Thomas Jejaw Molla - ቶማስ ጀጃው ሞላ
6.4K subscribers
2.98K photos
372 videos
1 file
31 links
No pain No gain
Download Telegram
ስለ እኔና ስላንቺ ነፃነት ሰላምና ደህንነት ስለእናት ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ክብር በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ ለምትገኙ የእናት ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ጀግኖች ስለሁላችንም አለኝታዎቻችን ከሁሉም አስቀድሜ ከማንም በላይ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ!

ማህፀነ ለምለሟ እናት ኢትዮጵያ ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በእልፍ ጀግኖች ልጆቿ የተባበረ ክንድ የገጠማትን ፈተና በአንፀባራቂ ድሎች ትሻገረዋለች‼️

በዓልን ከማክበር ጎን ለጎን ማንነታችንንና ነፃነታችንን ለማስከበር በሰሜን አካባቢ ለጥፋት እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው የሕልውናችን ስጋት ከሆነው ዘላለማዊ ደመኛ ጠላታችን አይናችንን ለአፍታም ቢሆን መንቀል የለብንም‼️

መልካም በዓል!
መልካም ልደት‼️

በበዓለ ልደቱ ኢትዮጵያዊያን ያገኘናትን ስጋ ጠብሰን በልተን በዓልን እያሳለፍ ይሆናል። ነገር ግን ለዚህ ቀን እንድንበቃ በተለይ ብዙ የአማራ ክልል አካባቢዎች የነበረው ህዝባችን ከአሸባሪው ወረራ ነጻ ለማውጣት ስጋቸው በአረር ተቃጥሎ በየህክምና መስጫ ተቋማት ያሉትን እና ዛሬም ገላቸው በቁር እና በሀሩር እየተጠበሰ በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ ሆነው ስለእኛ የሚጎሳቆሉ ጀግኖቻችንን ውለታ ማስታወስ አለብን። የቆሰሉትን ለማስታመም ፣ ለተሰውት ምህረት ለመለመን፣ ቤተሰብ ሲረዳ ለማጽናናት እና በግንባር ላሉት ደጀን ለመሆን ከመቸውም ጊዜ በላይ ታጥቀን ለመነሳት ቃል የምንገባበት እለት ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው‼️
እስካሁን ቢሆኑ ብለን የምናስባቸውና የምንመኛቸው ነገሮች ሳይዛነፉ በስኬትና በድል መስመራቸውን ጠብቀው በመሄዳቸው እጅጉን ደስተኞች ነን። በፀናው ትግላችንም የጠላትን ሴራ አሸንፈነዋል። ወደከፍታው የጀመርነው ጉዞም በማንም በየትኛውም ምድራዊ ኃይል ፈፅሞ ወደኋላ ላይመለስና ላይደናቀፍም ቀጥሏል።

ገና ብዙ ሰርፕራይዞች ይኖሩናል‼️
ይህ ጦርነት እኛን አይመለከትም ጦርነቱ የአብይና የሕዋሓት ነው፤ ምንም እንኳን በአደባባይ በአዋጅ ወያኔ ከአማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ቢልም ማንም አማራ በጦርነቱ እንዲሳተፍ አንፈልግም እያለ ሲለፍፍ የነበረው አፍቃሬ ወያኔን በሙሉ መቼም ቢሆን ነብስ እንዳይዘራ አድርገን ወደአፈርነት እንቀላቅለዋለን ሳይሆን ቀላቅለነዋልም‼️

የጦርነቱ ባለቤቶችና አሸናፊዎች ስለቀጣዩ ሁኔታ ለሐገርና ለሕዝብ ይጠቅማል ያሉትን የተጠና እርምጃ ይወስናሉ። መወሰንም ጀምረዋል‼️
የሕልውና ጦርነቱን በባለቤትነት ይዛችሁ አቅማችሁ በፈቀደ ልክ ከመጀመሪያው እስከአሁን በፅናት ቆማችሁ የምትችሉትን ሁሉ እረፍት አጥታችሁ የደከማችሁ የታገላችሁ ወገኖች በመንግሥት ውሳኔ ላይ የማጉረምረም የመጠየቅ የመቆጣት ማብራሪያ የመጠየቅ መብታችሁ መብታችን የተጠበቀ ነው! ተገቢም ነው! ከዚህ ውጭ ያላችሁ አፍቃሬ ትልነጋዊያን ግን አደናግራችሁ የምታልፉ መስሏችሁ ተሸወዳችሁ እንጅ የአማራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ተፀፅታችሁ ይቅርታ በመጠየቅ ንስሃ ከመግባት ውጭ ሌላ የመዳን አማራጭ የላችሁም!

መንግስት እነ ስብሐት ነጋን ለመፍታት የወሰነውን ውሳኔ እነስብሓትን ከእስር ቤት ለማስወጣት፣ ወያኔን አዲስ አበባ ለማስገባት የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደጥልቅ ጨለማ መልሶ ለማስገባት ሁሉንም ነገራቸውን 24/7 አሟጠው የተጠቀሙት የአማርኛው ክንፍ የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ የበላይ አዛዦችና አባላት ዛሬ ተመልሰው ራሳቸውን እንደ ሕዝብ ተቆርቋሪ ያለምንም መሸማቀቅም...በብለናችሁ ነበር እና በእነ እንትናም... ብለዋችሁና ብለውን ነበር ባንዳነታቸውን ከመሸፈን ባለፈ አሁንም የወያኔን አጀንዳ በማሻሻጥ እስከመጨረሻው የፀና ድጋፍና አቋማቸውን ለማሳየት እየሞከሩ ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ተክደሃል በማስባል እሪታቸውን በማቅለጥ ድንኳን አስጥለው ነጠላ አዘቅዝቀው ንፍሮ ቀቅለው ሆድ ለማስባስ የተካኑበትን እዬዬ በአዲስ ሞራል ጀምረዋል።

አመቱን በሙሉ ያለ ስሙ ስም እየሰጡ ሲያጠለሹት የከረሙትን ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንንም እንደተለመደው በሴራ አለ የሴራ ጉንጎናቸው ተገልብጠው የሰራዊቱን የመዋጋት ሞራል ለማደብዘዝ የአዞ እንባቸውን እያፈሰሱ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ለሐገር ብሎ አንድያ ነብሱን የሰጠበትን ጦርነት አብይ ውሃ ቸለሰበት መከላከያችንም በፋሽስቱ አብይ ተከዳብን በማለት አዛኝ መሳይ ቅቤ አኝጓችነታቸው ቀጥለዋል።

እነዚህ አካላት ሰሜን ዕዝ በወያኔ ሲጠቃ ራሱን መከላከል የማይችል መከላከያ ሰራዊት እንዴት የኢትዮጵያን ሕዝብ ደህንነት ሊከላከል ይችላል? መከላከያ ትግራይ ክልልን ሲቆጣጠር የትግራይ እናቶች እህቶች ተደፈሩብን ምን አይነት ዲስፕሊን የሌለው መከላከያ ነው? እያሉ ከመጀመሪያው ጀምሮ በስመ የአማራ ተቆርቋሪነት ካምፕ ከመንቀሳቀሳቸው በቀር በግብር ከወያኔ እንደ አንዱ አለመሆናቸውን አላሳዩንም።
በዚህ የሕልውና ጦርነትም በየጊዜው መከላከያ አማራን ካደ በተገኘበት እርምጃ ይወሰድበት (ምኞት ባይከለከልም መሬት ላይ አቅም ከየትም ሊያገኙ ባይችሉም ) እያሉ ወጣቱን በመከላከያ ላይ ለማነሳሳት ሕዝቡ በጥርጣሬ ደጀንነቱን እንዳያሳይ ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ልዩሃይሉ መከላከያውን ሚሊሻው መከላከያውን ፋኖ መከላከያውን በጥርጣሬ እንዲመለከተው ከቻለ እርስ በርስ እንዲተኳኮስ ያልተዘራ የልዩነት የሴራ አጀንዳ አልነበረም።ብዙ ከተሞችን በማሸበር እስከ ደብረ ሲና ድረስ ለመያዝ የተደረገው የጠላትነት ስራና አዲስ አበባን ለመያዝ ጫፍ ደርሰናል የተባለው አለቀ የተባለው ጦርነትም በግንባር በሚፈፀም ጀግንነት ሳይሆን በሴራ አለ ሴራና በሽብር ወሬ ነበር መጨረስ ታስቦ የነበረው። አብይ ወደ ዱባይ ወይስ ወደኤርትራ የሚለውን ካልሆነ መፈርጠጡን አረጋግጠው ሲነግሩን የነበሩ ሰዎች በአብይ ወደግንባር መፈርጠጥ(መዝመት) ሙሉ በሙሉ የጦርነቱ ድል ከመቀልበሱም በላይ አፍቃሬ ትህነጎች አንገታቸውን ለመድፋት መገደድ ግድ ሆነባቸው እንጅ።

የአማርኛው ክንፍ የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ የበላይ አዛዦችና አባላቶች በመቀናጀት ከወያኔ ተልዕኮ በመቀበል ወያኔን በገመድ ጎትተው አዲስ አበባ ለማስገባት ያደረጉት የሴራ አለ የሴራ ትንተና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደብረት በፀናው የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያዊያን አንድነትና የተባበረ ክንድ ተበጣጥሶ ተንበርክከዋል።
ለሰላም ብለን ነው የወጣነው እንጅ ተሸንፈን አይደለምን የወያኔን የሽንፈት ማስቀየሻን የደጋፊዎቹን ማፅናኛን በመቀበል አብሮ ለማስተጋባት ከመሞከር ውጭ ሌላ ምርጫ የላቸውምና ይሄንኑ የመደጋገም መብታቸው የተጠበቀ ነው።
ለዚህ የጥፋት ሃይል የትናንቱ የመንግስት ውሳኔ የሞኞች ጆሮ ካገኘና ጥሩ ማደንዘዣና ማታለያ መሸወጃ አጀንዳ ሊሆናቸው ይችላል። ለተለመደው የተክደናል ጨዋታ ጥሩ ማጫወቻ ካርድ ይሆናልና።

መታወቅ ያለበት ወያኔ በስውር በማኒፌስቶው ሳይሆን በአደባባይ በአዋጅ ነው "ከአማራ ጋር ሒሳብ አወራርዳለሁ፤ ኢትዮጵያንም ለማፍረስ ሲኦልም ድረስ እወርዳለሁ" ያለው። ይህን የሞት የጭፍጨፋ አዋጅ ወያኔ እየነገረ ሲመጣ ለእኛ አይደለም ቢሆንም ግድ የለንም። አማራም ይጎሳቆል፣ አንገት ይድፋ፣ ኢትዮጵያም ትፈራርስ ያለው ሁሉ ዛሬ ደርሶ ጦርነቱን በባለቤትነትና በድል አድራጊነት ከፊት ቀድሞ እየመራ የዘመተ ይመስል ስንት መስዋዕትነት የከፈልነበትን ጦርነት አቦይ ስብሓትን በመፍታት አይጠናቀቅም እያለ አካኪ ዘራፍ ለማለት የሚሞክረውን አካሄድ ቀዳዳ መንገድ አንሰጠውም።

ስለ ጦርነቱ ስለ ድርድር አስፈላጊነት ለመወሰን አይደለም ሐሳብ ለመስጠት ባለሙሉ ስልጣን ጦርነቱን በባለቤትነት በቅንነት የተመለከተውና የያዘው ወገን ብቻ ነው የሚችለው። ጦርነቱ እንደማይመለከተው ከመግለፅ ባለፈ ሌሎችን አትዝመቱ (ማስቀረት ባይችልም) ያለና በዘመቱት ሰዎች ላይ አቃቂር እያወጣ አፉን ሲከፍት የነበረና የስነልቦና ጦርነት የከፈተው ውሪ ሁሉ ጦርነቱ በምን መልኩ በድርድር ወይስ መቀሌ ገብተን አሁን በቆምንበት ላይ ሆነን ወይስ ቆላ ተንቤን ገብተን ይጠናቀቅ ስለሚለው የመወሰን መብት ፈፅሞ የለውም።
በወሎ በራያ ጥሙጋና በግዳን ወረዳ በኩል ወረራ ከፈፀመው ጠላት ጋር ጀግናው የወገን ጦር ከፍተኛ ውጊያ እያደረገ ነው። በወልቃይት በኩልም በትናንትናው ዕለት ንስሩ አየር ሃይላችን ጠላትን እንደቅጠል ሲያረግፈው ውሏል። መንግስት እነ ስብሐትን የፈታበት መንገድ ፍፁም የሚያቃጥልና ያልተጠበቀ ስለሆነ ስለጉዳዩ ማብራሪያ ሊሰጥበትም ይገባል። ጠላት ወያኔም አጀንዳውን ከግብር ልጆቹ ጋር ተቀናጅቶ ለሚፈልገው አላማ ፍሬም አድርጎ እየተጠቀመበትም ነውና ተሎ መላ መባል አለበት። ጦርነቱን በድል ለመደምደም የእኛ ሙሉ ትኩረት አሁንም ዋናው ጠላታችን ወያኔ ላይ ይሁን። ወልቃይት ራያ ላይ ይሁን!
ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ሁለንተናዊ ጥቅም መከበር የእውነት የሚገደንና አላማችን ይህ ተሳክቶ ማየት ነው ፍላጎታችን። ሌሎቻችንም የምንፈልገው ከዚህ የተለየ ካልሆነ ፖለቲካችን ከጣና ዳር ወጥቶ ቀይ-ባህርን መመልከት መጀመር አለበት። ቀጣናዊ እና አለማቀፋዊ ጂኦፖለቲክሱን ያጢን። የፖለቲካ ዳይናሚዙን ይረዳ። የተፈጠሩና ሊፈጠሩ የሚችሉ ነገሮችን በጥበብና በማስተዋል በመገምገም ጠላት በመቀነስ ወዳጅ በማብዛት ወደፊት ለመራመድ ይሞከር።

ከምንም በላይ በዚህ ሶስት አመት የነበረው ወያኔ መሩ የአማራ ብሔርተኝነት የሳይበር ትግል ብቻ ነው። መሬት በሌለ እንዲሁ በአየር ላይ በባዶ ቀረርቶና ሽለላ ኒውክሌር እንደታጠቀ ምጡቅ ኃይል በስሜት በመገንፈል ብዙ ነገሮችን ሲያበላሽ ቆይቷል። ስለሆነም የአማራው ፖለቲካ በሌሎች ብሔሮች በስጋት እንዳይታይ ለጥፋት የተዘጋጀ መስሏቸው ለጥፋት እንዳይደራጁና እንዳይዘጋጁ ሊያደርግ የሚችል የሰከነ መሬት የነካ ከተጨባጩ ሁኔታ ጋር አብሮ መራመድ የሚችል ብልህነት መላብስ አለበት።

ራስህን ልታፅናናበት ወይም ልታጃጅልበት ካልሆነ በስተቀር የወያኔን ስትራቴጅ በመከተል ግብሩን በመውረስ ከአማራ እሴት በመፋታት አላማ በሌለው ነገር ተዘፍቀህ በመንቦጫረቅ ማንንም አካል በሩቁ ሆነህ በስድብ የመርገም ናዳ በማውረድ ከሁሉም ጋር በመናከስ ፈፅሞ ማሸነፍ አትችልም። ጠላት ባልከው አካል ጥግ ያለውን ወገንህን ከማስጨረስ ያለፈ ፋይዳ የለውም። የመጣንበት የሶስት አመቱ የጩኸት እና የተናካሽነት መንገድ የምርቃናና የሞቅታ መንገድ ስለሆነ አንድ ኢንችም ወደፊት መራመድ አይቻልም።
በስብሓት ነጋና በሱ የቅርብ ሰዎች ከእስር ቤት ተነጥሎ መፈታት ከአማራ ይልቅ ትልቅ ኪሳራ የሚያደርሰው በወያኔ ላይ ነው። ከሰራው ወንጀልና ከአማራ ጠልነቱ አንፃር የስብሓት ነጋ ከእስር ቤት መውጣቱ መላው አማራንና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ማስቆጣቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ውሳኔው ወሽመጣቸውን የቆረጠው የተከዜ ማዶ ሰዎች ነው። ህወሓቶች ያልጠበቁት ነገር ስለሆነ ቅስማቸውን የሚሰብር የማይታረቅ መከፋፈልን እንደሚፈጥር በመስጋታቸው ሌሊቱኑ በወሎ እና ጎንደር አዲስ ጦርነት ከፍተዋል። የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፅሑፍም የሚያመላክተው በወያኔ ጓዳ ሕመም መኖሩን ነው። ከሌሎቹ የወያኔ ሰዎች ጽሁፎች መረዳት እንደቻልነው የስብሃት ቤተሰብ ከሺዎች የህወሓት እስረኞች ተነጥሎ መፈታት ለዛውም በፍፁም ባልተጠበቀ ሰዓት ችግር እንደፈጠረ የሚያሳይ ነው።

ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ትልቁ ግብ የሕወሓት መዳከም ከተቻለ መክሰም እንጅ አንድ ሐሙስ የቀረው ስብሓት ነጋ ከእስር ቤት መለቀቅ አይደለም። ስብሓት መፈታት ባይገባውም ለአማራ ግን የተለየ ስጋት ሊሆን የሚችል ሰው አይደለም። ፈፅሞ።

ሊያጠፋን በእብሪት የተነሳን ጠላት ማስተንፈስ፣ ማንበርከክ እና እጣፈንታውን በራስህ እጅ ማድረግ መቻልን የሚመስል አሸናፊነት የለም። እንደ ስዩም መስፍን ወይም አባይ ፀሓዬ ገ*ሎ መጣል ይቻል ነበር። ሞት ለማናችንም የማይቀር ፀጋ ስለሆነ እንደ ስብሀት ያሉ ሰዎችን ከመግደል እንዲህ አቆይቶ የራሳቸውን ቡድን ለማዳከም መጠቀሙ ብልህነት ነው።

እምዬ ሚኒሊክ የጣልያን ምርኮኞችን በፈረስ ተንከባክበው የሸኙት ጠላት ስላልነበሩ ወይም ስለማይሆኑ አልነበረም። ንጉስ ጦናንና ንጉስ ተክለሃይማኖትን በከፍተኛ ጦርነት አሸንፈው ምህረት ከማድረግ አልፈው መልሰው የሾሟቸው በጠላትነት ስላልተዋጉ አልነበረም። ማሸነፍ ማለት ትርጉሙ ጠላትን አገልጋይ ማድረግም ስለሆነ ነው። አለም ላይ የተደረጉ ጦርነቶች መጨረሻቸው ድርድርና ሰላም መፍጠር መሆኑን ማንም የሚስተው ጉዳይ አይደለም። በእኛ ሐገር ያለውና ወደፊት የሚኖረውም የጦርነቱ መደምደሚያ አዲስ ክስተት ይዞ ሊመጣ አይችልም። በጦርነት ያሸነፈ አካል ያሸነፈውን እጣፈንታ መወሰን የሚያስችል የአሸናፊነት ማንበርከኪያ ቁልፍን በእጁ ላይ ከማስገባት በላይ አሸናፊነት ወይም የድል ማድመቂያ የለም!

የስብሓት ነጋ መፈታት እንደማንኛውም አማራ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ክፉኛ ቢያስቆጣኝም ቀጣዩን ወደመመልከት ተሸጋግሬያለሁ!
ሕወሓት ያለ ጦርነት ግጭት ሕልውና የሌለው አካል ሆኖ ይቅርና ባይሆን እንኳን በትግራይ ክልል የሚነሳበትን ሕዝባዊ ጥያቄ ለመመለስና ለማስተዳዳር የሚያስችል ሁኔታና ቁመና ላይ አይደለምና ጦርነት መክፈቱ የሚጠበቅ ነው። በጦርነት ውስጥ ራሱን ለመደበቅ መሞከሩን አጠናክሮ ይቀጥላልና ሁላችንም ትኩረታችንን ጦርነቱ ላይ በማድረግ ለአፍታም ሳንዘናጋ የተለመደውን ታሪካዊ ኋላፊነታችንን የመወጣት አሻራችንን ማሳረፍ ይገባናል!
በነገሮች ሁሉ እንበርታ! እስከመጨረሻውም በፅናት እንቁም!
by አይቸው ሰንደቅ
እኔ ሁሌም ትግሌ በመርህና በዓላማ ነው። ህወሓትን ስታገል፣ መንግስትንም ስቃወም በመርህ ነው።

ያልገባኝ ነገር በአማራ ፓለቲካ ትግልና ብሔርተኝነት ውስጥ ሆናችሁ እያለ ለህወሓት በባንዳነትና ከሃዲነት ስሰሩ የነበራችሁ፣ በዚህም አማራን ያስወረራችሁ ለምን የህወሓት አባት ሲፈታ እንደምትቃወሙ ነው ያልገባኝ። የሚከተለውን ስሰሩ ነበር ብየ ነው፣ ከፌስቡክ ከገጻችሁ ካላጠፋችሁት ብዙውን በግልጽ በይፋ በህዝብ ፊት በአደባባይ የጻፋችሁት ነው፣ ጥቂቱን ልጥቀስ:-

1/ ጦርነቱ ለአብይ ስልጣን ነው
2/ ጦርነቱ በህወሓትና አብይ መካከል ነው
3/ አራት ኪሎ ያለው ኦነግ ነው፣ አብይ እነግ ነው፣ ከህወሓት ጋር እናስወግደው
4/ ከአብይ/ ኦነግ ህወሓት ይሻለናል
5/ የሰሊጥ ፓለቲካ (ወልቃይት)
6/ ለቁራሽ መሬት (ወልቃይት፣ ራያ) ብለን ከህወሓት ጋር አንዋጋም
7/ እነ አምባቸው - የአማራ መሪዎች እንኳን ተገደሉ (ህወሓትን የታገሉ መሪዎች መሆናቸው ይታወቃል)
8/ ለእነ አምባቸው -የአማራ መሪዎች ፍትህ አያስፈልግም፣ ፍትህ አጠይቁ እውነቱ አይውጣ (ህወሓትን የታገሉ መሪዎች መሆናቸው ይታወቃል)
9/ ጦርነቱ የአምቻ ፓለቲካ ነው፣ አይመለከተንም
10/ ብልጽግና፣ ኢዜማ፣ አብን በህወሓት ተሸንፈዋል፤ አህወሓት ጋር የሽግግር መንግስት እንመስርት
11/ ብልጽግና ተሸንፏል፣ ባህር ዳር የክልሉን መንግስት እንረከብ፤ ከህወሓት ጋር ተባብረን የክልሉን መንግስት እንረከብ
12/ መከላከያ ከድቶናል
13/ መከላከያ ኦነግ ነው
13/ ሴራ አለ፣ አማራ መዋጋት የለበትም
14/ የአማራ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አትወጋ
15/ ወጣቱ መሳሪያ ከመከላከያ ተቀበል/ቀማ
16/ ከህወሓት ጋር እንደራደር
17/ ብልጽግና ተሸንፏል፣ ያለቀ ጉዳይ ነው፣ ለወደፊቱ መነጋገር ይሻላል
18/ ህወሓት ደብረ ሲና ስደርስ ለህዝብና ለሀገር የሚታገሉት ላይ መሳለቅ
19/ በህወሓት ወረራ በተፈናቀሉት ላይ መሳለቅ
20/ በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ ከህወሓት ጋር እያደረገ ያለው ትግል ላይ የመጎተት የመከፋፈል የመበተን ስራ በመስራት አማራን ማስወረር ስትሰሩ ነበር።

እና፣ እናንተ፣ በአቦይ ስብዓት መፈታት ልትደሰቱ ሲገባ ለምን ትቃወማላችሁ/ለምን ይከፋችኋል⁉️ ወይስ የምትፈልጉትን አታውቁም፣ አቋም የላችሁም⁉️ Check yourself‼️
ባለ ከዘራው ጀግናው ብርጋዴር ጀኔራል ሻምበል በየነ እንኳን ደስ አለህ!
ብርጋዴር ጀነራል አማረ ባህታ እንኳን ደስ አለህ!

በቅርበት ከማውቃቸውና በጀግንነቱ እጅግ በጣም ከማደንቀው ቆፍጣና የጦር መኮንን አንዱ ነው!

ይገባሃል!
"አማራ ይንቀናል! ይንቀናል! ወደታች ነው የሚያዩን! በጣም ይንቀናል፣ እያልክ እንዴት 50 አመታት ታለቅሳለህ?"
(ኢሳያስ ትናንት ካደረገው ንግግር ውስጥ በጥቂቱ)👇

".... ህዳር 4 በስለላዎቻችን አማካኝነት ትህነግ ጦርነት እንደሚጀምር እርግጠኞች ነበርን።
ሚሳኤል ተኮሱብን። ኤርትራን ለመምታት ያሠቧቸው ታርጌቶች 100 ነበሩ በወያኔ ተመርጠው የተቀመጡት።

ራሣችንን የመከላከል መብታችንን ተጠቅመን ነው ወደጦርነት የገባነው። እንጂ ጦርነቱንማ 18 አመታትኮ ታግሰናል መሬታችን ተወርሮ።
በለውጡ ሰሞን ደብረጽዮንን ሁመራ አግኝቼው ሌላ ምንም አልተናገርኩትም አንድ ጥያቄ ብቻ አነሳሁለት "ለምንድነው ለጦርነት የምትዘጋጁት?" አልኩት።

በሰሜን እዝ ከ32,000 በላይ ወታደሮች ሲኖሩት ከ10,000 በላይ ወያኔዎች ነበሩ።

በአአው (83?) ኮንፈረንስ ቢያንስ የብሔር ክፍፍሉን ተውት ትግላችሁ ላይ የነበረውን ክፍፍል ያብሰዋል ብያቸዋለሁ።

4ጊዜ የህገመንግስቱን ድራፍት አንብቤዋለሁ ተቃውሞየንም ሰጥቻለሁ። ይሄ አገር አይገነባም። ይህ ህግ ethnic institutionalization ያመጣል ለኛም ለቀንዱም ጥሩ አይደለም። አሁን ተቀራርባችሁ አገር መገንባት የሚያቀራርብ እንጂ እንዴት የሚያራርቅ ነገር ትሰራላችሁ? ብየ ሀሳቤን ሰጠሁ። ቃል በቃል "እኛ መግዛት የምንፈልገው ሁሉም ቦታ ላይ ቦንብ በመትከል ነው" ነው ያሉኝ።
አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው ሁሉ በወያኔ ፕላን የተሰራ ነው፣ ባጋጣሚ አይደለም።

ኋላቀርነት፣ ርሃብ፣ ችግር secondary ነገሮች ናቸው። አገር እንድትፈርስ የመጀመሪያው ምክንያት በዘር የተዋቀሩ ተቋማት ሲቋቋሙ የሚያመጡት ችግር ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ለውጦች እኛንም ይነካሉ፣ ኢትዮጵያ ብትወድቅ የውጭ ሃይሎች መጫወቻ ነው የምንሆነው።
ወያኔን ወደ ስህተት ከወሰዱት አንዱ የውጭ ደጋፊዎች በተረጎሙት miscalculation ነው።

አሁንም ጦርነቱ አላለቀም። ስስታምና ስግብግብ የሆነ ሃይል መቸም በሰላም ሊተኛልህ አይችልም። ሰሞኑንም የጀመርነው ክተት መክት ዘመቻ ከዚህ ጋር ዳይሬክት ባይገናኝም ግን የወያኔ ወንበዴዎች አርፈው ስለማይቀመጡ ነው።

አሁን ላይ አሜሪካ በተለይ በኢኮኖሚ በቻይና ተበልጣለች። እኛና ኢትዮጵያ ላይ የምታሣድረው ጫና ያረጀው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የጀመረ የmonopolar ፖለቲካቸው ውጤት ነው። እኔን ጨንቆኝ አያቅም ምክንያቱም አቀዋለሁ የራሷ ጉዳይ ነው። የራሣቸው የፈጠሩትን ቴረሪዝም ለሌሎች ማዕቀብ መጣያ ነው ያደረጉት። ... ውሳኔያቸው ሁሉ የሚገዛው በlaw of the jungle ነው። ... በሂደት አለም አንድ እየሆነ እነሱን መታገል ይችላል።
ቀንና ሌሊት ኤርትራ እንድትጠላ ሰይጣን እንድትመስል ሲሰሩ ነበር።
ኤርትራ የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ አለባት ይሄ ለራሣችንም ሰላም ስንል የምናደርገው ነው። (😋)

... የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋሚ በአፋኙ ህወሀት የሚመራ የሚመስለው ራሱ ሞኙ ህወሀት ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊያን እኔ የሚመስለኝ በርግጥ በዘር መከፋፈሉ ያኗኑረናል ወይ? ብለው መጠየቅ አለባቸው። እኛ ሽግግራችሁ 10አመታት ይወስዳል እንደዛ አድርጉ ብለናቸው ነበር ተጣድፈው የዘር ፌደራሊዝሙ ውስጥ ገቡ ቀጥለውም አንቀጽ 39ን አስቀመጡ።
የሁሉም የኢትዮጵያ ችግር መነሻ የወያኔ ቡድን የ50 አመት ጥላቻ ነው።

አማራ ይነቀናል! ይንቀናል! ይንቀናል! amahara chauvinism እያሉ ህዝባቸውን ቀሰቀሱበት። ት*ግ*ሬ ብቻ ሳይሆን ብዙ ህዝብን የሚንቅ በጣም ትንሽ ስልጣን የነበረው ቡድን ነበረ እንጂ ያማራ ህዝብ አይደለም። በመጨረሻም ት*ግ*ሬን የተለየህ ነህ ብሎ ሌላ ኢጎ ፈጠሩበት። ይሄው አሁን ጥላቻው በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ት*ግ*ሬ ብቻውን ቀረ። ሰው እንዴት ለ50 አመታት ሙሉ ጥላቻን ማኔጅ እያደረገ ይኖራል?
ባለፉት 14ወራት ስንት ት*ግ*ሬ አለቀ? ስንቱ ተፈናቀለ? ይሄንን ኪሳራ ማወቅ አለበት የት*ግ*ሬ ህዝብ። ...
ወንዴ ብርሃኑ እንደተረጎመው
የትናንቱ ማታ የክቡር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ ምልልስ ዋና ነጥቦችን ወደአማርኛ ጳውሎስ ሶሪ እንደሚከተለው መልሶልናል!

- ደብረፂዮንን በሁመራ ለምን ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ ጠየኩት።
- ህወሓት በኤርትራ ውስጥ ከ100 በላይ ቦታዎች ላይ ኢላማ ለማድረግ ማቀዱን የሚያሳይ ማስረጃ አለን።
- የህወሓት ጀብዱ የተሳሳተ ስሌት ነበር።
- በህዳር 2020 የመጀመሪያ ሳምንት ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች የኤርትራን ድንበር አቋርጠዋል።
- የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ ይወጣል ብለን አልጠበቅንም።
- የህወሓት አመራር ከስልጣን መውጣቱን እንኳን አልጠበቀም። የውጭ አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ እንዲወጣ ግፊት ያደርጉ ነበር።
- ማንኛውም ጤነኛ ወታደራዊ አመራር ያለ ሎጂስቲክስ እስከ ኮምቦልቻ እና ደሴ ድረስ ሊገባ ባልደፈረ ነበር።
- የህወሓት የውጭ ሃይሎች በጦርነቱ ውጤት አልረኩም።
- ወያኔ በኤርትራ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከኃይለሥላሴና ከመንግስቱ ኃ/ማርያም የከፋ ነው።
- የትግራይ የነጻነት ሪፐብሊክ የለም፣ አይሆንምም።
- ወያኔ የኢትዮጵያን የተረቀቀውን ሕገ መንግሥት ከማንም በፊት እንዳነብ ሰጠኝ። ሕገ መንግሥቱ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነበር፣ እናም ቅሬታዬን አንስቻለሁ።
- ከብሄር ፌደራሊዝም ፖሊሲ የበለጠ አደጋ የለም።
- አገሪቱ አንድ ካልሆነ ለውጭ አገሮች በሉዓላዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ቀላል ነው።
- ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ አንድነት ለኒዮ-ቅኝ ገዢ አገሮች ትምህርት ሆኖ ቆይቷል።
- የአሜሪካን ህዝብ እና መንግስትን መለየት አለብን። በአለም አቀፍ ደረጃ ውድመትን የሚፈጥሩት መቶኛ ከአሜሪካ ህዝብ 0.1% እንኳን አይደለም።
- በአሁኑ ጊዜ በዩኤስኤ ውስጥ የተሰራ የለም. ሁሉም ነገር በቻይና የተሰራ ነው.
- ቻይና ሩብ የአሜሪካ ዕዳ አለባት። ዩኤስኤ በኢኮኖሚ ኃያል አገር ናት የሚለው ግምት የተሳሳተ ነው።
- ስማቸው እንጂ ኢጋድ ወይም AU የሉም። የግል ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አበላሽተውታል።
- ቻይና ምዕራባውያንን አንቀሳቅሳለች። ምዕራባውያን አገሮች ሩሲያንና ቻይናን መያዝ አልቻሉም።
- በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ ዓለም ለበጎ ነገር የተለየ ይሆናል.
- የዓለም ልዕለ ኃያል መንግሥት እንደ ኤርትራ ትንሿን አገር ለስምንት ዓመታት እንዴት ማዕቀብ ይጥላል? ይህ በእነርሱ በኩል ተስፋ መቁረጥ ነው, እኛ ለመሾም ፈቃደኛ ባለመሆኑ.
- የአሜሪካ ልዑክ ሥራ ለአገሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማዘዝ ነው።
- ሽብርተኝነት የተፈጠረው ‘በነሱ’ ነው።
- ባለፈው አመት ሲሰራጭ የነበረው 40% ዶላር በህገ ወጥ መንገድ በአሜሪካ ታትሟል።
-በአሜሪካ መንግስት ላይ 'immunity' ፈጥረናል።
- የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፖሊሲዎች እና 'የዓለም ስርዓት' የጫካ ህግ ናቸው. ተሃድሶ ተከልክሏል።
- ኤርትራን ሰይጣናዊ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።
- የአፍጋኒስታን ሰዎች ለምን ይሰቃያሉ?
- በተሞክሮአችን ምክንያት የዩኤስን ማዕቀብ መቃወም እና ማቆየት እንችላለን።
- የሰማንያ አመታት ታሪካችን ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው። የእነሱ ሰላም እና ብልጽግና ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው.
- በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው አስከፊው ነገር ወያነ ነው።
- ኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ።
- ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና አንድነት እንዲኖር የጎሳ ፌደራሊዝምን ማሻሻል ወይም ማስወገድ አለባት።
- ህወሀት ለተጋሩ ከአማራ ያነሱ መሆናቸውን በመንገር ጥላቻን እየዘራ ነበር።
-የመጀመሪያው ወያነ አስተሳሰብ ከሁለተኛው እና ከአሁኑ ወያነ የተለየ ነበር።
- ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት የሚሰቃዩት ተጋሩ ናቸው።
- አሁን በሱዳን ያለው መጥፎው የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት ነው።
በአማራ ብሔርተኝነት ፖለቲካ የተቀመጠው የጠራ የጋራ አላማና ግብ ምንድነው ? አይነኬው ቀይ መስመርስ? አንድ ሰው ቀይ መስመር አለፈ ወይም ካደ የሚባለው ምን ሲያደርግ ነው? ማን ምን ሲያደርግ ነው የእሱ/ሷ የአካሄድ እንጅ ግቡ የተለየ አይደለም አንድ መስመር ላይ ነን የሚባለው? ትግሉ የሚመራባቸው ታክቲኮች እና ስትራቴጂዎችስ ተለይተዋል ወይ? ሁሉንም ጠላት በማድረግ ካገኘው ጋር መላተም የትግሉ ዋናው ስትራቴጅ ነውን?

(አንደ ሰው ×) ... በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ የእነ እንቶኔ ልዩነት የአካሄድ (የታክቲክ) እንጂ የመሰረታዊ የትግል መስመር አይደለም የሚባለው ምን ሲፈጽሙ ነው?

የአማራ ህዝብን ትግል ዕውን ለማድረግ ስትራቴጅካል እና ታክቲካል አጋሮች እነማን ናቸው? የአማራን ትግል ሊያደናቅፉ ወይም ከህዝባችን ትግል በተጻራሪ ሊቆሙ ይችላሉ ተብለው የተለዩ ስትራቴጅካልና ታክቲካል ጠላቶች እነማን ናቸው? የአማራ ህዝብን ትግል ውጤታማ በማድረግ ሂደት ጠላቶችን ለመቀነስ ወዳጆችን ለማብዛት የተቀመጡ ስልቶች ምን ም ናቸው? እራሳቸውን የአማራ ህዝብ ታጋይ ብለው የሚያቀርቡ እህቶችና ወንድሞች ከሁሉም ጋር የሚጋጩት/የሚላተሙት በምን ምክንያት ነው? ከዚህ አዙሪት የመውጫ ቁልፉስ ምንድን ነው?

ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከሞላ ጎደል የአማረኛ ቋንቋን የመናገር፣ የመጻፍ፣ የማንበብ እና የማዳመጥ ክኀሎት ስላላቸው አማራ መስለው የአማራን ትግል ከሚቀለብሱ ወይም ለእነርሱ ዓለማ ከሚጠቀሙ ሰርጎ-ገቦች እንዴት መለየት ይቻላል?

የአማራ ብሔርተኛ ወይም ተቆርቋሪ ለመባል ዋናው መስፈርት ብልፅግናን ብአዴን ማለት ነው? ዘወትር ለአማራ የሚታገሉ እና ለኢትዮጵያ የሚቆረቆሩ ወያኔን አምርረው የሚታገሉ ሰዎችን እየመረጡ አጀንዳ በማድረግ ሲሳደቡና ሲራገሙ መዋል ነው?የሚጠቅመውስ ማንን ነው?

የብልፅግና አመራር ሆኖ ብልፅግናን ብአዴን በማለት ብአዴንን ይውደም ማለት እንዴትስ ይቻላል? ከብልፅግና ሰዎች ይህ ልዩ መብት ያላቸው እነማን ናቸው? ለምን? በብአዴንነት የሚሰደቡትስ ለምን ተለይተው ይሰደባሉ? ያለመሰደብ መብት ያላቸውስ እነማን ናቸው? በምን መስፈርት ተለዩ? ብልፅግና ይወ*ገድ ከተባለስ አስ*ገጁ ማነው? በብልፅግና መልካም ፈቃድ ወይም አቅሙን አይቶ ለዲሞክራሲው ማሳያ ንቆ ትቶት ካልሆነ በስተቀርስ የእውነት ብልፅግናን ለማክሰም የሚችል አካል ማን ነው? የትስ መሬት ላይ ሆኖ ነው ሊታገል የሚችለው? ለመሆኑ ብልፅግናን በምን መርህ የቆመ እንዴትስ ያለ ሃይል ነው የሚያስወግደው? ቅዠት ከመሆን የሚያልፍና አንድም ግለሰብ ይህን የሚያስበው እንደሌለ ይታወቃል እንጅ የእውነት ይሁን አቅሙ አለ ቢባል ብልፅግና/ብአዴንን በማስ*ገድ የአማራ ሕዝብ ሕልውና ሁለንተናዊ ጥቅም ሊረጋገጥ ይችላል ?

ብልፅግና/ብአዴን ይውደም በማለት (በእርግጥ ከእኛ ውጭ ነው የሚባለውን አመራር ነው) የተሻለ ሰው ወደብልጽግና/ብአዴን እንዳይቀላቀል ውስጥ ላይ ያለውም አንድነቱን አጠናክሮ በሞራል ለተሻለ ድል እንዳይነሳሳ ከአመት እስከ አመት ሲሰራ እየተከረመ ችግር ሲፈጠር ብአዴን የት ነህ ? ምን ትሰራለህ? አቃቂርስ አብረው የሚሄዱ ጉዳዮች ናቸውን? አያስገምትም? እስከመቼስ ይህ ቀልድ ይቀጥላል? ምን ያህልስ ይጠቅማል?

እንዲያው ብዙ ነገሮች ቢያስገርሙኝና ብአዴን የሆነ ሰው ሁሉ ሌላውን ሰው ብአዴን ሲል ስለምሰማ ታላቅ ግርምትን ቢፈጥርብኝ ጊዜ ነው!
ወልቃይትን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ የተንበረከከው አፍቃሬ ወያኔ አሁን ደግሞ አፍቃሬ ወያኔዎችን በመጠቀመ ለአማራ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መከላከያ ከሑመራ ወጣ ሊወጣ ነው በማለት የሴራ አለ ሴራ የፖለቲካ ትንተናን ተጠቅሞ ለማጭበርበር ሌላ የሴራ ጨዋታ ለመሞከር እየጣረ ነው።


ያም ሆነ ይህ ያለኛ ፈቃድ ሊሆን የሚችል አንዳችስ እንኳን ነገር ሊኖር እንደማይችል በእርግጠኝነት ለማሳወቅ እንወዳለን!!

የኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም የሚከበረው በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድና መልካም ፈቃድ ነው‼️
"ሀገራችን ኢትዮጵያ ከምትገኝበት የታሪክ አጣብቂኝ ውስጥ ለመውጣትና በአስተማማኝ ጎዳና ለመራመድ እንዲቻል ከምንጊዜውም በላይ የመላው ኢትዮጵያውያን ርብርብ አስፈላጊ መሆኑን ጠንቅቆ ይረዳል"

አብን!