Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.41K subscribers
2.98K photos
372 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በጎንደር እስከዛሬ ከነበሩት በዓላት በተለየ መንገደ ደምቋል!

የወያኔንና የግብረ-አበሮቹን አማራን አንገት የማስደፋት ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ አላማን በተባበረ ክንዳችን አክሽፈን ቅስማቸውን በሰበርነው ማግስት በታላቅ የአሸናፊነት የኩራት ስሜት የምናከብረው በዓል መሆኑ ከእስከ ዛሬው በዓል ድምቀቱን ለየት አድርጎታል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገር ውስጥ የበረራ ታሪኩም ከፍተኛ ቁጥር ያለው በረራ ወደ ጎንደር እያካሄደ መሆኑ አዲስ ታሪክም ሆኖ እየተመዘገበ ነው!

ጎንደር በተከበሩ እንቁ እንግዶች ምሽቱን ደምቃለች!

ክብር ለዚህ ቀን ላበቁን ውድ ጀግኖቻችን በሙሉ ይሁን ብያለሁ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ!
ነገም ገና ይቀጥላል!

ክቡራን እንግዶቻችን ወደጥንታዊቷና ታሪካዊቷ እምዬ ጎንደር እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ!

መልካም ጊዜ!
ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች በመጡ በውብ የባህል ልብስ ባጌጡ የተከበሩ እንግዶች የጎንደር አደባባዮች፣ መንገዶች ሆቴሎች ሁሉ ደምቀዋል። ጎንደርን ዞር ዞር ብሎ ለተመለከተ የቀረ ሰው ያለ አይመስልም። ውበቷና ድመቀቷ ጎልቷል።

ስለቀጠናው የተወራውንና የተናፈሰውን ስጋት ከእቁብ ባለመቁጠር፣ በልበ ሙሉነት በሐገር ፍቅር በጀግንነት ስሜት ወደጎንደር በመምጣት በዓሉን ለመታደም የቻላችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በመሉ እንኳን ወደታሪካዊቷና ጥንታዊቷ የነገስታት አገር ጎንደር በደህና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን። ለእናንተ ያለን ክብር ታላቅ ነው። ኮርተንባችኋልም።

በቆይታችሁም እንደምትደሰቱ አንጠራጠርም!

መልካም የከተራ በዓል!
እናታለም እምዬ ጎንደር 🙏
ጥምቀትን በእናታለም ጎንደር!
ምሽታችን በእምዬ ጎንደር በደስታ እንደደመቀ ነው!
ከክቡራን እንግዶቻችንን ጋር መልካም ቀን አሳልፈን ምሽቱን ደግሞ ከውድ ወንድሞቼ ጋር በሙሽራዋ ጎንደር በደስታ ዘና ፈታ እያልን እንገኛለን!

ለሁላችሁም መልካም የደስታ ጊዜን እንመኛለን!
የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ርዕትህ፣ፍትህ የረቀቁባትና ፀድቀው የታወጁባት፣እንደ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት አገላለጥ የአስተዳደር ጥበብ ለዓለም የተሰበከባት፣ መፅሐፈ ሐይማኖት መፅሐፍተ ሕግጋት የተደነገገባትና የተተረጎመባት፣ የመማር ማስተማሩ ሂደት የተመሰረተባት፣ ስርዓተ መንግስት የተወጠነባትና ገቢራዊ የተደረገባት የሕግ መምህሩ የዮተር ምድር፣ ለዘመናት የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ የነገስታት አገር፣እብሪተኞች የወደቁባትና የተነፈሱባት፣ ዘመነ መሳፍንት ተጠናቆ ዘመናዊት ኢትዮጵያ በአጤ ቴዎድሮስ መሰረት የተጣለባት፣ሐገር አፍራሾች ድል ተነስተው ሐገር ሰሪዎች ከየትም ይምጡ የነገሱባትና የሚነግሱባት፣ ጥበብ መንፈሳዊና ጥበብ ዓለማዊ የተፈተሉባትና የተመሰጠሩባት የዕደ ጥበብና የኪነጥበብ ማዕከል፣በሐይማኖቱ ወይም በብሔሩ ምክንያት ማንም ያለሐጢያቱ የማይቀጣባት ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተመቻችና የተመቸሽ የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር የዜጎች አምባ ሙሽራዋ ጎንደር፣ የጥምቀት በዓልን ከመቼውም ጊዜ(በቀጠናው ስጋት የነበረና አሁንም ያልተቀየረ ቢሆንም) በተለየ መንገድ በድምቀትና በሰላማዊ መንገድ አክብራለች።

በቀጠናው በነበረውና ባለው የጦርነት ስጋት ማንም ሳይሸበርና ሳይረበሽ ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር በልበ ሙሉነት ከሐገር ውጭም በሐገር ውስጥም ከተለያዩ ክፍሎች ወደጎንደር የመጣችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በዓሉን በተለየ የደስታ መንፈስና ድምቀት በሰላማዊ መንገድ አክብራችሁ ስለተመለሳችሁ ደስታችን ወደር የለውም!

ጥምቀትን በጎንደር በደመቀ መንገድ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር፣ እንግዶቻችን በነብስም በስጋም በነበራቸው ቆይታ ሀሴት እንዲያደርጉ እሴቶቻችንን ባከበረ መልኩ በዓሉ በደመቀ መንገድ ሰላማዊ ሆኖ ሊጠናቀቅ የቻለው የደም ነጋዴ ልቡሳነ ስጋዎቹ ስላልተንቀሳቀሱና ስላልነበሩ አይደለም(እንደነሱ ምኞትና አላማ ቢሆንማ ኖሮ ሊፈጠር የሚችለውን አለማሰብ ይሻላል )። ግን አልሆነላቸውም። ምኞትና አላማቸው ከቅዥትነት ማለፍ እንዳይችል ሆኗል።
ከምንምና ከማንም በላይ ለዘንድሮው ጥምቀት ፍፁም ሰላማዊነትና ድምቀት ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ያላወለቀውና አጥብቆ የያዘው የጎንደር ሕዝብና ወጣት ለሰላሙና ለእንግዶቹ ከጀግናው የፀጥታ ሃይሉ ጋር ተቀናጅቶ ራሱ ከፊት ቀድሞ ቆሞ ያለእረፍት ሌትና ቀን በንቃትና በትጋት መስራት ስለቻለ ነው።

የከርሞ ሰው ይበለን!
ጥምቀት በጎንደር ሁሉም ነገር እጅግ ደስ ይል ነበር። የከርሞ ሰው ይበለን‼️