥፎ ጠባሳ ጥሎ የማለፍ ምርጫው የእኛው ነው።

ማናችንም በስማ በለው በደሳለኝና በመሰለኝ በስሜት ፈረስ ጋልበን ስለአንድ ጉዳይ አቋም ከመያዛችን በፊት በቂ መረጃ ይኖረን ዘንድ በሰከነ መንገድ ነገሮችን ለመከታተልና ለመመርመር እንሞክር። መረጃ ሰብስቦ ከተነተኑ በኋላ አቋም መያዝ የሚጠበቅ ነው።ከስማ በለው ወይም ከግብታዊነት ተነስተን እንደቀልድ የምንወስነው ውሳኔ ከራሳችን አልፎ በዙሪያችን ያለን የቅርብ ሰው ጨምሮ ሊጎዳ የሚችል እንዳይሆን በማሰብ በኋላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ያስፈልገናል።

በማስተዋልና በጥበብ እንራመድ‼️