Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.4K subscribers
2.98K photos
372 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ባለ ከዘራው ጀግናው ብርጋዴር ጀኔራል ሻምበል በየነ እንኳን ደስ አለህ!
ብርጋዴር ጀነራል አማረ ባህታ እንኳን ደስ አለህ!

በቅርበት ከማውቃቸውና በጀግንነቱ እጅግ በጣም ከማደንቀው ቆፍጣና የጦር መኮንን አንዱ ነው!

ይገባሃል!
"አማራ ይንቀናል! ይንቀናል! ወደታች ነው የሚያዩን! በጣም ይንቀናል፣ እያልክ እንዴት 50 አመታት ታለቅሳለህ?"
(ኢሳያስ ትናንት ካደረገው ንግግር ውስጥ በጥቂቱ)👇

".... ህዳር 4 በስለላዎቻችን አማካኝነት ትህነግ ጦርነት እንደሚጀምር እርግጠኞች ነበርን።
ሚሳኤል ተኮሱብን። ኤርትራን ለመምታት ያሠቧቸው ታርጌቶች 100 ነበሩ በወያኔ ተመርጠው የተቀመጡት።

ራሣችንን የመከላከል መብታችንን ተጠቅመን ነው ወደጦርነት የገባነው። እንጂ ጦርነቱንማ 18 አመታትኮ ታግሰናል መሬታችን ተወርሮ።
በለውጡ ሰሞን ደብረጽዮንን ሁመራ አግኝቼው ሌላ ምንም አልተናገርኩትም አንድ ጥያቄ ብቻ አነሳሁለት "ለምንድነው ለጦርነት የምትዘጋጁት?" አልኩት።

በሰሜን እዝ ከ32,000 በላይ ወታደሮች ሲኖሩት ከ10,000 በላይ ወያኔዎች ነበሩ።

በአአው (83?) ኮንፈረንስ ቢያንስ የብሔር ክፍፍሉን ተውት ትግላችሁ ላይ የነበረውን ክፍፍል ያብሰዋል ብያቸዋለሁ።

4ጊዜ የህገመንግስቱን ድራፍት አንብቤዋለሁ ተቃውሞየንም ሰጥቻለሁ። ይሄ አገር አይገነባም። ይህ ህግ ethnic institutionalization ያመጣል ለኛም ለቀንዱም ጥሩ አይደለም። አሁን ተቀራርባችሁ አገር መገንባት የሚያቀራርብ እንጂ እንዴት የሚያራርቅ ነገር ትሰራላችሁ? ብየ ሀሳቤን ሰጠሁ። ቃል በቃል "እኛ መግዛት የምንፈልገው ሁሉም ቦታ ላይ ቦንብ በመትከል ነው" ነው ያሉኝ።
አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው ሁሉ በወያኔ ፕላን የተሰራ ነው፣ ባጋጣሚ አይደለም።

ኋላቀርነት፣ ርሃብ፣ ችግር secondary ነገሮች ናቸው። አገር እንድትፈርስ የመጀመሪያው ምክንያት በዘር የተዋቀሩ ተቋማት ሲቋቋሙ የሚያመጡት ችግር ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ለውጦች እኛንም ይነካሉ፣ ኢትዮጵያ ብትወድቅ የውጭ ሃይሎች መጫወቻ ነው የምንሆነው።
ወያኔን ወደ ስህተት ከወሰዱት አንዱ የውጭ ደጋፊዎች በተረጎሙት miscalculation ነው።

አሁንም ጦርነቱ አላለቀም። ስስታምና ስግብግብ የሆነ ሃይል መቸም በሰላም ሊተኛልህ አይችልም። ሰሞኑንም የጀመርነው ክተት መክት ዘመቻ ከዚህ ጋር ዳይሬክት ባይገናኝም ግን የወያኔ ወንበዴዎች አርፈው ስለማይቀመጡ ነው።

አሁን ላይ አሜሪካ በተለይ በኢኮኖሚ በቻይና ተበልጣለች። እኛና ኢትዮጵያ ላይ የምታሣድረው ጫና ያረጀው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የጀመረ የmonopolar ፖለቲካቸው ውጤት ነው። እኔን ጨንቆኝ አያቅም ምክንያቱም አቀዋለሁ የራሷ ጉዳይ ነው። የራሣቸው የፈጠሩትን ቴረሪዝም ለሌሎች ማዕቀብ መጣያ ነው ያደረጉት። ... ውሳኔያቸው ሁሉ የሚገዛው በlaw of the jungle ነው። ... በሂደት አለም አንድ እየሆነ እነሱን መታገል ይችላል።
ቀንና ሌሊት ኤርትራ እንድትጠላ ሰይጣን እንድትመስል ሲሰሩ ነበር።
ኤርትራ የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ አለባት ይሄ ለራሣችንም ሰላም ስንል የምናደርገው ነው። (😋)

... የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋሚ በአፋኙ ህወሀት የሚመራ የሚመስለው ራሱ ሞኙ ህወሀት ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊያን እኔ የሚመስለኝ በርግጥ በዘር መከፋፈሉ ያኗኑረናል ወይ? ብለው መጠየቅ አለባቸው። እኛ ሽግግራችሁ 10አመታት ይወስዳል እንደዛ አድርጉ ብለናቸው ነበር ተጣድፈው የዘር ፌደራሊዝሙ ውስጥ ገቡ ቀጥለውም አንቀጽ 39ን አስቀመጡ።
የሁሉም የኢትዮጵያ ችግር መነሻ የወያኔ ቡድን የ50 አመት ጥላቻ ነው።

አማራ ይነቀናል! ይንቀናል! ይንቀናል! amahara chauvinism እያሉ ህዝባቸውን ቀሰቀሱበት። ት*ግ*ሬ ብቻ ሳይሆን ብዙ ህዝብን የሚንቅ በጣም ትንሽ ስልጣን የነበረው ቡድን ነበረ እንጂ ያማራ ህዝብ አይደለም። በመጨረሻም ት*ግ*ሬን የተለየህ ነህ ብሎ ሌላ ኢጎ ፈጠሩበት። ይሄው አሁን ጥላቻው በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ት*ግ*ሬ ብቻውን ቀረ። ሰው እንዴት ለ50 አመታት ሙሉ ጥላቻን ማኔጅ እያደረገ ይኖራል?
ባለፉት 14ወራት ስንት ት*ግ*ሬ አለቀ? ስንቱ ተፈናቀለ? ይሄንን ኪሳራ ማወቅ አለበት የት*ግ*ሬ ህዝብ። ...
ወንዴ ብርሃኑ እንደተረጎመው
የትናንቱ ማታ የክቡር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ ምልልስ ዋና ነጥቦችን ወደአማርኛ ጳውሎስ ሶሪ እንደሚከተለው መልሶልናል!

- ደብረፂዮንን በሁመራ ለምን ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ ጠየኩት።
- ህወሓት በኤርትራ ውስጥ ከ100 በላይ ቦታዎች ላይ ኢላማ ለማድረግ ማቀዱን የሚያሳይ ማስረጃ አለን።
- የህወሓት ጀብዱ የተሳሳተ ስሌት ነበር።
- በህዳር 2020 የመጀመሪያ ሳምንት ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች የኤርትራን ድንበር አቋርጠዋል።
- የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ ይወጣል ብለን አልጠበቅንም።
- የህወሓት አመራር ከስልጣን መውጣቱን እንኳን አልጠበቀም። የውጭ አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ እንዲወጣ ግፊት ያደርጉ ነበር።
- ማንኛውም ጤነኛ ወታደራዊ አመራር ያለ ሎጂስቲክስ እስከ ኮምቦልቻ እና ደሴ ድረስ ሊገባ ባልደፈረ ነበር።
- የህወሓት የውጭ ሃይሎች በጦርነቱ ውጤት አልረኩም።
- ወያኔ በኤርትራ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከኃይለሥላሴና ከመንግስቱ ኃ/ማርያም የከፋ ነው።
- የትግራይ የነጻነት ሪፐብሊክ የለም፣ አይሆንምም።
- ወያኔ የኢትዮጵያን የተረቀቀውን ሕገ መንግሥት ከማንም በፊት እንዳነብ ሰጠኝ። ሕገ መንግሥቱ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነበር፣ እናም ቅሬታዬን አንስቻለሁ።
- ከብሄር ፌደራሊዝም ፖሊሲ የበለጠ አደጋ የለም።
- አገሪቱ አንድ ካልሆነ ለውጭ አገሮች በሉዓላዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ቀላል ነው።
- ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ አንድነት ለኒዮ-ቅኝ ገዢ አገሮች ትምህርት ሆኖ ቆይቷል።
- የአሜሪካን ህዝብ እና መንግስትን መለየት አለብን። በአለም አቀፍ ደረጃ ውድመትን የሚፈጥሩት መቶኛ ከአሜሪካ ህዝብ 0.1% እንኳን አይደለም።
- በአሁኑ ጊዜ በዩኤስኤ ውስጥ የተሰራ የለም. ሁሉም ነገር በቻይና የተሰራ ነው.
- ቻይና ሩብ የአሜሪካ ዕዳ አለባት። ዩኤስኤ በኢኮኖሚ ኃያል አገር ናት የሚለው ግምት የተሳሳተ ነው።
- ስማቸው እንጂ ኢጋድ ወይም AU የሉም። የግል ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አበላሽተውታል።
- ቻይና ምዕራባውያንን አንቀሳቅሳለች። ምዕራባውያን አገሮች ሩሲያንና ቻይናን መያዝ አልቻሉም።
- በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ ዓለም ለበጎ ነገር የተለየ ይሆናል.
- የዓለም ልዕለ ኃያል መንግሥት እንደ ኤርትራ ትንሿን አገር ለስምንት ዓመታት እንዴት ማዕቀብ ይጥላል? ይህ በእነርሱ በኩል ተስፋ መቁረጥ ነው, እኛ ለመሾም ፈቃደኛ ባለመሆኑ.
- የአሜሪካ ልዑክ ሥራ ለአገሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማዘዝ ነው።
- ሽብርተኝነት የተፈጠረው ‘በነሱ’ ነው።
- ባለፈው አመት ሲሰራጭ የነበረው 40% ዶላር በህገ ወጥ መንገድ በአሜሪካ ታትሟል።
-በአሜሪካ መንግስት ላይ 'immunity' ፈጥረናል።
- የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፖሊሲዎች እና 'የዓለም ስርዓት' የጫካ ህግ ናቸው. ተሃድሶ ተከልክሏል።
- ኤርትራን ሰይጣናዊ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።
- የአፍጋኒስታን ሰዎች ለምን ይሰቃያሉ?
- በተሞክሮአችን ምክንያት የዩኤስን ማዕቀብ መቃወም እና ማቆየት እንችላለን።
- የሰማንያ አመታት ታሪካችን ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው። የእነሱ ሰላም እና ብልጽግና ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው.
- በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው አስከፊው ነገር ወያነ ነው።
- ኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ።
- ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና አንድነት እንዲኖር የጎሳ ፌደራሊዝምን ማሻሻል ወይም ማስወገድ አለባት።
- ህወሀት ለተጋሩ ከአማራ ያነሱ መሆናቸውን በመንገር ጥላቻን እየዘራ ነበር።
-የመጀመሪያው ወያነ አስተሳሰብ ከሁለተኛው እና ከአሁኑ ወያነ የተለየ ነበር።
- ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት የሚሰቃዩት ተጋሩ ናቸው።
- አሁን በሱዳን ያለው መጥፎው የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት ነው።
በአማራ ብሔርተኝነት ፖለቲካ የተቀመጠው የጠራ የጋራ አላማና ግብ ምንድነው ? አይነኬው ቀይ መስመርስ? አንድ ሰው ቀይ መስመር አለፈ ወይም ካደ የሚባለው ምን ሲያደርግ ነው? ማን ምን ሲያደርግ ነው የእሱ/ሷ የአካሄድ እንጅ ግቡ የተለየ አይደለም አንድ መስመር ላይ ነን የሚባለው? ትግሉ የሚመራባቸው ታክቲኮች እና ስትራቴጂዎችስ ተለይተዋል ወይ? ሁሉንም ጠላት በማድረግ ካገኘው ጋር መላተም የትግሉ ዋናው ስትራቴጅ ነውን?

(አንደ ሰው ×) ... በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ የእነ እንቶኔ ልዩነት የአካሄድ (የታክቲክ) እንጂ የመሰረታዊ የትግል መስመር አይደለም የሚባለው ምን ሲፈጽሙ ነው?

የአማራ ህዝብን ትግል ዕውን ለማድረግ ስትራቴጅካል እና ታክቲካል አጋሮች እነማን ናቸው? የአማራን ትግል ሊያደናቅፉ ወይም ከህዝባችን ትግል በተጻራሪ ሊቆሙ ይችላሉ ተብለው የተለዩ ስትራቴጅካልና ታክቲካል ጠላቶች እነማን ናቸው? የአማራ ህዝብን ትግል ውጤታማ በማድረግ ሂደት ጠላቶችን ለመቀነስ ወዳጆችን ለማብዛት የተቀመጡ ስልቶች ምን ም ናቸው? እራሳቸውን የአማራ ህዝብ ታጋይ ብለው የሚያቀርቡ እህቶችና ወንድሞች ከሁሉም ጋር የሚጋጩት/የሚላተሙት በምን ምክንያት ነው? ከዚህ አዙሪት የመውጫ ቁልፉስ ምንድን ነው?

ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከሞላ ጎደል የአማረኛ ቋንቋን የመናገር፣ የመጻፍ፣ የማንበብ እና የማዳመጥ ክኀሎት ስላላቸው አማራ መስለው የአማራን ትግል ከሚቀለብሱ ወይም ለእነርሱ ዓለማ ከሚጠቀሙ ሰርጎ-ገቦች እንዴት መለየት ይቻላል?

የአማራ ብሔርተኛ ወይም ተቆርቋሪ ለመባል ዋናው መስፈርት ብልፅግናን ብአዴን ማለት ነው? ዘወትር ለአማራ የሚታገሉ እና ለኢትዮጵያ የሚቆረቆሩ ወያኔን አምርረው የሚታገሉ ሰዎችን እየመረጡ አጀንዳ በማድረግ ሲሳደቡና ሲራገሙ መዋል ነው?የሚጠቅመውስ ማንን ነው?

የብልፅግና አመራር ሆኖ ብልፅግናን ብአዴን በማለት ብአዴንን ይውደም ማለት እንዴትስ ይቻላል? ከብልፅግና ሰዎች ይህ ልዩ መብት ያላቸው እነማን ናቸው? ለምን? በብአዴንነት የሚሰደቡትስ ለምን ተለይተው ይሰደባሉ? ያለመሰደብ መብት ያላቸውስ እነማን ናቸው? በምን መስፈርት ተለዩ? ብልፅግና ይወ*ገድ ከተባለስ አስ*ገጁ ማነው? በብልፅግና መልካም ፈቃድ ወይም አቅሙን አይቶ ለዲሞክራሲው ማሳያ ንቆ ትቶት ካልሆነ በስተቀርስ የእውነት ብልፅግናን ለማክሰም የሚችል አካል ማን ነው? የትስ መሬት ላይ ሆኖ ነው ሊታገል የሚችለው? ለመሆኑ ብልፅግናን በምን መርህ የቆመ እንዴትስ ያለ ሃይል ነው የሚያስወግደው? ቅዠት ከመሆን የሚያልፍና አንድም ግለሰብ ይህን የሚያስበው እንደሌለ ይታወቃል እንጅ የእውነት ይሁን አቅሙ አለ ቢባል ብልፅግና/ብአዴንን በማስ*ገድ የአማራ ሕዝብ ሕልውና ሁለንተናዊ ጥቅም ሊረጋገጥ ይችላል ?

ብልፅግና/ብአዴን ይውደም በማለት (በእርግጥ ከእኛ ውጭ ነው የሚባለውን አመራር ነው) የተሻለ ሰው ወደብልጽግና/ብአዴን እንዳይቀላቀል ውስጥ ላይ ያለውም አንድነቱን አጠናክሮ በሞራል ለተሻለ ድል እንዳይነሳሳ ከአመት እስከ አመት ሲሰራ እየተከረመ ችግር ሲፈጠር ብአዴን የት ነህ ? ምን ትሰራለህ? አቃቂርስ አብረው የሚሄዱ ጉዳዮች ናቸውን? አያስገምትም? እስከመቼስ ይህ ቀልድ ይቀጥላል? ምን ያህልስ ይጠቅማል?

እንዲያው ብዙ ነገሮች ቢያስገርሙኝና ብአዴን የሆነ ሰው ሁሉ ሌላውን ሰው ብአዴን ሲል ስለምሰማ ታላቅ ግርምትን ቢፈጥርብኝ ጊዜ ነው!
ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ የተንበረከከው አፍቃሬ ወያኔ አሁን ደግሞ አፍቃሬ ወያኔዎችን በመጠቀመ ለአማራ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መከላከያ ከሑመራ ወጣ ሊወጣ ነው በማለት የሴራ አለ ሴራ የፖለቲካ ትንተናን ተጠቅሞ ለማጭበርበር ሌላ የሴራ ጨዋታ ለመሞከር እየጣረ ነው።


ያም ሆነ ይህ ያለኛ ፈቃድ ሊሆን የሚችል አንዳችስ እንኳን ነገር ሊኖር እንደማይችል በእርግጠኝነት ለማሳወቅ እንወዳለን!!

የኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም የሚከበረው በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድና መልካም ፈቃድ ነው‼️
"ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምትገኝበት የታሪክ አጣብቂኝ ውስጥ ለመውጣትና በአስተማማኝ ጎዳና ለመራመድ እንዲቻል ከምንጊዜውም በላይ የመላው ኢትዮጵያውያን ርብርብ አስፈላጊ መሆኑን ጠንቅቆ ይረዳል"

አብን!
እጃችን ላይ ባለ ጉዳይ ካልናቅነውና ካልፈለግነው በስተቀር ከእኛ በላይ ዋና ወሳኝ አካል ማንም ሊኖር አይችልም። ዋናው በእጅ ያለን ነገር በአግባቡ ለመጠቀም በጥንቃቄ ልንሰራ ነው የሚገባን።
እምዬ ጎንደር ጥምቀትን ለማክበር እየተሰናዳች ነው!

በዓሉን ከማክበር ጎን ለጎን ማንነታችንንና ነፃነታችን ለማስከበር ዙሪያ ገባውን ነቅተን እንጠብቅ!

መቼም ቢሆን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረግና ለአፍታም መዘናጋት እንደሌለብን ማወቅ ይገባናል‼️
የወልቃይት ሱዳን ኮሪደርን ቃኝተን ስናበቃ ወደ ደቡብ አምርተን የሞያሌ ኬንያን ኮሪደር ጎብኝተን በዚያውም ዘመድ አዝማድ ጠይቀን ተመልሰናል!

ኢትዮጵያ አሁን ያለባትን ስጋቶቿን መቅረፍ ከቻለች ልትጠቀምባቸው የሚገባ እልፍ ፀጋዎች ያሏት ሀገር መሆኗን ሰፋ አድርገን አይተናል።

ትግላችንና ጉዟችን ለከፍታና ወደከፍታ ነው!
ከሰኔ ጀምሮ ያስተጋባነውን ሀይለ ቃል ዛሬም እንደግመዋለን "የነቃ የተደራጀ የፀና ሕዝብ ያሸንፋል"!

ሰላም በመሰለ ቀን ለጦርነት መዘጋጀት ጦርነትን ለማሸነፍ ይረዳልና በረባ ባረባው ጉዳይ ከመዘናጋት ወጥተን አስፈላጊውን ሁሉ የጦርነት ዝግጅት እናድርግ‼️
ሕወሓትንና በተለያየ መንገድ ከጎኑ ተሰልፎ አማራን አንገት ለማስደፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለ የሌለ ሃይሉን የተጠቀመውን ሁሉ መቼም ቢሆን አቅም ፈጥሮ ሐገር ማፍረስ ወደማይችሉበት ደረጃ አድርሰናቸዋል። የሆነ ቦታ ላይ ወይም በሆነ መንገድ ጉዳት የማድረስ አቅም የላቸውም እንደማለት ግን አይደለምና ለዚህ ሁሌም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል። ከዚህ ውጭ ወያኔም ሆነ የግብር ልጆቹ ሰበብ እየፈለጉ ወይም ተገቢ ባልሆነ መንገድ ሁሉ የመነፋረቅ ዘወትር የመቆዘም መብታቸው የተጠበቀ ነው። ትግላችንና ፅናታችን ለከፍታ ነው!
ታላቅ የመጽሐፍ ምረቃ በመናገሻ ጎንደር ከተማ!

ግሩም ስራ ነው። በአዘጋጆቹ እጅጉን ኮርተንባችኋል!

ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ያለማቋረጥ ግፍ፣ በደልና አለም አቀፍ ወንጀል ሲፈጸምበት የነበረው የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ዐማራ ሕዝብ ትርጉም በሚሰጥ መስዋዕትነት ነፃ ወጥቷል።

ወያኔ በሕዝባችን ላይ ያደረሰው የወል ሰቆቃ ግን በሚገባ አልተሰነደም። በዚህ ቁጭት የተነሱ ስድስት ባለሙያዎች በአካባቢው ይደርስ የነበረውን ሁለንተናዊ ጭቆናና በደል ከፖለቲካ ሳይንስ፣፣ ሕግ፣ ታሪክ፣ ባህልና ኢኮኖሚ አንፃር በመተንተን ለአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ተቋማት ለማሳወቅ ያለመ፤ “የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የታፈኑ እውነታዎች” የተሰኘ መጽሐፍ ጥናትን መሰረት በማድረግ ተዘጋጅቷል። መጽሐፉ በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም በትብብር አሳትሞታል፡፡

ይህ ታሪካዊ መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ጥር 08 ቀን 2014 ዓ.ም. በመናገሻ ጎንደር ከተማ ኃይሌ ሪዞርት ምንትዋብ አዳራሽ በይፋ ይመረቃል።

በመሆኑም እርስዎ በዚህ ታሪካዊ የመጽሐፍ ምረቃ ዝግጅት እንዲታደሙ በማክበር ጠርተንዎታል።


የመጽሐፉ ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች፡-

=> ዐማራ በኢትዮጵያ ሐገረ-መንግሥት ግንባታ ያበረከተውን አበርክቶ ከታሪክ አውድ አኳያ መተንተን፤

=> ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተመሰረተው ህወሓት በዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጠረውን ሐሳዊ ትርክት በታሪክ ማስረጃዎች ዋጋ ማሳጣት፤

=> ከ1983 ዓ.ም በፊት ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የስሜን በጌምድር ጠቅላይ ግዛት አካል መሆናቸውን በሚያረጋገጡ ሰነዶች የተመሰረተ ትንታኔ ማቅረብ፤

=> ባለፉት 30 ዓመታት የህወሓት አሸባሪ ቡድን በወልቃት፣ ጠገዴና ጠለምት በዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመላ ኢትዮጵያውያን፣ ለዓለማቀፉ ማኀበረሰብና ተቋማት፣…እውነቱን እንዲውቁት ማድረግ፤

=> ህወሓት በትረ-ሥልጣኑን ከተቆጣጠር በኃላ በወልቃት፣ ጠገዴና ጠለምት በባህልና በማንነት እንዲሁም በኢኮኖሚ ላይ ያደረሰውን ምዝበራና ጥፋት መተንተን፤

=> ህወሓት ከምስረታው ጀምሮ በጫካ፣ በአገዛዝና በአሸባሪነት ዘመኑ በሕዝብ እና በሀገር ላይ የፈፀማቸውን ዋና ዋና ክህደቶች አጉልቶ ማውጣት፤

=> ጥቅምት 24 የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ ተከትሎ ነጻ በወጡት ወልቃይት፣ ጠገዴ የድኀረ-ነጻነት ሁኔታዎች ምን እንደሚመስሉ እውነታዎችን ለማሳወቅ፤

=> በቀጣይ በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ጉዳይ መሆን ስላለባቸው የሕግ፣ የፖለቲካ የማህበራዊ ውል መፍትሔዎች ዙሪያ ምክረ-ሀሳቦችን ለማቅረብ ያለመ ነው፡፡

በጥቅሉ የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የታፈኑ እውነታዎችን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ዓለማቀፉ ማኀበረሰብና ተቋማት በማሳወቅ፤ የትግሬ ወራሪ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ላደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛና ሌሎች ግፍና በደሎች ካሳ እንዲከፈል በማስገደድ ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ወደቀደመ እናት ግዛታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ያለመ ታሪካዊና ዘመን ተሻጋሪ መጽሐፍ ነው!!

በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች፣ የአደባባይ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋጊ ግለሰቦች በተገኙበት መጽሐፉ ይመረቃል፤ ምሁራዊ ውይይትም ይካሄዳል፡፡

በዚህ የመጽሐፍ ምረቃ መርሐ-ግብር እንድትታደሙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡

የመጽሐፉ አሰናጆች፡-
1) ሲሳይ ምስጋናው (ዶ/ር)
2) ዓለማየሁ እርቅይሁን (ዶ/ር)
3) ጌታቸው ሽፈራው
4) ቴዎድሮስ ታደሠ
5) ጎሹ አለበል
6) ሙሉዓለም ገ/መድኀን ናቸው፡፡
ጥምቀትን በታሪካዊቷና በታላቋ ጎንደር እናከብራለን! ጎን ለጎን ማንነታችንንና ነፃነታችንን የሐገር ልዑላዊነታችንንና የግዛት አንድነታችንን የሚያስከብርና የሚያስጠብቅ ስራዎችን እንሰራለን!

በጣም ከማከብራቸውና ከምወዳቸው ከአርቆ አሳቢዎቹ ውድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወንድሞቼ ከሕግ ባለሙያው Andualem Buketo Geda እና ኢ/ር Tesfaye K Ali Faris ጋር!


ጥምቀትን ኑ በእምዬ ጎንደር እናሳልፍ፤ ስለቀጠናው ሁኔታም በአካል በመገኘት በተጨባጭ መረጃ በቂ ግንዛቤ እንፍጠር!

በበዓሉ ይዘናጉልኛል ብሎ የሚያስበውና የበዓሉን ድምቀት ለማደብዘዝ በተለያዩ ግንባሮች ትንኮሳ እያደረገ በመሆኑ እንዳንዘናጋም ከዋናው ጉዳይ ለአፍታም ትኩረታችንን ማንሳት የለብንም!

ትግላችንና ፅናታችን ለከፍታ ነው!

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ የተባበረ ክንድ ነፃነቷን አስከብራ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!
የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በጎንደር እስከዛሬ ከነበሩት በዓላት በተለየ መንገደ ደምቋል!

የወያኔንና የግብረ-አበሮቹን አማራን አንገት የማስደፋት ኢትዮጵያን የማፍረስ እኩይ አላማን በተባበረ ክንዳችን አክሽፈን ቅስማቸውን በሰበርነው ማግስት በታላቅ የአሸናፊነት የኩራት ስሜት የምናከብረው በዓል መሆኑ ከእስከ ዛሬው በዓል ድምቀቱን ለየት አድርጎታል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገር ውስጥ የበረራ ታሪኩም ከፍተኛ ቁጥር ያለው በረራ ወደ ጎንደር እያካሄደ መሆኑ አዲስ ታሪክም ሆኖ እየተመዘገበ ነው!

ጎንደር በተከበሩ እንቁ እንግዶች ምሽቱን ደምቃለች!

ክብር ለዚህ ቀን ላበቁን ውድ ጀግኖቻችን በሙሉ ይሁን ብያለሁ!